Ethiopian Media Authority - ኢመብባ

Ethiopian Media Authority - ኢመብባ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ethiopian Media Authority - ኢመብባ, Public & Government Service, Addis Ababa.

This is the official page of the Ethiopian Media Authority of the Federal Democratic Republic of Ethiopia, a government body with a mission of Promoting Pluralistic and Responsible Media through enabling Regulation, Capacity Building, and Partnership.

የብሮድካስት አገልግሎት ባለፈቃድ ግዴታዎችየመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁጥር 1238/13 አንቀፅ 55 ንዑስ አንቀፅ አንድ (ሰ) እንደሚያስረዳው ማንኛውም የብሮድካስት አገልግሎት ባለፈቃድ በፕሮግራ...
02/09/2026

የብሮድካስት አገልግሎት ባለፈቃድ ግዴታዎች

የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁጥር 1238/13 አንቀፅ 55 ንዑስ አንቀፅ አንድ (ሰ) እንደሚያስረዳው ማንኛውም የብሮድካስት አገልግሎት ባለፈቃድ በፕሮግራም ሥርጭቱ ተገቢና ጨዋ የቋንቋ አጠቃቀም ተግባራዊ የማድረግ ግዴታ አለበት፡፡

በመደበኛ እና በማህበራዊ ሚዲያ አውታሮች ላይ የህግ ጥሰት፣ የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ ሲመለከቱ፤ "በእጅ ስልክዎ፣በታብሌት፣ በዴስክቶፕ፣ በላፕቶፕ እና በሁሉም የዲጂታልና የቋንቋ አማራጮች" ለባለሥልጣኑ በማሳወቅ ሀገራዊ ግዴታዎን ይወጡ!!

EMA APP

https://play.google.com/store/apps/details?id=et.aii.mediacomplanitapp

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን አባይ ቴሌቪዥን ባሰራጫቸው  ዜናዎች እና ኘሮግራሞች ላይ ለተፈፀሙ የሕግና የጋዜጠኝነት ሙያ ስነ-ምግባር ጥሰቶች ማስጠንቀቂያ ሰጠ፤ የጣቢያው ሃላፊዎችም ...
01/09/2026

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን አባይ ቴሌቪዥን ባሰራጫቸው ዜናዎች እና ኘሮግራሞች ላይ ለተፈፀሙ የሕግና የጋዜጠኝነት ሙያ ስነ-ምግባር ጥሰቶች ማስጠንቀቂያ ሰጠ፤ የጣቢያው ሃላፊዎችም የተሰጠውን ማስጠንቀቂያ አምነው በመቀበል ለተፈጠረው ስህተት ይቅርታ ጠይቀዋል።

​የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን አባይ ቴሌቪዥን ባለፉት 3 ወራት ባሰራጫቸው (ከሰኔ - ነሐሴ / 2018 አ.ም) ዜናና የተለያዩ ፕሮግራሞች እንዲሁም ማስታወቂያዎች ላይ ያካሄደውን የሚዲያ ሞኒተሪንግ ይዘት ክትትል መሠረት በማድረግ የተፈፀሙ የሕግና የሙያ ስነ-ምግባር ጥሰቶች ላይ ከጣቢያው ሃላፊዎች ጋር ውይይት አካሂዷል፤ በዚህም ጣቢያው አፋጣኝ የማስተካከያ እርምጃ እንዲወስድ በማሳሰብ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኃይማኖት ዘለቀ በውይይቱ ላይ አባይ ቴሌቪዥን የአገራችንን ብሔራዊ ጥቅም ያስቀደሙ፣ በዲጂታል ቴክኖሎጅ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የታገዙ አስተማሪ እና አዝናኝ ፕሮግራሞችን እያሰራጨ የሚገኝ የንግድ ሚዲያ መሆኑን አውስተው ይሁን እንጂ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ አልፎ አልፎ የሚስተዋሉ የሕግና የሙያ ስነ-ምግባር ጥሰቶች በምንም መልኩ ተቀባይነት የሌላቸውና አፋጣኝ የማስተካከያ እርምጃ ሊወሰድባቸው የሚገባቸው ናቸው ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

