የካ ወረዳ 2 ኮሙዩኒኬሽን - Yeka Woreda 2 Communication

የካ ወረዳ 2 ኮሙዩኒኬሽን - Yeka Woreda 2 Communication ይህ የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 02 ኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት የፌስቡክ ገፅ ነው።

ፔጃችንን ፎሎው በማድረግ አዳዲስና ትኩስ መረጃዎችን ያግኙ።

የዘመነ መሰረተ ልማት፤ የዘመነ አገልግሎት ለዘመናዊ ከተማ! ዛሬ በከተማችን አራት ዘመናዊ የተሽከርካሪ ማቆሚያዎች፣ ተርሚናሎችና ገበያ ማዕከላት (በጎተራ፥ ቦሌ፣ የካ እና ቀበና)   መርቀን ...
26/08/2026

የዘመነ መሰረተ ልማት፤ የዘመነ አገልግሎት ለዘመናዊ ከተማ!

ዛሬ በከተማችን አራት ዘመናዊ የተሽከርካሪ ማቆሚያዎች፣ ተርሚናሎችና ገበያ ማዕከላት (በጎተራ፥ ቦሌ፣ የካ እና ቀበና) መርቀን አገልግሎት አስጀምረናል።

እነዚህ መሰረተ ልማቶች የትራፊክ መጨናነቅን የሚያቃልሉ፣ የትራንስፖርት ሥርዓትን የሚያሻሽሉ፣ ህዝባችንን ከዝናብና ፀሐይ እንግልት የሚከላከሉ፣ በርካታ የስራ እድሎችን የሚፈጥሩ ምቹ ፣ ንፁህ እና የሰውን ክብር የሚመጥኑ የዘመነ አገልግሎት የሚሰጡ ናቸው።

መሰረተ ልማቶቹ በአንድ ጊዜ በርካታ ተሽከርካሪዎችን የማስተናገድ ዓቅም ያላቸው ዘመናዊ የተሽከርካሪ ማቆሚያዎች፣ የታክሲ እና የአውቶቡስ ተርሚናሎች፣ የአየር ብክለትን የሚከላከሉ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ ማድረጊያዎች፣ ሰፊ የህዝብ መዝናኛ ስፍራዎች፣ የንግድ ሱቆች፣ ካፍቴሪያና ሬስቶራንቶች፣ የልጆች መጫወቻና ማረፊያ ስፍራዎች፣ ምቹ የተሳፋሪ መጠበቂያ ስፍራዎች፣ የአስተዳደር እና የትኬት መቁረጫ ቴክኖሎጂዎች፣ አሳንሰሮች እና ንፁህ መፀዳጃ ቤቶች እንዲሁም የደህንነትና የአደጋ ቅድመ መከላከል ሥርዓቶች የተሟሉላቸው የኢኮኖሚና የማህበራዊ አገልግሎትን ለማሳለጥ ትልቅ አስተዋጽዖ የሚያበረክቱ ናቸው።

ከለውጡ በፊት 3 ሺህ ብቻ የነበረውን የአንድ ጊዜ የተሽከርካሪ ማቆሚያ አቅም እና ምንም ያልነበረንን ተርሚናል በአሁኑ ጊዜ በጥራትና በፍጥነት የተገነቡ፣ ዘመናዊ የተሽከርካሪ ማቆሚያዎችን እና ተርሚናሎችን ከ170 ሺህ በላይ ማድረስ ችለናል ።
ለከተማችን ነዋሪዎች ተጠቃሚነት በተጨባጭ ቃላችንን በተግባር ስራዎችን እየፈጸምን በቅንነትና በታማኝነት እየሰራን እንገኛለን። አዲስ አበባ ከዚህ በላይ ይገባታል ቀጣይም ከሰራነው በላይ እንተጋለን!

