OCS ICT

OCS ICT one center service bole woreda 7

29/06/2020

ፕሮጀክት ቀረፃ
▃▃▃▃▃▃

❖አንድ ፕሮጀክት ቀረፃ (proposal) ሊያካትታቸው የሚገባቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡-

✠A) ማውጫ (Table of contents)

ገፁ ከሦስት ከበለጠ ማውጫ ሊዘጋጅለት ይገበዋል፡፡ ማውጫ ሁሉንም ምዕራፎችና ንዑስ ምዕራፎች ያሉበትን ገፅ ባመላከተ መልኩ መዘጋጀት ይኖርበታል፡፡

✠B) አጭር መግለጫ (Executive Summary)

ከግማሽ ገፅ ያልበለጠ ሆኖ ለያካትታቸው ሃሳቦች
☞ ፕሮጀክቱ እንዲሰራ ያስገደደው ዋና ችግር
☞ፕሮጀክቱ የሚያመጣው ተፅዕኖ
☞ለችግሩ የተቀመጠ መፍተሄ
☞የፕሮጀክት አዋጭነት የሚያመላክት ግምገማ
☞ፕሮጀክቱ የሚያስገኘው ጥቅም
☞ፕሮጀክቱ የሚያስፈልገው የገንዘብ መጠንና የሚወስደው ጊዜ መካተት አለባቸው፡፡

✠C) መግቢያ (Back Ground)

ከአንድ ገፅ ባልበለጠ መገለፅ ሲገባው የሚያካትታቸው ነጥቦች፡-
☞ ፕሮጀክቱ የሚፈታው ችግር ምን እንደሆነ
☞ ችግሩን ለምን መፍታት እንዳስፈለገው
☞ ስለፕሮጀክቱ አጠር ያለ ማብራሪያ የሚሉትን ይይዛል፡፡

✠D) ፕሮጀክቱ የሚመልሳቸው ችግሮች (Rationale)

ፕሮጀክቱ እንዲሰራ ምክንያት የሆኑ ነገሮች ተሰርተው መገለፅ አለባቸው በተጨማሪም የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ግብ
ለአንባቢው ግልፅ በሆነ መንገድ መስፈር አለበት፡፡

✠E) የፕሮጀክቱ ዓላማ (project objective)

ፕሮጀክቱ ሊሰራበት የሚችሉ ዋናውንና ዝርዝር ዓላማዎች ለይቶ ማቅረብ አለበት፡፡ ይህም ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ
ሊያስገኘው ይችላል ተብሎ የታሰበውን ወጤት መግለፅ ያስፈልጋል፡፡

✠F) የፕሮጀክቱመግለጫ (project Description):-

☞ የፕሮጀክቱ ስያሜና ዓላማ
☞ ጉዳዮን የሚያስረዳ ገለፃ
☞ የፕሮጀክቱ ቀጣይነት
☞ የፕሮጀክተ የሚተገበርበት ስልት
☞ ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችና የፕሮጀክቱን የግዜ ሰሌዳ ከአስር ገፅ ባልበለጠ መገለፅ አለበት፡፡

✠G) የፕሮጀክቱ አመራርና አደረጃጀት (project management and organization):-

☞ ፕሮጀክቱን የሚመሩቱና የሚሳተፉ
☞ የባለሙያዎችን ኃላፊነትና ተግባር
☞ የፕሮጀክቱን ውስጣዊ አሰራር አደረጃጀት አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘም መግለፅ አለበት፡፡

✠H) የፕሮጀክቱ ያገባኛል ባዮችና ተጠቃሚዎች (stakeholders and Beneficiaries):-

☞ ተጠቃሚዎች (Beneficiaries) ማለት በፕሮጀክቱ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተጠቃሚ የሚሆኑትን ይገልፃል፡፡
☞ ያገባኛል ባዮች (stakeholders):-
የመጀመሪያ ደረጃ ያገባኛል ባዮች (Primary stake holders)፡-በፕሮጀክቱ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በአሉታዊም ሆነ በአወንታዊ ተፅዕኖ የሚደርስባቸው ወይም በፕሮጀክቱ ላይ የሚያደርሱትን ያካትታል፡፡
የሁለተኛ ደረጃ ያገባኛል ባዮች (secondary stake holders)፡- ለፕሮጀክቱ መሰራት የራሳቸው ድርሻና ተፅዕኖ ያላቸው ግለሰቦች፤ ቡድኖችና ተቋማት ተለይተው መዘርዘር አለባቸው፡፡

✠I) የፕሮጀክቱ ትግበራ (project implementation):-

የፕሮጀክት ዕቅድ ማለት የሚሰሩት ስራዎች፤ ስራውን ለመስራት የሚያስፈልጉ የሀብት ድልድል፤ ስራው በማን፤ እንዴት፤ መቼና የት እንደሚፈፀም መገለፅ አለበት፡፡

✠J) ሊያጋጥሙ የሚችሉ ስጋትና በጎ ጎኖች (Risk and Assumption):-

☞ ፕሮጀክቱ ተግባራዊ ሲሆን ሊያጋጥሙ ይችላሉ ተብሎ የሚታሰቡ ስጋቶች ይገለፁበታል፡፡
☞ ለፕሮጀክቱን ተፈፃሚነት የሚያፋጥኑ፤ የሚረዱ በጎ ጎን ያላቸው ነገሮች አብራርቶ በሰንጠረዥ መገለፅ አለበት፡፡

✠K) ክትትና ግምገማ (Monitoring and Evaluation):

