Documents Authentication and Registration service

Documents  Authentication and Registration service ምንግዜም ቅድሚያ ለተገልጋይ!

አገልግሎቱ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የአረንጓዴ አሻራና ለአቅመ ደካማ ወገኖች የበጎአድራጎት ስራዎች አከናወነ።ሃምሌ 29 ቀን 2018 ዓ.ም የሰነዶችማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ካውንስል አ...
05/08/2026

አገልግሎቱ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የአረንጓዴ አሻራና ለአቅመ ደካማ ወገኖች የበጎአድራጎት ስራዎች አከናወነ።

ሃምሌ 29 ቀን 2018 ዓ.ም

የሰነዶችማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ካውንስል አባላት በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በመገኘት የችግኝ ተከላ እና የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ ለተማሪዎች አድርገዋል።

የአረንጓዴ አሻራና ለሶስት መቶ አቅመደካማ ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ በተደረገበት በዚህ መርሀግብር ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀሚድ ኪኒሶ ባስተላለፋት መልእክት የተቋሙ አመራሮች እና ሠራተኞች ዜጋ ተኮር የሆነ የልማት ተግባራት ላይ ሲሳተፉ የቆዩ መሆኑን ገልጸው በተለይ በድሬዳዋ ከተማ የተቋሙ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የሚገኝበት እና በድሬ መሶብ የአንድ አገልግሎት ማእከል ውስጥ በተደራጀ ሁኔታ አገልግሎቱን ተደራሽ እያደረገ በመሆኑ የአረንጓዴ አሻራና በጎ አድራጎት ተግባራትን በማከናወን ትብብርና አብሮነትን እየገለጸ ይገኛል ብለዋል።

አቶ ሀሚድ አያይዘውም ለተተኪ ሀገር ተረካቢ ተማሪዎች የተደረገው ድጋፍም ትውልድን የሚያንጽ እና ተጠናክሮ ሊቀጥል የሚገባ ተግባር ነው ብለዋል።

የሠነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት አመራር እና ሰራተኞች በአንድ ጀምበር አረንጓዴ አሻራ ተግባር ላይ ሰፊ ተሳተፎ ያደረጉ ሲሆን በጎንደር ከተማ በመገኘት የአምስት አረጋውያንን ቤት ግንባታ የሶስት መቶ ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍና የአረንጓዴ አሻራ ተግባራትን ማከናወናቸው ይታወቃል።

የተቋሙ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ውይይት  እየተካሄደ ይገኛል::ሃምሌ 28 ቀን  2018 ዓ.ም የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት የካውንስል አባላት በ2018 በ...
04/08/2026

የተቋሙ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል::

ሃምሌ 28 ቀን 2018 ዓ.ም

የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት የካውንስል አባላት በ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ በድሬዳዋ ከተማ ውይይት እያካሄዱ ይገኛሉ።

የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀሚድ ኪኒሶ በውይይቱ መክፈቻ ላይ ባስተላለፋት መልዕክት በ2018 በጀት ዓመት ተቋሙ ከጉዳይ እና ከተገልጋይ አንጻር ከፍ ያለ አፈጻጸም ያስመዘገበበትና ከፍተኛ የኢኮኖሚ ዝውውር ያስመዘገበበት ዓመት መሆኑን ገልጸው ይህ ስኬት በሰራተኛውና አመራሩ የጋራ ርብርብ በመሆኑ በአዲሱ በጀት ዓመትም ይህ ትጋት ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘውም በውይይት መድረኩ ትኩረት ሊደረግባቸው የሚገቡ ጉዳዮችን ያብራሩ ሲሆን በተለይም በአፈጻጸም ላይ የነበሩ ተግዳሮቶች ና የቀጣይ በጀት አመት እቅድን የሚያዳብር የሀሳብ ግብአት የሚሰጥበት፣ የሰነድ አስተዳደርና እና ደህንነት ማስጠበቅ በተመለከተ ፣ የሰነድ ማረጋገጥና መመዝገብ ሲስተም (DARIS) ማሻሻያ ስራ ፣ እንዲሁም ወጥ ሀገራዊ መረጃ ቋት እንዲኖር ክልሎችን መደገፍ እና ከተለያዩ ተቋማት ጋር የተፈረሙ የመግባቢያ ሰነዶችን ዲጂታላይዝ የማድረግ ስራ በተመለከተ የሀሳብ ግብአት የሚሰጥበት ሊሆን እንደሚገባ ገልጸዋል።

