Grand Ethiopian Renaissance Dam

Grand Ethiopian Renaissance Dam የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት

ዜና ዕረፍት------------------------የውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር የማናጀመንት አባልና የክቡር ሚኒስቴር አማካሪ የነበሩት ወ/ሮ ገበያነሽ ነጋሽ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ ። ወ/ሮ ገበ...
14/04/2026

ዜና ዕረፍት
------------------------
የውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር የማናጀመንት አባልና የክቡር ሚኒስቴር አማካሪ የነበሩት ወ/ሮ ገበያነሽ ነጋሽ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ ።
ወ/ሮ ገበያነሽ ነጋሽ ከአባታቸው ከአቶ ነጋሽ በየነ እና ከእናታቸው ከወይዘሮ አለሚቱ ሞገስ ግንቦት 14፣ 1972 ዓ.ም. በጂማ ዞን በጌራ ወረዳ ተወለዱ። ዕድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስም የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በጌራ አንደኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ደግሞ በአጋሮ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተከታትለዋል። ወ/ሮ ገበያነሽ በመጋቢት ወር 2000 ዓ.ም፣ ከኦሮሚያ ፐብሊክ ሰርቪስ ኮሌጅ በግብርና ቢዝነስ ማኔጅምንት ዲፕሎማ፤ በሐምሌ 12 ቀን 2006 ዓ.ም፣ ከሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ በህዝብ ስራ አመራር የመጀመሪያ ድግሪ እና በነሐሴ 13 ቀን 2008 ዓ.ም፣ ከሪፍት ቫሊ ዩኒቨርስቲ በሶሾሎጂ ሁለተኛ ዲግሪያቸዉን አግኝተዋል፡፡
ከመስከረም 01 ቀን 1992 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መስከረም 28 ቀን 2003 ዓ.ም ድረስ በተለያዩ የባለሙያና የሃላፊነት የስራ መደቦች ላይ በኦሮምያ ክልላዊ መንግስት ጅማ ዞን ጌራ ወረዳ አስተዳደር ም/ቤት አገልግለዋል፡፡ ከጥቅምት 01 ቀን 2003 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መስከረም 21 ቀን 2014 ዓ.ም. ድረስ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል በመሆን ወረዳቸዉን በመወከል በተለያዩ የቋሚ ኮሚቴዎች አባልነት ሀገራቸዉንና ህዝባቸዉን ሲያገለግሉ የነበረ ሲሆን፣ በዉሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በአማካሪነት ከመስከረም 22 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ህይወታቸዉ እስካለፈበት ቀን ድረስ መ/ቤቱን በታማኝነትና በቅንነት ሲያገልግሉ ቆይተዋል፡፡ በስራ ዘመናቸውም ለተተኪ ባለሙያዎች አርአያ በመሆን እና ተቋማዊ ለውጥ በማምጣት ይታወቃሉ።
ወ/ሮ ገበያነሽ ነጋሽ ከባለቤታቸዉ ከዶ/ር ሀብቴ ጅፋር ጋር ትዳር መስርተው የአንድ ወንድና የአንድ ሴት ልጆች እናት ነበሩ። በነበራቸው ማህበራዊ ህይወትም በደግነታቸው፣ በታታሪነታቸውና ሰውን በመርዳት የሚታወቁ የአካባቢው እና የሀገር ባለውለታ ነበሩ።
ባጋጠማቸዉ ድንገተኛ ህመም ሚያዚያ 05 ቀን 2018 ዓ.ም በተወለዱ በ46 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ወ/ሮ ገበያነሽ ነጋሽ በነበራቸዉ የህይወት ታሪክ ዉስጥ ስራቸዉን አክባሪና ትጉህ፣ ታታሪ ፣ ቅን አገልጋይ ፣ ከስራ ባልደረቦቻቸዉ ጋር ተግባቢ፣ ሳቂታ ምንም አይነት መከፋት የማይታይባቸው ለሰዉ አዛኝና ሩህሩህ ነበሩ፡፡
የቀብር ስነ-ስርዓታቸዉ ሚያዚያ 6 ቀን 2018 ዓ.ም በትውልድ ቦታቸው በጅማ ዞን ጌራ ወረዳ ከቀኑ 8:00 ሰዓት የሚፈፀም ይሆናል።
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ጋር በቅርበት የሚሰራ ተቋም ነው፤ በዚሁ አጋጣሚ ሁሉ ባለው የሥራ ግንኙነት ወ/ሮ ገበያነሽ ነጋሽ ተባባሪ፣ ቅን፣ ታታሪ እና መልካም ተግባቦት የነበራቸው አመራር ነበሩ፡፡
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት አመራርና ሠራተኞች በወ/ሮ ገበያነሽ ነጋሽ ሞት የተሰማውን ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቻቸው እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን ይመኛል።