ይህ ርዕስ የሚይዛቸው፡-
☞ የስብሰባ ቃለ ጉባኤ፤ የስራ ጉብኝት፤ የማማከር ስራ መቸ እንደሚደረግና በስንት ጊዜ ልዮነት እንደሚቀርብ
☞ የክትትል ስራ የሚሰራበት ስልት
☞ የግምገማ ዕቅድን
☞ ፕሮጀክት እንዴት ለሚመለከታቸው ሪፖርት እንደሚደረግ

✠L) የፕሮጀክቱ ቀጣይነት (sustainability):

ፕሮጀክቱ የሚሰጠውን ጥቅም ዘላቂነት መገለፅ አለበት፡፡
ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ በተጨማሪም በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን ይጫኑ https://t.me/MuhammedComputerTechnology በቴሌግራም መከታተል ትችላላችሁ
እንዲሁም በፌስቡክ ፔጅ https://m.facebook.com/mameamin.6te.net
መከታተል ትችላላችሁ።
ስለዚህ ፔጁን 👍 #ላይክ 👉 #ሼር በማድረግ ለሌሎች እህት ወንድሞች ጓደኞቻችሁ እንዲደርስ ያድርጉ።

29/06/2020

✍ #የህጻናት #ምግብ #አዘገጃጀት
*******************************

ውድ የዶክተር አለ ቤተሰቦች በዚህ ጽሁፋችን ላይ ለልጆቼ ምልሰራ ብለው ለሚያስቡ ወላጆች ቀላል እና ጣፋጭ የሆነ ሁለት አይነት የህጻናት ምግብ አቅርበናል ይጠቀሙት ልጆቾን ያስደስቱበታል

👉👉 #የሩዝ #፣ካሮትና #ድንች #ውህድ #ለህጻናት #ልጆቻችን

✅ #ግብዓቶች

📌 ሁለት የሻይ ማንኪያ ሩዝ
📌 አንድ መካከለኛ መጠን ያለው ካሮት
📌 አንድ መካከለኛ መጠን ያለው ድንች

👉👉 #አዘገጃጀት

📌 ሩዙን በደንብ ማጠብ
📌 ካሮቱንና ድንቹን ልጦ በትንንሽ መጠን መክተፍ
📌 አንድ የውሃ ብርጭቆ ውሃ ወይም የተዘጋጀ ወተት ጨምሮ አንድ ላይ ጨምሮ ማብሰል።
📌 በጎድጓዳ ሳህን ጨምሮ በማንኪያ መመገብ

👉👉 #የምስር #እና #አትክልት #ሾርባ

✅ #ግብአቶች

📌 1 የቡና ሲኒ የተለቀመ ምስር
📌 1 ሽንኩርት
📌 1 ድንች
📌 1 ካሮት
📌 4 የአበባ ጎመን ግንድ
📌 4 የጥቅል ጎመን ቅጠሎች
📌 1 የሻይ ማንኪያ እርድ
📌 1 የሾርባ ማንኪያ ዘይት
📌 4 የቡና ሲኒ ውሃ

👉👉 #አዘገጃጀት

📌 የተለቀመውን ምስር በደንብ ማጠብ
📌 ሽንኩርት ልጦና አጥቦ መክተፍ፤ ሽንኩርቱን ከዘይቱ ከምስሩ እና ከእርዱ ጋር ለ 5 ደቂቃ ማቁላላት እና ውሃ ከልሶ ማንተክተክ
📌 ድንቹንና ካሮቱን ልጦ አጥቦ መክተፍ፤ ጥቅል ጎመኑንና አበባ ጎመኑን አጥቦ መክተፍ
📌 የተከተፉትን አትክልቶች ድስቱ ውስጥ ጨምሮ ከ15-20 ደቂቃ ማብሰል
📌 መብሰሉን ካረጋገጥን በኃላ፤ በመፍጫ በምንፈልገው የልስላሴ መጠን ማላም (ከወፈረ ለማቅጠን ውሃ መጠቀም ይቻላል)
📌 የተፈጨውን ውህድ ደስት ላይ ገልብጦ ለ10 ደቂቃ ማንተክተክ
📌 በመመገቢያ ሰሃን ቀንሶ መመገብ፡፡
📌 የተረፈ ካለ በ24 ሰዓት ውስጥ አሙቆ መመገብ፡፡
**********************************

👌👌👌 ከህጻናት አመጋገብ ጋር በተያያዘ እንዲሁም በማንኛውም የጤና ጉዳይ ጋር በተያያዘ ማማከር ከፈለጉ የዶክተር አለ 8809 ሀኪሞች ላይ በመደወል ያማክሩ!! ከጧት 2 ሰዓት እስከ ማታ 12 ሰዓት ከሰኞ እስከ ሰኞ ቢደዉሉ የዶክተር አለ ሀኪሞች ሊያማክሩዎ በመስመር ላይ ይገኛሉ!!!
**********************************
👌👌👌ተጨማሪ የጤና መረጃ እንዲደርሶ፦

✅ የዶክተር አለ 8809 የቴሌግራም ገፅ ፦
👉👉👉 T.ME/DOCTORALLE8809

✅ የዶክተር አለ 8809 የፌስቡክ ገፅ፦
👉👉👉 http://tiny.cc/gf606y

( #በጤና #ባለሙያ #ርብቃ)

