Arada communcation/አራዳ ኮሙኒኬሽን

Arada communcation/አራዳ ኮሙኒኬሽን Arada sub city communcation office
ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃን ለህብረተሰባችን ተደራሽ ማድረግ ቀዳሚ ተግባራችን ነው።
(3)

በአርቲስት እና የነፃነት ተጋይ እልፍነሽ ቀኖ ህልፈት ህይወት የሰማሁት በጥልቅ ሀዘን ዉስጥ ነው ።አርቲስት እልፍነሽ ድምፃዊት ብቻ ሳትሆን የሰባዊመብትና እኩልነት ታጋይ ነበረች።ለቤተሰቦቿ ፣...
06/09/2026

በአርቲስት እና የነፃነት ተጋይ እልፍነሽ ቀኖ ህልፈት ህይወት የሰማሁት በጥልቅ ሀዘን ዉስጥ ነው ።

አርቲስት እልፍነሽ ድምፃዊት ብቻ ሳትሆን የሰባዊመብትና እኩልነት ታጋይ ነበረች።
ለቤተሰቦቿ ፣ለወዳጅ ዘመዶቿና ለአድናቂዎቿ መጽናናትን እመኛለሁ።
ፈጣሪ ነብሷን በአፀደ ገነት ያኑር

Lubbuun darbuu Artistii fi Qabsooftuu Bilisummaa Ilfinash Qannoo kanan dhagahe gadda guddaa keessatti.

Artist Ilfinash weellistuu qofa osoo hin taane qabsooftuu mirga namummaa fi wal-qixummaa turte.
Maatii ishee, firoottan ishee fi dinqisiifattoota isheef jajjabinan hawwa.
Waaqni Lubbuu ishee Jeennata haa jiraachisu

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ኢትዮጵያ የራሷን የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሥነ ምሕዳር እያነፅች እንደሆነ ያውቁ ኖሯል?ለበለጠ መረጃ:➜ መላ ኤአይ: mela.aii.et➜ ፋይዳ: id.gov.et➜ መሶብ: https://mesob...
06/09/2026

ኢትዮጵያ የራሷን የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሥነ ምሕዳር እያነፅች እንደሆነ ያውቁ ኖሯል?

ለበለጠ መረጃ:

➜ መላ ኤአይ: mela.aii.et

➜ ፋይዳ: id.gov.et

➜ መሶብ: https://mesobcenter.et/

➜ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት: aii.et

06/09/2026

ጷጉሜ 1
የእመርታ ቀን
የፎቶግራፍ አውደርዕይ ቅኝት

በአራዳ ክፍለ ከተማ “እኛ ከነሱ ጋር፤ እነሱ ከኛ ጋር ናቸው” በሚል መሪ ቃል ለአረጋውያን የተቀናጀ የድጋፍ እና የበጎ አድራጎት መርሃ ግብር ተካሄደ።ጷጉሜ 1/2018 ዓ.ም ‎‎የአዲስ አበባ...
06/09/2026

በአራዳ ክፍለ ከተማ “እኛ ከነሱ ጋር፤ እነሱ ከኛ ጋር ናቸው” በሚል መሪ ቃል ለአረጋውያን የተቀናጀ የድጋፍ እና የበጎ አድራጎት መርሃ ግብር ተካሄደ።

ጷጉሜ 1/2018 ዓ.ም

‎የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር የአራዳ ክፍለ ከተማ ቅርንጫፍ ከራስ ደስታ ዳምጠው ሆስፒታል ጋር በመተባበር ለአረጋውያን እና በጎዳና ላይ ለሚገኙ ወገኖች የመልካምነት እና የአጋርነት እጃቸውን ዘርግተዋል።

‎የክረምት በጎ ፈቃድ መርሃ ግብር አካል የሆነው ይህ “በጎነት በሆስፒታል” ሰብአዊ መርሃ ግብር በራስ ደስታ ዳምጠው ሆስፒታል ግቢ ውስጥ የተካሄደ ሲሆን በርካታ ወገኖችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል።

‎በመርሃ ግብሩ ‎የነፃ ህክምና እና የጤና ምርመራ አገልግሎት፣ የአልባሳት እና የቁሳቁስ ድጋፍ፣ የንፅህና መጠበቂያ ድጋፍ አገልግሎት፣ የማዕድ ማጋራት እና የምሳ ግብዣ ተደርጓዋል።

‎በመርሃ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር የአራዳ ክፍለ ከተማ ቅርንጫፍ ሰብሳቢ ወጣት ማቲዮስ ብርሃኑ፣ የራስ ደስታ ዳምጠው ሆስፒታል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተሾመ ሁንዴ፣ የአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ባይሳ ታዬ፣ የአራዳ ክፍለ ከተማ የበጎ ፈቃድና ህብረተሰብ ተሳትፎ ጽ/ቤት ኃላፊ እንዲሁም የወረዳ 04 ወጣቶች ማህበር አመራሮችና በርካታ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ተገኝተዋል።

