FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት, Government Organization, General Mulugeta Buli Street, Addis Ababa.
(3)

Seeing a modern defense force that is absolutely faithful to the constitution, government and people of our nation, center of excellence and love who can put an end to war, and who can safely and effectively succeed at the national and international duty

ዜና መከላከያ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ጳጉሜ 01 ቀን 2018 ዓ.ም
06/09/2026

ዜና መከላከያ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ጳጉሜ 01 ቀን 2018 ዓ.ም

Enjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት መግለጫ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጷጉሜን 01 ቀን 2018 ዓ.ምእመርታ ለዘላቂ ከፍታ!እንኳን ለእመርታ ቀን አደረሳችሁ! እመርታ ከአሉበት የከፍታ ደረጃ ወደ...
06/09/2026

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት መግለጫ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጷጉሜን 01 ቀን 2018 ዓ.ም

እመርታ ለዘላቂ ከፍታ!
እንኳን ለእመርታ ቀን አደረሳችሁ! እመርታ ከአሉበት የከፍታ ደረጃ ወደ ላይኛዉ መስፈንጠር ነው፡፡ ከፍታን በአዝጋሚ ሂደትም ዘመናትን ወስዶ ማሻሻል ይቻላል፤ በዚያ አግባብ የሚመጣ መሻሻል ከታለመዉ ግብ ለመድረስ የትውልዶችን ጥረት የሚጠይቅ ነው፡፡

ኢትዮጵያውያን ግን በቁጭት ለዘመናት ከቆየንበት ኋላ ቀርነት እና ድህነት በአዝጋሚ ጉዞ ለመላቀቅ ስለማይቻል እመርታዊ ለውጥ ማምጣትን ግብ አድርገን ሠርተን ስኬቶችን እያስመዘገብን ነው፡፡ ያለፉት ጥቂት ዓመታት ጥረቶቻችን ውጤቶች የሚያሳዩትም ይህንኑ ነው፡፡

የኢትዮጵያን ጀርባ ያጎበጡ የውጭ ዕዳዎችን ጫና በመቀነስ፣ ገቢ የመሰብሰብ ዐቅምን በማሳደግ፣ የኢንዱስትሪዎችን የማምረት ዐቅም በማሻሻል፣ የማዕድን ሀብቶች አጠቃቀምን በማላቅ እመርታዊ ለውጦች ተመዝግበዋል፡፡ የመንግሥት አጠቃላይ የማድረግ ዐቅም በእጅጉ ተለውጧል፡፡

ይህንን እመርታዊ ስኬት ማስመዝገብ የተቻለው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን በማድረግ፤ የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል፤ የዜጎችን ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት በማሳደግ፤ የቢዝነስ ሥርዐቱን ቀልጣፋና ግልጽ በማድረግ፤ የኢትዮጵያን የዲፕሎማሲ ዐቅም ከዜጋ ተኮር እና ብሔራዊ ጥቅም አንጻር በመግራት የመደመር መንግሥት ባደረገዉ ሰፊ ጥረት ነው፡፡

ኢትዮጵያ የማዕድን ሀብቶቿን በላቀ የኃላፊነት ስሜት በሕጋዊ አግባብ መጠቀም ጀምራለች፤ ታዳሽ ኃይልን በማምረት ከራስ አልፎ ለቀጠናዉ የኃይል ምንጭ ኾናለች፤ ብዝኃ ዘርፍ ኢኮኖሚን በመተግበር ኹለንተናዊ ዕድገቶችን እያስመዘገበች መጥታለች፤ የኢንዱስትሪ ምርቶችን በዓለም ገበያ ተወዳድራ የመሸጥ ዐቅም ፈጥራለች፡፡