ለሁለት ቀናት የሚቆየው የዉይይት መድረክ የ2019 በጀት አመት እቅድ የሚቀርብ ሲሆን ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የአፈጻጸም ሪፖርታቸውን ያቀርባሉ።

ከዚህም ሌላ በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ውስጥ የተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥ እንዲሁም የተቋሙ የሰነድ ማረጋገጥና መመዝገብ ሂደት ጨምሮ ልዩ ልዩ የውይይት አጀንዳዎች ይነሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት አመራርና ሰራተኞች በአንድ ጀንበር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃግብርን ተሳተፋ::ሃምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም አረንጓዴ ዐሻራ የአካባቢን የደን ሽፋንን ከማሳ...
03/08/2026

የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት አመራርና ሰራተኞች በአንድ ጀንበር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃግብርን ተሳተፋ::

ሃምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም

አረንጓዴ ዐሻራ የአካባቢን የደን ሽፋንን ከማሳደግ ባሻገር በእለት ተእለት እንቅስቃሴአችን ውስጥ ያለው አዎንታዊ አስተዋጽኦ የላቀ ነው ሲሉ በአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሃግብር የተሳተፉ የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት አመራርና ሰራተኞች ተናገሩ::

የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት አመራርና ሰራተኞች በዘንድሮው 2018 ዓ.ም የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በአዲስ አበባ ቀበና አካባቢ የአረንጓዴ አሻራ ላይ የነቃ ተሳትፎ አከናውነዋል::

የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሃሚድ ከኒሶ እንዲሁም የኦፕሬሽን ምክትል ዳይሬክተር አቶ ቶፊቅ ሻፊ የተገኙ ሲሆን በመርሐ ግብሩ ላይ የመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ ኃላፊ ጀነራል ደስታ አብቼ : የየካ ክፍለ ከተማ ህብረተሰብ ተሳትፎ በጎፍቃድ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለሙ ኢሚሮ እንዲሁም የየካ ክፍለከተማ ወረዳ 03 ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ እሱባለዉ መንዴዶ ተሳትፈዋል ::

የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በባለፉት ሰባት አመታት ሲተገበር የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት አመራርና ሰራተኞች ሲሳተፉ እንደነበር የሚታወስ ነው::

የተቋሙ የስራ ኃላፊዎች በጎንደር ከተማ በመገኘት በከተማዋ የተከናወኑ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ተዘዋውረው ጎበኙ::ሃምሌ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ለአረንጓዴ አሻራ እና ለክረምት በጎ አድራጎት ...
28/07/2026

የተቋሙ የስራ ኃላፊዎች በጎንደር ከተማ በመገኘት በከተማዋ የተከናወኑ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ተዘዋውረው ጎበኙ::

ሃምሌ 21 ቀን 2018 ዓ.ም

ለአረንጓዴ አሻራ እና ለክረምት በጎ አድራጎት ስራዎች በጎንደር ከተማ የተገኙት የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተርና ማኔጅመንት አባላት በከተማው የተሰሩ የኮሪደር ልማቶች እና ታሪካዊ ስፍራዎች ጉብኝት አካሂደዋል።

የከተማው ከንቲባ አቶ ቻላቸው ዳኘው ከተማውን ገጽታ እጅግ ያሳመረውን የኮሪደር ልማት ስራዎችን ሲያስጎበኙ እንደገለጹት የኮሪደር ልማቱ የከተማውን ታሪካዊነትና ዘመናዊነትን በማጣመር ጊዜውን በሚመጥን መልክ የተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