‎የክፍለ ከተማው ወጣቶች ማህበር ሰብሳቢ ወጣት ማቲዮስ ብርሃኑ ዛሬ የምናደርገው ድጋፍ ተራ የበጎ ፈቃድ ስራ ብቻ ሳይሆን የአብሮነታችንን፣ የአጋርነታችንና የሀገራዊ ኃላፊነታችን እውነተኛ መገለጫ ነው ብለው ወጣቶች በተለያዩ የበጎ ፈቃድ ተግባራት ላይ በነቃ ሁኔታ በመሳተፍ የሀገራቸውን ልማትና ሰላም ለማጠናከር የበኩላቸውን ሚና መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

‎የራስ ደስታ ዳምጠው ሆስፒታል ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ተሾመ ሁንዴ በበኩላቸው የወጣቶችን በጎ ፈቃደኝነትና ወገንተኝነት አድንቀው፤ ህብረተሰብ ተኮር እንቅስቃሴዎች በሆስፒታል ለሚገኙና በጎዳና ለሚገኙ ወገኖችና አረጋውያን ትልቅ ሞራላዊና ማህበራዊ ብርታትን ይፈጥራል ብለዋል።

‎ይህ መርሃ ግብር የወጣቶችን የበጎነት፣ የመረዳዳትና የሀገራዊ አጋርነት እሴት አብልጦ የሚያጠናክር ሲሆን የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበርም በቀጣይም ወጣቶችን በማስተባበር የጋራ የመረዳዳት ባህልን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

https://linktr.ee/Arada_communication

በአራዳ ክፍለ ከተማ በአካባቢ ጥበቃ ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸው ተገለፀ።አራዳ ጳጉሜ 1/2018 ዓ.ም በአራዳ ክፍለ ከተማ ከኮሪደርና ወንዝ ዳርቻ ልማት ስራዎች ጋር በተቀናጀ መልኩ በተከናወ...
06/09/2026

በአራዳ ክፍለ ከተማ በአካባቢ ጥበቃ ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸው ተገለፀ።

አራዳ ጳጉሜ 1/2018 ዓ.ም

በአራዳ ክፍለ ከተማ ከኮሪደርና ወንዝ ዳርቻ ልማት ስራዎች ጋር በተቀናጀ መልኩ በተከናወኑት ስራዎች የከተማውን ገፅታ በዘመናዊ መልኩ መቀየር ተችሏል።

በዘርፉ የ7/24 የስራ ባህልን በማዳበር የሰዓታት ገደብ የሌለው ንቁ የስራ እንቅስቃሴ በመፍጠር ፈጣን አፈፃፀም ማምጣት የተቻለ ሲሆን ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል በመፍጠር የህዝብን ሁለገብ ተጠቃሚነትና የከተማዋን የገቢ ምንጭ ማሳደግ ተችሏል።

በተጨማሪም የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎችን በማሻሻል እንዲሁም የወንዝ ዳርቻዎችን በማልማት ለከተማው ውበትና ስነ-ምህዳር ልዩ ድምቀት ተሰጥቷል።

አካባቢን ከብክለት በመከላከል ጤናማ አካባቢን መፍጠር እና ወጭ ቆጣቢ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በስፋት መጠቀም መቻሉም ተመላክቷል።

የአራዳን ታሪካዊ ቁመና ከዘመናዊው የኮሪደር ልማት ጋር በማጣጣም የተሰሩት ስራዎች ክፍለ ከተማውን ለኑሮ ምቹ፣ ፅዱና ማራኪ እያደረጉት የሚገኙ ሲሆን ጽ/ቤቱ ይህንን አረንጓዴና የብልጽግና ጉዞ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ጽ/ቤቱ ገልጿል።

https://linktr.ee/Arada_communication

06/09/2026

ጷጉሜ 1
የእመርታ ቀን

በአራዳ ክፍለ ከተማ በኮንስትራክሽን ዘርፍ አመርቂ ውጤቶች መመዝገባቸው ተገለፀ።አራዳ ጳጉሜ 1/2018 ዓ.ም በአራዳ ክፍለ ከተማ በኮንስትራክሽን ዘርፍ በርካታ ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸውን...
06/09/2026

በአራዳ ክፍለ ከተማ በኮንስትራክሽን ዘርፍ አመርቂ ውጤቶች መመዝገባቸው ተገለፀ።

አራዳ ጳጉሜ 1/2018 ዓ.ም

በአራዳ ክፍለ ከተማ በኮንስትራክሽን ዘርፍ በርካታ ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸውን የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ገለፀ።

በበጀት ዓመቱ በዘርፉ በተከናወኑ ስራዎች የከተማውን ገፅታ በዘመናዊ መልኩ መቀየር የተቻለ ሲሆን የ7/24 የስራ ባህልን በማዳበር የግንባታ ፈጣን አፈፃፀም ማምጣት ተችሏል።