የዛሬዎቹ ፕሮጀክቶች እውን እንዲሆኑ ለተጋችሁ፣ ላስተባበራችሁ የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች፣ የትራንስፖርት ቢሮ አመራሮች፣ ኮንትራክተሮች፣ አማካሪዎች በዚህ ስራ የተሳተፋችሁትን ሁሉ ከልብ አመሰግናለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ፤ እንኳን ለ1 ሺህ 501ኛው  የነቢዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!በዓሉን  ስናከብር እንደከዚህ ቀደሙ የተቸገሩ ወገኖችን በመ...
24/08/2026

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ፤ እንኳን ለ1 ሺህ 501ኛው የነቢዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
በዓሉን ስናከብር እንደከዚህ ቀደሙ የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት፤ ለሌላቸው በማካፈል፣ የታረዙትን በማልበስ፣ የታመሙትን በመጠየቅ እንዲሆን እመኛለሁ።

በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ - ኢድ ሙባረክ!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

እንኳን ለ1501ኛው የነቢዩ መሐመድ(ሰዐወ) የመውሊድ በዓል አደረሳችሁየነቢዩ መሐመድ ታሪክ ትውልድን ለበጎ ከሚቀርጹ ታሪኮች መካከል አንዱ ነው፡፡ የተጠሩበትን ዓላማ ማክበር፤ ለተጠሩበት ዓላ...
24/08/2026

እንኳን ለ1501ኛው የነቢዩ መሐመድ(ሰዐወ) የመውሊድ በዓል አደረሳችሁ

የነቢዩ መሐመድ ታሪክ ትውልድን ለበጎ ከሚቀርጹ ታሪኮች መካከል አንዱ ነው፡፡ የተጠሩበትን ዓላማ ማክበር፤ ለተጠሩበት ዓላማ ዋጋ መክፈል፤ የተጠሩበትን ለሌሎች ማካፈል፤ የተጠሩበትን አክብሮ መኖር - እነዚህ ሁሉ ሺ መጻሕፍት የሚወጧቸው ትምህርቶች ናቸው፡፡

ነቢዩ የተጠሩበትን ዓላማ በሚገባ ስለተገነዘቡ አክብረው ኖረዋል፡፡ የተጠሩት ለተራና ርካሽ ነገር እንዳልሆነ ተገንዝበዋል፡፡ የተጠሩት ትውልድን ለመቅረጽና ታሪክን ለመቀየር መሆኑን አምነዋል፡፡ ያንንም በቃላቸው፣ በሥራቸውና በኑሯቸው አክብረውት ነኖረዋል፡፡ ለታላቅ ሀገራዊ ዓላማ ተጠርተናል ብለን የምናምን ከሆነ ይህ የነቢዩ ሕይወት ታላቅ ትምህርት ይሆነናል፡፡ የተጠራንበትን ዓላማ በንግግራችን፣ በሥራችንና በሕይወታችን እንግለጠው፡፡

ነቢዩ ለተጠሩበት ዓላማ ዋጋ ከፍለዋል፡፡ ከቦታቸው ተሰደዋል፤ ምግብና መጠለያ ተነፍገዋል፤ ከቤተሰቦቻቸው ተለይተዋል፡፡ ለሞት በሚያበቁ ፈተናዎች ውስጥ አልፈዋል፡፡ ጦርነት ተከፍቶባቸዋል፡፡ ነገር ግን ሁሉንም በአላህ ኃይል አሸንፈዋል፡፡ ክብር ያለ መከራ አይገኝምና፡፡ እውነተኛ ሰው ለዓላማው እንደ ነቢዩ መሐመድ(ሰዐወ)ዋጋ ይከፍላል፡፡ ዓላማው የሚያስገኘውን ክብርና ጥቅም ብቻ ሳይሆን ዓላማው የሚያስከፍለውን መሥዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ይሆናል፡፡

ነቢዩ መሐመድ(ሰዐወ) ከአላህ የደረሳቸውን መልእክት ለራሳቸው ብቻ አላስቀሩም፡፡ የተጠሩበትን ለሌሎች ለማካፈል ተግተዋል፡፡ መጀመሪያ በጣት ለሚቆጠሩ ሰዎች፣ በኋላም ለቅርብ ሱሐባዎች፣ በመጨረሻም ለዓለም መልእክቱን አዳርሰዋል ፡፡ እሳቸው የዘሩት ዘር እያፈራና እየጎመራ ተጉዟል፡፡ ዓላማችንን እኛ ማወቃችንና ማመናችን ብቻ ጥቅም የለውም፡፡ ሌሎች እንዲያውቁና እንዲያምኑ ልክ እንደነቢዩ ተገትተን መድከም አለብን፡፡