27/06/2020

#ማሳሰቢያ የቤት ባለእድለኞች
እንደሚታወቀው ኮሚቴው ባደረገው ትልቅ ጥረት የቅፅ 09 ማስሞላት ሂደት በሁሉም ወረዳዎች በተሳካ ሁኔታ ተከናውኗል:: የዚህ ስራ መቀላጠፍን ተከትሎም ከከተማው ቤቶች ልማትና አስተዳደር ጋር በመነጋገር ቀጣዩ ቅፅ 03 የማስሞላት ስራን ማስጀመራችንን ገልፀንላችሁ እንደነበረ ይታወሳል:: በዚሁ መሠረትም በመጀመሪያው ዙር ከእያንዳንዱ ክፍለ ከተማ 50 ሠው የተስተናገደ ሲሆን በዚህ ሳምንት ደግሞ ሁለተኛው ዙር ተጀምሯል። ከየክፍለ ከተማውም 60 ሠው እየተጠራ እየተስተናገደ ይገኛል።
ስራው በዚህ መንገድ እየሄደ ባለበት ሁኔታ ሠሞኑን አላማቸው ምን እንደሆነ የማይታወቅ አካላቶች በተለያየ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ እያሠራጩት ባለው ውዥንብር ምክንያት በርካታ ባለእድለኞች ወደኮሚቴው ስልክ በመደወል ስጋታቸውን በመግለፅ ላይ ይገኛሉ። ይህ ደግሞ ኮሚቴው ላይ ከፍተኛ ጫና የፈጠረ ከመሆኑም በላይ ሌሎች የራሱን ስራዎችንም እንዳይሠራ እንቅፋት እየሆነበት ይገኛል። ስለሆነም ኮሚቴው ከዚህ በታች ያሉትን ማሳሰቢያዎች ማስተላለፍ ይወዳል።
1 ኮሚቴው እስከ አሁን የሠራቸውን ስራዎች የሠራው ፍፁም ሠላማዊና ህጋዊ በሆነ መንገድ እና ትእግስትን ከአስተዋይነት በተላበሠ መልኩ መሆኑ ይታወሳል። አሁንም መንገዳችንን የምንቀጥለው በዚሁ አካሄድ ነው። ስለሆነም ይህ አካሄድ ያዋጣናል የምትሉ ባለእድለኞች ሁሉ ከኮሚቴው ጎን በመቆም የበኩላችሁን አስተዋፅኦ እንድታበረክቱ እንጠይቃለን።
2 ቅፅ 03 የሚሞሉ ሠዎች ቁጥር አነስተኛ መሆኑን ቀድመን ተገንዝበን ለቢሮው ጥያቄዎች አቅርበን ምላሽ እየጠበቅን ነው። ስለሆነም ሁሉም ባለእድለኛ በትእግስት እንዲጠብቀን እናሳውቃለን። በተለያየ ማህበራዊ ሚዲያዎች የሚሠራጩ አሉባልታዎች አሁኑ እና ሠውን የማነሳሳት ስራዎች በፍፁም የኮሚቴው ሀሳቦች አለመሆናቸውን እንድትገነዘቡ እናሳስባለን። ኮሚቴው የሚጠቀምበትም ብቸኛ የቴሌግራም ቻናልም
https://t.me/joinchat/IQ9nqBWh7v2k90DyhlvigQ ይህ መሆኑን እናሳውቃለን።
3 ቅፅ 03 የሞላችሁበትን ተራ ኮሚቴው ለእያንዳንዳችሁ መንገር ስለማይችል በየወረዳችሁ እየሄዳችሁ ማረጋገጥ የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን በዚህ ጉዳይ ላይ ለኮሚቴው ባለመደወል እንድትተባበሩን እንጠይቃለን።
4 ለቅፅ 03 ቦሌ ክ/ከተማ መሄድ ያለባችሁ ከየወረዳችሁ ሲደወልላችሁ ብቻ ሲሆን ያልተደወለለት ሠው ቢሄድ ግን የማይስተናገድ መሆኑን እንገልፃለን። በዚሁ መሠረት በየእለቱ የሚስተናገዱ ክ/ከተሞች እና የሚስተናገደው የሠው ቁጥር እንደሚከተለው ይሆናል
ከዚህ በፊት ከአንድ ክ/ከተማ 50 ሰው የነበረውን በዚህ ሳምንት 60 ሰው በማድረግ፣ በቀን 100የነበረውን ወደ 120 ተደርጓል
በየሳምንቱ 60:60 የሚወሠዱ የሁሉም ክ/ከተማ ፕሮግራም ወጥቷል በዚሁ መሰረት፣

1. ሠኞ = ጠዋት =አ/ከ/ክ/ከተማ
=ከሠዓት =ቂ/ክ/ከተማ
2.ማክሰኞ= ጠዋት = አቃ/ክ/ከተማ
= ከሰዓት = አራ/ክ/ከተማ
3. እሮብ = ጠዋት = ን/ላ/ክ/ከተማ
= ከሰዓት = የካ/ክ/ከተማ
4.ሐሙስ = ጠዋት = ኮ/ቀ/ክ/ከተማ
= ከሰዓት = ልደታ /ክ/ከተማ
5. አርብ = ጠዋት =ጉ/ክ/ከተማ
= ከሰዓት= ቦሌ/ክ/ከተማ

ሰኔ 18/2012ዓ.ም
ኮሚቴው

______________________
በገጻችን የምናቀርባቸውን መረጃዎች በአማራጭነት በቴሌግራም ቻናላችን ለማግኘት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ።
👇👇👇👇👇
t.me/housinginaddisababa