በዘርፉ ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል መፈጠሩ፣ የህብረተሰቡ ተጠቃሚነት መረጋገጡ፣ የመንግስትና የግል ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ በዘመናዊ አሰራር መታገዙ የዘርፉ እመርታዎች ናቸው።

የሀገር ውስጥ የስራ ተቋራጮች፣ አማካሪዎች፣ ባለሙያዎች፣ ጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅቶችን አቅም በዘላቂነት ለመገንባት የተሰሩ ስራዎች ተጠናክረው የቀጠሉ ሲሆን ባለሙያዎች ወጭ ቆጣቢና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በግንባታ ሂደቶች ውስጥ የመጠቀም አቅም በከፍተኛ ደረጃ አድጓል።

እነዚህ አመርቂ ውጤቶች ከአራዳ ክፍለ ከተማ ታሪካዊ ቁመና እና አሁን አዲስ አበባ ከምታከናውነው አጠቃላይ የኮሪደር ልማት ማዕቀፍ ጋር ተጣጥመው መተግበራቸው ለዘርፉ የላቀ ስኬት መሠረት ሆኗል።

የኮሪደር ልማቱ አካባቢዎችን ለኑሮ ምቹ፣ ንጹህና ማራኪ በማድረግ የከተማዋን ነዋሪዎችና የቱሪስቶች እንቅስቃሴ ምቹ እንዲሆን አድርጎታል።
የክፍለ ከተማው አስተዳደር የኮንስትራክሽንና የኮሪደር ልማት ስራዎችን በማቀናጀት አራዳን የዕድገትና የብልጽግና ምዕራፍ ማሳያ ለማድረግ በቀጣይም የተጠናከሩ ስራዎች እንደሚሰሩ ጽ/ቤታ ገልጿል።

https://linktr.ee/Arada_communication

የ"ጎቤ" እና "ሺኖዬ" ፌስቲቫል በዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ ነውከክረምት ወደ ጸደይ ወቅት መሸጋገርን የሚያበስረው “የጎቤ” እና “ሺኖዬ”ፌስቲቫል በዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ ነው፡...
06/09/2026

የ"ጎቤ" እና "ሺኖዬ" ፌስቲቫል በዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ ነው

ከክረምት ወደ ጸደይ ወቅት መሸጋገርን የሚያበስረው “የጎቤ” እና “ሺኖዬ”ፌስቲቫል በዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ ነው፡፡

በኦሮሞ ባህል ዘንድ የክረምቱን መውጣትና የጸደይ መዳረሻን ለማብሰር ከሚከናወኑ ባህላዊ ሥርዓቶች መካከል “የጎቤ” እና “ሺኖዬ” ጨዋታ ተጠቃሽ ነው።
AMN

በአራዳ ክፍለ ከተማ ጷጉሜ 1 የእመርታ ቀንን በማስመልከት የከተማ ግብርና ልማት ስራዎች ጉብኝት ተካሄደ።አራዳ ጷጉሜ 1/2018 ዓ.ም ጷጉሜ 1 የእመርታ ቀን በማስመልከት በአራዳ ክፍለ ከተማ...
06/09/2026

በአራዳ ክፍለ ከተማ ጷጉሜ 1 የእመርታ ቀንን በማስመልከት የከተማ ግብርና ልማት ስራዎች ጉብኝት ተካሄደ።

አራዳ ጷጉሜ 1/2018 ዓ.ም

ጷጉሜ 1 የእመርታ ቀን በማስመልከት በአራዳ ክፍለ ከተማ የተከናወኑ የከተማ ግብርና ልማት ስራዎችን የመስክ ጉብኝት ተካሂዷል።

በጉብኝቱ ላይ አመራሮች፣ የዘርፉ ባለሙያዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተሳተፉ ሲሆን በክፍለ ከተማው በሚገኙ ወረዳዎች የተከናወኑ የጓሮ አትክልት ልማት፣ የዶሮ እርባታ፣ የንብ ማነብ እና የሃይድሮፎኒክ (አፈር አልባ) የግብርና ስራዎች ተጎብኝተዋል።

ነዋሪዎች ባላቸው አነስተኛ ቦታ በመጠቀም ያለሟቸውን ፍራፍሬዎች እና የጓሮ አትክልቶች የመጎብኘት ስራ ተከናውኗል።

በክፍለ ከተማው ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር የተጀመሩት የከተማ ግብርና ስራዎች ውጤት እያሳዩ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን የከተማ ግብርና የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት፣ የቤተሰብን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥና ለወጣቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑን የጉብኝቱ ተሳታፊዎች ገልፀዋል ።

https://linktr.ee/Arada_communication

Address

Hailesilase Street
Addis Ababa
ST.MARRYSTREET

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Arada communcation/አራዳ ኮሙኒኬሽን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Arada communcation/አራዳ ኮሙኒኬሽን:

Shortcuts

Share