የመንግሥት የልማት ዕቅድ ከቁጥ ቁጥ ወጥቶ ትውልድን ታሳቢ ያደረገ ግብ አስቀምጦ እየተተገበረ ነው፡፡ በ2018 ዓ/ም በሁሉም መስክ ከተስፋ ብርሃን ወደሚጨበጥ ለውጥ የመሸጋገር ሀገራዊ ራዕይን ማሳካት ተችሏል፡፡ ኢትዮጵያን በ2023 ዓ.ም አፍሪካዊት የብለጽግና ተምሳሌት የማድረግ ግብ ተቀምጦ ርብርብ እየተደረገ የስኬቱ ዋዜማ እየተቃረበ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በመደመር መንግሥት በተነደፉ የፖሊሲ ሐሳቦች ኹለንተናዊ ሉዓላዊነትን የማረጋገጥ ጉዞን ጀምራለች፡፡ በገቢ አሰባሰብ ላይ የታየዉ እመርታ አንዱ አብነት ነው፡፡ የግብር እና ታክስ መሠረትን በማስፋት፣ ገቢ የመሰብሰብ ዐቅምን በማሳደግ፤ የግብር ከፋዩን የመንግሥት አገልግሎት እርካታ በመሶብ አንድ ማእከል እና በዲጂታል አገልግሎቶች ከፍ በማድረግ የላቀ አፈጻጸም ማሳየት ተችሏል፡፡ በዚህም የበጀት ጉድለትን በእጅጉ ማጥበብ ተችሏል፡፡

ባለፉት ጥቂት ዓመታት የመንግሥት ፕሮጀክቶችን የመፈጸም ዐቅም በእጅጉ አድጓል፡፡ ፕሮጀክቶች መቼ እንደሚጀመሩ እና በምን ያህል በጀት እንደሚፈጸሙ ብቻ ሳይኾን መቼ ተጠናቅቀው በትክክል አገልግሎት እንደሚሰጡ ጭምር በከፍተኛ የራስ መተማመን የመሠረት ድንጋይ ሲቀመጥ መናገር የሚቻልበት ቁመና ላይ ተደርሷል፡፡

እመርታዊ ስኬቶችን ዕውቅና ለመስጠት፣ በቀጣዮቹም ዓመታት የበለጠ እመርታዊ ስኬቶችን ለማስመዝገብ መዘጋጀት አስፈላጊ በመኾኑ ዛሬ ጳጒሜን 01 ቀንን “የኢትዮጵያ ማንሰራራት!” በሚል መሪ መልእክት እያከበርን ነው፡፡

እንኳን ለእመርታ ቀን አደረሳችሁ፣ አደረሰን!
ጳጒሜን 01 ቀን 2018 ዓ.ም
የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/

https://youtube.com/-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

https://www.facebook.com/fdredefense.official

ጤና ይስጥልን ጥቂት ሥለጤናዎ፦ የስኳር በሽታ ዓይነቶች ምንድን ናቸው ? የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጷጉሜ 01 ቀን 2018 ዓ.ም • ዓይነት 1 የስኳር በሽታ (አጠቃላይ የኢንሱሊን እጥረት) ...
06/09/2026

ጤና ይስጥልን ጥቂት ሥለጤናዎ፦ የስኳር በሽታ ዓይነቶች ምንድን ናቸው ?

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጷጉሜ 01 ቀን 2018 ዓ.ም

• ዓይነት 1 የስኳር በሽታ (አጠቃላይ የኢንሱሊን እጥረት) ዓይነት 1 የስኳር በሽታ፣ የወጣቶች የስኳር በሽታ ወይም የኢንሱሊን ጥገኛ የስኳር በሽታ በመባልም የሚታወቀው፣ ቆሽት ኢንሱሊን የሚያመነጨው ትንሽ ወይም ምንም ዓይነት ሥር የሰደደ በሽታ ነው።

• ዓይነት 2 የስኳር በሽታ (በቂ ያልሆነ የኢንሱሊን እና የኢንሱሊን መቋቋም) በ 2 ዓይነት የስኳር በሽታ ሰውነት ኢንሱሊንን በአግባቡ አይጠቀምም ይህም የኢንሱሊን መቋቋም ይባላል. መጀመሪያ ላይ፣ ቆሽት እሱን ለማካካስ ተጨማሪ ኢንሱሊን ይሠራል፣ ነገር ግን በጊዜ ሂደት መቆጠብ አልቻለም እና መደበኛውን የደም ግሉኮስ ለመጠበቅ በቂ ኢንሱሊን መፍጠር አይችልም።

