Addis Ababa Health Bureau

Addis Ababa Health Bureau This is the Official Addis Ababa City Administration Health Bureau page
(2)

የራስ ደስታ ዳምጠው መታሰቢያ ሆስፒታል ከ250 በላይ ለሚሆኑ የጎዳና ተዳዳሪዎች '' የእመርታ ቀንን'' ምክንያት በማድረግ  የበጎ አድራጎት ተግባራትን አከናውኗል።አአ ጤና ቢሮ ጳጉሜ  1 ቀ...
06/09/2026

የራስ ደስታ ዳምጠው መታሰቢያ ሆስፒታል ከ250 በላይ ለሚሆኑ የጎዳና ተዳዳሪዎች '' የእመርታ ቀንን'' ምክንያት በማድረግ የበጎ አድራጎት ተግባራትን አከናውኗል።

አአ ጤና ቢሮ ጳጉሜ 1 ቀ 2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ስር ከሚገኙ ሆስፒታሎች አንዱ የሆነው የራስ ደስታ ዳምጠው መታሰቢያ ሆስፒታል ጳጉሜ1 የእመርታ ቀንን በማስመልከት ከ250 በላይ ለሚሆኑ በጎዳና ለሚገኙ ወገኖች የበጎ አድራጎት ተግባራትን አከናውኗል።

በእለቱ በሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ ከ 250 በላይ ለሚሆኑ በጎዳና ለሚገኙ ወገኖች የተለያዩ የህክምና አገልግሎቶችን የስኳር ፣ የአይን ፣ የደም ግፊት ፣ የቲቢ ፣ኤች አይቪ ምርመራ ያደረገ ሲሆን ለእነዚሁ ወገኖች የንፅህናቸውን ለመጠበቅ ፀጉር መቁሰጥ ፣ ገላቸውን በማጠብ የአልባሳት እና የማዕድ ማጋራት ድጋፍ አድርጓል።

የራስ ደስታ ዳምጠው መታሰቢያ ሆስፒታሉ ዋና ስራ አስኪጅ አቶ ተሾመ ሁንዴ በሆስፒታሉ ነፃ ህክምናን ጨምሮ በርካታ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎቶች ሲሰጡ መቆየታቸውን ገልፀው በዛሬው ዕለትም የዚሁ አካል የሆነውና የእመርታ ቀንን በማስመልከት ነፃ ህክምና አገልግሎት ፣ ማዕድ ማጋራት ፣ ፀጉር መቁረጥ ፣ ገላ ማጠብ እና መሰል የበጎ አድራጎት ስራዎች መተግበራቸውን ተናግረዋል።

ነፃ ህከምና ተደርጎላቸው ቀጣይ ተጨማሪ የህክምና ክትትል ለሚያስፈልጋቸው ሆስፒታሉ አመቱን ሙሉ በነፃ ህክምና የሚያደርግላቸው መሆኑን አቶ ተሾመ አክለው ገልፀዋል።

በዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሆስፒታሉ ከ5ሺህ 700 በላይ ለሚሆኑ የተለያዩ ድጋፋ ለሚሹ የማህበረሰብ ክፍሎች በነጻ የተለያዩ ህክምና እንዲያገኙ መደረጉን እና 146 ዩኒት ደም መሰብሰብ አቅመ ደካሞችና አረጋውያን ማቆያ ለሚገኙ ወገኖች ነፃ ህክምና በመሰጠት እና ሌሎች በርካታ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎቶች መተግበራቸውን አቶ ተሾመ ተናግረዋል።

ጳጉሜን 1 የሚከበረውን “ የእመርታ ቀን”  በማስመልከት የፎቶ አወደርዕይ በታላቅ ድምቀት ተከፈተ"የእመርታ ቀን" ምክንያት በማድረግ፣ የከተማችንን ሁለንተናዊ የልማት ጉዞ በሚያሳይ በዚህ  አ...
06/09/2026

ጳጉሜን 1 የሚከበረውን “ የእመርታ ቀን” በማስመልከት የፎቶ አወደርዕይ በታላቅ ድምቀት ተከፈተ

"የእመርታ ቀን" ምክንያት በማድረግ፣ የከተማችንን ሁለንተናዊ የልማት ጉዞ በሚያሳይ በዚህ አውደርዕይ እና የፓናል ውይይት የዕለቱ የክብር እንግዳ የአዲስ አበባ ከተማ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ በተገኙበት ተከፍቷል ፡፡

