Ethiopian Health professionals

Ethiopian Health professionals page to voice for Ethiopian health professionals burning issues and general public health concerns

10/06/2026

የጤና ባለሙያ ስቃይ መንግስት እስከ መቼ ነው ዝም ብሎ የሚያየው ???

ጤና ባለሙያ ራሱን አጠፋ ነፍስ ይማር 😭😭😭 እስከ መቼ ነው የጤና ባለሙያ ሞት ዝም የሚባለው ???በትውልድ አከባቢው ምሳሌ የነበረው ሃኪም ራሱን አጠፋ በሲዳማ ክልል ከኩታዮ ቀበሌ ፈልቆ፣ በ...
10/06/2026

ጤና ባለሙያ ራሱን አጠፋ
ነፍስ ይማር 😭😭😭
እስከ መቼ ነው የጤና ባለሙያ ሞት ዝም የሚባለው ???

በትውልድ አከባቢው ምሳሌ የነበረው ሃኪም ራሱን አጠፋ

በሲዳማ ክልል ከኩታዮ ቀበሌ ፈልቆ፣ በኦሳ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ብርሃኑን ማብራት የጀመረው ድንቅ ኮከብ፤ የማትሪክ ውጤቱን ሰቅሎ ለአካባቢው አይንና ኩራት የሆነው ወጣት ምሳሌ ቡዙነህ በድንገት ተለየን።

በአርሲ ዩኒቨርስቲ የሕክምና ትምህርት ክፍልን በመቀላቀል በማዕረግ (With Distinction) የተመረቀ የነገ ትልቅ ተስፋ የነበረው ባለሙያ ነበር።

ለቤተሰቦቹ ብቸኛ ወንድ ልጅ በመሆኑ ከምንም በላይ የሚሳሱለት፣ በአካባቢው ታላላቅ ልጆች ዘንድ "ተከታያችን" ተብሎ ትልቅ ተስፋ የተጣለበት፣ ታናናሾቹም እንደ ስሙ 'ምሳሌ' አድርገው የሚያዩት እጅግ ትሁት እና ከተባለው በላይ Excellent ልጅ ነበረ።

በቅርቡ በሞጆ አካባቢ በሚገኝ የሕክምና ተቋም ውስጥ በሙያው ማኅበረሰቡን ማገልገል ጀምሮ እንደነበር ሰምተን ሳይጠገብ፣ ትናንትና አመሻሽ ግን ሕይወት አዳኝ በነበሩት በእነዚያ ጎበዝ እጆቹ በራሱ ላይ ጨክኖ ሕይወቱን ማጥፋቱን ስንሰማ ልባችን በሐዘን ተሰበረ። ኦሳ መብራቷን አጥታለች፤ ሎካም የነገ ተስፋዋን ተነጥቃለች።

የውድ ልጃችን ሃኪም ምሳሌ ቡዙነህ የቀብር ሥነ-ሥርዓት በነገው ዕለት በተወለደበት በኩታዮ ቀበሌ ልዩ ስሙ 'ባዲቻ' በሚባለው ቦታ ከቀኑ 6:00 ሰዓት ጀምሮ ይፈጸማል።

ለተከበሩ ቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ እና ለጠቅላላው የኦሳ፣ የኩታዮ እና የሎካ ማኅበረሰብ ጥልቅ መጽናናትን እንመኛለን።

ነፍስህን በአጸደ ገነት ያኑራት ምሳሌ! 🕊️🕯️

Via: ምሳሌ ፈንታ

ሰው ለካ እየኖረ ነው ባለ 4.1 ሚሊዮን  የእጅ ስዓት አጃእቢ ነው 🤔🤔Rolex GMT-Master II "Root Beer22,000-26,000usd
10/06/2026

ሰው ለካ እየኖረ ነው
ባለ 4.1 ሚሊዮን የእጅ ስዓት
አጃእቢ ነው 🤔🤔

Rolex GMT-Master II "Root Beer
22,000-26,000usd

09/06/2026

2,339,268,126,738(2.3trillion) annual budget of Ethiopia
,from this 1/2goes to corruption network

  የሙያ ፈቃድ (License) የብቃት ማረጋገጫ እንጂ የገቢ ምንጭ አይደለም!የሙያ ፈቃድ ማለት አንድ የጤና ባለሙያ የብቃት መመዘኛዎችን Exit Exam እና COCአልፎ፣ ህዝብና ሀገሩን በታ...
09/06/2026



የሙያ ፈቃድ (License) የብቃት ማረጋገጫ እንጂ የገቢ ምንጭ አይደለም!