ምንጭ፡- (የውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር የፌስ ቡክ ገፅ)

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች  እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሠላም አደረሳችሁ። በዓሉ የሰላም፣ የጤና እና የመረዳዳት እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት...
13/04/2026

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሠላም አደረሳችሁ። በዓሉ የሰላም፣ የጤና እና የመረዳዳት እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት

የ9 ወራት ዕቅድ አፈፃጸም ሪፖርት እና የ15ኛ ዓመት በዓልን በማስመልከት ውይይት ተካሄደ። መጋቢት 24  ቀን 2018 ዓ.ም. የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት የ2018 በጀ...
03/04/2026

የ9 ወራት ዕቅድ አፈፃጸም ሪፖርት እና የ15ኛ ዓመት በዓልን በማስመልከት ውይይት ተካሄደ።
መጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የ9 ወራት የዕቅድ አፈፃጸም ሪፖርት እና የታላቁ ህዳሴ ግድብ የመሰረት ድንጋይ የተጣለበትን 15ኛ ዓመት በማስመልከት አመራሮችና ሰራተኞች ውይይት አደረጉ፡፡
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስፈፃሚ አረጋዊ በርሄ (ዶ/ር) በመድረኩ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር እንደገለጹት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ከተጠናቀቀ ማግስት የመሰረት ድንጋይ የተጣለበትን 15ኛ ዓመት ለመዘከር በመብቃታችን መላው የሀገራችን ህዝብ ደስታና ኩራት ይገባዋል ብለዋል፡፡ መላ ኢትዮጵያውያን በዓለም ምሳሌ የሚሆን ተግባር በዓባይ ግድብ ፈጽመናል፤ የታላቁ ህዳሴ ግድብን ዕውን ማድረጋችን አይችሉም፣ ክህሎት የላቸውም፣ የገንዘብና የአስተዳደር አቅም የላቸውም ያሉበትን ምላስ ወደ ኋላ እንዲመልሱ ያደረገ ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡
ዋና ሥ/አስፈፃሚው ላለፉት 15 ዓመታት በጽ/ቤቱ የተከናወኑ ተግባራት የሚያኮሩ መሆናቸውን ገልጸው በያዝነው የበጀት ዓመትም የተቋሙ ስራዎችን መገምገምና መወያየት ክፍተቶችን ለማረምና የነበሩ ጠንካራ ጎኖችን ማስቀጠል ያስችላል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
የፕሮጀክት ጽ/ቤቱ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ተካ በበጀት ዓመቱ ታቅደው የተከናወኑ ቁልፍ ጉዳዮችን፣ የነበሩ ችግሮችንና የተወሰዱ መፍትሄዎች እንዲሁም የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን የ9 ወር አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበዋል፡፡ የግድቡ መጠናቀቅን መነሻ በመድረግ በነበረው የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ በነበረው ዕቅድ መሰረት 600 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ እስከ መጋቢት ድረስ አንድ ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብ

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በሠላም አደረሳችሁ። በዓሉ የሰላም፣ የጤና እና የመረዳዳት እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።የታላቁ ህዳሴ ግድብ ...
19/03/2026

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በሠላም አደረሳችሁ። በዓሉ የሰላም፣ የጤና እና የመረዳዳት እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት

ለመላው ኢትዮጵያውያን በሙሉ!!የካቲት 23 ቀን 2018 ዓ.ም (የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት) “ከአኩሪ ታሪክ፣ ወደ ብሩህ ዓድማስ!” በሚል መሪ ሀሳብ ለሚከበረው ለ130...
02/03/2026

ለመላው ኢትዮጵያውያን በሙሉ!!
የካቲት 23 ቀን 2018 ዓ.ም (የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት)
“ከአኩሪ ታሪክ፣ ወደ ብሩህ ዓድማስ!” በሚል መሪ ሀሳብ ለሚከበረው ለ130ኛው የአድዋ ድል በዓል እንኳን አደረሰን፤ አደረሳችሁ!