• የእርግዝና የስኳር በሽታ (በእርግዝና ወቅት የሚከሰት የስኳር በሽታ) የእርግዝና የስኳር በሽታ የስኳር በሽታ ያለባት ሴት በእርግዝና ወቅት በደም ውስጥ ያለው የስኳር መጠን የሚጨምርበት እና አብዛኛውን ጊዜ ከወለደች በኋላ የሚቀለበስ በሽታ ነው። በማንኛውም የእርግዝና ደረጃ ላይ ሊከሰት ይችላል ነገር ግን በእርግዝና ሁለተኛ አጋማሽ ላይ በጣም የተለመደ ነው.

ለስኳር በሽታ የሚያጋልጡ ምክንያቶች ምንድን ናቸው?
• የስኳር በሽታ የቤተሰብ ታሪክ አለው (በተለይ ወላጆች)
• ከመጠን በላይ መወፈር / ከመጠን በላይ መወፈር
• ዕድሜው 45 ዓመት ነው
• ዘና ያለ የአኗኗር ዘይቤ አለው።
• እንደ የፓንጀሮ በሽታዎች, ፖሊሲስቲክ ኦቫሪ ሲንድረም የመሳሰሉ ሌሎች በሽታዎች አሉት
• የእርግዝና የስኳር በሽታ የቀድሞ ወይም የቤተሰብ ታሪክ አለው

የስኳር በሽታ ምልክቶች ምንድን ናቸው?
አንዳንድ ጊዜ የስኳር በሽታ ምንም ምልክቶች አይታይም እና ለረጅም ጊዜ ሳይታወቅ ይቆያል. ለወንዶች እና ለሴቶች በጣም የተለመዱት የስኳር በሽታ ምልክቶች የሚከተሉት ናቸው ።

በወንዶች እና በሴቶች ላይ የተለመዱ የስኳር በሽታ ምልክቶች
• ያልታሰበ ክብደት መቀነስ።
• የማይጠፋ ድካም
• የደበዘዘ የዓይን እይታ
• ከመጠን በላይ የመጠማት ስሜት

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ዙሪያ ወረዳ የፅንፈኛው ታጣቂዎች እጅ እየሠጡ ነው። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ምበሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ዙሪያ ወረዳ በሰራና መረባ...
05/09/2026

በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ዙሪያ ወረዳ የፅንፈኛው ታጣቂዎች እጅ እየሠጡ ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም

በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ዙሪያ ወረዳ በሰራና መረባ አካባቢዎች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የፅንፈኛው ቡድን ታጣቂዎች ለሠራዊታችን እጅ መስጠታቸውን ቀጥለዋል።

በ10ኛ ዕዝ መረጃ ፣በሀገር ሽማግሌዎች እና በወረዳው "ፀጥታ ለሰላም በሰላም" በሚል ሃሳብ በአካባቢው ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የፅንፈኛው ቡድን ታጣቂዎች በሰላማዊ መንገድ እጅ እንዲሰጡ በተደረገው ጥረት 46 ታጣቂዎች ለሰራዊታችን እጃቸው ሰጥተዋል።

በዛሬው እለት እጃቸው የሰጡ ታጣቂዎች ብሬን፣ ስናይፐር፣ ክላሽ እና ኋላ ቀር መሳሪያ ይዘው መግባታቸውን የዕዙ መረጃ ክፍል አስታውቋል።