እንዲሁም፦

እና ቢያደርጉ መረጃዎች በቀላሉ ይደርሶታል።

20/06/2020

🟣🚹 ከ200 በላይ አስገራሚ የታክሲ ላይ ጥቅሶች 🚹🟣

1. እንኑር ብለን ነው እንጂ መሞት አያቅተንም!
2. የያዝናት እድሜ አይደለም ለጠብ ለፍቅር እንኩአን
አትበቃም!
3. ብቸኝነት ደስ የሚለው ሽንት ቤት ብቻ ነዉ
4. ማች ከመሞቱ በፊት ፍቅረኛውን ዜብራላይ ይስም ነበር
5. ጭቅጭቁን ትተን ብንፋቀር ምነው ሁሉም ቅርብ ወራጅ ነው
ከፈጣሪ በቀር
6. ታክሲ ዉስጥ መጨቃጨቅ ኣሸባሪነት ነው
7. ሰዉ ብቻ ነዉ የምንጭነዉ በስህትት የተሰቀለ ካለ ይዉረድ
8. የሰራ የእጁን የተቀመጠ የቂጡን ያገኛል
9. አንገትክ ብቆረጥም ዋናዉ ጤና ነዉ
10. መብትዎን ታክሲ ላይ ትዝ ኣይበልዎ
11. ጤፍና በርበሬ ሲወደድ ችላቹ ታክሲ ላይ ታማርራላቹ
12. መንግስትና ተሳፋሪ ሊወርዱ ሲሉ ነገር ነገር ይላቸዋል
13. ስልጣን የህዝብ ማስተዳደሪያ እንጂ ማስፈራሪያ አይደለም
14. የምተኛዉ የማይተኛ ጌታ ስላለኝ ነዉ
15. አምላኬ 100000000 ዶላር እና ጤንነቴን ስጠኝ
16. ጡትና መንግስት ጊዜውን ጠብቆ መውደቁ አይቀርም
17. ምከረው ምከረው አንቢ ካለ በሴት አስመክረው
18. ጎንበሥ ቀና ብዬ ባገለግላቸው ከወንዝ የተገኘ ድንጋይ
መሠልኳቸው
19. ፍቅረኛዬን አጣው ብለህ አትጨነቅ ታክሲም ማጣት አለና
20. ጠጋ ጠጋ በሉ! ! በኛ ታክሲ ተዋውቀው ብዙ ሰው ተጋብቷል
21. ነገረኛ ተሳፋሪ አደባባይ ላይ " ወራጅ አለ " ይላል
22. ሰውን ስትወድ ከመልካም ስብዕናው ውጪ ምኑንም ሳታይ
ይሁን
23. አንድ ማፍቀር ግድ ነው ሁለት ማፍቀር ግን ንግድ ነው
ሶስት ማፍቀር ግን ኮንትሮባንድ ነው
24. መዶሻ ጭንቅላት ያለው ሰው ሁሉም ስው ሚስማር
ይመስለዋል
25. ከሰራህ ትበላለህ ካልሰራ ሲበሉ ታያለህ
26. እግዝአብሄር ድሃን ማስደሰት ሲፈልግ አህያውን አጥፍቶ
እንዲያገኘው ያደርጋል
27. የበታችነት ከተሰማ ዛፍ ላይ ዉጣ
28. ጨበሶ ከመቃጠል በልቶ መመዘን ይሻላል
29. ቅናት ያገረጣዉ ፊት ቅባት አያወዛዉም
30. አስተዉሎ የሚራመድ ጫት ተራ ይደርሳል
31. እንኳን ተሳፋሪ ሙታንም ይሸጋሸጋል
32. ተሳፍሪ ጠጋጠጋ በሉ የአባይ አደራ አለብን
33. ባለጌ ሰው ዜብራ ላይ ወራጅ ይላል
34. ከጫት ሙቀት እንጂ አይገኝም እውቀት
35. ዜብራውን አንስተን አህያ እናስተኛልህ ወይ(ለሹፌሮች)
36. ለወሬኛ እና ለአምስት ሳንቲም መልስ የለንም
37. ፍቅር ፍቅር እያልሽ አትጨማለቂ ልቤ ዉስጥ ለመግባት
ጫማሽን አዉልቂ
38. አባይን ያላየ ሄዶ ማየት ይችላል
39. ሴት ልጅ ታርሳ የምትገኝ ቢሆን ኖሮ ወንድ ሁላ ገበሬ
ይሆን ነበር
40. ሰዉን አትናቁ ሰው እንዴት ይናቃል ቅማል እንኳን በአቅሙ
ሱሪ ያስወልቃል
41. እስቲ ይሁን ብለን የተከለዉ ቃጋ ጎበስ ጎበስ አለ እኛኑ
ሊወጋ
42. ባላገር ሲሰለጥን በዜና ይደንሳል
43. መሀይም ሀብታም ደሃን የፈጠረ ይመስለዋል
44. ምን ጊዜው ቢረዝምም ቋንጣ እና ባለ ስልጣን መውረዱ
አይቀርም
45. ዝናብ ጥሎ ጥሎ መሬቱ ጭቃ ሲሆን ያን እያነሱ
ግርግዳዉ ላይ ልጥፍ
46. በፍየል ዘመን በግ አትሁን
47. ሹፌሩን በፍቅር ማሣቅ እንጅ በነገር ማሣቀቅ ክልክል ነው
48. ትሞህርት በዱላ ቢሆን ኖሮ አህያ ፕሮፌሰር ትሆን ነበር
49. ሴት ልጅ ሒሣብ ሥትማር እንጂ ስትከፍል አይተን አናቅም
50. ደሀ ነዉ ችስታ ነዉ ብለሽ ትይኛለሽ ጭንና ዳሌ እንጂ
አንችስ ምን አለሽ