ዋና ዳይሬክተሯ አክለውም በጣቢያው ላይ ከተስተዋሉ የስነምግባር ጥሰቶች መካከል ከማህበረሰባችን ባህል ወግና እሴት ያፈነገጡ ፀያፍ ንግግሮችና አባባሎች ማሰራጨት፣ በመልካም ባህሪና በስነምግባር የታነፀ ወጣት ትውልድ በማፍራት ሂደት ላይ አሉታዊ ተፅእኖ ያላቸው ይዘቶችን እና እንዲሁም የሴቶችን ክብር የሚነኩ ፕሮግራሞች ላይ የተስተዋሉ ግድፈቶች በአፋጣኝ እርምት እንዲደረግባቸው አሳስበዋል።

አክለውም በዜናዎች ላይ የሚስተዋሉ ያልተረጋገጡ ምንጮቾን መጠቀም ሊደገም እንደማይገባም ዋና ዳይሬክተሯ አስገንዝበው አባይ ቴሌቪዥን የአገራችንን ህጎች፣ የመገናኛ ብዙሃን አዋጁን እና የጋዜጠኝነት የሙያ ስነምግባር ን ከኤዲቶሪያል ፖሊሲው ጋር አቀናጅቶ በጥንቃቄ እንዲተግበርም አሳስበዋል።

​የአባይ ቴሌቪዥን ሃላፊዎች በበኩላቸው በባለስልጣኑ የሚዲያ ሞኒተሪንግ የቀረቡ አብዛኛው ይዘቶች ላይ የተፈፀሙ ጥሰቶች በጣቢያው ኤዲቶሪያል የተገመገሙና የማስተካከያ እርምት እርምጃ ለመውሰድ መግባባት የተደረሰባቸው እንደሆነ ጠቅሰው በክትትል ሂደቱ የተሰጣቸውን አስተያየትም በአዎንታዊ ጎን ወስደው እንደሚያስተካክሉ አሳውቀዋል።

​ሃላፊዎቹ አክለውም በጣቢያው ላይ በባለስልጣኑ የተሰጡትን ማስተካከያዎችን ወስደው በፍጥነት በማረም ጣቢያው አገራዊ መልካም ተሞክሮዎችና ይዘቶቾ የሚቀርቡበት ጣቢያ እንዲሆን የሰነቁትን ራእይ በቁርጠኝነት አንደሚተገብሩም አመልክተዋል።


Ethiopia Media Authority Renews Reuters’ Reporting Licenses after Six-Month Suspension Following Discussions with Reuter...
28/08/2026

Ethiopia Media Authority Renews Reuters’ Reporting Licenses after Six-Month Suspension Following Discussions with Reuters Executives

Following discussions with senior executives of Reuters, the Ethiopia Media Authority has renewed the reporting licenses of Reuters’ three permanent news agency correspondents, whose licenses had been suspended in Ethiopia for the past six months.

During a discussion, Haimanot Zeleke, Director General of the Ethiopia Media Authority, explained to Nick Tattersall, Executive Editor of Reuters and Silvia Aloisi, Reuters’ Africa Editor, that based on the Authority’s media monitoring findings, some of the media content Reuters had disseminated about Ethiopia over the past seven months had been inconsistent with Ethiopia’s laws, the Media Proclamation, and the country’s national interests, and had also failed to comply with professional journalistic ethics.

The Director General further noted that Reuters has been operating in Ethiopia through its permanently licensed news agency correspondents, as permitted under Ethiopian law and the Media Proclamation, while also producing a significant volume of media reports through its correspondents based in various countries.

However, the Director General explained that, more recently, some Reuter’s reports concerning Ethiopia had raised concerns regarding balance, accuracy, credibility, and objectivity. Referring to the dates and subjects of the reports in question, she explained to the Reuters executives that some of the reports appeared to be one-sided and contained issues that were considered violations of Ethiopian law, the Media Proclamation, and professional journalistic standards. In response, the Reuters executives agreed that the news organization would take the necessary corrective measures and issue appropriate corrections where required.

For their part, the Reuters executives explained that Reuters is an independent media organization and follows strict editorial guidelines to ensure that its reporting is balanced, based on sufficient information, and free from bias. They also acknowledged that errors can occasionally occur and stated that, where such errors occur, Reuters apologizes and issues corrections as appropriate.