የሙያ ፈቃድ ማለት አንድ የጤና ባለሙያ የብቃት መመዘኛዎችን Exit Exam እና COCአልፎ፣ ህዝብና ሀገሩን በታማኝነት እያገለገለ መሆኑን የሚያሳይ የክብር ምስክር ወረቀት ነው። የዚህ የላብና የደምና ውጤት ማረጋገጫ የሆነው "የሙያ ፈቃድ" ባለሙያውን ማበረታቻ መሆን ሲገባው፣ አላግባብ ገንዘብ መበዝበዣ መንገድ እየሆነ ይገኛል።
​የጤና ባለሙያው ለከፈለው መስዋዕትነት ክብር ይሰጠው! ከሙያ ፈቃድ ጀርባ ያለውን የዕውቀትና የክህሎት ዋጋ እናክብር።

​📢 ያለአግባብ ከጤና ባለሙያዎች ላይ ገንዘብ የመሰብሰብ ስራ በአስቸኳይ ይቁም!

​🛑 ከጤና ባለሙያዎች ላይ የሚደረግ አላግባብ የገንዘብ ብዝበዛ በአስቸኳይ ይቁም!

CC
Ministry of Health,Ethiopia
Office of the Prime Minister-Ethiopia

08/06/2026

1990ዓ.ም የወጣውን ጤና ባለሙያዎች የጥቅማ ጥቅም መመሪያ ለማሻሻል ጊዜ የሌለው መንግስት ለራሱ ገቢ ሲል በፍጥነት የሙያ ፊቃድ እድሳት ክፍያ ከ100ብር ወደ 700ብር -1000ብር ማሳደጉ ምን ይባላል ????

Ethiopian Health professionals

08/06/2026

ጤና ባለሙያ ህዝብ ይዳኘኝ ብሎ መንግሰት ጤና ተቋም ባዶ ህንፃ ነው ግብዓት የለም ፤ጤና ባለሙያ ራበኝ ስል ግድ አይሰጠኝ ብለ ግል ተቋም ሄደ ተወደደብኝ ለምን ልብስህ አውልቀው አይወስዱም አይመለከተንም

ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የሙያ ፊቃድ መዝገባና እድሳት ከ 100ብር ወደ 700ብር ያሳደገበት ጤና ባለሙያዎች መብት ጥያቄ ስጠይቁ ነገሮች እንድታስተካክሉ እንጅ ከድጡ ወደ ማጡ እንድሄድ...
08/06/2026

ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የሙያ ፊቃድ መዝገባና እድሳት ከ 100ብር ወደ 700ብር ያሳደገበት ጤና ባለሙያዎች መብት ጥያቄ ስጠይቁ ነገሮች እንድታስተካክሉ እንጅ ከድጡ ወደ ማጡ እንድሄድ ነውን ???
አስተያየት ስጡበት
NB:-የቀን ምድር ዝርፊያ ነው የሚመለከተው አካል ቶሎ የማስተካከያ እርምጃ እንድወስድ እናሳስባለን

የአማራ ሕክምና ማኅበር ይፋዊ የአቋም መግለጫቀን፦ ሰኔ 1 ቀን 2018 ዓ.ም (የሰኔ 7/2026 እ.ኤ.አ)©©©«የጤና ባለሙያው መብትና ክብር ይጠበቅ፤ የደከመበት የዱቲ (ተረኝነት) ክፍያ በ...
08/06/2026