የነቢዩን መውሊድ ስናከብር ከሕይወታቸው እየተማርን፤ የተማርነውንም ለሀገረ መንግሥት ግንባታችን እየተጠቀምን እንዲሆን አደራ እላለሁ፡፡

በድጋሚ መልካም የመውሊድ በዓል ይሁንልን።

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ዛሬ የኒው ሊፍ ሜዲካል ኮምፕሌክስን መርቀን ሥራ አስጀምረናል።  እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን!ከተማችን አዲስ አበባ የጤና ቱሪዝም  ማዕከል እናደርጋታለን ስንል በመንግስት ብቻ የ...
23/08/2026

ዛሬ የኒው ሊፍ ሜዲካል ኮምፕሌክስን መርቀን ሥራ አስጀምረናል።

እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን!
ከተማችን አዲስ አበባ የጤና ቱሪዝም ማዕከል እናደርጋታለን ስንል በመንግስት ብቻ የምናሳካው ሳይሆን በግሉ ዘርፍ የሚገነቡትንም ታሳቢ በማድረግ ስለሆነ፣ ዛሬ ያስመረቅነው የኒው ሊፍ ሜዲካል ሆስፒታልም የዚህ አንዱ ማሳያ ነው ።

ኒው ሊፍ ሜዲካል ኮምፕሌክስ በሃገራችን ከላፍቶ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ቀጥሎ ሁለተኛው PET-CT SCAN CAT LAB እና ሌሎች ዘመኑን የዋጁ ቴክኖሎጂዎች የተሟሉለት ትልቅ የጤና ማዕከል ነው። በጤናው ዘርፍ የምናደርገው ኢንቨስትመንት ክፍያው ከሁሉ የላቀ ስለሆነ እንደዚህ አይነት በጤናው ዘርፍ ለሚሰሩ የጤና ተቋማት እና ሆስፒታሎች ድጋፋችንን አጠናክረን እንቀጥላለን።

የኒው ሊፍ ሜዲካል ኮምፕሌክስ መስራችና ስራአስኪያጅ ዶ/ር ኢማን አብዱልራህማን እና ባለቤታቸው አቡበከር መሃመድ ሳላህን በራሴና በከተማው አስተዳደር ስም በጣም እናመሰግናለን።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!

22/08/2026
70 ሺህ 544 ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት አምጥተዋል - ትምህርት ሚኒስቴር አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ 550 ሺህ 210...
22/08/2026

70 ሺህ 544 ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት አምጥተዋል - ትምህርት ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ 550 ሺህ 210 ተማሪዎች ውስጥ 70 ሺህ 544 ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት አምጥተዋል አለ የትምህርት ሚኒስቴር፡፡

የትምህረት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ በዘንድሮ ዓመት የተሻሻለ ውጤት መመዝገቡን ገልጸዋል።

ዘንድሮ በአጠቃላይ ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ማለፍ የቻሉት 70 ሺህ 544 ተማሪዎች ብቻ መሆናቸውን አመልክተዋል፡፡

ፈተናውን ከወሰዱት ውስጥ 12 ነጥብ 8 በመቶ የሚሆኑት ተማሪዎች 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት ማምጣታቸውን አብራርተዋል፡፡

በዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና 563 ሺህ 960 ተማሪዎች ተመዝግበው 550 ሺህ 210 ተማሪዎች ፈተናውን መውሰዳቸውን ጠቁመዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 32 ነጥብ 3 በመቶ ተማሪዎችን በማሳለፍ ቀዳሚ ነው ብለዋል።

በዓመቱ ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 62 በመቶ የሚሆኑት በኦንላይን መፈተናቸውን አስረድተዋል፡፡

በ2018 የትምህርት ዘመን አጠቃላይ 563 ሺህ 501 ተማሪዎች በ607 የፈተና ማዕከላት ውስጥ የተፈተኑ ሲሆን ፈተናው በ6 ዙሮች መሰጠቱን አስታውሰዋል።