The Reuters executives expressed their strong respect for Ethiopia and emphasized their firm belief that, given the country’s population and economic significance, Ethiopia deserves broad and comprehensive international media coverage. They further stated that Reuters is committed to respecting Ethiopian law and wishes to provide coverage of the country’s political, economic, and cultural affairs. They also affirmed that Reuters journalists are expected to adhere to professional journalistic ethics, understand Ethiopia’s national interests, and respect the country’s position.

At the conclusion of the discussions, the Ethiopia Media Authority renewed the reporting licenses of Reuters’ permanent news agency correspondents in Ethiopia, which had previously been suspended temporarily in connection with concerns regarding violations of the law and professional journalistic ethics.

Finally, the Authority called on all relevant stakeholders to take note that the licenses of Reuters’ permanent news agency correspondents in Ethiopia have been renewed and to provide them with the necessary cooperation to carry out their work.


የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከሮይተርስ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ከተወያየ በኋላ በኢትዮጵያ ላለፋት ስድስት ወራት ታግዶ የቆየውን የሶስት ቋሚ የዜና ወኪሎቹን የዘገባ ፈቃድ አድሷል።የባለ...
28/08/2026

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከሮይተርስ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ከተወያየ በኋላ በኢትዮጵያ ላለፋት ስድስት ወራት ታግዶ የቆየውን የሶስት ቋሚ የዜና ወኪሎቹን የዘገባ ፈቃድ አድሷል።

የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኃይማኖት ዘለቀ ከዓለም አቀፉ የዜና ተቋም ሮይተርስ ኤክስክዩቲቭ ኤዲተር ኒክ ታተር እና የአፍሪካ ኤዲተር ሲልቪያ አሎይሲ ጋር ባካሄዱት ውይይት ሮይተርስ ኢትዮጵያን አስመልክቶ ባለፉት ሰባት ወራት ካሰራጫቸው የሚዲያ ይዘቶች መካከል የተወሰኑት የአገራችን ህጎች፣ የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ እና የአገራችንን ብሔራዊ ጥቅም የሚጻረሩ እንዲሁም የጋዜጠኝነት ሙያዊ ስነምግባር ያልተከተሉ እንደነበሩ የባለስልጣኑ የሚዲያ ሞኒተሪንግ ዉጤቶችን መሠረት በማድረግ ገልጸውላቸዋል።

ዋና ዳይሬክተሯ አክለውም ሮይተርስ የአገራችን ህግና አሰራር እንዲሁም የመገናኛ ብዙሃን አዋጁ በሚፈቅደው መሠረት በኢትዮጵያ ቋሚ የዜና ወኪልነት ፈቃድ ተሰጥቷቸው በሚሰሩ አና በተለያዩ የውጭ አገራት ባሉ ዘጋቢዎቹ ጭምር በርካታ የሚዲያ ዘገባዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል።
አያይዘውም ይሁንና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሮይተርስ ኢትዮጵያን አስመልክቶ ያሰራጫቸው ዘገባዎችን ይዘት የተሰራጩበትን ቀንና ርእሰ ጉዳዮቾን በመጥቀስ የሚዛናዊነት፣ የትክክለኝነት ፣ የተአማኒነትና የተጨባጭነት ችግር የተስተዋለባቸውና ወደ አንድ ወገን ያደሉ እንደነበሩ ለሮይተርስ ሃላፊዎች አስረድተው ይህም የአራችንን ህግ፣ የመገናኛ ብዙሃን አዋጁን እንዲሁም የጋዜጠኝነት የሙያ ስነምግባር ጥሰት የተስተዋላባቸው ነበሩ ሲሉ አፅንኦት ሰጥተዋል። ለዚህም የሮይተርስ ሃላፊዎች አስፈላጊዉን እርማትና ማስተካከያ የዜና ተቋሙ እንደሚያደርግ መግባባት ላይ ደርሰዋል።

በውይይቱ ላይ የሮይተርስ ሃላፊዎች በበኩላቸው የዜና ወኪሉ ገለልተኛ ሚዲያ መሆኑን ገልፀው ዘገባዎችን ሚዛናዊ በሆነ፣ በበቂ መረጃ ተመስርቶ፣ ከአድልዎ በጸዳ መልኩ ለመሥራት ጥብቅ የኤዲቶሪያል መመሪያዎችን እንደሚከተል አስታውቀዋል።እንዲሁም አልፎ አልፎ ለሚፈጠሩ ስህተቶችም ይቅርታ ጠይቀው ማስተካከያ እንደሚሰጡም አስገንዝበዋል።

