Addis Ababa Light Rail Transport Service Enterprise

Addis Ababa Light Rail Transport Service Enterprise የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት

የጷጉሜ ቀናት ስያሜዎች :-
03/09/2026

የጷጉሜ ቀናት ስያሜዎች :-

የስራ ኃላፊዎች የትኬት ቍጥጥር በሀያት መስመር
03/09/2026

የስራ ኃላፊዎች የትኬት ቍጥጥር በሀያት መስመር

በሀያት ቅርንጫፍ ፅ. ቤት ቆሻሻን የማፅዳትና የማስወገድ እንዲሁም አትክልቶችን የመትከል ስራ በፎቶ:
01/09/2026

በሀያት ቅርንጫፍ ፅ. ቤት ቆሻሻን የማፅዳትና የማስወገድ እንዲሁም አትክልቶችን የመትከል ስራ በፎቶ:

የሙያ ልህቀት (Professional Excellence)                   - የወርቃማው ሰኞ የመወያያ ርዕስአቅራቢ - ሚሊዮን  ደነቀ( ከትራንስፖርት ዘርፍ )ቀን :- ነሐሴ 25/ ...
31/08/2026

የሙያ ልህቀት (Professional Excellence)
- የወርቃማው ሰኞ የመወያያ ርዕስ
አቅራቢ - ሚሊዮን ደነቀ( ከትራንስፖርት ዘርፍ )
ቀን :- ነሐሴ 25/ 2018 ዓ.ም

እንደ አቅራቢው ገለፃ የሙያ ልህቀት (Professional Excellence) ማለት በአንድ በተሰማሩበት የሥራ መስክ ላይ ከፍተኛ ብቃትን፣ ጥራትን፣ እና ተደራሽነትን ማሳየት ማለት ነው። ይህ ደረጃ በአንድ ጀምበር የሚገነባ ሳይሆን በተከታታይ ጥረት፣ በክህሎት ማሳደግ እና በሥነ-ምግባር የሚመጣ ስኬት ነው።የሙያ ልህቀትን ለማምጣትና ለማስቀጠል የሚረዱ ዋና ዋና ምሰሶዎች የሚከተሉት ናቸው፦
ቀጣይነት ያለው ትምህርት: በሥራ መስኩ ላይ የሚመጡ አዳዲስ እውቀቶችን፣ ቴክኖሎጂዎችን እና አሰራሮችን ሁልጊዜ መማር እና መተግበር።
ጠንካራ የሥራ ሥነ-ምግባር: ለሥራ ታማኝ መሆን፣ ሰዓት ማክበር፣ ኃላፊነትን መወጣት እና የሥራ ባልደረቦችን እንዲሁም ደንበኞችን በአክብሮት ማገልገል።
ችግር ፈቺነት: በሥራ ቦታ የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን ከማማረር ይልቅ ስልታዊ እና ፈጣሪ የሆኑ መፍትሄዎችን ማፈለግ።
ውጤታማ ተግባቦት: ሀሳብን በግልጽ፣ በአጭሩ እና በጨዋነት ለሌሎች ማጋራት እንዲሁም የሌሎችን ሀሳብ በጥንቃቄ ማዳመጥ።
ግንኙነት መገንባት (Networking): በሙያ መስኩ ካሉ ሌሎች ባለሙያዎች ጋር ጠንካራ እና እርስ በእርስ የሚደጋገፍ ሙያዊ ግንኙነት መፍጠር።የሙያ ልህቀትን ማሳደግ በሥራዎ ላይ ከፍተኛ ዕድገትና እውቅና እንድታገኙ ይረዳዎታል።

25/08/2026
አንድ ቤተሰብ በባቡር ኦፕሬሽን" - የወርቃማው ሰኞ የመወያያ ርእስ              አቅራቢ ፦ ታዲዎስ ወርቁ( ኢ/ር)                          ከሜንቴናንስ ዲፓርትመንት  ...
24/08/2026