51. መልስ ለረሳ ማትሪክ ላይ እንመልሳለን
52. ሴትና ሎተሪ ለማይፈልጋቸዉ እንጂ ለሚፈልጋቸዉ
አይወጡም
53. ሹፌር ለጠበሰ ባለ 100ብር ረዳት ለጠበሰ ባለ 50
ብርካርድ እንሞላለን
54. የቅድብ ፀጉርና ምቀኛ አያድጉም
55. ንፁህ ህሊና ምቹ ትራስ ነዉ
56. ላታመልጪኝ አታሩጪኝ
57. ስራ ያጣ ተሳፋሪ ጋቢና ይቀመጣል
58. የማያልፍለት ደሃ ሀብታምን ይጋብዛል
59. በባጃጅ ስትጋዝ ንፋስ መታኝ አትበል ባጃጅ የመኪናዎች
የልጅ ልጅ ናትና
60. ደንበኛ ካልቀበጠ ንጉስ ነዉ
61. ጧት ስትሄድ በእንቅፋት የመታህ ድንጋይ ማታ ከደገመህ
ድንጋዩ አንተ እንጂ እሱ አይደለም
62. ጋይስ እንጀራ የለም እንጂ ወጥ ቢኖር ኖሮ በልታቹ ትሄዱ
ነበር
63. ድብርትንና ጥይትን ተኝቶ ማሳለፍ ነው
64. ጠጋ ጠጋ በሉ ሁሉም ቅርብ ወራጅ ነው ከፈጣሪ በቀር
65. ከድሃ ቤት ጥቅስ ከሀብታም ቤት ጥብስ አይጠፋም
66. የቤትክን አመል እዛው
67. በፍርፍር ያዘነ በጥብስ ይደሰታል በፍቅር ያዘነ.....?
68. የመኖር ወርቃማ ዘዴ መቻቻል ብቻ ነው
69. ሁለት ክንድ አንድ ሜትር ነው ከዛ ያሳለፈ ውሸታም ነው
70. የሰው ልጅ አረም የበዛበት የመከራ ተክል ነው
71. የሚፈልገውን ያላገኘ ልብ ዘውትረ መንገደኛ ነው
72. የአለም ሙቀት መጨመር መንስኤ ጭቅጭቅ ነው
73. ፈገግታዬ ብዙ ነው ልቤ ግን ለአንድ ሠው ነው
74. ባለጌና ዋንጫ ወደ አፉ ሰፊ ነው
75. መስታወት በቆጣሪ ቢሆን ኖሮ ሴቶች ምን ይዉጣቸዉ ነበር
76. ድሀ በህልሙ ቂቤ ባይጠጣ ኖሮ ምን ይዉጠዉ ነበር ?
77. ማንበብ ከቻልክበት ሁሉም ሰው መፅሀፍ ነው
78. ለሚያልፍ ቀን የማያልፍ ቃል አትናግር
79. ባጃጅን አወቅሽ አወቅሽ ሲሏት ታፔላ አወጡላት
80. ይሄ አናት ለቴስታ እንጂ ለትምህርት አይሆንም
81. ለኛ ከራሳችን የበለጠ የሚያስብልን የለም
82. ዝቅ ብለህ ስትሰራ ሁሉም ነገር ዝቅ ብሎ ይታይሃል
83. ማንም ሠው የጣለውን ሲያነሱበት አይወድም
84. ከሹፌሩ ጋር የምትጨቃጨቁ በኢቦላ እለቁ
85. ፍቅር ካለ ታክሲ ባሥ ይሆናል
86. የኪስ ሌቦች ቆዩ ሒሳቡን ሳንቀበል ስራ እንዳትጀምሩ
87. ሲጠሉህ ሳይሆን ሲወዱህም ለምን በል
88. ለሰዉ ሳይሆን ለራስህም ታመን
89. አለመዘጋጀት ለውድቀት መዘጋጀት ነው
90. ሂሳብ ሳይከፍሉ ሀሳብ አይጀምሩ
91. ሰርቶ የማይዝናና አህያ ብቻ ነዉ
92. ሹፌሩን በፍቅር እንጂ በነገር መጥበስ ክልክል ነው
93. እንደምን አደራቹ ውሸት መሮኛል ስራ ፈልጉልኝ
94. ኑሮና ታክሲ ካልታገሱት አይሞላም
95. እስክናውቅ እንጂ እስክናብድ አንማርም
96. የትም ፍጪው ምግቡን ብቻ ስጪኝ
97. አንድን ሳትይዝ ሁለትን አታገኝም
98. ያለዉን የሰጠ ባዶዉን ይቀራል
99. ሱሪህን ሳይሆን ራስህን ዝቅ አድርገህ ኑር
100. ህይወት በደረጃ ፈተና በኩረጃ