የክቡር እንግዳው በመክፈቻ ንግግራቸው “የገቢዎቻችን ማደግና የፋይናንስ ሥርዓታችን መጠናከር፣ በፕላንና በዲዛይን የታገዙ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች፣ በኢንዱስትሪና በአርሶ አደርና ከተማ ግብርና የታየው ምርታማነት፣ ከአካባቢ ጥበቃ ጋር ተጣጥሞ የልማት አካሄዳችን ዘላቂ የወደፊት ጉዞ ያመላክታል በማለት እነዚህ ውጤቶች መድረሻችን ሳይሆኑ ለአዲሱ የዕድገት ምዕራፍ መነሻ ናቸው ሲሉ ገልፀዋል።

አክለውም በከተማዋ የተመዘገቡት ስኬቶች የሀገሪቱን አጠቃላይ የእመርታ ጉዞ የሚያጠናክሩ በመሆናቸው ይህን በጎ ልምድ አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ሲሉ ተናግርዋል።

በአራዳ ፓርክ በተከፈተው በዚህ አውደርዕይ እና የፓናል ውይይት ባለፉት የለውጥ ዓመታት የተመዘገቡ ታላላቅ ከተማ አቀፍ ስኬቶችን የቀረበ ሲሆን ፤ የፕላንና ልማት ቢሮ፣ የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን፣ የኢንዱስትሪ ቢሮ፣ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን፣ የዲዛይንና ግንባታ ቢሮ፣ የገቢዎች ቢሮ እና የፋይናንስ ቢሮ በጋራ በመሆን ያዘጋጁት እንደሆነ ተነግሯል ።

በመድረኩ የዕለቱ የከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች ጨምሮ ከ400 በላይ የሚሆኑ ጥሪ የተደረገላቸው ተሳታፊዎች የከተማዋን ሁለገብ የእድገት እመርታ፣ የከተማ ግብርና ልማቶች፣ የዲጂታልና የመሰረተ ልማት የሚያሳይ የፎቶ አውደርዕይ ጎብኝተዋል።

06/09/2026

የእመርታ ቀን!

በአዲስ አበባ ከተማ እመርታ ያስገኙ ኢኮኖሚያዊ ስኬቶች!

በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ የልማት ስኬቶች የከተማዋን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ ለነዋሪዎች ሰፊ የሥራ እድል በመፍጠር እንዲሁም የኢንቨስትመንት ዘርፉን በማነቃቃት ከፍተኛ ለውጥ ያመጡ ናቸው፡፡

ከተማዋን እንደ አዲስ ከፈጠሩ ኢኮኖሚያዊ ስኬቶች መሀከል የኮሪደር ልማት እንዱና ዋንኛው ነው፡፡ በዚህ ሰፊና ዘመን ተሻጋሪ ስራ ዘመናዊ የመንገድ ግንባታዎች በመግንባትና አስቸጋሪ እና በርካታ አመታት ያስቆጠሩ የፍሳሽ አወጋገድ ስርዓት በመለወጥ እንዲሁም ያረጁና የጎሰቆሉ መኖሪያ መንደሮችን በአዲስ በመተካት ብሎም ለንግድ እንቅስቃሴ ምቹ የሆኑ ዘመናዊ ሱቆችንና ማዕከላትን በመገንባት ለነዋሪዎች ምቹ ከባቢን በመፍጠር የተሻለች ውብ ከተማ እንድትሆን ማድረግ ተችሏል፡፡

በከተማዋ የተገነቡ የወንዝ ዳርቻ ልማት ስራዎች እና የቱሪዝም መዳረሻዎችም ከተማዋን አረንጓዴ ገፅታን በማላበስ ለጤና ምቹ ከተማ እንድትሆን በማድረግ ለቱሪስት ምቹ እና ቀልብ ማረፊያ ከተማ እንድትሆን በማድረግ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ጎብኚዎችን ቁጥር በማሳደግ ለሀገር ኢኮኖሚው ከፍተኛ ሚና ማበርከት ችለዋል፡፡

