Ethiopian National Theatre

Ethiopian National Theatre Information about Ethiopian National Theater

🎭 ለበዓል ልዩ ድግስ፡ «ዝክረ አዲስ ዓመት» በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር እና በኤን.ቢ.ሲ (NBC) ኢትዮጵያ! 🌟የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ከኤን.ቢ.ሲ (NBC) ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የሚ...
22/08/2026

🎭 ለበዓል ልዩ ድግስ፡ «ዝክረ አዲስ ዓመት» በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር እና በኤን.ቢ.ሲ (NBC) ኢትዮጵያ! 🌟

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ከኤን.ቢ.ሲ (NBC) ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የሚያዘጋጀው «ዝክረ አዲስ ዓመት» ልዩ የኪነ-ጥበብ ድግስ፣ የ2019 አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ለሕዝብ ዕይታ ለመብቃት በከፍተኛ ጥበባዊና ቴክኒካዊ ዝግጅት ላይ ይገኛል።

የዝግጅቱን የልምምድ ሂደት ነሐሴ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከኤን.ቢ.ሲ (NBC) ኢትዮጵያ በመጡ ከፍተኛ አመራሮችና የቴክኒክ ባለሙያዎች ተገመግሟል።

በግምገማው ወቅት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ዋና ዳይሬክተር አቶ ባረክ ታደሰ ዝግጅቱ የቴአትር ቤቱን ታሪካዊና ባህላዊ ግርማ ሞገስ በሚመጥን ደረጃ እንዲቀርብ አቅጣጫ ያስቀመጡ ሲሆን፣ በባህላዊ ዜማዎችና ውዝዋዜዎች ጥራት፣ በመድረክ ምጥጥን (Stage Balance) እና በብርሃን አደረጃጀት ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ ይገኛል።

በተጨማሪም ከኤን.ቢ.ሲ (NBC) ኢትዮጵያ የመጡ የቴክኒክ ባለሙያዎች የአዘጋጆቹን የፈጠራ ክህሎት በመደነቅ፣ የማህበራዊ ሚዲያ የቅጅ መብት (Copyright) ህግጋትን እና የመልቲሚዲያ ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን የተመለከቱ ጠቃሚ የሙያ አስተያየቶችን አቅርበዋል። በአሁኑ ወቅት ዝግጅቱ በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ ተጠናቆ ለበዓል እንዲበቃ የቀሩት የልምምድ ጊዜያት በከፍተኛ ትጋት እየተከናወኑ ይገኛሉ።

📌 የጥበብ አፍቃሪያን እንዳያመልጥዎ! ይህን አስደሳችና ብሩህ የአዲስ ዓመት ስጦታ የመጀመሪያ ተከታታይ ለመሆን አሁኑኑ፡

• 🔔 የፌስቡክ ገጻችንን ማሳወቂያዎች (Notifications) «ON» ያድርጉ!

• ልዩ ዝግጅቱ እንዳያመልጥዎ ገጻችንን Like እና Follow በማድረግ የቤተሰባችን አባል ይሁኑ!

ስለዝግጅቱ የሚወጡ ተጨማሪ መረጃዎችን፣ ከቴሌቪዥን መስኮትና ከማህበራዊ ሚዲያ የቀጥታ ስርጭቶች ጋር ቀድመው ይከታተሉ።

#ኢትዮጵያብሔራዊቴአትር #ዝክረአዲስዓመት #ኪነጥበብ #አዲስዓመት2019

🎭 ታላቁ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የአቅም ግንባታ ስልጠና በአዳማ ከተማ እየሰጠ ይገኛል! 🇪🇹አዳማ | ነሐሴ 15 ቀን 2018 ዓ.ምየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር በግዥና ፋይናንስ ዘርፍ ስራ አ...
21/08/2026

🎭 ታላቁ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የአቅም ግንባታ ስልጠና በአዳማ ከተማ እየሰጠ ይገኛል! 🇪🇹

አዳማ | ነሐሴ 15 ቀን 2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር በግዥና ፋይናንስ ዘርፍ ስራ አስፈፃሚ አዘጋጅነት በአዳማ ከተማ መልካ አዳማ ሆቴል ለዘርፉ ባለሙያዎችና ለተቋሙ የስራ መሪዎች የሚሰጠው አቅም መገንቢያ ስልጠና በዛሬው ዕለት ተጀምሯል።

ይህ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ያለው ስልጠና በዋናነት በሁለት አበይት ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው፦

• የኤሌክትሮኒክስ መንግስታዊ ግዥ (e-GP) አሰራር፦ አጠቃላይ የግዥ ሂደቱን ዘመናዊ፣ ግልጽና ፈጣን ለማድረግ የሚያስችል የቴክኖሎጂ ትግበራ፤

• የግዥ መሰረተ-ሀሳቦችና አሰራሮች፦ በዘርፉ የሚስተዋሉ አሰራር ነክ ክፍተቶችን ለመድፈንና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ የተዘጋጀ የተግባር ልምምድ።

•በስልጠናው ላይ የዘርፉ ባለሙያዎች እና ከተለያዩ የስራ ክፍሎች የተወጣጡ የስራ መሪዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ። ይህ ስልጠና ተቋሙ የፋይናንስና የግዥ ስርዓቱን ይበልጥ ቀልጣፋና ተጠያቂነት ያለው በማድረግ፣ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ጥራት በአዲስ መልክ ለማሳደግ ትልቅ ሚና ይጫወታል ተብሎ ይጠበቃል።

ጽሁፉ ለሌሎችም እንዲደርስ Like እና Share በማድረግ ይተባበሩ!

