ቦሌ 02 ኮሚዩኒኬሽን/Bole 02 Communication

ቦሌ 02 ኮሚዩኒኬሽን/Bole 02 Communication THIS PAGE IS CREATED TO INFORM THE PEOPLE OF BOLE SUB CITY WEREDA 02 ABOUT EVERY THINGS DONE IN THE

06/09/2026
 #ጳጉሜ1
06/09/2026

#ጳጉሜ1

 #ጳጉሜ1  #የእመርታቀንበቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 አስተዳደር የጳጉሜን 1 «የእመርታ ቀን» አከባበር የቀጠለ ሲሆን በሌማት ትሩፋትና በከተማ ግብርና ልማት የተመዘገቡ አበረታች ውጤቶች መ...
06/09/2026

#ጳጉሜ1
#የእመርታቀን
በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 አስተዳደር የጳጉሜን 1 «የእመርታ ቀን» አከባበር የቀጠለ ሲሆን በሌማት ትሩፋትና በከተማ ግብርና ልማት የተመዘገቡ አበረታች ውጤቶች መስክ ምልከታ እየተካሄደ ይገኛል።

ጳጉሜን 1/2018 ዓ.ም
ቦሌ ወረዳ 02 ኮምዩኒኬሽን ፅ/ቤት

«በትጋትና ጥረታችን፣ የኢትዮጵያን ክብር ከፍ እናደርጋለን!»በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 አስተዳደር የጳጉሜን 1 «የእመርታ ቀን» በሚል መሪ ቃል በታላቅ ድምቀትና ተስፋ ሰጭ መንፈስ እየተከ...
06/09/2026

«በትጋትና ጥረታችን፣ የኢትዮጵያን ክብር ከፍ እናደርጋለን!»

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 አስተዳደር የጳጉሜን 1 «የእመርታ ቀን» በሚል መሪ ቃል በታላቅ ድምቀትና ተስፋ ሰጭ መንፈስ እየተከበረ ይገኛል።

የበዓሉን ዓላማ አስመልክተው ፤ የእመርታ ቀን ዋና ዋና ግቦች፡

የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ፡-
በምግብ ራስን ለመቻል የተደረጉ ጥረቶችንና የተመዘገቡ ስኬቶችን ማሳየት።

የ«ኢትዮጵያ/አዲስ አበባ ታምርት» ንቅናቄ፡-የሀገር ውስጥ ምርትን ለማሳደግ የተከናወኑ አበራች ተግባራትን ማጎላት፤

ታሪካዊ ሽግግር፡-ከተማችን ከተረጂነት እና ከጥገኝነት ወጥታ ወደ አምራችነት እያደረገች ያለችውን ጉዞ ማበሰር፤

የተስፋና የመነሳሳት መንፈስ፡-ለላቀ አገራዊ ውጤትና ለበለጠ ስኬት የህብረተሰቡን የመስራት ፍላጎት ማነቃቃት ናቸው።

ይህ ታሪካዊ ሽግግር በእያንዳንዳችን ትጋትና ጥረት የሚረጋገጥ በመሆኑ፣ ሁላችንም እጃችንን ለአምራችነት እና ለእድገት እንዘርጋ ሲሉ መልክት አስተላልፈዋል።

ቦሌ ወረዳ 02 ኮምዩኒኬሽን ጽ/ቤት
ጳጉሜን 1/2018 ዓ.ም

የአከራይና ተከራይ ውል እድሳት ማጠናቀቂያ የጊዜ ገደብ እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ለመጨረሻ ጊዜ ተራዝሟል፡፡ከሀምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ሲሰጥ የቆየው የአከራይና ተከራይ ውል ...
05/09/2026

የአከራይና ተከራይ ውል እድሳት ማጠናቀቂያ የጊዜ ገደብ እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ለመጨረሻ ጊዜ ተራዝሟል፡፡

ከሀምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ሲሰጥ የቆየው የአከራይና ተከራይ ውል ምዝገባና እድሳት አገልግሎት ለመጨረሻ ጊዜ እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ መራዘሙን የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ፡፡

ቢሮው የውል ምዝገባና እድሳት ስራው እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም እንዲጠናቀቅ ጊዜ ገደብ አስቀምጦ የነበረ ቢሆንም፣ አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎችን በጊዜው አሟልተው ያልቀረቡ፣ በተሰጠው የጊዜ ገደብ በልዩ ልዩ ምክንያት ከአዲስ አበባና ከሀገር ውጭ የነበሩ ተዋዋዮች መኖራቸውን ተረድቷል።በህብረተሰቡ ተደጋጋሚ ጥያቄ መሰረት የመጨረሻ ተጨማሪ እድል መስጠት አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን ቢሮው ገልጿል።