88 ት/ቤቶች ሙሉ ለሙሉ ያሳለፉ ሲሆን 565 ት/ቤቶች ደግሞ ምንም ተማሪ ማሳለፍ እንዳልቻሉ ገልጸዋል፡፡

ካለፉት ተማሪዎች መካከል በተፈጥሮ ሳይንስ 16 ነጥብ 5 በመቶ ሲሆኑ በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ 8 ነጥብ 33 በመቶ መሆናቸውን አመልክተዋል፡፡

ለረዳን ፈጣሪ አምላክ ታላቅ ክብርና ምስጋና ይሁንለት!አዲስ ታሪክ፣ አዲስ ምእራፍ፣ በአዲስ የመከባበር፣ የመመካከርና የመደማመጥ የመግባባት ታሪክ የተደረገ ሽግግር!!"ከአሸናፊ-ተሸናፊ” ትርክ...
22/08/2026

ለረዳን ፈጣሪ አምላክ ታላቅ ክብርና ምስጋና ይሁንለት!

አዲስ ታሪክ፣ አዲስ ምእራፍ፣ በአዲስ የመከባበር፣ የመመካከርና የመደማመጥ የመግባባት ታሪክ የተደረገ ሽግግር!!

"ከአሸናፊ-ተሸናፊ” ትርክት በመላቀቅ፣ በሀሳብ ልዕልና ወደ በጋራ የማሸነፍ፣ ለጋራ ተጠቃሚነት ሲባል የጋራ መፍትሄ ለማምጣት በጠረጴዛ ዙሪያ ቁጭ ብሎ ወደ መግባባት የተሸጋገርንበት ታላቅ የታሪክ እጥፋት ነው፡፡ በዚህ የምክክር ሂደት የተለየ አሸናፊና ተሸናፊ ፈጽሞ አልተፈጠረም፤ ይልቁንም ኢትዮጵያ አሸንፋለች!

እንዲመከሩባቸው ከቀረቡት 400 ከሚጠጉ አበይት ጉዳዮች (ምክረ ሀሳቦች) ኢትዮጵያውያን ተደማምጠውና አንዱ የሌላውን ህመም ተረድተው ወደ አንድ በመሰብሰብ በ99 % ላይ ሙሉ ሙሉ ስምምነት ላይ መድረስ ተችሏል። አንድ አይነት ድምዳሜ ላይ ባልተደረሰባቸው በአራት 4 (1%) ጉዳዮች ላይ ብቻ በአማራጭ መፍትሄዎች እንዲታለፉ በሙሉ መግባባት ላይ ተደርሷል። ይህም ሂደቱን እስካሁን በዓለም ላይ ከሰማናቸው የምክክር ሂደቶች እጅጉን በምሳሌነት የሚጠቀስና አስደናቂ አድርጎታል።

ያለፉት ትውልዶች በጽኑ ተመኝተውት ያላዩትን ይህንን የሰለጠነ አብሮነት የሰፈነበት ታሪካዊ የምክክር መድረክ በዓይናችን እንድናይ ስለፈቀደልን ቸሩ አምላካችንን ከልብ እናመሰግናለን። የእኛም ትውልድ ይህን ስላሳካን በእውነትም እጅግ የታደልን ትውልዶች ነን።

ለዚህ ሀገራዊ ድል መሳካት ከየአካባቢው የመጡ ውድ ኢትዮጵያውያን ያሳዩት አስደናቂ በሳልነት እና ጥልቅ አስተዋይነት እጅግ የሚመሰገን ነው።

ሀገር የምትገነባውና ኢትዮጵያ የምትጸናው በትክክልም በዚህ የሰለጠነ መንገድ ነው! በመተሳሰብ፣ በአብሮነት፣ አንዱ የሌላውን ሀሳብ ለማዳመጥና ለመቀበል ፈቃደኛ በመሆን፣ እንዲሁም በመከባበር የምንገነባት ኢትዮጵያ የሁላችንም ኩራት ናት። ይህ አስደናቂ የመደማመጥ አዲስ ባህል እና የጋራ ታሪካችን በመሆኑ ላሳኩት ሁሉ ክብር ይገባቸዋል።