የአማራ ሕክምና ማኅበር ይፋዊ የአቋም መግለጫ
ቀን፦ ሰኔ 1 ቀን 2018 ዓ.ም (የሰኔ 7/2026 እ.ኤ.አ)
©©©
«የጤና ባለሙያው መብትና ክብር ይጠበቅ፤ የደከመበት የዱቲ (ተረኝነት) ክፍያ በአስቸኳይ ይፈጸም!»
የአማራ ሕክምና ማኅበር (አሕማ) በክልላችን የሚገኙ የሕክምናና የጤና ባለሙያዎች ያሉባቸውን ዘርፈ-ብዙ መዋቅራዊና ወቅታዊ ችግሮች ለመፍታት፣ እንዲሁም ሙያዊ መብቶቻቸው እንዲከበሩ ከተለያዩ የመንግሥትና አጋር አካላት ጋር በቅርበት ሲወያይና ሲሠራ መቆየቱ ይታወቃል።
ሆኖም ግን፣ በአሁኑ ወቅት በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ የጤና ተቋማት ውስጥ ሌት ከቀን ሕዝባቸውን እያገለገሉ ያሉ የህክምና ባለሙያዎች ላለፉት 5 (አምስት) ወራትና ከዚያ በላይ የሠሩበት የዱቲ (የተረኝነት ሰዓት) ክፍያ እንዳልተፈጸመላቸው ማኅበራችን በምሬትና በትዕግሥት ሲከታተለው የቆየው መራራ እውነታ ነው። ማኅበራችን ይህንን ሕጋዊና ፍጹም ሙያዊ የሆነ የክፍያ ጥያቄ ከክልል ጀምሮ እስከ ፈደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ድረስ በተደጋጋሚ በደብዳቤና በአካል በማቅረብ መፍትሔ እንዲሰጠው ቢወተውትም፣ እስካሁን ድረስ ኃላፊነት ወስዶ ክፍያውን የሚፈጽም አካል አልተገኘም።
ከዚህም በላይ፣ ባለሙያዎች መብታቸውንና የደከሙበትን ጥሪት በሕጋዊ መንገድ በጠየቁበት ወቅት ከተለያዩ የመንግሥትና የጤና ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች ዛቻ፣ ማስፈራሪያና አስተዳደራዊ ጫናዎች እየደረሰባቸው መሆኑን የሚያሳዩ ተጨባጭ መረጃዎች ለማኅበራችን ደርሰውታል። ይህ ድርጊት ሙያዊ ስነ-ምግባርን የሚጻረር፣ የባለሙያውን ሞራል የሚሰብርና ሕገ-ወጥ አሠራር በመሆኑ ማኅበራችን አጥብቆ ያወግዘዋል።
ስለሆነም የአማራ ሕክምና ማኅበር የሁኔታውን አሳሳቢነትና የዘመኑን የኑሮ ውድነት ከግምት ውስጥ በማስገባት የሚከተሉትን የአቋም መግለጫ ነጥቦች በጽኑ ያሳስባል፦
1. ያለምንም ቅድመ-ሁኔታ የዱቲ ክፍያ በአስቸኳይ ይፈጸም
የበጀት ዓመቱ ከመዘጋቱና ሂሳብ ከመታሸጉ በፊት፣ የሚመለከታቸው አሰሪ ተቋማት፣ የዞንና የከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያዎች እንዲሁም የክልሉ ጤና ቢሮ የጤና ባለሙያዎች ባለፉት አምስት ወራትና ከዚያ በላይ የሠሩበትን የዱቲ ክፍያ ያለምንም ቅድመ-ሁኔታና ያለምንም መስተጓጎል በአስቸኳይ እንዲከፍሉ እናሳስባለን። የሰው ልጅ በላቡና በደሙ የሠራበትን ክፍያ መከልከል ሰብአዊም ሆነ ሕጋዊ መሠረት የለውም።
2. ሕጋዊና ሰላማዊ የጥያቄ ማቅረቢያ መንገዶች ይጠቀሙ