ሮይተርስ ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ክብር እንዳለው የገለጹት የአለምአቀፉ የዜና ወኪል የሥራ ኃላፊዎች፣ ሀገሪቱ ባላት የህዝብ ቁጥርና የኢኮኖሚ ግዝፈት ልክ ዓለም አቀፍ ሰፊ የሚዲያ ሽፋን ማግኘት አለባት የጸና እምነት እንዳላቸውም አስረድተዋል።

ሮይተርስ የኢትዮጵያን ሕግ አክብሮ እንደሚሠራ፣ የሀገሪቱን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ባህላዊ እሴቶች ሽፋን መስጠት እንደሚፈልግም አመልክተው ጋዜጠኞቹም የሙያ ሥነ-ምግባርን አክብረው መሥራት እንዳለባቸው እና የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም እንደሚረዱና አቋሟንም እንደሚያከብሩም አረጋግጠዋል።

በውይይቱ ማጠናቀቂያ ላይም ከህግና የሙያ ስነምግባር ጥሰት ጋር ተያይዞ ለጊዜው ታግዶ የቆየው የሮይተርስ የኢትዮጵያ የዜና ወኪሎች የዘገባ ፈቃድ እንዲታደስላቸው በባለሥልጣኑ ተደርጓል።

በመጨረሻም ባለስልጣኑ የሚመለከታቸዉ አካላት በሙሉ የሮይተርስ የኢትዮዮጵያ ቋሚ የዜና ወኪሎቹች ፈቃዳቸው እንደታደሰላቸው አውቀው አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉላቸዉ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

የኢትዮጵያ  መገናኛ  ብዙኃን አዋጅ ቁጥር 1238/13  ንዑስ  ክፍል ሶስት አንቀጽ 70 እንደሚያስረዳው የሃይማኖት  ተኮር ፕሮግራሞች 1,  ሃይማኖት  ተኮር ፕሮግራሞችን  የሚያሰራጭ ማንኛ...
27/08/2026

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁጥር 1238/13 ንዑስ ክፍል ሶስት አንቀጽ 70 እንደሚያስረዳው

የሃይማኖት ተኮር ፕሮግራሞች

1, ሃይማኖት ተኮር ፕሮግራሞችን የሚያሰራጭ ማንኛውም የብሮድካስት አገልግሎት ባለፈቃድ ለሁሉም ሃይማኖቶችና እምነቶች ተገቢ ክብር እንደተሰጣቸው ሊያረጋግጥና የሃይማኖት እና የእምነት ነፃነትንና መሠረታዊ ሰብዓዊ መብትን ሊጠብቅ ይገባል ።

2, ማንኛውም የሃይማኖት ተኮር ፕሮግራም በሃይማኖቶች ተከታዮች መካከል የእርስ በእርስ ግጭት ማነሳሳት ፥ የሌሎችን ሃይማኖት ወይም እምነት ማንኳሰስ፥ ወይም በሃይማኖቶች ተከታዮች መካከል አለመቻቻል እንዲፈጠር መቀስቀስ የለበትም ።

በመደበኛ እና በማህበራዊ ሚዲያ አውታሮች ላይ የህግ ጥሰት፣ የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ ሲመለከቱ፤ "በእጅ ስልክዎ፣በታብሌት፣ በዴስክቶፕ፣ በላፕቶፕ እና በሁሉም የዲጂታልና የቋንቋ አማራጮች" ለባለሥልጣኑ በማሳወቅ ሀገራዊ ግዴታዎን ይወጡ!!