በመሆኑም እስከ ዛሬ ውላቸውን ያላደሱ ሁሉም አከራዮችና ተከራዮች ይህንን የመጨረሻ እድል በመጠቀም እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በክፍለ ከተሞች፣ በሁሉም የመሶብ አንድ ማዕከላት እና ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጁ ቦታዎች በመቅረብ ውላቸውን እንዲያድሱ ቢሮው ጥሪ አቅርቧል።

የመጨረሻ እድል — ጊዜዎ ሳያልቅ ውልዎን ያድሱ!!

ነሀሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ
ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aahdab

አዲሱን ዓመት ስንቀበል የመኖሪያ ቤታችንን ብቻ ሳይሆን የምንኖርበትን አካባቢ, ብሎኮችን የጋራ ግቢያችንን በህብረት እናጽዳ።በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 02 አስተዳደር መጪ በዓላትን በማስመልከት አ...
03/09/2026

አዲሱን ዓመት ስንቀበል የመኖሪያ ቤታችንን ብቻ ሳይሆን የምንኖርበትን አካባቢ, ብሎኮችን የጋራ ግቢያችንን በህብረት እናጽዳ።

በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 02 አስተዳደር መጪ በዓላትን በማስመልከት አካባቢን ብሎኮችን በህብረት ና በጋራ ማጽዳትን በተመለከተ ከብሎክ ነዋሪዎች ጋር የውይይትና የቡና ጠጡ መድረክ ተካሄደ።

በመድረኩም ላይ የወረዳው አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ወ/ሮ ሀያት አብደላ ,የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ በሬሳጅራ ፍቃዱ እንዲሁም የወረዳው ም/ዋና ስራ አስፈጻሚና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ሀላፊ የሆነት ወ/ሮ ደስታ ለብሴ የተገኙ ሲሆን።

በመድረኩም ​ፅዳት ከደጃፋችን ይጀምራል አካባቢያችንን ከቆሻሻ ቦታዎች በማፅዳት የብሎክና ሰፈር ጽዳት በህብረት ማካሄደ እንደሚገባ

​የጸዳ አካባቢ የጸዳ ብሎክ ውብ አካባቢ መፍጠር እንደሚገባ በመድረኩ ተነስቷል።

ነሀሴ 28/2018 ዓ.ም

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 አስተዳደር በወረዳው የሚገኙ በጎ ፈቃደኞችን በማስተባበር  የቤት ግንባታና እድሳት በታቀደለት ጊዜ ለማጠናቀቅ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል።​የወረዳው አ...
03/09/2026

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 አስተዳደር በወረዳው የሚገኙ በጎ ፈቃደኞችን በማስተባበር የቤት ግንባታና እድሳት በታቀደለት ጊዜ ለማጠናቀቅ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል።

​የወረዳው አስተዳደር ከአካባቢው ወጣቶች፣ ባለሀብቶችና በጎ ፈቃደኛ ነዋሪዎች ጋር በመቀናጀት የተጀመረውን የእድሳት ሥራ በተቀመጠለት የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ለማጠናቀቅ ርብርብ እያደረገ ነው። ይህ በጎ አድራጎት ሥራ የአቅመ ደካሞችን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻልና ወገን ለወገን የመደጋገፍ ባህልን ለማጠናከር ያለመ ነው።
​በግንባታውና በእድሳት ሥራው ላይ እየተሳተፉ የሚገኙ በጎ ፈቃደኞችም ጉልበታቸውን፣ እውቀታቸውንና ቁሳቁሳቸውን በማስተባበር የማኅበረሰባዊ ኃላፊነታቸውን እየተወጡ ይገኛሉ። ወረዳ አስተዳደሩም ለሁሉም በጎ ፈቃደኞችና ደጋፊ አካላት ያለውን ምስጋና ገልጾ፣ የቀሩትን ቤቶች በወቅቱ ለማጠናቀቅ የተቀናጀው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።

ነሃሴ 28/2018
በዚህ ድህረገጽ በሁሉም ፕላትፎርማ ይከታተሉን
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://linktr.ee/bole02communica

Address

Around Bole Japan Condiminium Near To 17/20 Health Center
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ቦሌ 02 ኮሚዩኒኬሽን/Bole 02 Communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share