ሁለተኛው የዘመናችን አድዋ የሆነው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት እና አድዋ የዚህ ትውልድ የአንድነት መገለጫና የኩራት ምንጮች ናቸው፡፡

ታላቁ የዓድዋ ድል በተለያዩ ቋንቋዎች፣ ሀይማኖቶች ነገር ግን በአንድ ልብ የተጻፈ ታሪክ ነው። ጀግኖች አያት ቅድመ አያቶቻችን ህይወታቸውን ገብረው ነፃነት እንዳቀዳጁንና ጀግንነት እንዳወረሱን ሁሉ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ለሀገራችን ሁለንተናዊ ልማት መሰረት የሚጥለውን በመንግስት ቁርጠኛ አመራርና በመላው ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እውን የሆነው የታላቁ ህዳሴ ግድብ የቅርብ ጊዜ የጋራ ታሪካችን ነው።

በህዳሴ ግድብ ላይ የተጀመረውን የድል አድራጊነት ስኬት በሌሎች ሀገራዊ ፕሮጀክቶቻችንም ላይ በመድገም የሀገራችንን ዕድገት ይቀጥላል።

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት የመላው ዓለም ጥቁር ህዝብ አንድነት እና ኩራት ለሆነው ለ130ኛው ዓመት የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል መልካም ምኞቱን ይገልፃል፡፡

“በህብረት ችለናል!”
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት

"ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አሁን ቤቶችንና ኢንዱስትሪዎችን በሃይል እያደመቀ ነው፤ ለጎረቤት ሀገራት የኤሌክትሪክ ኃይል ይልካል። ይህም የአፍሪካ ብልሃት እንዴት የጋራ ብልጽግናን እንደሚያ...
16/02/2026

"ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አሁን ቤቶችንና ኢንዱስትሪዎችን በሃይል እያደመቀ ነው፤ ለጎረቤት ሀገራት የኤሌክትሪክ ኃይል ይልካል። ይህም የአፍሪካ ብልሃት እንዴት የጋራ ብልጽግናን እንደሚያመጣ ያሳያል። "
የካቲት 9 ቀን 2018 ዓ.ም (የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ኅብረት 39ኛው የመሪዎች ጉባኤ ላይ ካስተላለፉት መልዕክት የተወሰደ። ( የፎቶ ምንጭ EBC እና ኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)

የሐዘን መግለጫየታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት አመራሮችና ሰራተኞች የኢ.ቢ. ኤስ (EBS) ቴሌቪዥን ዋና ስራ አስፈጻሚ እና መስራች በነበሩት አቶ አማን ፍስሃጽዮን ህልፈተ-...
11/02/2026

የሐዘን መግለጫ
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት አመራሮችና ሰራተኞች የኢ.ቢ. ኤስ (EBS) ቴሌቪዥን ዋና ስራ አስፈጻሚ እና መስራች በነበሩት አቶ አማን ፍስሃጽዮን ህልፈተ-ህይወት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጽን ለቤተሰቦቻቸው እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን እንመኛለን፡፡ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት

በተለያዩ አምዶች ተከፋፍሎ በተዘገጀው የውሃና ኢነርጂ ዘርፍ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎረም ስልጠና ተሰጠ።የካቲት 3 ቀን 2018 ዓ.ም (የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት...
11/02/2026