EMA APP

https://play.google.com/store/apps/details?id=et.aii.mediacomplanitapp

እንኳን ለ1501ኛው የነቢዩ መሐመድ(ሰዐወ) የመውሊድ በዓል አደረሳችሁየነቢዩ መሐመድ ታሪክ ትውልድን ለበጎ ከሚቀርጹ ታሪኮች መካከል አንዱ ነው፡፡ የተጠሩበትን ዓላማ ማክበር፤ ለተጠሩበት ዓላ...
24/08/2026

እንኳን ለ1501ኛው የነቢዩ መሐመድ(ሰዐወ) የመውሊድ በዓል አደረሳችሁ

የነቢዩ መሐመድ ታሪክ ትውልድን ለበጎ ከሚቀርጹ ታሪኮች መካከል አንዱ ነው፡፡ የተጠሩበትን ዓላማ ማክበር፤ ለተጠሩበት ዓላማ ዋጋ መክፈል፤ የተጠሩበትን ለሌሎች ማካፈል፤ የተጠሩበትን አክብሮ መኖር - እነዚህ ሁሉ ሺ መጻሕፍት የሚወጧቸው ትምህርቶች ናቸው፡፡

ነቢዩ የተጠሩበትን ዓላማ በሚገባ ስለተገነዘቡ አክብረው ኖረዋል፡፡ የተጠሩት ለተራና ርካሽ ነገር እንዳልሆነ ተገንዝበዋል፡፡ የተጠሩት ትውልድን ለመቅረጽና ታሪክን ለመቀየር መሆኑን አምነዋል፡፡ ያንንም በቃላቸው፣ በሥራቸውና በኑሯቸው አክብረውት ነኖረዋል፡፡ ለታላቅ ሀገራዊ ዓላማ ተጠርተናል ብለን የምናምን ከሆነ ይህ የነቢዩ ሕይወት ታላቅ ትምህርት ይሆነናል፡፡ የተጠራንበትን ዓላማ በንግግራችን፣ በሥራችንና በሕይወታችን እንግለጠው፡፡

ነቢዩ ለተጠሩበት ዓላማ ዋጋ ከፍለዋል፡፡ ከቦታቸው ተሰደዋል፤ ምግብና መጠለያ ተነፍገዋል፤ ከቤተሰቦቻቸው ተለይተዋል፡፡ ለሞት በሚያበቁ ፈተናዎች ውስጥ አልፈዋል፡፡ ጦርነት ተከፍቶባቸዋል፡፡ ነገር ግን ሁሉንም በአላህ ኃይል አሸንፈዋል፡፡ ክብር ያለ መከራ አይገኝምና፡፡ እውነተኛ ሰው ለዓላማው እንደ ነቢዩ መሐመድ(ሰዐወ)ዋጋ ይከፍላል፡፡ ዓላማው የሚያስገኘውን ክብርና ጥቅም ብቻ ሳይሆን ዓላማው የሚያስከፍለውን መሥዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ይሆናል፡፡

ነቢዩ መሐመድ(ሰዐወ) ከአላህ የደረሳቸውን መልእክት ለራሳቸው ብቻ አላስቀሩም፡፡ የተጠሩበትን ለሌሎች ለማካፈል ተግተዋል፡፡ መጀመሪያ በጣት ለሚቆጠሩ ሰዎች፣ በኋላም ለቅርብ ሱሐባዎች፣ በመጨረሻም ለዓለም መልእክቱን አዳርሰዋል ፡፡ እሳቸው የዘሩት ዘር እያፈራና እየጎመራ ተጉዟል፡፡ ዓላማችንን እኛ ማወቃችንና ማመናችን ብቻ ጥቅም የለውም፡፡ ሌሎች እንዲያውቁና እንዲያምኑ ልክ እንደነቢዩ ተገትተን መድከም አለብን፡፡

የነቢዩን መውሊድ ስናከብር ከሕይወታቸው እየተማርን፤ የተማርነውንም ለሀገረ መንግሥት ግንባታችን እየተጠቀምን እንዲሆን አደራ እላለሁ፡፡

በድጋሚ መልካም የመውሊድ በዓል ይሁንልን።

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ
ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ  መገናኛ  ብዙኃን አዋጅ 1238/13አንቀጽ  61  እንደሚያስረዳው የበይነመረብ መገናኛ  ብዙኃን  ግዴታዎች ማንኛውም  የበይነመረብ  መገናኛ  ብዙኃን   የሚከተሉት  ግዴታዎች  ...
24/08/2026

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን አዋጅ 1238/13
አንቀጽ 61 እንደሚያስረዳው