በሌላ በኩል በአዲስ አበባ ከተማ እምርታን ካመጡ ኢኮኖሚያዊ ስኬቶች መሀከል የስራ ዕድል ፈጠራ ተጠቃሽ ነው፡፡ በዚህ እምርታ አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች በማስፋፋት ማዕከላቱን ለስራ አጥ ወጣቶች በማስተላለፍ አምራች እንዲሆኑ ማድረግ የተቸለ ሲሆን ከዚህ ጎን ለጎን የከተማዋን ኢኮኖሚ በማሳደግ የከተማ አስተዳደሩ የግል ኢንቨስትመንት በመሳብ ለበርካታ ባለሀብቶች ፍቃድ በመስጠት በግንባታ፣ በሆቴልና ቱሪዝም፣ እንዲሁም በሪል-እስቴት ዘርፎች ሰፊ የሥራ እድሎች እንዲፈጠሩ ምቹ ሁኔታን ተፈጥሯል ፡፡

አዲስ አበባ ያከናወነችው ለትውልድ ተሸጋሪ ሌላኛው ስኬታማ ስራ የትምህርት፣ ጤና እና ማህበራዊ መሰረተ ልማት በማዘመን ትምህርት ቤቶችና የጤና ተቋማትን በማስፋፋት ለትውልድ ተሻጋሪ አንዲሆን የተሰራው አመርቂ ስራ ማሳያ ነው፡፡

በአጠቃላይ አዲስ አበባ ከተማ በተመዘገበው የላቀ ስኬታማ ስራ ከተማዋ ለህፃናት እና ለወጣቶች ምቹ በማድረግ የስፖርት ሜዳና የመጫወቻ ስፍራዎች በመገንባት ለሁሉ የምትመች እና ሁሉን አካታች ከተማ በመሆን አመርቂ እመርታን ማስመዝገብ ችላለች፡፡

የእመርታ ቀን አባቶቻችን የኢትዮጵያን ዳር ድንበር በደምና በአጥንታቸው አስከብረው ታላቅ ሀገር አውርሰውናል፤ ዛሬ ደግሞ እውነተኛ ሉዓላዊነትን እያረጋገጥን ያለነው ከልመናና ከጥገኝነት በተላቀ...
06/09/2026

የእመርታ ቀን

አባቶቻችን የኢትዮጵያን ዳር ድንበር በደምና በአጥንታቸው አስከብረው ታላቅ ሀገር አውርሰውናል፤ ዛሬ ደግሞ እውነተኛ ሉዓላዊነትን እያረጋገጥን ያለነው ከልመናና ከጥገኝነት በተላቀቀው አዲሱና ታሪካዊው መንገዳችን ነው! በሚሊዮን በሚቆጠር ዶላር ስንዴ ከማስገባት ተነስተን ዛሬ የአፍሪካ ቀዳሚ ስንዴ አምራች በመሆን የሚሊዮን ዶላሮችን ወጪ ማስቀረት ችለናል። በ«ሌማት ትሩፋት» የምግብ ዋስትናን በተግባር እያረጋገጥን፣ በ«ኢትዮጵያ ታምርት» ንቅናቄም አዳዲስ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋትና የሥራ ዕድል በመፍጠር ሉዓላዊነታችንን እያረጋገጥን እንገኛለን። ከዚህ ቀደም የማይደፈሩና አይነኬ ይባልላቸው የነበሩ ከባድ የማክሮ-ኢኮኖሚ ሪፎርም ውሳኔዎችን በቁርጠኝነት በመተግበር፤ የሀገራችንን ኢኮኖሚ በፅኑ መሠረት ላይ እየገነባን እንገኛለን። እነዚህ ሁሉ ታላላቅ ድሎች ኢትዮጵያ በሚያጋጥሟት ውስጣዊና ውጫዊ ፈተናዎች ሸብረክ ሳትል በፅናት መጓዝ መቻሏን የሚያረጋግጡ ህያው ምስክሮች ናቸው፤ ይህ የእመርታ ጉዟችን ለመጪው ዓመት የሰነቀው ተስፋ እጅግ ግዙፍ ነው!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

05/09/2026
የየካቲት12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ዛሬ ለ9ኛ ዙር  በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያስመረቃቸው 251 ተመራቂዎች በሙያ ዘርፍ ።👉 በቅድመ ምረቃ መርሃግር በህክምና ዶክትሬት ለ9ኛ ዙር የቀረቡ...
05/09/2026

የየካቲት12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ዛሬ ለ9ኛ ዙር በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያስመረቃቸው 251 ተመራቂዎች በሙያ ዘርፍ ።