101. ለመኖር ብላ እንጂ ለመብላት አትኑር
102. ሾርባ ያቃጠለው በርጎ ይናደዳል
103. ያልተነገረ እንጂ ያልተባለ የለም
104. ሠርቶ የማይዝናና አህያ ብቻ ነዉ
105. የጊዜ ጀግና እንጂ የሰው ጀግና የለውም
106. ሰው እና ድፎ በትዛዝ እንደፋለን
107. እንደ ባሪያ ከሰራ እንደ ንጉስ ትኖራለህ
108. አንድ ጎል እና አንድ ሚስት አትመን
109. ወይ ጉድ ሀይሩፍ በዶልፊን ይስቃል አሉ
110. ሰዉን ማመን ቀብሮ ሳይሆን ቀብድ ተቀብሎ ነዉ
111. በፍቅር ለወደቀ የመሬት ስበት ተጠያቂ አይደለም
112. የማያልፍለት ደሀ ሀብታም ይጋብዛል
113. በሰዉ ላይ ከምትስቅ መጀመሪያ ራስህን እወቅ
114. አበሻ አንድ እግሩን ካልቆጹለት የሁለተኛው እግር ጥቅም
አይገባውም
115. ከምታማ ወንጌል ሰማ
116. ዝቅ ብሎ የሠራ ከፍ ብሎ ይኖራ
117. የሰነፍ አእምሮ የሰይጣን ቤተ_ሙከራ ነዉ
118. ለስራ ያልታደለ አእምሮ ለተንኮል ማንም አይወዳደረዉም
119. የሴት ልጅ ውበቷ ታማኝኀቷ
120. ከማይረባ ጉልበት ይሸለል ልብ አርጉልኝ ማለት
121. መኖር ደጉ ብር ባያስቆጥረን ቀን ያስቆጥረናል
122. የእናት ሞትና የድንጋይ መቀመጫ እያደር ይቆሮቁራል
123. "ቀስ ብሎ ማደግን ሳይሆን ቁሞመቅረትን ፍራ"አለች
ባጃጅ!!!
124. አራዳ እናቱን ሚረዳ
125. ሞላ የሰው ስም ነዉ ተጠጉ
126. አፍ ከመክፈት ሱቅ መክፈት
127. ውፍረትና ውሸት ለባለቤቱ አይታወቅም
128. ለላዳና ለካፌ ብዙብዙ ይከፍላሉ ምነው እኛጋ ሲመጡ
ለምን ይጨቃጨቃሉ
129. አንበሳ ሲያረጅ ቢሾፍቱ መጣ
130. ያለ ምክንያት መኖር ክልክል ነዉ
131. ታክሲና መግስተ ሰማያት ሞልቶ አያውቅም
132. ሲሰሩ አትስራና አዞሩብኝ በል ስትዞር ዋልና
133. በጎ አሳቢ ከስድብ ምክር ያወጣል
134. ዝምታዬ ካልገባችሁ ንግግሬ አይገባችሁም
135. ተጠጉ ሲባሉ ቦታ የለም አይበሉ፣ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ
ነዉ
136. ጥይትንና ድህነትን ተኝቶ ነዉ ማለፍ
137. ጠጋ ጠጋ በሉ የቻይና እዳ አለብን
138. መቆጨት የለብክ በማፍቀርክ ሳይሆን ማፍቀር ያለብክን
ሠው ባለማወቅክ ነው
139. ጠንካራ ሠው በጨለማ በስተጀርባ ብርሀን ይታየዋል
140. ሣያሥቡ መናገር ሣያልሙ መተኮስ ነው
141. ጓደኞችህ አካውንት ይከፍታሉአንተ አፍህን ትከፍት አለህ
142. ከምታማኝ ምከረኝ
143. በፍየል ዘመን በግ አትሁን
144. ድንች ቢውፍር ሹካ ያነሳዋል
145. ያሳደግናት ውርንጫ መልሳ በእርግጫ
146. አመል ከሌለሽ ወደ ባስሽ።
147. ወረድ ወረድ ይህ ታክሲ እንጂ ፌስቡክ አይደለም
148. እዉነት የሚያዳምጥ እዉነት ከሚናገር አይተናነስም
149. መማሩንስ ተምረሃል ማስተዋልን ዘንግተሃል
150. ያለፈለት ሀብታም ደሀን አይጋብዝም