በተለያዩ አምዶች ተከፋፍሎ በተዘገጀው የውሃና ኢነርጂ ዘርፍ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎረም ስልጠና ተሰጠ።
የካቲት 3 ቀን 2018 ዓ.ም (የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና ለተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሰራተኞች በተለያዩ አምዶች ተከፋፍሎ በተዘገጀው የውሃና ኢነርጂ ዘርፍ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎረም ላይ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።
የዕለቱ ስልጠና የሚያተኩረው "የመንግስት ሰራተኞች የብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ስርዓት መገንባትና የማስፈፀም አቅም ማሳደግ"፣ "ፈጣንና ተደራሽ የመንግስት አገልግሎት ግንባታ" እና "የፕሮግራም በጀት አዘገጃጀት፣ አጠቃቀምና አፈፃፀም" በሚሉ አምዶች ነው።
የስልጠናውን መርሃ-ግብር የማስጀመሪያ ንግግር ያደረጉት የውሃና ኢነርጂ ዘርፍ አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም የአብይ ኮሚቴ ፀሐፊ አቶ ኦልቀባ ባሼ የሪፎርሙ ትልቁ አላማ ብቃትን ከሪፎረም ተግባራት ጋር በማገናኘት በተቋሙ የሚጠበቀውን ውጤት ለማምጣት ነው ብለዋል። አያይዘውም የሪፎርሙ ስራ በአግባቡ ተግባራዊ ሲሆን ብቃት በተግባር ይረጋገጣል፣ ተቋማት ትክክለኛውን ባለቤት ያገኛሉ፣ ለውጥን ከራሱ የሚጀምርና በተግባር የሚያሳይ ፈፃሚና አመራር ይፈጠራል ብለዋል። የሪፎርሙ ስራ ውጤታማ እንዲሆን የሚመደበውን በጀት በውጤት የሚያሳይ፣ ሙስናን እጅግ የሚፀየፍና የሚቃወም፣ ለሚፈጠሩ ችግሮች ተጠያቂና ሀላፊነት የሚወስድ አመራርና ፈፃሚ መፍጠር የግድ ይላልም ብለዋል። በተጨማሪም የሪፎርሙ ፍኖተ-ካርታ ሁሉንም አመራርና ፈፃሚ ባለቤትነት ስለሚጠይቅ ለውጡ የራሴ ነው በሚል ስሜት ሰልጣኞች ስልጠናውን ትኩረት ሰጥተው እንዲከታተሉ በቬርቿል ለሚከታተሉ ሰልጣኞችም ጭምር አሳስበዋል።
አቶ በላይነህ ይርዳው "የመንግስት ሰራተኞች የብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ስርዓት መገንባትና የማስፈፀም አቅም ማሳደግ" በሚለው አምድ ዝርዝር አፈፃፀሙን በሚገልፅ ሁኔታ የተዘጋጀን ሰነድ ለሰልጣኞች አቅርበዋል ሰፊ ማብራሪያም ሰጥተዋል።
አቶ መኮንን ዓለሙ "ፈጣንና ተደራሽ የመንግስት አገልግሎት ግንባታ" በሚለው አምድ ላይ ዝርዝር አፈፃፀምና ሰፊ ይዘት ያለውን ሰነድ ለሰልጠኞች ከማብራራያ ጋር አቅርበዋል።
አቶ ኑረዲን መሃመድ በተሰጣቸው ጊዜ "የፕሮግራም በጀት አዘገጃጀት፣ አጠቃቀምና አፈፃፀም" በሚል አምድ ስር የተዘጋጀን ሰነድ ስለበጀት ምንነት፣ አጠቃቀምና ውጤታማነት ምን ማለት እንደሆነ በስፋት በማብራራት አቅርበዋል።
ስልጠናውን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች፣ የቤዚን አስተዳደር ጽ/ቤት እና የቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊዎችና ሰራተኞች ፊት ለፊትና በቨርቿል ተሳትፈዋል። በቀረቡ ሰነዶችና በአጠቃላይ በሪፎርሙ አተገባበር ዙሪያ ሰልጣኞች በርካታ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን አንስተው ከመድረክ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል።

የነጻና ገለልተኛና የብዝሃነትና አካታችነት ሲቪል ሰርቪስ ግንባታ አምድ ላይ ስልጠና ተሰጠ።ጥር 29 ቀን 2018 ዓ.ም (የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት) የውሃና ኢነርጂ ዘ...
06/02/2026