👉 በቅድመ ምረቃ መርሃግር በህክምና ዶክትሬት ለ9ኛ ዙር የቀረቡት 60 ተመራቂዎች ሲሆኑ 10ሴት እና 50 ወንድ

👉 በቅድመ ምረቃ መርሃግር በነርሲንግና ህክምና ላቦራቶሪ ቅድመ-ምረቃ መርሃ-ግበር ለመጀመሪያ ጊዜ 72 ተመራቂዎች ሲሆኑ 60 ሴትእና 12 ወንድ

በአጠቃላይ ነርስነት ሙያ = 23 ተመራቂዎች ሲሆኑ 22 ሴት እና 1ወንድ

👉 በድንገተኛ እና ጽኑ ሕሙማን ክብካቤ ነርስነት = 19ተመራቂዎች ሲሆኑ 17 ሴት፥ 2 ወንድ

👉 በጨቅላ ህፃናት ነርስነት= 15ተመራቂዎች ሲሆኑ 15ሴት

👉 በሕክምና ላቦራቶሪ ሳይንስ= 15ተመራቂዎች ሲሆኑ 6ሴት ፥ 9ወንድ

በድህረ ምረቃ ስፔሻሊቲ መርሃ ግብሮች ለ4ኛ
👉. በህፃናት ህክምናና ጤና አጠባበቅ ስፔሻሊቲ - 14 ተመራቂዎችን [5 ሴ፥ 9ወ]

👉. በውስጥ ደዌ ስፔሻሊቲ - 15 ተመራቂዎች ሲሆኑ [4 ሴ፥ 11 ወ]
ለ3 ዙር ተመራቂዎች
👉 በማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊቲ - 18[4 ሴ፥ 14 ወ]
👉 በጠቅላላ ቀዶ ህክምና ስፔሻሊቲ = 12 [3 ሴት እና ፥ 9 ወንድ

👉 የአፍ ውስጥ: የመንጋጋና የፊት ቀዶ ጥገና ስፔሻሊቲ = 4 ወንድ ተመራቂዎች

👉 ለመጀመሪያ ጊዜ: Anesthesia and critical care Medicine= 4ወንድ ተመራቂዎችን

👉 ለመጀመሪያ ጊዜ በUrogynecology= 1ሴት ተመራቂ

👉 ለሁለተኛ ጊዜ በMaternal & Fetal Medicine)=2ወንድ

ከሕብረተሰብ ጤና ትምህርት ቤት-በ በህብረተሰብ ጤና አጠባበቅ የማስተርስ ዲግሪ -ለ5ኛ ዙር

👉 በጤና አገልግሎት ጥራት ትምህርት 18 ተመራቂዎችን 4ሴት እና 14ወንድ

👉 በአጠቃላይ ህብረተሰብ ጤና ትምህርት – 20 ተመራቂዎችን 3 ሴት እና ፥ 17 ወንድ

👉 በሥነ-ተዋልዶ ጤና ትምህርት - 14 ተመራቂዎችን [8ሴት እና 6ወንድ

በጠቅላላው - 251(ወንድ -150፡ ሴ-ት 101 እጩ ተመራቂዎችን “የየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 31/2004 በተሰጠው ስልጣን መሰረት የሆስፒታል ኮሌጁ ሴኔት በነሃሴ 26 2018 ዓ.ም ባደረገው መደበኛ ስብሰባ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻው አመት የወሰዱትን ትምህርት በመመርመር እና በመተንተን፤ በየትምህርት መርሃ-ግብሩ የሚጠበቅባቸውን ትምህርት ያጠናቀቁ ስለሆኑ እንዲመረቁ አጽድቋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች በአዲስ አበባ የተለያዩ የቱሪዝም መዳረሻዎች እና የወንዝ ዳርቻ ልማትን ጎበኙ፡፡የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች በአዲስ አበባ ከአንጦጦ መቀጠያ እስከ ፒኮ...
05/09/2026

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች በአዲስ አበባ የተለያዩ የቱሪዝም መዳረሻዎች እና የወንዝ ዳርቻ ልማትን ጎበኙ፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች በአዲስ አበባ ከአንጦጦ መቀጠያ እስከ ፒኮክ ፓርክ ድረስ የተሰሩትን የወንዝ ዳርቻ ልማትን ጉብኝተዋል:: ሰራተኞቹ የመዲናዋን አዲስ ገጽታና የቱሪዝም ሳቢነት የሚያጎሉ የመሰረተ ልማት እና የአካባቢ ጥበቃ ስራዎችን ተመልከተዋል።