በርግጥ ዛሬ ተመካክረን በእነዚህ ጉዳዮች ተግባብተናል ማለት ነገ ምንም አይነት ልዩነቶች አያጋጥሙንም ማለት አይደለም። ነገር ግን ልዩነትን በመመካከርና በሰለጠነ መንገድ መፍታት ተጀምሯል፤ በሩም ተከፍቷል፤ ከእንግዲህ ወደ ኋላ አንመለስም። ከእንግዲህ ልጆቻችን ልዩነቶቻቸውን በጠመንጃ ለመፍታት በመሞከር እና እርስ በእርስ በመገዳደል አይቀጥሉም። ይህ የጦርነት እዳ ወደ እነሱ እንደማይተላለፍ እምነት አለን።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የሰንበት ገበያ ግብይት ተጠናክሮ ቀጥሏል።የካ ወረዳ 2 ኮሙኒኬሽን ነሀሴ 16/2018ዓ.ምበዛሬው ዕለት በወረዳችን የሚገኘው የሰንበት ገበያ የተለያዩ የፍጆታና የምግብ ምርቶችን በጥራትና በበቂ...
22/08/2026

የሰንበት ገበያ ግብይት ተጠናክሮ ቀጥሏል።

የካ ወረዳ 2 ኮሙኒኬሽን ነሀሴ 16/2018ዓ.ም

በዛሬው ዕለት በወረዳችን የሚገኘው የሰንበት ገበያ የተለያዩ የፍጆታና የምግብ ምርቶችን በጥራትና በበቂ መጠን በማቅረብ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርግ የምርት ግብይት በማካሄድ ላይ ይገኛል።

የዛሬው የግብይት እንቅስቃሴ እንደ ሽንኩርት፣ እንቁላል፣ ድንች፣ ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ያሉ መሠረታዊ የምግብ ፍጆታዎች በስፋት ለሸማቹ ቀርበዋል።

ምርቶች ከአምራችና ከአካባቢው አቅርቦት አከፋፋዮች በቀጥታ የቀረቡ በመሆናቸው ከመደበኛው ገበያ በተሻለና በቅናሽ ዋጋ እየተሸጡ የሚገኝ ሲሆን የወረዳው ነዋሪዎች ወደ ገበያው በመመላለስ የሚፈልጉትን ምርት በተረጋጋ ሁኔታ በመሸመት ላይ ናቸው።

ይህ እንቅስቃሴ የኑሮ ውድነትን ለማቃለልና የአካባቢውን ህብረተሰብ የአቅርቦት ፍላጎት ለማሟላት የተዘጋጀ ሳምንታዊ መርሃግብር አካል በመሆኑ ዘወትር ቅዳሜና እሁድ ግብይቱ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።

"ይምጡ በቅናሽና በጥራት ይሸምቱ"

በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር “6400 A” የዲጂታል በጎነት ፕሮጀክት በይፋ ተጀመረነሐሴ 14/2018 ዓ•ም የካ ኮሙኒኬሽንበየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተሳትፎንና ተ...
20/08/2026

በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር “6400 A” የዲጂታል በጎነት ፕሮጀክት በይፋ ተጀመረ

ነሐሴ 14/2018 ዓ•ም የካ ኮሙኒኬሽን

በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተሳትፎንና ተጠቃሚነትን ለማሳደግ “6400 A” የዲጂታል በጎነት ፕሮጀክት የማስተዋወቂያና በክፍለ ከተማ ደረጃ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሂዷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር ያስጀመረው ይህ የዲጂታል በጎነት ፕላትፎርም፣ የዜጎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ከተረጅነት በዘላቂነት ለማቃለል የሁሉንም የማህበረሰብ ክፍል በቀላሉ በበጎ ፈቃድ ተግባራት ላይ ለማሳተፍ ያለመ ነው።

በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የየካ ክፍለ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ መገርሳ ገላና በክፍለ ከተማው በርካታ ሰው ተኮር የሆኑ የበጎ ፈቃድ ተግባራት መከናወናቸውን ገልፀው ሁሉም ሰው የበኩሉን አስተዋፅኦ ሲያደርግ የሰው ሰራሽና ተፈጥሮዊ አደጋን በእራሳችን አቅም ለመፍታት በጋራ መስራ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።