አቶ ቻላቸው አክለውም በተለይም የጎንደር ስልጣኔ የታተመባቸው አብያተ መንግስታት በአለም ቅርስነት የተመዘገቡ በመሆናቸው የተደረገላቸው እድሳት ታሪካዊነቱን ሳያዛንፍ በሀገራችን የዘርፉ ባለሙያዎች የተሠሩ በመሆናቸው ልዩ ኩራት ይሰማናል ብለዋል።

ከታሪካዊ ስፍራዎች በተጨማሪ የከተማ አስተዳደሩን ፍትህ ጽ/ቤት የሰነድ ማረጋገጥና መመዝገብ ስራ ሂደት የተጎበኘ ሲሆን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀሚድ ስራው በደብረብርሃን ባህርዳር ደሴ እና ሌሎች ከተሞችም እየተሠራ ያለው የተቋሙን ሰነድ ማረጋገጥና መመዝገብ ሲስተም(DARIS) በመጠቀም በመሆኑ የጎንደር ከተማ ፍትህ ጽ/ቤትም አገልግሎት አሰጣጡን ዲጂታላይዝድ ማድረግ እንዳለበት እና ለዚህም ተቋማቸው አስፈላጊውን ድጋፍ እና ትብብር ለማድረግ ዝግጂ መሆኑን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀሚድ ለጽ/ቤቱ የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ገልጸዋል።

የጉብኝት መርሀግብሩ በጎንደር ዩኒቨርስቲ የተካሄደ ሲሆን የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት አስራት አፀደወይን (ዶ/ር) የዩኒቨርስቲውን የለውጥ ጉዞ በተመለከተ አጠር ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የአረንጓዴ አሻራ እና በጎ አድራጎት ተግባራት  በጎንደር ከተማ ተካሄደ።ሀምሌ 20 ቀን 2018 ዓ.ምየተቋሙ የበላይ አመራሮች "ተስፋን መትከል" በሚል መሪ ቃል በሀገርአቀፍ ደረጃ እየተከሄደ ...
27/07/2026

የአረንጓዴ አሻራ እና በጎ አድራጎት ተግባራት በጎንደር ከተማ ተካሄደ።

ሀምሌ 20 ቀን 2018 ዓ.ም

የተቋሙ የበላይ አመራሮች "ተስፋን መትከል" በሚል መሪ ቃል በሀገርአቀፍ ደረጃ እየተከሄደ ያለውን የ2018 ዓም አረንጓዴ አሻራ እና የክረምት በጓ አድራጎት መርሀግብር ምክንያት በማድረግ በታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ የችግኝ ተከላ እና የአቅመደካሞች ቤት እድሳት እንዲሁም ለተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ።

የጎንደር ከተማ ከንቲባ አቶ ቻላቸዉ ዳኘው እና ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ ደብሬ የኋላ፣ የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀሚድ ኪኒሶ እና ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ቶፊቅ ሻፊ እንዲሁም የማኔጅመነት አባላት ጨምሮ ከጎንደር ከተማ የተውጣጡ የማህበረሰብ ክፍሎች በተገኙበት በተካሄደው መርሀግብር 1500 ያህል የልዩ ልዩ ፍራፍሬ ችግኞች ተከላ የተካሄደ ሲሆን ለ300 አቅመ ደካማ ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጎላቸዋል።

ተቋሙ ከፍተኛ በጀት በመመደብ የአረጋውያን እና አቅመደካማ ዜጎች የመኖሪያ ቤት ግንባታ ያስጀመረ ሲሆን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀሚድ ኪኒሶ በመርሀግብሩ እንደገለጹት የተደረገው ድጋፍ መንግስት ተኩረት ያደረገባቸው ዜጋ ተኮር የልማት ተግባራትን መነሻ በማድረግተቋሙ የራሱን ኃላፊነትለመወጣት እያደረገ ያለው አስተዋጽኦ አንድ ማሳያ ነው ያሉ ሲሆን የችግኝ ተከላውም ሆነ የአቅመደካሞች ድጋፍ ለዜጎቻችን አለኝታነታችንን የምንገልጽበት መሆኑን አመልክተዋል።
የጎንደር ከተማ ከንቲባ አቶ ቻላቸው ዳኘው በበኩላቸው ተቋሙ የነገ ተስፋ ለሆኑ ተማሪዎች እና ለሀገር ባለውለታ አረጋውያን ያደረገው ድጋፍ እጅግ የላቀ መሆኑን ጠቅሰው ድጋፍ በተደረገላቸው ዜጎች ስም ልባዊ ምስጋናቸቸውን አቅርበዋል።