ታጣቂዎቹ የአካባቢውን ሰላም በማወክ የተሳሳተ ተግባር ላይ እንደነበሩ እና ይህም ለራሳቸው፣ ለቤተሰቦቻቸውና ለአካባቢው እንቅፋት ሆኖው መቆየታቸው አውስተው አሁን ግን ወቅቱን የሚጠብቀው ህዝብን እና መንግስትን በሚጠቅም ስራ በመሰማራት የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡ ገልፀዋል። ዘገባው የዕዙ የሠራዊት ሥነ ልቦና ግንባታ ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/

https://youtube.com/-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

https://www.facebook.com/fdredefense.official

ለኩሩ ህዝብ፤ ጀግና ሠራዊት  የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም  ህዝብ የሀገር መሠረት ነው፤ ሠራዊት ደግሞ የዚያን ሀገር ሰላም፣ ሉዓላዊነትና ደህንነት የሚጠብቅ ጋሻ ...
05/09/2026

ለኩሩ ህዝብ፤ ጀግና ሠራዊት

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም

ህዝብ የሀገር መሠረት ነው፤ ሠራዊት ደግሞ የዚያን ሀገር ሰላም፣ ሉዓላዊነትና ደህንነት የሚጠብቅ ጋሻ ነው። ሁለቱ በእምነትና በመተማመን ሲተሳሰሩ የሚፈጠረው ኃይል የሀገርን ጽናት ያጠናክራል። ህዝቡ የጦር ልጆቹን እንደ የራሱ አካል ሲቆጥር፣ ወታደሩም የሚጠብቀው የራሱን ቤትና ህዝብ መሆኑን ሲያምን ትስስሩ የበለጠ ይጠናከራል።

ጀግንነት የሚለካው በውጊያ ጊዜ ብቻ አይደለም። የተሰጠንን ቃል መጠበቅ፣ አደራን በታማኝነት መወጣት፣ ችግር ሲመጣ ኃላፊነትን ሳንሸሽ መቀበል የጀግንነት መገለጫዎች ናቸው። ወታደር የሚለየውም በዚህ አደራ ነው፤ ራሱን ከሀገር ጥቅም በታች አስቀምጦ ለሌሎች ሰላም የሚቆምበት መንፈስ ነው።

የኢትዮጵያ ህዝብ በተለያዩ ዘመናት በፈተና ውስጥ ያሳለፈው ጉዞ የጽናትና የመስዋዕትነት ትምህርት ትቶ አልፏል። የሀገር ክብር ሲፈተን ህዝብና ወታደር በአንድ ልብ መቆም መቻላቸው በታሪክ የተመሰከረለት ነው። የዚህ ትስስር ዋጋ የሚታየው በአስቸጋሪ ወቅት ነው፤ ያኔ የተከማቸ እምነት ወደ ተግባራዊ ኃይል ይቀየራል።

የዘመናዊ ሠራዊት ብቃት በመሣሪያ ብዛት ብቻ አይወሰንም። የሙያ ብቃት፣ ዲሲፕሊን፣ ዕውቀት፣ ፈጣን ውሳኔና ተጠያቂነት የጦር ኃይልን የሚያጠናክሩ መሠረታዊ እሴቶች ናቸው። ከዚህ በላይ ግን የሠራዊት ጥንካሬ ከሚጠብቀው ህዝብ ጋር ባለው መተማመን ይጠናከራል።

ይህ እምነት በቃል ብቻ የሚገነባ አይደለም። ወታደሩ በተሰማራበት ቦታ ሕግንና ሥርዓትን ሲያከብር፣ ህዝቡን በክብር ሲያገለግል፣ የሰው ልጅ ክብርን ሲጠብቅ እምነቱን በተግባር ያረጋግጣል። ህዝቡም ለሀገር ጉዳይ በኃላፊነት ሲሳተፍና ለሠራዊቱ የሚገባውን ድጋፍ ሲያደርግ ይህንኑ እምነት ይመልሳል።

ዛሬ የሚጠበቀው ከትውልድ የተላለፈውን አደራ በአዲስ ብቃት ማስቀጠል ነው። ሠራዊቱ በሙያዊ ዝግጁነትና በሥነ-ምግባር እየጠነከረ ሲሄድ፣ ህዝቡም ለሀገር ጉዳይ ያለውን ተሳትፎ ማጠናከር ይገባዋል። የጋራ ጥቅም ከግል ፍላጎት በላይ ሲቀመጥ የሀገር አቅም ይሰፋል።