በጉብኝታቸውም በመዲናዋ የተከናወኑት የልማት ስራዎች እጅግ የሚደነቁ መሆናቸውን ጠቁመው፣ አዲስ አበባን የአፍሪካ የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ የተጀመረውን ሁሉን አቀፍ የልማት ስራ እንደሚደግፉ እና የድርሻቸውን ለመወጣት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።

የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን በከተማዋ የሚገኙ የተለያዩ ተቋማት ሰራተኞች በመዲናዋ የለሙትን የቱሪዝም መዳረሻዎች እንዲጎበኙ በርካታ የማስተዋወቅ ስራን እያከናወነ ይገኛል::የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች በአዲስ አበባ የተለያዩ የቱሪዝም መዳረሻዎች እና የወንዝ ዳርቻ ልማትን ጎበኙ፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች በአዲስ አበባ ከአንጦጦ መቀጠያ እስከ ፒኮክ ፓርክ ድረስ የተሰሩትን የወንዝ ዳርቻ ልማትን ጉብኝተዋል:: ሰራተኞቹ የመዲናዋን አዲስ ገጽታና የቱሪዝም ሳቢነት የሚያጎሉ የመሰረተ ልማት እና የአካባቢ ጥበቃ ስራዎችን ተመልከተዋል።

በጉብኝታቸውም በመዲናዋ የተከናወኑት የልማት ስራዎች እጅግ የሚደነቁ መሆናቸውን ጠቁመው፣ አዲስ አበባን የአፍሪካ የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ የተጀመረውን ሁሉን አቀፍ የልማት ስራ እንደሚደግፉ እና የድርሻቸውን ለመወጣት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።

የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን በከተማዋ የሚገኙ የተለያዩ ተቋማት ሰራተኞች በመዲናዋ የለሙትን የቱሪዝም መዳረሻዎች እንዲጎበኙ በርካታ የማስተዋወቅ ስራን እያከናወነ ይገኛል::

የካቲት 12  ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ለ9ኛ ዙር በተለያዩ የሙያ ዘርፍ ያሰለጠናቸውን 251 የጤና ባለሙያዎች አስመርቋል።አ/አ/ጤ/ቢሮ ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ምሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጁ ለ9...
05/09/2026

የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ለ9ኛ ዙር በተለያዩ የሙያ ዘርፍ ያሰለጠናቸውን 251 የጤና ባለሙያዎች አስመርቋል።

አ/አ/ጤ/ቢሮ ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም

ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጁ ለ9ኛ ዙር በቅድመ ምርቃ መርሃ-ግብር በዶክትሬት ዲግሪ ፣ በነርሲንግ እና ህክምና ላብራቶሪ እንዲሁም በድህረ ምርቃ በስፔሻሊቲ እና ሰብስፔሊቲ መርሃ-ግብር በዛሬው ዕለት 251 ተማሪዎች አስመርቋል፡፡

በምርቃት ስነ- ስርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስተዳደር ጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊዎች ዶክተር ዱሬቲ ጀማል እና ዶክተር ሙሉጌታ እንዳለ ፣ የሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ዋና ፕሮቮስት ዶክተር አበበ ታደሰ ፣ የኮሌጁ የሴኔት አባላት ፣ የጤና ቢሮ የማኔጅመንት አባላት ፣ የሆስፒታል ኮሌጁ ኃላፊዎች እና መምህራን ፣ ተመራቂዎች እና የተመራቂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል ።

የዕለቱ የክብር እንግዳ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዱሬቲ ጀማል በከተማ አስተዳደሩ ለጤናው ዘርፍ በሰጠው ልዩ ትኩረት በሽታን ከመከላከል በተጨማሪ አክሞ ማዳንን በማካተት እየተተገበረ ላለው የጤና ፖሊሲ አዳዲስ የጤና ተቋማትን በመገንባት እና ነባሮቹን በማስፋት እንዲሁም ዘመኑን የዋጁ የህክምና ግብዓት በማሟላት ጥራቱን የጠበቀ የህክምና አገልግሎት በመስጠት አዲስ አበባን የጤና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ ከፍተኛ ስራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል ።

የጤና አገልግሎቱን ዲጂታላይዝ በማድረግ ቀልጣፋ እና ውጤታማ የጤና የአገልግሎት ተደራሽ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል፡፡