የበይነመረብ መገናኛ ብዙኃን ግዴታዎች

ማንኛውም የበይነመረብ መገናኛ ብዙኃን የሚከተሉት ግዴታዎች ይኖሩበታል ።

1, ይዘት ለማመንጨት ፣ ለማሣተም እና ለማሠራጨት የሚጠቀሙት ቋንቋ ፀያፍ፣ የብልግና፣ ፆታን ፣ ብሔርንና ሃይማኖትን መሠረት ያደረጉ አስቀድመው የነበሩም ሆነ ያልነበሩ የጥላቻ ስሜቶች እንዲፈጠሩ አስተዋጽኦ የሚያደረጉና ግጭት የሚያነሳሳ እንዳይሆን የማድረግ ።

2,በበይነመረብ መገናኛ ብዙሃኑ ከመነጨ ይዘት ጋር የሚያምታታ እንዳይሆን ለማረጋገጥ ከሦስተኛ ወገን ተባባሪዎች ፣ ልዩ ፍላጎት ካላቸው ቡድኖችና ከማስታወቂያ አስነጋሪዎች የሚመነጭ ይዘትን በግልጽ የመለየት ።

3,የይዘት አመንጪዎችና አሳታሚዎች ይዘቶችና የይዘት ማመንጨትና ማሠራጨት ይዘቶች ሂደት የጠበቀ ና ፍትሐዊ እንዲሁም ብዝሃነት ያላቸው ድምፆችን ያካተተ መሆኑን ለማረጋገጥ ጥረት የማድረግ ።

በመደበኛ እና በማህበራዊ ሚዲያ አውታሮች ላይ የህግ ጥሰት፣ የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ ሲመለከቱ፤ "በእጅ ስልክዎ፣በታብሌት፣ በዴስክቶፕ፣ በላፕቶፕ እና በሁሉም የዲጂታልና የቋንቋ አማራጮች" ለባለሥልጣኑ በማሳወቅ ሀገራዊ ግዴታዎን ይወጡ!!

EMA APP

https://play.google.com/store/apps/details?id=et.aii.mediacomplanitapp

የኢትዮጵያ  መገናኛ  ብዙኃን አዋጅ 1238/13አንቀጽ  60  እንደሚያስረዳው የቴሌቪዥን  ብሮድካስት  አገልግሎት  ባለፈቃድ ግዴታዎች ማንኛውም  የቴሌቪዥን  ብሮድካስት  አገልግሎት  ባለፈ...
23/08/2026

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን አዋጅ 1238/13

አንቀጽ 60 እንደሚያስረዳው

የቴሌቪዥን ብሮድካስት አገልግሎት ባለፈቃድ ግዴታዎች

ማንኛውም የቴሌቪዥን ብሮድካስት አገልግሎት ባለፈቃድ የሚከተሉት ግዴታዎች ይኖሩበታል

1, በባለፈቃዶች መካከል የሚደረግ የፕሮግራም ልውውጥ እንደተጠበቀ ሆኖ በፈቃዱ ላይ በተመለከተው የፕሮግራም '' ቻናል'' ብቻ ፕሮግራሙን ማሠራጨት

2,በቀጥታ ሥርጭት የሚሠራጩ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ፕሮግራሞችን ሲያቀርብ የፕሮግራሙን ይዘት በምልክት ቋንቋ የማቅረብ እና

3, በጽሑፍ የሚያቀርባቸውን አስፈላጊ መረጃዎች በድምጽ አስደግፎ የማቅረብ ።

በመደበኛ እና በማህበራዊ ሚዲያ አውታሮች ላይ የህግ ጥሰት፣ የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ ሲመለከቱ፤ "በእጅ ስልክዎ፣በታብሌት፣ በዴስክቶፕ፣ በላፕቶፕ እና በሁሉም የዲጂታልና የቋንቋ አማራጮች" ለባለሥልጣኑ በማሳወቅ ሀገራዊ ግዴታዎን ይወጡ!!

EMA APP

https://play.google.com/store/apps/details?id=et.aii.mediacomplanitapp

የኢትዮጵያ  የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁጥር 1238/13 ንዑስ ክፍል ሶስት አንቀጽ 68 እንደሚያስረዳው የይዘት  ግዴታዎች አጠቃላይ  ግዴታዎች 1,በእርስ በእርስ ቁጥጥር  የሚወጡ የሥነ ምግባ...
22/08/2026

የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁጥር 1238/13 ንዑስ ክፍል ሶስት አንቀጽ 68 እንደሚያስረዳው