ለኩሩ ህዝብ ጀግና ሠራዊት ያስፈልገዋል፤ ጀግና ሠራዊትም ከህዝቡ እምነት ይጠነክራል። ይህ የጋራ መተማመን ሲጸና የሀገር ጋሻ ይበረታል፤ የትውልድ ተስፋም ይለመልማል።

የዛሬ ትውልድ የተረከበውን ታሪክ በትጋት ማስቀጠል፣ የተሰጠውን አደራ በታማኝነት መወጣትና ለሚቀጥለው ትውልድ የተሻለች ሀገር ማስረከብ አለበት። ምክንያቱም የሀገር ጽናት የሚገነባው በአንድ ተቋም ብቻ ሳይሆን፣ በህዝብና በሠራዊት የጋራ አደራ ነው።

ለኩሩ ህዝብ፤ ጀግና ሠራዊት።ለጀግና ሠራዊት፤ የማይሰበር እምነት። ለጋራ አደራ፤ የጸናች ሀገር።

በፍፁም ከተማ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/

https://youtube.com/-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

https://www.facebook.com/fdredefense.official

11ኛ ዕዝ ለኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር  ትምህርት መምሪያ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 30 ቀን 2019 ዓ.ምየ11ኛ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ በኮምቦልቻ ከ...
05/09/2026

11ኛ ዕዝ ለኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 30 ቀን 2019 ዓ.ም

የ11ኛ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ በኮምቦልቻ ከተማ ለሚገኙ 336 ተማሪዎች 224 ደርዘን ደብተርና እስክርቢቶ ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፉ ተማሪዎች ትምህርታቸውን በተሻለ ሁኔታ እንዲከታተሉ ከማገዝ ባሻገር በእውቀት የበለጸገና ለሀገር ግንባታ የሚያበረክት ትውልድ ለመገንባት የሚደረገው አስተዋፅኦ አካል መሆኑ ተገልጿል።

በዝግጅቱ ላይ የ11ኛ ዕዝ ሎጅስቲክስ ኃላፊ ኮሎኔል እሸቱ ከበደ እንደገለጹት፣ ሠራዊቱ የሀገርን ሉዓላዊነት ከማስጠበቅ ባሻገር ከህዝቡ ጎን በመቆም በትምህርትና በልማት ዘርፎች የበኩሉን አስተዋፅኦ እያደረገ ይገኛል።

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ሰዒድ ዓሊ በበኩላቸው፣ ሠራዊቱ በልማትና በበጎ ፈቃድ ተግባራት የሚያደርገው ተሳትፎ ህዝባዊነቱንና ወገንተኝነቱን ከማሳየት ባሻገር በሠራዊቱና በህዝቡ መካከል ያለውን ፍቅርና አጋርነት የሚያጠናክር መሆኑን ተናግረዋል።

የኮምቦልቻ ከተማ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ ኢብራሂም አብዱ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበው፣ ድጋፉ ተማሪዎች በእውቀት እንዲበለጽጉና የነገ ሀገር ተረካቢዎች በትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያግዝ ተግባር ነው ብለዋል።

በመጨረሻም ሠራዊቱ የሀገርን ሉዓላዊነት ከማስጠበቅ ጎን ለጎን በትምህርትና በልማት ዘርፎች የሚያደርገውን ህዝባዊ ተሳትፎ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል። ዘገባው የ11ኛ ዕዝ የሠራዊት ስነ-ልቦና ግንባታ ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/

https://youtube.com/-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

https://www.facebook.com/fdredefense.official

የዕዙ ሜንተናንስ ክፍል ውጤታማ ስራዎች ማከናወኑ ተገለፀ።የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ምበ10ኛ ዕዝ ሜንተናንስ ክፍል በዓመቱ ተጠጋኝ ንብረቶችን በኢንስፔክሽን በማረጋ...
05/09/2026

