Addis Ababa City Plan & Development Bureau

Addis Ababa City Plan & Development Bureau የአዲስ አበባን ገፀምድራዊ፣ማህበረ ምጣኔሀብታዊ የልማት ዕቅድ ማዘጋጀት፤ በከተማው ምክር ቤት ማስፀደቅና አፈፃፀሙን መከታተል፣ መቆጣጠር፤የጥናትና ምርምር ስራዎችን መስራትና ማስረፅ
'City Plan for Prosperous Urbanization'

ጳጉሜን 1 የሚከበረውን “ የእመርታ ቀን”  በማስመልከት የፎቶ አወደርዕይ በታላቅ ድምቀት ተከፈተ"የእመርታ ቀን" ምክንያት በማድረግ፣ የከተማችንን ሁለንተናዊ የልማት ጉዞ በሚያሳይ በዚህ  አ...
06/09/2026

ጳጉሜን 1 የሚከበረውን “ የእመርታ ቀን” በማስመልከት የፎቶ አወደርዕይ በታላቅ ድምቀት ተከፈተ

"የእመርታ ቀን" ምክንያት በማድረግ፣ የከተማችንን ሁለንተናዊ የልማት ጉዞ በሚያሳይ በዚህ አውደርዕይ እና የፓናል ውይይት የዕለቱ የክብር እንግዳ የአዲስ አበባ ከተማ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ በተገኙበት ተከፍቷል ፡፡

የክቡር እንግዳው በመክፈቻ ንግግራቸው “የገቢዎቻችን ማደግና የፋይናንስ ሥርዓታችን መጠናከር፣ በፕላንና በዲዛይን የታገዙ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች፣ በኢንዱስትሪና በአርሶ አደርና ከተማ ግብርና የታየው ምርታማነት፣ ከአካባቢ ጥበቃ ጋር ተጣጥሞ የልማት አካሄዳችን ዘላቂ የወደፊት ጉዞ ያመላክታል በማለት እነዚህ ውጤቶች መድረሻችን ሳይሆኑ ለአዲሱ የዕድገት ምዕራፍ መነሻ ናቸው ሲሉ ገልፀዋል።

አክለውም በከተማዋ የተመዘገቡት ስኬቶች የሀገሪቱን አጠቃላይ የእመርታ ጉዞ የሚያጠናክሩ በመሆናቸው ይህን በጎ ልምድ አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ሲሉ ተናግርዋል።

በአራዳ ፓርክ በተከፈተው በዚህ አውደርዕይ እና የፓናል ውይይት ባለፉት የለውጥ ዓመታት የተመዘገቡ ታላላቅ ከተማ አቀፍ ስኬቶችን የቀረበ ሲሆን ፤ የፕላንና ልማት ቢሮ፣ የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን፣ የኢንዱስትሪ ቢሮ፣ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን፣ የዲዛይንና ግንባታ ቢሮ፣ የገቢዎች ቢሮ እና የፋይናንስ ቢሮ በጋራ በመሆን ያዘጋጁት እንደሆነ ተነግሯል ።

በመድረኩ የዕለቱ የከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች ጨምሮ ከ400 በላይ የሚሆኑ ጥሪ የተደረገላቸው ተሳታፊዎች የከተማዋን ሁለገብ የእድገት እመርታ፣ የከተማ ግብርና ልማቶች፣ የዲጂታልና የመሰረተ ልማት የሚያሳይ የፎቶ አውደርዕይ ጎብኝተዋል።

06/09/2026

የእመርታ ቀን

አባቶቻችን የኢትዮጵያን ዳር ድንበር በደምና በአጥንታቸው አስከብረው ታላቅ ሀገር አውርሰውናል፤ ዛሬ ደግሞ እውነተኛ ሉዓላዊነትን እያረጋገጥን ያለነው ከልመናና ከጥገኝነት በተላቀቀው አዲሱና ታሪካዊው መንገዳችን ነው! በሚሊዮን በሚቆጠር ዶላር ስንዴ ከማስገባት ተነስተን ዛሬ የአፍሪካ ቀዳሚ ስንዴ አምራች በመሆን የሚሊዮን ዶላሮችን ወጪ ማስቀረት ችለናል። በ«ሌማት ትሩፋት» የምግብ ዋስትናን በተግባር እያረጋገጥን፣ በ«ኢትዮጵያ ታምርት» ንቅናቄም አዳዲስ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋትና የሥራ ዕድል በመፍጠር ሉዓላዊነታችንን እያረጋገጥን እንገኛለን። ከዚህ ቀደም የማይደፈሩና አይነኬ ይባልላቸው የነበሩ ከባድ የማክሮ-ኢኮኖሚ ሪፎርም ውሳኔዎችን በቁርጠኝነት በመተግበር፤ የሀገራችንን ኢኮኖሚ በፅኑ መሠረት ላይ እየገነባን እንገኛለን። እነዚህ ሁሉ ታላላቅ ድሎች ኢትዮጵያ በሚያጋጥሟት ውስጣዊና ውጫዊ ፈተናዎች ሸብረክ ሳትል በፅናት መጓዝ መቻሏን የሚያረጋግጡ ህያው ምስክሮች ናቸው፤ ይህ የእመርታ ጉዟችን ለመጪው ዓመት የሰነቀው ተስፋ እጅግ ግዙፍ ነው!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