የነጻና ገለልተኛና የብዝሃነትና አካታችነት ሲቪል ሰርቪስ ግንባታ አምድ ላይ ስልጠና ተሰጠ።

ጥር 29 ቀን 2018 ዓ.ም (የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት) የውሃና ኢነርጂ ዘርፍ አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም የነጻና ገለልተኛና የብዝሃነትና አካታችነት ሲቪል ሰርቪስ ግንባታ አምድ ላይ ለዘርፉ አመራሮችና ሰራተኞች ስልጠና ተሰጠ።

የስልጠና መድረኩ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የስራ አመራር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ኦልቀባ ባሼ በለፉት ስድስት ወራት የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርምን ውጤታማ ለማድረግ በርካታ የቅድመ ዝግጅት ሰራዎች መሠራታቸውን ገልጸው በሀገራችን የሲቪል ሰርቪስ ታሪክ ውስጥ አዲስ ምእራፍ ለመጀመር በታለመው መጠነ ሰፊ የሪፎርም ጉዞ ላይ በመወያየት ግንዛቤ ለመያዝ መድረኩ መዘጋጀቱን ገልጸዋል።

ሪፎርሙ የቆዩ አሰራሮችን ማሻሻል ብቻ ሳይሆን ተቋማዊ ሀይሎችና የአሰራር ስርዓቶች መሠረት ዳግም በጽኑ አለት ላይ የምንገነባበት ታሪካዊ ሂደት ነው ብለዋል።

የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ፍኖተ ካርታ በዘጠኝ ጽኑ አምዶች ላይ የተገነባ ነው ያሉት አቶ ኦልቀባ እነዚህ አምዶች የተቋማችን ህልውና የሚያረጋግጡ ምሰሶዎች በመሆናቸው ከአምዶቹም መካከል ቁልፍ በሆኑት በነጻና ገለልተኛና ብዝሃነትና አካታችነት ላይ ያተኮረ ስልጠና አዘጋጅተናል ብለዋል።

ነጻና ገለልተኛ አገልግሎት ተደራሽ ማድረግየህዝብን አመኔታ ከማረጋገጥ ባለፈ ተቋማት የሁሉም ዜጎች አስተማማኝ መጠለያ መሆናቸውን ለማረጋገጥም እንደሚያስችል ነው አቶ ኦልቀባ የገለጹት።

ብዝሃነትና አካታችነትን የተቋማችን ጥንካሬ ፣ የውበት ምንጭ እንዲሁም ጸጋና አቅም መሆኑን በመገንዘብ ስብጥሩን ይበልጥ ፍትሃዊና አካታች ለማድረግ በተለይም ሴቶችን ወደ አመራርነት ለማምጣት ብሎም የወጣቱን አቅም ከሙያ እና ተሞክሮ ጋር በማቀናጀት ተቋማችንን ውጤታማ ማድረግ ይጠበቅብናል ብለዋል።
ብዝሃነትን ያላከበረና አካታችነትን ያላረጋገጠ ተቋም ግማሽ አካሉ ሽባ እንደሆነ ሰው ነው ያሉት አቶ ኦልቀባ ሙሉ አቅማችንን ተጠቅመን አገራዊ ለውጡን ማፋጠን የውዴታ ግዴታችን ነው ብለዋል። ከዚሁ ጋር አያይዘው ስልጠናው ግንዛቤ ማስጨበጫ ብቻ ሳይሆን ለሙያችንና ለህሊናችን ታማኝ ልንሆን ፣ለሁሉም ዜጋ ያለአድሎና ገለልተኝነት አገልግሎት ልንሰጥ፣ ብዝሃነት ውስጥ ያለውን ውበትና ጥንካሬ አውጥተን ለተቋማችን እድገት ልንጠቀም ቃል የምንገባበት የቃል ኪዳን ማደሻና የለውጥ ሀይል መፍጠሪያች መሆኑን አሳስበዋል። ይህ ሪፎርም በሚገባ ተግባራዊ ሆኖ የዜጎችን ህይወት እንዲቀይር ሰራተኛውና አመራሩ ቀዳሚና ወሳኝ ሚና መጫዎት እንዳለበት አቶ ኦልቀባ አጽንኦት ሰጥተዋል።