የዕዙ ሜንተናንስ ክፍል ውጤታማ ስራዎች ማከናወኑ ተገለፀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም

በ10ኛ ዕዝ ሜንተናንስ ክፍል በዓመቱ ተጠጋኝ ንብረቶችን በኢንስፔክሽን በማረጋገጥ ብልሽት የገጠማቸውን ተሽከርካሪና የጦር መሳሪያዎችን በመጠገን ለግዳጅ የማዘጋጀት ስራዎች ተሰርቷል ሲሉ የዕዙ ሜንተናንስ ሃላፊ ኮሎኔል ፍቃዱ ጌታሁን ተናግረዋል።

የመሳሪያ ጫኝ፣ የውሃ ቦቴዎች እና ፈጣን ተሽከርካሪዎች ለግዳጅ ዝግጁ በማድረግ ውጤታማ ስራዎች መሰራቱን ጠቅሰው መለዋወጫ እቃ ያልተገኘላቸውን ሞደፊክ በመስራት ወደስራ በመመለስ የተቋሙን ወጪ መቆጠብ እንደተቻለም አብራርተዋል።

የደረጃ 4 ሜንተናንስ ሃላፊ የሆኑት ሌተናል ኮሎኔል ወንደሰን እጅጉ በበኩላቸው በግዳጅ የተሰማራው ሰራዊት በተጠጋኝ ንብረቶች ችግር ምክንያት ስራው እንዳይተጓጎል እና ከግዳጅ እንዳይዘገይ ሌት ተቀን በመስራት ግዳጅን የሚያሳልጥ አገልግሎት በመስጠት አመርቂ ስራ መሰራቱን ገልፀዋል።

የዕዙ ሜንተናንስ ሲነር የብየዳ ሙያተኛ አሥር አለቃ በሃይሉ ወንድሜነህ በክፍሉ ውስጥ ከተሰሩ ስራዎች በግጭት ምክንያት የሚያጋጥሙ የመኪና ቦዲ፣ የበር፣ የኦክስጅን ብየዳና የስታንዳርድ ጊር ቦክስ የብየዳ ስራዎችን በመስራት ማቴሪያሎች ለግዳጅ የማዘጋጀት ስራ መሠራቱን ገልፀዋል። ዘገባው የዕዙ የሠራዊት ሥነ ልቦና ግንባታ ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/

https://youtube.com/-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

https://www.facebook.com/fdredefense.official

በአንጎላ ለሚካሄደው ውድድር የመቻል እጅ ኳስ ቡድን እየተዘጋጀ ነው።የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ምበአንጎላ ሉዋንዳ ለሚካሄደው 47ኛ የአፍሪካ እጅ ኳስ ሻምፒዮና ተሳ...
05/09/2026

በአንጎላ ለሚካሄደው ውድድር የመቻል እጅ ኳስ ቡድን እየተዘጋጀ ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም

በአንጎላ ሉዋንዳ ለሚካሄደው 47ኛ የአፍሪካ እጅ ኳስ ሻምፒዮና ተሳታፊ የሚሆነው የመቻል እጅ ኳስ ቡድን ዝግጅቱን አጠናክሮ ቀጥሏል።

ከመስከረም 28 እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም በአንጎላ ሉዋንዳ በሚካሄደው 47ኛው የአፍሪካ እጅ ኳስ ሻምፒዮና ውድድር ላይ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ከአሰልጣኝ ቀጠራ ጀምሮ አዳዲስ እና ልምድ ያላቸውን ተጫዋቾች ወደ ቡድኑ በማካተት የተሻለ ዝግጅት እያደረገ ነው።

የመከላከያ መቻል ስፖርት እጅ ኳስ ቡድን ባሳለፍነው 2018 የውድድር አመት አስከመጨረሻው ድረስ የዋንጫ ተፎካካሪ በመሆን ሁለተኛ ደረጃ በመያዝ ውድድሩን ያጠናቀቀ ሲሆን ሁለተኛ ደረጃ ይዞ በማጠናቀቁ ሀገራችንን ወክሎ በ47ኛው የአፍሪካ እጅ ኳስ ሻምፒዮና ውድድር ላይ ተሳታፊ ይሆናሉ።