የሕክምና ባለሙያዎች መብታችሁን ለማስከበር የምታደርጉትን ጥረት ማኅበራችን ሙሉ በሙሉ ይደግፋል። ሆኖም ግን፣ የሚነሱ ጥያቄዎችና አቤቱታዎች ሁሉ ሕጋዊና ሰላማዊ በሆነ መንገድ ብቻ ለሚመለከታቸው የሕግ አካላት (ለፍትሕ አካላት፣ ለሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ እንዲሁም ለሰብአዊ መብት ተሟጋቾች) በጽሑፍና በማስረጃ በማቅረብ ህጋዊ መብታቹህን መጠየቅ ይገባቹሃል።
3. በባለሙያዎች ላይ የሚደርሰው ዛቻና ማስፈራሪያ በአስቸኳይ ይቁም!
መብትን መጠየቅ ወንጀል አይደለም። በቅንነትና በታማኝነት ሕዝብን እያገለገለ ያለን ባለሙያ ማስፈራራትና ማሸበር የጤና ሥርዓቱን ማፍረስ ማለት ነው። በመሆኑም በየደረጃው ያሉ የተቋም መሪዎች በባለሙያው ላይ የሚያደርሱትን ማንኛውንም ዓይነት ተጽዕኖና ዛቻ በአስቸኳይ እንዲያቆሙ እንጠይቃለን። ማኅበራችን በማስፈራሪያ ድርጊት ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚሳተፉ አካላትን በሕግ የመጠየቅ መብቱ የተጠበቀ ነው።
4. የጤና ሥርዓቱ እንዳይጎዳ ቅድሚያ ለጤና ትኩረት እንስጥ
አሁን ባለው አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የጤና ባለሙያው ተስፋ ከቆረጠና መሠረታዊ ጥቅማ ጥቅሞቹ ከተነፈጉ፣ በክልሉ የጤና መዋቅር ላይ ከባድ ጠባሳ እንደሚጠል ግልፅ የሆነ ጉዳይ ነው።ስለዚህ የክልሉ መንግሥትና የፌደራል ጤና ሚኒስቴር የጉዳዩን አሳሳቢነት በግልፅ በመረዳት ፣ የፋይናንስና የበጀት ማነቆዎችን ፈትተው ለአገልግሎት ሰጪው ባለሙያ ዋስትና እንዲሰጡ በጥብቅ እንጠይቃለን።
«የጤና ባለሙያዎችን መብት ማክበር፤ የሕዝብን ጤናና ደኅንነት የመጠበቅ የመጀመሪያው እርምጃ ነው!»
©©©
ቅድሚያ ለጤና
የአማራ ሕክምና ማኅበር /AMA/
ባህርዳር ኢትዮጵያ

07/06/2026

የጤና ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ውድቀት 4ቱ ወሳኝ ምክንያቶች
💔💔💔💔💔💔💔
1ኛ. 12ቱ መሰረታዊ የባለሙያ ጥያቄዎች በመንግስት ችላ መባል
2ኛ. የጤናው ሴክተር አመራር አካላት ተቋማቱን ከመቦጥቦጥ ባሻገር የአገልግሎት ጥራትና ተደረሻነት ግድ የማይሰጣቸው መሆን
3ኛ. በአመራሩ ዙሪያ የተኮለኮሉ Double standard ጡረተኞች
ሀ) ስራቸውን በአግባቡ አይሰሩም
ለ) የተቋሙ ልዩ ተጠቃሚ መሆናቸው
4ኛ. ከላይ በተዘረዘሩ ምክንያቶች በተለይም በ3ኛው ምክንያት የቆዘሙ ምን አገባኝ በሚል የስንፍናንና የራስ ወዳድነትን ካባን የደረቡ ከህሊናቸው የተፋቱ ባለሙያዎች መበራከት ናቸው።

Dr. Mebratu M.

Address

New Deldhi
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Health professionals posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share