Ethiopian Ministry of Industry

Ethiopian Ministry of  Industry The Ethiopian Ministry of Industry is one of The Ethiopian Federal Democratic Republic Gov

ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ የሀገራችንን ኢኮኖሚ በመምራት የማይናጋ የኢኮኖሚ ስርዓት በመገንባትና ቀጣይነት ያለው አድገትና የስራ እድል ፈጠራን እውን ለማድረግ የአስር ዓመት መሪ የልማት ዕቅድ አዘጋጅቶ፡-
👉ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ የኢኮኖሚ ድርሻ ከ 6.8 በመቶ በ2022 በጀት ዓመት መጨረሻ ወደ 17.2 በመቶ ማሳደግ፣
👉የአምራች ኢንዱስትሪዎች አማካይ የማምረት አቅም አጠቃቀም ከ 50% በ2022 ወደ 85% ማድረስ፤
👉ስትራቴጂክ ገቢ ምርት የሚተኩ አምራች ኢንዱስትሪዎች በማስፋፋት በመነሻ ዓመት ከነበረበት 30 በመቶ የሀገር ውስጥ የገበያ ድርሻ በ2022 ወደ 60 በመቶ ማድረስ፤
👉በአጠቃላይ በማኑፋክቸሪንግ

ኢንዱስትሪ ዘርፍ የሚፈጠው አዲስ የሥራ ዕድል 5 ሚሊዮን ማድረስ፤
👉ከማኑፋከችሪንግ ኢንዱስትሪ ዘርፍ አሁን ከተደረሰበት 405.6 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በ2022 ወደ የ9 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ገቢ ማድረሰ፤ የሚሉ ግቦችን እውን ለማድረግ በትጋት እየሰራ ይገኛል!

06/09/2026

እመርታ

06/09/2026

እመርታ ለኢትዮጵያ ማንሰራራት

የኢትዮጵያ ማንሠራራት ይቀጥላል፤ እመርታው ይፋጠናል፤ የኢትዮጵያ ከፍታ አይቀርም (ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ) ===========================ጳጉሜ 01/201...
06/09/2026

የኢትዮጵያ ማንሠራራት ይቀጥላል፤ እመርታው ይፋጠናል፤ የኢትዮጵያ ከፍታ አይቀርም (ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ)
===========================
ጳጉሜ 01/2018 ዓ.ም (ኢሚ) የኢትዮጵያ ማንሠራራት፡ ከዕድል ወደ እመርታ፣ ከእመርታ ወደ ከፍታ!
ኢትዮጵያ ከቆመችበት ከተነሣች እና ከተንቀሳቀሰች ቆይታለች፤ አሁን በሙሉ አቅሟ ወደ ላቀ ከፍታ እያንሠራራች ያለችበት ጊዜ ላይ እንገኛለን ሲሉ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ገለፁ።

ዛሬ የኢትዮጵያን ማንሠራራት የሚያመላክተውን የጳጉሜን 1 የእመርታ ቀን አክብረናል ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ በችግር ውስጥ ዕድልን፣ በጉድለት ውስጥ አቅምን፣ በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ተስፋን ፈልጋ የማግኘት ታሪካዊ ጽናት አላት ብለዋል።

የዛሬው እመርታችን የትናንት ቁርጠኝነታችን ፍሬ ነው፤ የነገው ከፍታችን ደግሞ የዛሬ ትጋታችን ውጤት ይሆናል።

በግብርና የምግብ ሉዓላዊነታችንን እያረጋገጥን፣ በኢንዱስትሪ ከሸማችነት ወደ አምራችነት እየተሸጋገረን፣ በማዕድን ዘርፍ የተፈጥሮ ፀጋችንን በዕሴት ጭማሪ ወደ ሀገራዊ ሀብት እየቀየርን እንገኛለን።

በዲጂታል ለውጥና የአገልግሎት አሠራር ዘመናዊነትም ጠንካራ የኢኮኖሚ መሠረት ጥለናል። ይህ ጉዞ ከጥገኝነት ወደ ራስን መቻል የሚያሸጋግር የኢትዮጵያ የእመርታ ጉዞ ነው።

ለእኛ አምራችነት ዕሳቤም፣ ስልትም፣ ግብም ነው። ሥራችን፣ ንግግራችን እና ፕሮጀክቶቻችን ሁሉ ዕሴት የሚጨምሩና ምርት የሚያስገኙ መሆን አለባቸው ብለዋል።

ዛሬ ያገኘነውን እመርታ ወደ ነገ ከፍታ ለመቀየር የበለጠ መሥራት፣ የበለጠ ማምረት፣ የበለጠ መፍጠር እና መፍጠን ይጠበቅብናል። በወጣቶቻችን እውቀት፣ በአምራቾቻችን ቁርጠኝነት እና በሕዝባችን አቅም ራሷን የቻለችና የማትበገር ኢትዮጵያን እንገነባለን ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ተመስገን የኢትዮጵያ ማንሠራራት ይቀጥላል፤ እመርታው ይፋጠናል፤ የኢትዮጵያ ከፍታ አይቀርም ሲሉ አፅንኦት ሰጥተዋል።














http://linktr.ee/fdremoi

የፖለቲካ አመራሩ ቁርጠኝነት ለአምራች ኢንዱስትሪው መሻሻል ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክቷል ( አለባቸው ንጉሴ (ዶ/ር)==============ጳጉሜን 1 2018 (ኢ.ሚ) — በፖለቲካ አመራሩ በኩ...
06/09/2026