የየካ ክፍለ ከተማ የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ መሰለች አቡዬ በበኩላቸው የበጎ ፈቃድ ተግባር ለበርካታ አቅመ ደካማ ወገኖች፣ ለሀገር ባለውለታዎችና ለዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ ማድረስ መቻሉን ያስረዱ ሲሆን የ“6400 A” ዲጂታል በጎነት ፕሮጀክትም በተለይ አቅመ ደካማና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎችን ለመድረስ የሚያግዝ በመሆኑ የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች በፕላትፎርሙ ላይ በመሳተፍ የበጎነት አሻራቸውን እንዲያሳርፉ ጥሪ አቅርበዋል።

የ“6400 A” ፕላትፎርም የበጎነት ባህልን በበለጠ ለማስፋፋት፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመቅረፍ እንዲሁም ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ዜጎች ዘላቂ ጠቀሜታ ለመፍጠር አስተዋጽኦው ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።

ህብረተሰቡ ወደ 6400 “A” የጽሑፍ መልዕክት (SMS) በመላክና በቀን 1 ብር በመለገስ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱን በመደገፍ በጎነትን ማስፋፋትና ፕሮጀክቱ የተቀመጠለትን ዓላማ እንዲያሳካ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ጥሪ ቀርቧል።

በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የ8ኛ ዙር የማካካሻ ኮርስ እጩ ምልምል የሰላም ሠራዊት አባላት ተመረቁ!የየካ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት በ8ኛ ዙር የማካካሻ ኮርስ ለ1,000...
20/08/2026

በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የ8ኛ ዙር የማካካሻ ኮርስ እጩ ምልምል የሰላም ሠራዊት አባላት ተመረቁ!

የየካ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት በ8ኛ ዙር የማካካሻ ኮርስ ለ1,000 እጩ ምልምል የሰላም ሠራዊት አባላት የንድፈ ሐሳብና የተግባር ሥልጠና በመስጠት አስመርቋል።

በምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፍፁም ኃይሌ እንደገለጹት የሰላም ሠራዊት አባላት ከጸጥታ መዋቅሩ ጋር በመቀናጀት የከተማችንን ሰላምና ጸጥታ በማስጠበቅ፣ ሀገራዊ፣ ከተማዊና ሃይማኖታዊ የአደባባይ ክንውኖች በሰላም እንዲከናወኑ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል።

አዲስ የሰላም ሠራዊት ምልምሎችም በሥልጠናው ያገኙትን እውቀትና ክህሎት በተግባር በመተርጎም ለአካባቢያቸውና ለክፍለ ከተማው ሰላምና ጸጥታ መጠበቅ የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚው አክለውም፣ የሰላም ሠራዊቱ የሰላም አምባሳደርነቱን በተግባር እያረጋገጠ የውስጥና የውጭ ግጭቶችን በመከላከል ረገድ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን በመጠቆም ዛሬ የተመረቁት አዲስ ምልምል የሰላም ሠራዊት አባላት የአካባቢያቸውንና የክፍለ ከተማውን ሰላምና ጸጥታ ከሚያውኩ ኃይሎች ለመጠበቅ የተሰጣቸውን ኃላፊነት በብቃት መወጣት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

የየካ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ደረጀ በበኩላቸው የሰላም ሠራዊት አባላት በሥልጠናው ያገኙትን የንድፈ ሐሳብና የተግባር እውቀት ወደ ተጨባጭ ውጤት በመቀየር የአካባቢያቸውንና የከተማዋን ሰላም በተጠናከረ መልኩ ማስቀጠል እንዳለባቸው ገልጸዋል።

የሥልጠናው ተሳታፊ አዲስ ምልምል የሰላም ሠራዊት አባላትም ከጸጥታ አካላት ጋር በቅንጅት በመሥራት የአካባቢያቸውን ሰላም ለማስፈን፣ ወንጀልን ለመከላከልና የሰላም አምባሳደርነታቸውን በተግባር ለማረጋገጥ ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ የሥልጠና ማጠናቀቂያ እና ለአሰልጣኞች ማስረጃ ለምልምል የሰላም ሠራዊት አባላት ተሰጥቷል።

Address

Ferensay Legasion
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የካ ወረዳ 2 ኮሙዩኒኬሽን - Yeka Woreda 2 Communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share