የይዘት ግዴታዎች

አጠቃላይ ግዴታዎች

1,በእርስ በእርስ ቁጥጥር የሚወጡ የሥነ ምግባር መመሪያዎች እንደተጠበቁ ሆነው በብሮድካስት አገልግሎት ለሥርጭት የሚቀርብ ማንኛውም ፕሮግራም ወይም ዜና የሚከተሉትን ማክበር ይኖርበታል ።

ሀ) ፕሮግራሞች ወይም ዜናዎችን የተለያዩ አመለካከቶችን በማንፀባረቅ አጠቃላይ ሕብረተሰቡን እንዲያገለግሉ ሚዛናዊና ከአድልዎ የፀዱ አድረጎ ማቅረብ እና

ለ) የሚሰራጨው ፕሮግራም ወይም ዜና ይዘትንና ምንጭ እውነተኛና ትክክለኛ መሆኑን ለማረጋገጥ አሠራጩ ሪፓርት ላይ ተገቢ ጥንቃቄ እንዲያደረግና ስህተት ሲገኝም እንዲያረም ይጠበቅበታል ።

በመደበኛ እና በማህበራዊ ሚዲያ አውታሮች ላይ የህግ ጥሰት፣ የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ ሲመለከቱ፤ "በእጅ ስልክዎ፣በታብሌት፣ በዴስክቶፕ፣ በላፕቶፕ እና በሁሉም የዲጂታልና የቋንቋ አማራጮች" ለባለሥልጣኑ በማሳወቅ ሀገራዊ ግዴታዎን ይወጡ!!

EMA APP

https://play.google.com/store/apps/details?id=et.aii.mediacomplanitapp

የጥላቻ ንግግርንና የሐሰተኛ መረጃን በጋራ እንከላከል!!የምንኖርበት ዘመን መረጃ በፍጥነት የሚሰራጭበት፣ ሀሳቦችን ለመጋራትና ከሌሎች ጋር ለመገናኘት ብዙ ዕድሎች የተፈጠሩበት ነው። መረጃ ለል...
21/08/2026

የጥላቻ ንግግርንና የሐሰተኛ መረጃን በጋራ እንከላከል!!

የምንኖርበት ዘመን መረጃ በፍጥነት የሚሰራጭበት፣ ሀሳቦችን ለመጋራትና ከሌሎች ጋር ለመገናኘት ብዙ ዕድሎች የተፈጠሩበት ነው። መረጃ ለልማት፣ ለዕውቀት፣ ለመግባባትና ለሰላም እጅግ ጠቃሚ ቢሆንም፣ ያልተረጋገጠ ሐሰተኛ መረጃና ጥላቻን የሚያባብስ ንግግር ግን በማኅበረሰብ መካከል ጥርጣሬን፣ መከፋፈልንና ግጭትን ሊያባብስ ይችላል።

በተለይም በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የሚሰራጩ መልዕክቶችን ስንጋራ ጥንቃቄ ማድረግ የዜግነት ኃላፊነታችን ነው። የሰዎችን ስም የሚያጠፋ፣ ጥላቻን የሚያባብስ፣ ማኅበረሰብን የሚያከፋፍል ወይም ግጭትን ሊያቀጣጥል የሚችል መረጃ ከማሰራጨት መቆጠብ ይገባል።

እውነተኛ መረጃን እንፈልግ፣ ምንጩን እንፈትሽ፣ ሳናረጋግጥ አናሰራጭ። ከሚለያየን ነገር ይልቅ የሚያገናኘንን እንመልከት፤ በልዩነት ውስጥ አክብሮትን፣ በንግግር ውስጥ ሰላምን፣ በመረጃ ውስጥ እውነትን እናስቀድም።

በመደበኛ እና በማህበራዊ ሚዲያ አውታሮች ላይ የህግ ጥሰት፣ የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ ሲመለከቱ፤ "በእጅ ስልክዎ፣በታብሌት፣ በዴስክቶፕ፣ በላፕቶፕ እና በሁሉም የዲጂታልና የቋንቋ አማራጮች" ለባለሥልጣኑ በማሳወቅ ሀገራዊ ግዴታዎን ይወጡ!!

EMA APP

https://play.google.com/store/apps/details?id=et.aii.mediacomplanitapp

Address

Addis Ababa
43142

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Media Authority - ኢመብባ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Ethiopian Media Authority - ኢመብባ:

Shortcuts

Share