የፖለቲካ አመራሩ ቁርጠኝነት ለአምራች ኢንዱስትሪው መሻሻል ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክቷል ( አለባቸው ንጉሴ (ዶ/ር)
==============
ጳጉሜን 1 2018 (ኢ.ሚ) — በፖለቲካ አመራሩ በኩል የታየው ቁርጠኝነትና ባለቤትነት የአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ እንዲሻሻልና የማምረት አቅሙ እንዲጎለብት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክቷል ሲሉ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር አለባቸው ንጉሴ (ዶ/ር) ገለጹ።

ዶክተር አለባቸው ይህንን የገለጹት፣ በዛሬው ዕለት የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ የግብርና ሚኒስቴር፣ የገቢዎች ሚኒስቴር፣ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር፣ የማዕድን ሚኒስቴር እና የብሔራዊ ባንክ በመተባበር “እምርታ ለኢትዮጵያ ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል በጋራ እንደ ሀገር በተከበረው የእምርታ ቀን አስመልክቶ በተካሄደው የፓናል ውይይት ላይ ነው።

የአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ አሁን ከደረሰበት ደረጃ እንዲያድግና ወደፊትም እንዲራመድ፣ ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጀምሮ እስከ ክልል አመራሮች ድረስ ያሳዩት ቁርጠኝነት፣ ባለቤትነትና የዘርፉን መሻሻል ለማምጣት የተተገበሩየማሻሻያ ስራዎች ከፍተኛ ሚና እንደነበረው ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በዘርፉ ያሉ ችግሮችን በመለየት፣ የኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም እንዲሻሻል፣ የምርት ጥራታቸው እንዲጨምር፣ በሀገር ውስጥ ገበያ ያላቸው ድርሻ እንዲያድግ እና ለወጣቶች የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድ ከፍተኛ ድርሻ አበርክቷል ብለዋል።

የአምራች ኢንዱስትሪ እመርታ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከፍታ

የኢትዮጵያ ማንሰራራት ማሳያዎች
ጳጉሜ 1

የእመርታ ቀን

እመርታ ለኢትዮጵያ ማንሰራራት!














http://linktr.ee/fdremoi

06/09/2026

የአምራች ኢንዱስትሪ እመርታ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከፍታ

የኢትዮጵያ ማንሰራራት ማሳያዎች
ጳጉሜ 1

የእመርታ ቀን

እመርታ ለኢትዮጵያ ማንሰራራት!














http://linktr.ee/fdremoi

የኢትዮጵያ ማንሰራራት ማሳያዎችጳጉሜ 1 የእመርታ ቀን እመርታ ለኢትዮጵያ ማንሰራራት!                  http://linktr.ee/fdremoi
06/09/2026

የኢትዮጵያ ማንሰራራት ማሳያዎች
ጳጉሜ 1

የእመርታ ቀን

እመርታ ለኢትዮጵያ ማንሰራራት!














http://linktr.ee/fdremoi

06/09/2026

ጳጉሜ 1

የእመርታ ቀን

እመርታ ለኢትዮጵያ ማንሰራራት!














http://linktr.ee/fdremoi

  ጳጉሜን 1 የእመርታ ቀን እመርታ ለኢትዮጵያ ማንሰራራት!                  http://linktr.ee/fdremoi
06/09/2026



ጳጉሜን 1

የእመርታ ቀን

እመርታ ለኢትዮጵያ ማንሰራራት!














http://linktr.ee/fdremoi

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት"የእመርታ ቀንአባቶቻችን የኢትዮጵያን ዳር ድንበር በደምና በአጥንታቸው አስከብረው ታላቅ ሀገር አውርሰውናል፤ ዛሬ ደግሞ እውነተኛ ሉዓላዊነት...
06/09/2026

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት

"የእመርታ ቀን

አባቶቻችን የኢትዮጵያን ዳር ድንበር በደምና በአጥንታቸው አስከብረው ታላቅ ሀገር አውርሰውናል፤ ዛሬ ደግሞ እውነተኛ ሉዓላዊነትን እያረጋገጥን ያለነው ከልመናና ከጥገኝነት በተላቀቀው አዲሱና ታሪካዊው መንገዳችን ነው! በሚሊዮን በሚቆጠር ዶላር ስንዴ ከማስገባት ተነስተን ዛሬ የአፍሪካ ቀዳሚ ስንዴ አምራች በመሆን የሚሊዮን ዶላሮችን ወጪ ማስቀረት ችለናል። በ«ሌማት ትሩፋት» የምግብ ዋስትናን በተግባር እያረጋገጥን፣ በ«ኢትዮጵያ ታምርት» ንቅናቄም አዳዲስ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋትና የሥራ ዕድል በመፍጠር ሉዓላዊነታችንን እያረጋገጥን እንገኛለን። ከዚህ ቀደም የማይደፈሩና አይነኬ ይባልላቸው የነበሩ ከባድ የማክሮ-ኢኮኖሚ ሪፎርም ውሳኔዎችን በቁርጠኝነት በመተግበር፤ የሀገራችንን ኢኮኖሚ በፅኑ መሠረት ላይ እየገነባን እንገኛለን። እነዚህ ሁሉ ታላላቅ ድሎች ኢትዮጵያ በሚያጋጥሟት ውስጣዊና ውጫዊ ፈተናዎች ሸብረክ ሳትል በፅናት መጓዝ መቻሏን የሚያረጋግጡ ህያው ምስክሮች ናቸው፤ ይህ የእመርታ ጉዟችን ለመጪው ዓመት የሰነቀው ተስፋ እጅግ ግዙፍ ነው!"

Address

Address, Adwa Street
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 08:30 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30
Thursday 08:30 - 17:00
Friday 08:30 - 17:30

Telephone

+251948748951

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Ministry of Industry posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Ethiopian Ministry of Industry:

Shortcuts

Share