አንድ ቤተሰብ በባቡር ኦፕሬሽን" - የወርቃማው ሰኞ የመወያያ ርእስ

አቅራቢ ፦ ታዲዎስ ወርቁ( ኢ/ር)
ከሜንቴናንስ ዲፓርትመንት

እንደ አቅራቢው ገለጻ ‘’አንድ ቤተሰብ" የሚለው ቃል በተለምዶ የሚያመለክተው የጋራ የዘር ሐረግ ወይም የዘር ተዛማጅ ግለሰቦችን ቢሆንም " አብረው የሚኖሩ፣ የሚሰሩ፣ የሚታገሉ እና የሚደሰቱ ሰዎች እርስ በርስ የሚደጋገፉ፣ የሚተማመኑ እና የሚዋደዱ አንድ ግብ ላይ ያተኮሩና የተደመሩ ሰዎችንም ሊያመለክት ይችላል፡፡

በባቡር ኦፕሬሽን ቤተሰባዊነትን የሚያጠናክሩ ነገሮች ፦
እርስ በርስ መረዳዳት እና መደጋገፍ፣ አብረው መማር ና መስራት፣ስኬቶቹን የጋራ ማድረግና ችግሮቹን በጋራ መፍታት፣የጋራ ግቦች መያዝ፣የቡድን ስራና የመሳሰሉት ተግባራት ተቋሙ እነደ አንድ ቤተሰብ እንዲንቀሳቀስ ያግዛል፡፡

ዋናው መልእክት፦

እያንዳንዱ የስራ ክፍል ልዩና አስፈላጊ ነው፡፡
እያንዳንዱ የስራ ክፍል ለአንድ አላማ የተሰለፈ ነው፡፡
እያንዳንዱ የስራ ክፍል በጋራ ከተባበረ ትልቅ ውጤት ያመጣል፡፡

የተቀናጀ የሥራ አስተዳደር - የወርቃማው ሰኞ የመወያያ ርዕስአቅራቢ - ኢዮብ በዳዳ ( ከትራንስፖርት ዘርፍ )ቀን :- ነሐሴ 11/ 2018 ዓ.ምእንደ አቅራቢው ገለፃ የተቀናጀ የስራ አስተዳደ...
17/08/2026

የተቀናጀ የሥራ አስተዳደር - የወርቃማው ሰኞ የመወያያ ርዕስ
አቅራቢ - ኢዮብ በዳዳ ( ከትራንስፖርት ዘርፍ )
ቀን :- ነሐሴ 11/ 2018 ዓ.ም

እንደ አቅራቢው ገለፃ የተቀናጀ የስራ አስተዳደር (Integrated Work Management ወይም Integrated Operations Management) ማለት የአንድን ድርጅት የተለያዩ የስራ ክፍሎች፣ ሰራተኞች፣ መረጃዎች እና ቴክኖሎጂዎች በአንድ ወጥ ስርዓት በማቀናጀት ውጤታማነትን ማሳደግ የሚያስችል ዘመናዊ የአመራር ዘዴ ነው።ይህ አሰራር በተበታተነ መልኩ የሚሰሩ ስራዎችን በማስቀረት የሀብት ብክነትን ይከላከላል።

የተቀናጀ ሥራ አስተዳደር (IWM) ዋና ጥቅሞች
፩. ውጤታማነት መጨመር (Increased Efficiency)
፪. ትብብርን ማጎልበት (Enhanced Collaboration)
፫. መረጃን ተደራሽ ማድረግ (Information Accessibility)
፬. የእውነተኛ ጊዜ ታይነት እና ሪፖርት ማድረግ (Real-time Visibility and Reporting)
፭. ቀጣይነት ያለው መሻሻል (Continuous Improvement)

ቅንጅታዊ አሰራሮች በ LRT Context

ውጤታማነት መጨመር (Increased Efficiency)
ምቹ የስራ አካባቢን መፍጠር፦ ቢሮዎች፣ የመፀዳጃ ቤቶች፣ ባቡሮችን እና ባቡር የሚያልፍባቸው መስመሮች ማፅዳት
የግዢ ትኩረታችን የባቡር ቁጥርን የሚጨምር ካልሆነም ያሉትን የሚያስቀጥል እንዲሆን ማድረግ
የትኬት ዋጋ ማሻሻያ ማድረግ
የትኬት ቁጥጥርን ማጠናከር
ሌሎች የገቢ ማግኛ አማራጮችን መፈለግ
የእውነተኛ ጊዜ ታይታነት እና ሪፖርት ማድረግ (Real-time Visibility and Reporting)
ሪፖርቶቻችን ለባለድርሻ አካላት የተሻለ ውሳኔ ለመስጠትን እሚያስችሉ እንዲሆኑ ማድረግ ይህም አስቀድሞ ችግሮችን ለመፍታትና ለእውነተኛ ሪፖርቶች መቅረብ እና መገምገም ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋል።