በመዲናዋ የእናቶችን እና ህጻናትን ጤና ለመጠበቅ ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ እና አበረታች ለውጦች እየተመዘገቡ መሆኑን የገለጹት ዶክተር ዱሬቲ በተለይም የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራም መተግበሩ ለሌሎች የአፍሪካ እና የአለም ሀገራት ተሞክሮ እየሆነ መምጣቱንም አመልክተዋል፡፡

በጤናው ዘርፍ እየመጡ ያሉ ለውጦችን ለማስቀጠል የሰለጠነ የሰው ሃይል ወሳኝ በመሆኑ የዛሬ ተመራቂ የህክምና ባለሙያዎች በገባችሁት ቃል መሰረት ህሙማንን ለመርዳት የበኩላቸውን እንዲወጡ እና በተለይም የጤና ሙያ ሁልጊዜ አቅምን ማሳደግ ፣ በርህራሄ እና በቀና ማገልገልን የሚጠይቅ በመሆኑ ይህንን በትጋት እንዲፈጽሙ አሳስበዋል፡፡

የየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ዋና ፕሮቮስት ዶክተር አበበ ታደሰ በበኩላቸው ሆስፒታሉ ኮሌጁ ለ 103 አመታት በጤናው ዘርፍ ትልቅ አበርክቶ እያደረገ መሆኑን ጠቅሰው በዛሬው ዕለትም በተለያዩ የሙያ መስክ የተመረቁት 251 የጤና ተመራቂዎች እያደገ የመጣውን የጤና አገልግሎት ለማሻሻል ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱ ጠቅሰዋል ።

ሆስፒታል ኮሌጅ በሀገሪቱ ግንባር ቀደም የህክምና ኮሌጅ መሆኑን የገለጹት ዶክተር አበበ ታደሰ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ሆኖ ከተቋቋመበት 2004 ዓ.ም ጀምሮ 1ሺህ 223 ብቁ የህክምና ባለሞያዎችን ያፈራና በአጭር ጊዜ ዉስጥ በርካታ ስኬቶችን ያስመዘገበ መሆኑን ገልጸው ተቋሙ በቅድመ ምረቃ የህክምና ዶክተሬት ትምህረት የጀመረውን ጉዞ ዛሬ ላይ በርካታ ስፔሻሊቲ እና ሰብ እስፔሻሊቲን ያካተተ 21 ፕሮግራሞችን ከፍቶ በማስተማርና በማስመረቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝም ተናግረዋል ፡፡


በዕለቱ የተመረቁ የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂዎች ሙያው የሚጠይቀውን ሁሉ ለመፈፀም ቃለመሃላ የፈፀሙ ሲሆን ከየሙያ ዘርለፉ የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ ተመራቂዎች እውቅና እና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል ።

የየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በተለያዩ የህክምና ሙያ ዘርፎች ያስተማራቸውን ተማሪዎች ያስመርቃል።አ/አ/ጤና ቢሮ ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ምየአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ...
05/09/2026

የየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በተለያዩ የህክምና ሙያ ዘርፎች ያስተማራቸውን ተማሪዎች ያስመርቃል።

አ/አ/ጤና ቢሮ ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ከህክምና አገልግሎቱ ጎን ለጎን ብቁ የጤና ባለሞያዎችን በማፍራት የድርሻውን እየተወጣ ይገኛል።

በቢሮው ስር ከሚገኙ የጤና ተቋማት እና የህክምና ኮሌጆች መካከል አንዱ የሆነው የየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በተለያዩ የህክምና ትምህርት ዘርፎች ያስተማራቸውን ተማሪዎች ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ያስመርቃል።

ኮሌጁ በ9ኛው ዙር ከ250 በላይ ተማሪዎችን በተለያዩ የህክምና ትምህርት ዘርፎች በመጀመሪያ ዲግሪ ፣ በማስተርስ ፣ በስፔሻሊቲ እና በሰብ ስፔሻሊቲ ያስመርቃል።

ኮሌጁ በጤናው ዘርፍ ብቁ ባለሞያዎችን በማፍራት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ ይገኛል።

Address

Wastena Trade Building , Piassa
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 08:30 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30
Thursday 21:00 - 05:30
Friday 08:30 - 17:30

Telephone

+251 11 833 2493

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Addis Ababa Health Bureau posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share