በ47ኛው የአፍሪካ እጅ ኳስ ሻምፒዮና ውድድር ላይ መቀሌ 70 እንደርታ ሌላኛው ተሳታፊ የሚሆን ቡድን ነው።

ዘጋቢ ገረመው ጨሬ
ፎቶግራፍ ሌሊሴ ዮሃንስ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/

https://youtube.com/-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

https://www.facebook.com/fdredefense.official

የሀገር ኩራት የህዝብ መከታ የሆነ ሠራዊት የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ኢትዮጵያ ለወታደር ከምንምና ከማንም በፊት ፣ የትምና መቼም ፣ ከድሮ እስከ ዘንድሮ ፣ ከት...
05/09/2026

የሀገር ኩራት የህዝብ መከታ የሆነ ሠራዊት

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም

ኢትዮጵያ ለወታደር ከምንምና ከማንም በፊት ፣ የትምና መቼም ፣ ከድሮ እስከ ዘንድሮ ፣ ከትላንት እስከ ዛሬ ፣ ነገም ከነገ ወዲያ እስከ እድሜው ፍፃሜ ድረስ አቻ የማይገኝላት ተቀዳሚ ጉዳዩ ናት።

እንኳንስ ከሌላው ከራሱ ጋር አወዳድሮ የሚያስበልጠው እሷን ነው። እድሜ ዘመኑን በጀግንነት አገልግሏት ፣ አጥፊዋን ለማጥፋት ህይወትና አካሉን ገብሮላት ፣ እኔ ለሃገሬ ምን ሰራሁ እንጅ ሃገሬ ለኔ ምን ሰራችልኝ የማይላት እውነተኛ ወዳጇ ነው።

ከአንደበቱ የማይነጥላት የዘወትር መዝሙሩ ፣ ከራሱ በላይ የሚያልቃት የዜግነት ክብሩ ፣የዘላለም ፍቅሩ ፣ ደሙን አፍስሶ የሚታደጋት፣ ህይወቱን ከፍሎ የሚያስቀጥላት ፣ ኢትዮጵያ ማለት ለወታደር ሁለንተናው ናት።

ታዲያ ይህን ጥልቅ የሃገር ፍቅር ስሜቱን በውል የተረዱ ፣ ለቆመለት አላማ ያለውን ፅናት ጠንቅቀው የሚያውቁ ፣ ለሰላም ሲል የሚከፍለውን የማይተመን ዋጋ በሚገባ ያስተዋሉ ፣ ሃገር የሚያገለግልበትን አስተሳሰብ በአግባቡ የተገነዘቡና ከህዝብ አብራክ ወጥቶ ለህዝብ የመቆመ ሃይል መሆኑ የገባቸው ዜጎች ወታደርን የሚጠሩት የኔ ብለው ነው።

ከዚህም የተነሳ ወታደሩ የሃገርን ሰላም ለማረጋግጥ የሚደክመውን ያህል ዜጎች ለሰራዊቱ ደህንነት ይጨነቃሉ። ምንጊዜም ግዳጅ ወስዶ ሲሰማራ ሃገር ወዳዶች በሃሳብ አብረውት ይዘምታሉ።

ባላንጣዎቹን ፊት ለፊት ተጋፍጦ ሁኔታን በብቃት ለመሻገር ሲፋለም ፤ የእናቶች ፀሎት ፣ የአባቶች ምርቃት ፣ የወጣቶች እገዛ ተለይቶት አያውቅም። እሱም አንዱ የድል አድራጊነቱ ሚስጥር ይህ እንደሆነ ያምናል!