06/09/2026
06/09/2026

ከሰሞኑ በማህበራዊ ሚዲያ እና በተለያዩ መንገዶች ከቦሌ - መገናኛ የቪአይፒ ኮሪደር ልማት አካል የሆነውና ቦሌ ብራስ አካባቢ በሚገኝ የመንገድ መሿለኪያ ውስጥ የተፈጠረውን የውሃ ማቆር ችግር አስመልክቶ የሰጣችሁትን ጥቆማ በአክብሮት ተቀብለናል።

በእርግጥም የሰጣችሁት ጥቆማ ትክክል እና ተገቢነት ያለው ከመሆኑ በተጨማሪ ለከተማችን ልማት ያላችሁን ተቆርቋሪነት እና የኔነት ስሜት ያሳየ በመሆኑ ከልብ እያመሰገንን።

ይህ ያልተጠናቀቀው የምድር ውስጥ መሿለኪያ ቦታ የውሃ ማቆር ችግር ያጋጠመው፤ ቀደም ሲል ስራውን ይዞት ከነበረው ኮንትራክተር ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ምክንያት የውል መቋረጥ በማጋጠሙ እና የግንባታ መጓተት በመከሰቱ ሲሆን ፤ ይህንን ያልተጠበቀ ችግር በመረዳት ተቋማችን አፋጣኝ መፍትሄ ለመስጠት ሲሰራ ቆይቷል።

በመሆኑም ያልተጠናቀቀውን የመሿለኪያ የምድር ውስጥ ስራ ዳግም ለማስጀመር በፍጥነት የአዲስ ኮንትራት ግዢ ጨረታ በማውጣት ሂደቱ ተጠናቋል።

በመጨረሻም ሀሳባችሁን ለሰጣችሁ እና በኔነት ስሜት ተቆርቋሪነታችሁን ለገለፃችሁ ሁሉ በድጋሚ ምስጋናችንን እያቀረብን፤ ይህንን የተጓተተ ስራ በማጠናቀቅ በአጭር ጊዜ ውስጥ ውጤቱን መልሰን ለእናንተው የምናሳውቅ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን ።

የከተማችንን ልማት ከነዋሪዎቿ ጋር በመሆን እናፋጥናለን!

05/09/2026
03/09/2026

ከመኪና ሽያጭ ጋር ተያይዞ የሕግ ጥሰቶች የሚፈጸሙ አካላት ላይ እርምጃ እየተወሰደ ነው - የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ

በመዲናዋ በመኪና አስመጪዎች እና በኮሚሽን ሠራተኞች በኩል የሚፈጸምን የታክስ ስወራ እና የግብር ማጭበርበር ድርጊት ለመግታት ጠንካራ የሕግ ማስከበር ሥራ እየሠራ መሆኑን የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ።

ቢሮው በሰጠው መግለጫ እንደገለጸው፣ በርካታ የመኪና አስመጪዎች ለከተማ አስተዳደሩ የሚገባውን ወርሃዊ ቫት እና ዓመታዊ ግብር ላለመክፈል ሲሉ ሽያጮቻቸውን በኮሚሽን ሠራተኞች አማካይነት እያካሄዱ ይገኛሉ።

በተጨማሪም አብዛኞቹ አስመጪዎች አድራሻቸው ሳይታወቅ ከዋጋ በታች ደረሰኝ በመቁረጥ ከፍተኛ የግብር ስወራ ወንጀል እንደሚፈጽሙ በተካሄደው ጥናት መረጋገጡ በመግለጫው ተጠቅሷል።

በታክስ ሕጉ መሠረት በሌሎች ክልሎች የተመዘገቡ አስመጪዎች አዲስ አበባ ውስጥ ሽያጭ ለማካሄድ በሚያስችል መልኩ የክልል ንግድ ፈቃዱን ማስጠቀስ፣ የመሸጫ ቦታ መከራየት እና የሽያጭ መመዝገቢያ ማሽኖቻቸውን ማስተካከል ይጠበቅባቸዋል።

ማንኛውም አስመጪ ያስገባውን መኪና መሸጥ ያለበት በኮሚሽን ሠራተኞች አድራሻ ሳይሆን ንግድ ፈቃድ ባወጣበት ቦታ ብቻ ሊሆን እንደሚገባም ቢሮው አሳስቧል።

የኮሚሽን ንግድ ፈቃድ ያላቸው ሠራተኞችም ቢሆኑ በኮሚሽን ፈቃድ የመኪና መሸጫ ግቢዎችን ተከራይተው ከአስመጪዎች የተረከቧቸውን መኪኖች መሸጥ በሕግ ተጠያቂ የሚያደርግ የታክስ ስወራ ወንጀል መሆኑን ተገንዝበው ከድርጊቱ እንዲቆጠቡ ጥሪ ቀርቧል።

ቢሮው ከመኪና ሽያጭ ጋር ተያይዞ የሕግ ጥሰቶችን የሚፈጸሙ አካላት ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት ሕግ የማስከበር እርምጃውን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጿል።

Address

2Q8V+J75, Equatorial Guinea Street, አዲስ አበባ 1000 ኢኳቶሪያል ጊኒ መንገድ፣ ለም ሆቴል አካባቢ፣ Addis Ababa
Addis Ababa

Telephone

+251912316293

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Addis Ababa City Plan & Development Bureau posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Addis Ababa City Plan & Development Bureau:

Shortcuts

Share