151. ፍቅር ማለት የምትወዳትን ልጂ ደስታ ማገኘት ማለት ነዉ
152. መኖርህ ማንንም ካልጠቀመ መሞትህ ማንንም
አይጎዳም
153. ወረኛ ገንፎ አድሮም ላቃጥል ይላል
154. ማቀድ ካልቻክ ዉድቀትህን እያቀድክነዉ
155. ያህያ ውርንጫ ጠጉሮ ጉፍፍ ያለው
156. የምንወደውን ስንከተል የምወደንን እናጣለን
157. ማስቲካ የሚታደል መስሎቹ አፋቹን አትክፈቱ
158. ይህችም እንጀራ ሆና ምጥምጣ በዝብት
159. ትችትና ሻወር ከራስ ይጀምራል
160. አራዳ እና ጭስ መውጫ አያጣም
161. ፋራ ከሚስመኝ አራዳ ይንከሰኝ
162. የምግብ ቅመሙ ረሀብ ነዉ
163. ፍቅር ካለ ፍሪጅ ይሞቃል
164. ባጎረስኩ ተነከስኩ
165. ወሬ ዳቦ አይሆንም
166. ዘሎ የወረደ ዋጋው ይቀንሳል
167. ቆንጆ ቆንጆ ሴቶች አትግቡ ጋቢና ሹፈሩ ላደጋ
ይጋለጣልና
168. ብድር መጠየቅና እንግሊዝኛ መናገር ድፍረት ይጠይቃል
169. ለኔ ብላ ለኔ ብላ ትገዛለች ሊፋን መኪና
170. የምትወደዉን እስክትሰራ የምትሰራዉን ዉደደዉ
171. ፍቅር ካለ የቁንጫ ቆዳ ለሺ ሠው ይበቃል
172. በሬ ያረደና ቆንጆ ያገባ ብቻውን አይበላም
173. የዉሸት እየኖርን የእዉነት እንሞታለን
174. ከሰው ጋር ስትሆን አፍህን ብቻህን ስትሆን ራስህን
ጠብቅ
175.የማታፈቅርህን ማፋቀር ኤርፕርት ሄዶ በቡር መጠበቅ
ነዉ
176. መባልን ሳይሆን መሆንን ፍራ
177. የአራዳ ልጅ መልስ አይጠይቅም
178. ነጋልሽ ደግሞ ልትጠበሽኝ
179. ከባጃጅ ላይ ሳይከፍሉ መዉረድ ከህፃን ልጅ ላይ ዳቦ
እንደመንጠቅ ይቆጠራል
180. ገንዘብ ከድህነት እንጂ ከሞት አያስጥልም
181. እባክዎን በፀባይ ይዉረዱ እምቢ ካሉ እንደ ጋዳፊ
ይወርዳሉ
182. ሦስት ቀን ለመኖር አራት ቀን አትጨነቅ
183. እባክዎን መስኮት በመክፈት ለትራፊክ አያጋልጡን
184. ከሙስና የፀዳ የስራ ዘርፍ የታክሲ ሹፌር ብቻ ነዉ
185. ለሰዉ ቅን እንጂ ቅንቅን አትሁን
186. ከስልጣን እና ከጫት ላይ መነሳት ይከብዳል
187. ምንም ብታምሪ ከሚስትነት አታልፊም
188. ሐብታም ግጦ በጣለዉ አጥንት ደሀዉ ይሰቃያል
189. የእከክ መድሀኒት ጠንክሮ ማከክ ነዉ
190. ፊትሽ ላይ የሌለዉ የካዲስኮ ቀለም ብቻ ነዉ
191· የታክሲ ከሌለህ ወርደህ በባስ ሂድ
192· ፍቅር ካለ ባጃጅ ባስ ይሆናል
193· ሒሳብ ሳይከፍሉ ሀሳብ አይጀምሩ
194· ባለጌና ዋንጫ ከወደአፉ ይሠፋል
195· ኤች.አይ.ቪንና የጫማ ሽታን በጋራ እንከላከል
196· ማንችስተር ያሸንፋል አርሠናል ለዘለዓለም ይኑር
197· ሠው አካውንት ይከፍታል አንዳንዱ አፉን ይከፍታል
198· ሞባይል ለጣለ ሲም እንመልሳለን
199· ሹፌሩን መጥበስ ክልክል ነው በነገር
200· ሠው ብቻ ነው የምንጭነው በስህተት የገባ ይውረድ
201· ታክሲ ለሚጠቀሙ ብቻ
202· ክቡራን ተሳፋሪዎቻችን በአገልግሎት አሰጣጣችን
ላይአስተያየት፣ ቅሬታ፣ ትዝብት ወይም መሻሻል
አለበት የምትሉት ነገር ካለ
አንቀበልም!! መውረድ ይቻላል::
203. ለሠው ቅን ሁን እንጂ ቅንቅን አትሁን
204· ማስቲካ የሚታደል መስሎአችሁ አፋችሁን እንዳትከፍቱ
205· መስኮቱን በመክፈት ለትራፊክ ፖሊስ አያጋፍጡን!
206· ጥብቅ ማሳሰቢያ ለክቡራን ሌቦች ሒሳብ
ሰብስበን ሳንጨርስ ስራችሁን መጀመር አትችሉም!
የማይስማማ ሌባ ካለ መውረድ ይችላል፡፡
207· ታክሲና መንግስተ ሰማያት ሞልቶ አያውቅም።
የተደደጋገሙት ቁጥር ለማብዛት
ሳይሆን ከዚህም ከዚያም የተሰበሰበ ስለሆነ ነው።

ምርጥ መጣጥፎች
ሼርርርር

04/05/2020

ልጅዎ የአራት ወር እድሜ ሳለ የእድገት ሁኔታ ደረጃዎች
ከዚህ በፊት የህፃን ልጅዎን የአጨዋወት፣ አነጋገር/ ቋንቋ፣ እንዴት እንደሚማር እና እንቅስቃሴዎችን እንዴት እንደሚተገብር በመከታተል ስለልጅዎ የእድገት ሁኔታ ፍንጭ ማግኘት እንደሚቻልና የሁለት ወር ህፃን ሊያሳይ የሚችለዉን ነገሮች መነጋገራችን ይታወሳል፡፡ ዛሬ ደግሞ ከዘዚያ የቀጠለ የአራት ወር ልጅ የእድገት ክትትልን እናያለን፡፡
ሕፃናት በዚህ እድሜ ምን ነገሮችን ሊተገብሩ ይችላሉ?
ማህበራዊና ስሜታዊ ነገሮች / Social and Emotional
• ሰዎችን ሲያዩ ፈገግ ማለት
• ከሰዎች ጋር መጫወት መዉደድና ጨዋታዉ ሲቋረጥ ማልቀስ
• አንዳንድ እንቅስቃሴዎችን ከሰዎች መኮረጅ መቻል( መሳቅና የግንባር ቆዳን መሸብሸብ)
ቋንቋ/መግባባት (Language/Communication)
• በብል ማድረግ/ድምፅ ማዉጣት/
• ድምፅ እያወጡና የሚሰሙትን ድምጽ መኮረጅ
• በሚራቡበት፣ ህመም ሲሰማቸዉና ሲደክማቸዉ ለየት ያለ አለቃቀስ ማልቀስ
አዕምሮያዊ/ Cognitive (የመማር፣ የማሰብና ችግርን መፍታት መቻል)