በጎንደር ከተማ ሙሉ በሙሉ ፈርሰው በአዲስ መልክ የሚሰሩት አምስት የአረጋውያን ቤቶች ግንባታ በቀጣይ ሶስት ወራት ተጠናቆ ለባለቤቶች እንደሚሰጥ በመርሀግብሩ ላይ ተገልጿል።

27/07/2026
የአእምሮአዊ ንብረት ሽያጭ፣ ስጦታ ወይም የኪራይ ውል ለመዋዋል ትኩረት የሚደርግባቸው ነጥቦችሐምሌ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ሀ. የሚረጋገጠው የውል ሰነድ ይዘት በተቋሙ የኦንላይን ሲስተም ተሞል...
25/07/2026

የአእምሮአዊ ንብረት ሽያጭ፣ ስጦታ ወይም የኪራይ ውል ለመዋዋል ትኩረት የሚደርግባቸው ነጥቦች

ሐምሌ 18 ቀን 2018 ዓ.ም

ሀ. የሚረጋገጠው የውል ሰነድ ይዘት በተቋሙ የኦንላይን ሲስተም ተሞልቶ የጉዳይ መከታተያ ቁጥር

ለ. የሰነድ ፈራሚዎች መታወቂያ እና ፋይዳ

ሐ. ፈራሚው ከህግ፤ ከውል ወይም ከፍርድ ቤት ውሳኔ የመነጨ ስልጣን ያለው መሆኑን፤

መ. ስጦታው የሚደረገው በውክልና ከሆነ ስጦታው ለማን እንደሚሰጥ እና የንብረቱን ዓይነት በውክልናው ይዘት ላይ በግልፅ የተመለከተ መሆኑን፣

ሠ. ፈራሚው የንግድ ማህበር ከሆነ የመመስረቻ ጽሁፍ፣ ዋና የንግድ ምዝገባ፣ንግድ ፈቃድ እንዳስፈላጊነቱ ቃለ ጉባኤ መቅረቡን፤

ረ. ፈራሚው ለንግድ ያልሆነ ማህበር ከሆነ ጊዜው ያላለፈበት የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ መተዳደሪያ ደንብ፣ ኃላፊነትን የሚገልጽ ከመዝጋቢው መንግስታዊ አካል የተፃፈ ደብዳቤ መቅረቡን፤

ሰ. ንብረቱ እግድ የሌለበት ስለመሆኑ ከንብረት መዘጋቢው አካል ከተሰጠ ማስረጃ እና ከተቋሙ የመረጃ ቋት እግድ አለመኖሩን፣
ሸ. እንደ ፈጠራው ዓይነት አግባብነት ካለው የመንግስት አካል የተሰጠ የፈጠራ ባለቤትነት ማስረጃ መቅረቡን፤

ቀ. የፈጠራ ባለቤቱ ያላገባ ማስረጃ ወይም ያገባ ከሆነ የጋብቻ ማስረጃ እና የትዳር አጋር የፈቃድ ስምምነት መኖር አለበት፡፡

የተቋሙ የስራ አመራር አባላት የተለያዩ የኮሪደርና የወንዞች ዳር ፕሮጀክቶችን ጎበኙ።ሐምሌ 12 ቀን 2018 ዓ.ም የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ካውንስል አባላት በከተማችን በቅርቡ ...
20/07/2026