17/08/2026
የዱቴ ስቱዲዮ ልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የሥራ ጉብኝት አደረገ።ኢብቴ| ነሐሴ 07/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ​መቀመጫውን በዱባይ ያደረገው ታዋቂው የዱቴ ስቱዲዮ (DUTTE STU...
13/08/2026

የዱቴ ስቱዲዮ ልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የሥራ ጉብኝት አደረገ።

ኢብቴ| ነሐሴ 07/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ

​መቀመጫውን በዱባይ ያደረገው ታዋቂው የዱቴ ስቱዲዮ (DUTTE STUDIO) የልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ተገኝተው የሥራ ጉብኝት አካሂደዋል።

​በጉብኝቱ ወቅት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ዋና ዳይሬክተር አቶ ባረክ ታደስ ለልዑካን ቡድኑ አቀባበል በማድረግ ስለ ተቋሙ ታሪክና ወቅታዊ እንቅስቃሴዎች ገለጻ ያደረጉ ሲሆን፤ በቀጣይ የሁለትዮሽ የሥራ ግንኙነቶች ዙሪያም ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።

​በውይቱም የተነሱ ዋና ሀሳቦች በቴአትር ጥበብ እድገት እና ዘመናዊ አቀራረቦች፣በቴክኒክና ክህሎት ማሳደግ (Capacity Building)፣በቀጣይ የጋራ የሁለትዮሽ ትብብሮች ዙሪያ ያተኮረና ፍሬያማ እንደነበር ተገልጿል።

​የኢትዮጵያን የቴአትር ጥበብ ወደ ተሻለና ወደ ላቀ የዓለም አቀፍ ደረጃ ለማሸጋገር የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል! 🇪🇹✨🇦🇪

👉 ለበለጠ መረጃና ወቅታዊ ዜናዎች ገጻችንን Like እና Follow በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።

11/08/2026
የኢትዮጵያ  ብሔራዊ ቲያትር ቤት ከኢፌድሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ጋር የ2019 በጀት ዓመት የእቅድ ትስስር ስምምነት ተፈራረመየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ከኢፌዴሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ...
11/08/2026

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቲያትር ቤት ከኢፌድሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ጋር የ2019 በጀት ዓመት የእቅድ ትስስር ስምምነት ተፈራረመ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ከኢፌዴሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ጋር የ2019 በጀት ዓመት የእቅድ ትስስር ስምምነት ተፈራርሟል። የስምምነት ሰነዱን በክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ እና የቴአትር ቤቱን በመወከል የስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ አቶ በየነ ጎንፋ መካከል የተፈረመ ሲሆን፣ በቀጣዩ በጀት ዓመት በጋራ የሚከናወኑ ዋና ዋና የኪነ-ጥበብና የባህል ግቦችን ያካተተ ነው።
የስምምነቱ ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች፡

• የኪነ-ጥበብ ስራዎችን ጥራትና ብዛት ማሳደግ፡ የሀገሪቱን ባህላዊ፣ ማህበራዊና ታሪካዊ እሴቶች የሚያንጸባርቁ አዳዲስ የቴአትር፣ የሙዚቃና የባህላዊ ውዝዋዜ ስራዎችን ማቅረብ፤ እንዲሁም ዝግጅቶችን ከሀገሪቱ ዋና ከተማ ውጭ ወደተለያዩ ክልሎች በማድረስ የኪነጥበብ ስራዎችን ለሰፊው ህዝብ ተደራሽ ማድረግ።

• የባህል ዲፕሎማሲ እና ዓለም አቀፍ ትስስር፡ የኢትዮጵያን የባህልና የታሪክ ቅርስ በኪነ-ጥበብ አማካኝነት ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ በማስተዋወቅ አዎንታዊ የሀገር ገጽታን መገንባት።
የተቋማዊ አቅም ግንባታና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም፡ ለቴአትር ቤቱ ባለሙያዎች (ተዋንያን፣ ደራሲያን፣ አዘጋጆችና የቴክኒክ ባለሙያዎች) የአጭርና የረጅም ጊዜ ስልጠናዎችን በማመቻቸት የሰው ሀይል አቅምን ማሳደግ።

በስምምነቱ ወቅት የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ እንደገለጹት፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የሀገሪቱ የኪነ-ጥበብና የባህል ማዕከልነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስፈላጊውን ሁለገብ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልፀዋል፡፡
#የኢትዮጲያ ብሔራዊ ቴያትር ቤት

የምስጋና እና የእውቅና ፕሮግራምየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር በ2018 ዓ.ም የሥራ ዘመን ላስመዘገበው መልካም አፈፃፀም ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ የምስጋና ...
11/08/2026

የምስጋና እና የእውቅና ፕሮግራም

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር በ2018 ዓ.ም የሥራ ዘመን ላስመዘገበው መልካም አፈፃፀም ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ የምስጋና የምስክር ወረቀት ተበርክቶለታል።

በተጨማሪም በ6ኛው ዙር የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና፣ ማህበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባለፉት አምስት ዓመታት ከቴአትር ቤቱ ጋር ለነበረው ስኬታማ የጋራ ትብብርና መልካም ቆይታ ከቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ከተከበሩ ወ/ሮ ወርቀሰሙ ማሞ የእውቅና ስጦታ እና የቋሚ ኮሚቴው አባላት ሙሉ የፎቶ ስጦታ ተረክቧል።

ለተደረገው እውቅና እና ለአምስት ዓመታት አብረውን ለሰሩት የቋሚ ኮሚቴው አባላት በሙሉ ምስጋናችንን እናቀርባለን።

Address

Addis Ababa
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian National Theatre posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Ethiopian National Theatre:

Shortcuts

Share