የኢትዮጵያ ወታደር ህዝብና ሃገሩን ከራሱ አስቀድሞ በመመልከት ፣ ጠላቱን አምርሮ የጠላበትን ፣ ትውልዱን አብዝቶ የወደደበትን ፣ ነፍሱን እስከ መስጠት የታመነበትን፣ የአላማ ፅናት ጠንቅቆ ያወቀ ማህበረሰብ ሁሌም የሚመለከተው በእኔነት ስሜት ነው።

የኢትዮጵያ ወታደር ዳር ድንበሩን በአጥንቱ ፍላፃ የማገረ ፣ የሃገሩን ሉአላዊ ክብር በጀግንነት ያፀና ፣ አስተማማኝ መሰረት ሆኖ ኢትዮጵያን ያቆመ የማዕዘን መሠረት ነው። ይህን እውነት ለመረዳት ደግሞም ትውልድን ጠብቆ ያስቀጠለ የታሪክ ባለ አደራ ፣ የአርበኞችን ፈለግ ተከትሎ የጀገነ የቁርጥ ቀን ደራሽ ፣ ጠላቶቿን አምርሮ የጠላ የሃገር ባለውለታ ፣ አይበገሬነቱን በዘመናት ተጋድሎ በተግባር ያረጋገጠ የወንዶች ቁና ፣ አያሌ ጊዜ ተፈትኖ ሁኔታን በድል የቋጨ የአሸናፊነት ናሙና ነው። የኢትዮጵያ ወታደር ።

ፈተናውን ከፊት ሆኖ የሚጋፈጥ የህዝብ አልኝታና መከታ ፣ ፀረ-ሰልሞችን ታግሎ በማንበርከክ ለተጨቆኑት ነፃነትን የሚያውጅ የምስኪኖች ዋስትና ፣ በአለም ዙሪያ ሁሉ ለሰው ዘር በሙሉ ሰላም ይሁን በሚል ሃገራዊ ጥንተ ዜማ የተቀኘ የሰላም አምባሳደር ፣ ሊሰራ ሲነሳ አድማስ የማይጋርደው ወሰን አልባ የሰው ልጆች ብሩህ ተስፋ ነው።

በኤፍሬም አድማሱ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/

https://youtube.com/-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

https://www.facebook.com/fdredefense.official

በአርባያ በለሳ ታጥቀው ሲዘርፉ በነበሩ ፅንፈኞች ላይ እርምጃ ተወሰደ።የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ምበማዕከላዊ ጎንደር ዞን አርባያ በለሳ አብዬ ሚካኤል ተብሎ በሚጠራ...
05/09/2026

በአርባያ በለሳ ታጥቀው ሲዘርፉ በነበሩ ፅንፈኞች ላይ እርምጃ ተወሰደ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን አርባያ በለሳ አብዬ ሚካኤል ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ታጥቀው ሲዘርፉና ህብረተሰቡን ሲያሰቃዩ የነበሩ የፅንፈኛ ቡድኖች ላይ እርምጃ መውሰዱን የ10ኛ ዕዝ ክፍለ ጦር አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል አሰጋ አከለ ተናግረዋል።

እንደ ክፍለ ጦር አዛዡ ንግግር በቀጠናው እየተሽሎከሎኩ በነዋሪው ላይ እንግልት በማድረስ ሰላም ይነሱ የነበሩ የፅንኛው ቡድን አባላትን ለማጥፋት ድንገተኝነትን በመጠቀም መምታት መቻሉን ገልፀዋል።

የሀገር አፍራሹ ፅንፈኛ ቡድን የግል ጥቅማቸውን ለማስከበር በዘረፋና በእገታ ተግባር ተሰማርተው ሰዎችን ሲያሳድዱ በመቆየታቸው የክፍለጦሩ ሠራዊት በተጠና መልኩ በመሰማራት ብሬን፣ክላሽ፣ ኋላ ቀር መሳሪያ፣ በርካታ ቁጥር ያለው ቦምብና የክላሽ መጋዘን እንዲሁም ሎጀስቲካዊ ቁሳቁስ ማመረካቸውን አብራርተዋል። ዘጋቢ ብርሃኑ አባተ ነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/

https://youtube.com/-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

https://www.facebook.com/fdredefense.official

Address

General Mulugeta Buli Street
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት:

Shortcuts

Share