የተቋሙ የስራ አመራር አባላት የተለያዩ የኮሪደርና የወንዞች ዳር ፕሮጀክቶችን ጎበኙ።

ሐምሌ 12 ቀን 2018 ዓ.ም

የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ካውንስል አባላት በከተማችን በቅርቡ ተመርቀው ለህዝብ መዝናኛነት ክፍት የተደረጉ የአዲስ አበባ ከተማ የኮሪደር እና የወንዞች ዳር ፕሮጀክቶች አካል የሆኑትን የ አራዳ ፓርክ እና የቀበና ወንዝ ልማት ፕሮጀክቶችን ጎበኙ::

የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀሚድ ኪኒሶ በጉብኝቱ ወቅት እንደገለጹት ታሪክና ዘመናዊነትን ያጣመሩት መዝናኛ ማእከላት ከመዝናኛነታቸው ባሻገር ስራን በጥራት እና በታቀደ ጊዜ የማጠናቀቅ ባህል እየዳበረ መምጣት ማሳያ ናቸው ብለዋል።
አክለውም የጉብኝቱ ዋነኛ አላማም ይህንን ጠንካራ የስራ ባህል ወደራሳችን እና ወደተቋማችን እንድናመጣው ተነሳሽነት ለመፍጠር እንደሆነ አስረድተዋል።

የተጎበኙት የኮሪደር ልማትና የወንዝ ዳር ፕሮጀክቶች ሁሉም ማህበረሰብ ክፍል በእኩልነት የሚጠቀምባቸው እንደሆኑት ሁሉ ተቋማችንም ዲጂታላይዝ አገልግሎት በመስጠት በዘርፉ ጥራት እና ዘመናዊነትን በማጣመር ለዜጎች በእኩልነትና በፍትሀዊነት እያገለገለ እንደሚገኝ በጉብኝቱ ወቅት ተገልጿል።

በዕለቱ የማጠናቀቂያ ስራው እየተገባደደ የሚገኘው የተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት ባለ ሀያ አንድ ወለል ህንጻ ግንባታ ሂደትም በካውንስል አባላቱ ተጎብኝቷል።

17/07/2026
የሽርክና ውል ወይም በጋራ አብሮ የመሥራት (Partnership /Joint Work/ Agereement) አገልግሎት ለማግኘት ትኩረት  የሚደረግባቸው ጉዳዮች ሐምሌ 9 ቀን 2018 ዓ.ም   ሀ....
16/07/2026

የሽርክና ውል ወይም በጋራ አብሮ የመሥራት (Partnership /Joint Work/ Agereement) አገልግሎት ለማግኘት ትኩረት የሚደረግባቸው ጉዳዮች

ሐምሌ 9 ቀን 2018 ዓ.ም

ሀ.)የሚረጋገጠው የውል ሰነድ ይዘት በተቋሙ የኦንላይን www.dars.gov.et ሲስተም ላይ ተሞልቶ የጉዳይ መከታተያ ቁጥር የያዘ መሆኑን፣

ለ.)የሰነድ ፈራሚዎች በዘመኑ የታደሰ የማንነት መታወቂያ ፤

ሐ.)ፈራሚው ከህግ፤ ከውል ወይም ከፍርድ ቤት ውሳኔ የመነጨ ስልጣን ያለው መሆኑ(ውክልና)

መ.)ፈራሚው የንግድ ማህበር ከሆነ የመመስረቻ ጽሁፍ፣የንግድ ምዝገባ፣ የንግድ ፈቃድ እንዳስፈላጊነቱ ቃለ ጉባኤ

ሠ.)ፈራሚው ለንግድ ያልሆነ ማህበር ከሆነ ጊዜው ያላለፈበት የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ መተዳደሪያ ደንብ፣ ኃላፊነትን የሚገልጽ ከመዝጋቢው መንግስታዊ አካል የተፃፈ ደብዳቤ

ረ.)የተዋዋይ ወገኖች በየግላቸው ተመሳሳይ ወይም ተመጋጋቢነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና መሰል ሰነዶች

ሰ.)በውል ሰነዱ ውስጥ በዝርዝር የተገለጸና ማስረጃ የሚያስፈልገው የባለቤትነት ወይም የመብት ማጣቀሻ ካለ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃ

Address

Addis Ababa
29935

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Documents Authentication and Registration service posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Documents Authentication and Registration service:

Share