የኛ ቁርጠኝነት የተቋማችን ብቻ ሳይሆን የሀገራችንን ነገ ይወስናል ያሉት አቶ ኦልቀባ ብዝሃነትንና አካታችነትን መሰረት ያደረጉ ስራዎችን ስንሰራ ተቋምን ከመቀየር አልፈን አገርን የሚቀይር ውጤት በተጨባጭ የምናመጣበትና እንደችግር ስናነሳቸው የነበሩ ጉዳዮችን ከመሠረቱ መፍታት የሚቻልበት እድል ይፈጥራል ብለዋል።

በስልጠናው ንቁ ተሳትፎ እና ሀሳብን በነጻነት የማንሸራሸር መብት የተጠበቀ መሆኑንና ከስልጠናው በኋላም የተሻለ አመለካከት፣ የላቀ ሙያዊ ስነምግባርና አዲስ የስራ ወኔ እና ተነሳሽነት እንደሚጨምር አቶ ኦልቀባ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

በስልጠናው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባባሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤትና የውሃና ኢነርጂ ዘርፍ አመራሮችና ሰራተኞች እየተሳተፉ ሲሆን የቤዚን አስተዳደር ጽ/ቤት እና የቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊዎችና አመራሮች በዙም ሚቲግ እየተሳተፉ ሲሆን በውይይቱ በርካታ ሀሳቦች ፣ ጥያቄዎችና አስተያየቶች እየተንጸባረቁ ነው።

“ታላቁን የህዳሴ ግድብ ያለ አንድ ብር እርዳታ ያሳካ መንግስት” አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2018 (የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባባሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት)ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ...
03/02/2026

“ታላቁን የህዳሴ ግድብ ያለ አንድ ብር እርዳታ ያሳካ መንግስት”
አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2018 (የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባባሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት)

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር) ለተከበረው ፓርላማ በሰጠት ማብራሪያ፣ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ያለ አንድ ሳንቲም የውጭ እርዳታ፣ በኢትዮጵያውያን ጥረትና መስዋዕትነት ብቻ እዚህ መድረሱ የሀገሪቱን ሉዓላዊነትና የኢኮኖሚ ጥንካሬ አዲስ ምዕራፍ መሆኑን አንስተዋል፡፡

“ከውጭ የተገኘ አንድም ብድር የለም!” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ግድቡ በሀገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በቆጠቡትና በለገሱት ገንዘብ እንዲሁም በመንግስት ቁርጠኛ አቋም ብቻ የተገነባ መሆኑን አረጋግጠዋል። ይህም ኢትዮጵያውያን “በህብረት ችለናል!” የሚለውን መርህ ለዓለም ያሳዬበት ትልቁ ምሳሌ ነው።

“ኢትዮጵያ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ላይ አንድ ብር እርዳታ፣ አንድም ብር ብድር አልወሰደችም!” አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2018 (የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባባሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት) በኢትዮጵያ...
03/02/2026

“ኢትዮጵያ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ላይ አንድ ብር እርዳታ፣ አንድም ብር ብድር አልወሰደችም!”

አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2018 (የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባባሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት) በኢትዮጵያዊያን ሃብት ብቻ የተገነባ ታላቅ ፕሮጀክት የህዳሴ ግድብን ያለ አንድ ብር እርዳታና ብድር ያሳካ መንግስት ፕሮጀክት አይሰራም ሊባል አይችልም፤ በጀግኖች ኢትዮጵያዊያን ቁርጠኛ አቋም ጨክነው በጋራ ቁመው ስለሰሩ የተከወነ የጋራ ፕሮጀክት ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በ6ኛው የኢ.ፌ.ድ.ሪ. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ለምክር ቤቱ አባላት ምላሽና ማብራሪያ ሲሰጡ ከተናገሩት…

Address

Yared Street
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 08:30 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30
Thursday 08:30 - 17:30
Friday 08:30 - 17:30

Telephone

+2515570588

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Grand Ethiopian Renaissance Dam posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Grand Ethiopian Renaissance Dam:

Share