ቀጣይነት ያለው መሻሻል (Continuous Improvement)
ግዢዎቻችንን ለባቡር መለዋወጫ ቅድሚያ የሰጡ ማድረግ
የጥገና አቅምን ማሳደግ
የባቡር ቁጥርን መጨመር
የትኬት ሽያጫችንን ማዘመን
ባቡር የሚያልፍባቸውን ስቴሽኖች እና አጥሮች የማስዋብ ስራ መስራት
ምቹና ተመራጭ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተቋም መሆን

12/08/2026

BRT B2 Project – Professional Recruitment Announcement

The Addis Ababa Transport Bureau, with financial support in the form of a loan obtained from the Agence Française de Développement (AFD), has issued a recruitment announcement under the Bus Rapid Transit (BRT B2) Project, pursuant to RFP-IE No.: AATB/IB/04/2026, for the competitive selection and recruitment of a Project Implementation Unit Head (PIU Head).

The recruitment announcement has been published in the Addis Zemen and Ethiopian Herald newspapers in August 9, 2026. Accordingly, qualified professionals who possess the required qualifications, relevant professional experience, and technical skills in the field are hereby invited to participate in the selection process.

Interested and qualified professionals may access the DG Market website through the following link: www.dgmarket.com, download the relevant tender/procurement documents, and prepare and submit their Technical and Financial Proposals in accordance with the requirements and instructions specified in the tender documents.

በተቋም ውስጥ ሀብትን ማወቅ፣ መንከባከብ እና ማቆየት :- የወርቃማው ሰኞ የመወያያ ርዕስ ቀን ፡ - ነሃሴ 06፣/2018 ዓ/ምአቅራቢ ፡- ሄኖክ ሽታው(ኢ/ር)             ፓወር ማናጀ...
10/08/2026

በተቋም ውስጥ ሀብትን ማወቅ፣ መንከባከብ እና ማቆየት :- የወርቃማው ሰኞ የመወያያ ርዕስ
ቀን ፡ - ነሃሴ 06፣/2018 ዓ/ም
አቅራቢ ፡- ሄኖክ ሽታው(ኢ/ር)
ፓወር ማናጀር

"የሰው ኃይል እና የሚያፈስ ባልዲ" (The Leaking Bucket Analogy)

እንደ አቅራቢው ገለጻ አንድ ተቋም አዳዲስ ሰራተኞችን በብዛት እየቀጠረ ነገር ግን ነባርና ልምድ ያላቸውን ሰራተኞች የሚይዝበት/ሚያቆይበት የተመቸ ሁኔታ ከሌለው፣ በስሩ ቀዳዳ እያለ ውሃ እንደሚቀዳ ባልዲ ይሆናል። አዲስ ሰራተኛ ለመቅጠር እና ለማሰልጠን የሚወጣው ወጪ ነባሩን ሰራተኛ ከመያዝ ወጪው በእጥፍ ይበልጣል። ሀብትን ማቆየት ማለት አስቀድሞ የባልዲውን ቀዳዳ መድፈን ማለት ነው ።

በተቋም ውስጥ ሀብትን ማወቅ እና ማቆየት የአንድ ጊዜ ተግባር ሳይሆን የዘወትር ባህል እና የአሰራር ሂደት መሆን አለበት። ተቋማት የሰው ኃይላቸውን፣ ቁሳዊ ንብረታቸውን፣ መረጃቸውን እና ፋይናንሳቸውን በአግባቡ ሲንከባከቡ እና ሲጠብቁ፣ ከአላስፈላጊ ብክነት ይድናሉ፤ የሰራተኞች ተነሳሽነት ይጨምራል፤ እንዲሁም የረጅም ጊዜ አላማቸውን ያለ እንግልት ማሳካት ይቻላቸዋል።

እንኳን ደስ አለን!
04/08/2026

እንኳን ደስ አለን!

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Addis Ababa Light Rail Transport Service Enterprise posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Addis Ababa Light Rail Transport Service Enterprise:

Shortcuts

Share