• ሲያዝኑ ወይም ሲደሰቱ ማሳየት/ማሳወቅ መቻል
• ለፍቅር/መዉደድ ምላሽ መስጠት
• በአንድ እጃቸዉ መጫወቻ ለመያዝ መሞከር
• እጃቸዉንና አይናቸዉን በአንድነት መጠቀም መቻል ለምሳሌ መጫወቻ ማየትና ለመዉሰድ መጣር
• የሚንቀሳቀስ ነገርን በአይናቸዉ ከአንድ ጥግ እስከ ሌለኛዉ ጥግ ድራስ መከተል
• ፊትን አትኩሮ ማየት
• ከርቀት ቤተሰብንና የተለመዱ ነገሮችን/እቃዎችን መለየት መቻል
እንቅስቃሴ/ አካላዊ እድገት/ Movement/Physical Development
• እራስን ሳያስደግፉ ቀና ብሎ መቆየት መቻል
• ጠንከር ያለ ነገር ላይ እግራቸዉ ሲያርፍ ለመወጠር መሞከር
• እጅን ወደ አፋቸዉ ማምጣት መቻል
• በሆዳቸዉ ሲተኙ ወደ ጀርባቸዉ መገልበጥ መቻል
• በሆዳቸዉ ሲተኙ እጃቸዉን ተደግፈዉ ቀና ማለት መቻል
በዚህ እድሜ ልጅዎ የሚከተሉትን መተግበር ካልቻለ የህክምና ባለሙያዎን በወቅቱ ያማክሩ፡፡
• ነገሮች ሲንቀሳቀሱ የማይመለከት ከሆነ
• ሰዎችን ሲያይ ፈገግ የማይል ከሆነ
• እራሱን ችሎ የማይዝ ከሆነ
• ድምፅ የማያወጣ
• እቃን/ሌሎች ነገሮችን ወደ አፉ የማያመጣ ከሆነ
• እግሮቹ ጠንካራ ነገር ላይ ሲያርፍ ለመግፋት እግሩን የማይወጥር ከሆነ
• አንዱን ወይም ሁለቱን አይኖች ወደ ሁሉም አቅጣጫ በደንብ የማያንቀሳቅስ ከሆነ

#የእኛ #የዶክተር #ቤዛ (ጤና መረጃ #እንዲደርሶ #አሁኑኑ #ቤተሰብ #ይሁኑ!!!

#የዶክተር #ቤዛ #የቴሌግራም #ገፅ #ይቀላቀሉ
👉👉👉 https://t.me/Drbezaa

17/04/2020
20/09/2019

ቪፒኤን ለምን እንጠቀማለን? ጥቅሙስ ምንድን ነው?
ቪፒኤን (VPN) የኢንተርኔት ግንኙነታችንን ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን እና የምንለዋወጣቸዉ መረጃዎች ከመረጃ በርባሪዎች ጥቃት የተጠበቁ እንዲሆኑ የሚረዳ ሶፍትዌር ነው፡፡
ተጠቃሚዎች የቪፒኤን ግንኙነት ሲፈጥሩ ደህንነቱ የተረጋገጠ የመረጃ መተላለፊያ መንገድ ይፈጥራሉ፡፡
ቪፒኤን በተለየ ማስተላለፊያ መንገድ የሚተላለፉ ዳታዎችን ሚስጥራዊ የሚያደርግ በመሆኑ ማንኛዉም የመረጃ በርባሪ የመረጃዉን ይዘት ማዎቅ እንዳይችል ከማድረጉ ባሻገር የመረጃ ግንኙነቱ የሚሆነዉ በሁለቱ ባለመብት(ባለፍቃድ) አካላት ብቻ ነዉ፡፡
ሶፍትዌሩ የቀጥታ የበይነ-መረብ ግንኙነት 'የኦንላይን' እንቅስቃሴ በመደበቅ እንዲሁም እንዳይታይ በማድረግ(የትኛዉን ድረ-ገጽ እንደጎበኘን እና ምን አይነት ዳታዎችን እያስተላለፍን መሆኑን) ባለማሳዎቅ ያግዘናል፡፡
ይህን አገልግሎት በተገቢው መንገድ ማግኘት የምንችለው ደግሞ የቪፒኤን ሶፍትዌር ደንበኛ በመሆን አገልግሎቱን መጠቀም ስንጀምር ነዉ፡፡
ደንበኛ በመሆናችን የምናስተላልፋቸዉ ዳታዎች ከመዳረሻዉ ኔትወርክ ከመድረሳቸዉ በፊት ይመሰጠራሉ፡፡
ቪፒኤንን ለምን መጠቀም አስፈለገ?
• ማንኛዉንም የዌብ ተግባራት ኢንክሪፕትድ(የተመሰጠሩ) እንዲሆኑ ያደርጋል
• የቀጥታ የበይነመረብ ግንኙነት (online) ተግባራችንን በመደበቅ ከሚከታተሉን የመረጃ መንታፊዎች ያድነናል፡፡
• መዳረሻችንን በግልፅ እንዳይታይ እንዲሁም በቦታ የተገደቡ ዌቦችና ይዘቶችን አገልግሎት ማግኘት እንድንችል ይረዳናል
• በዌብ(በይነ-መረብ) ተግባር ላይ የማንነት መታዎቅ አጋጣሚን በእጅጉ ያጠባል
• የህዝብ ዋይፋይ ሆትስፖቶችን በምንጠቀምበት ጊዜ ግንኙነቱ ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን ያደርግልናል፡፡
በአጠቃላይ ደህንነቱ የተጠበቀ መረጃና የመረጃ ልዉዉጥ መንገድ ይፈጠርልናል ማለት ይቻላል፡፡

Address

Addis Ababa

Opening Hours

09:00 - 17:00

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when OCS ICT posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share