Ministry of Mines - Ethiopia

Ministry of Mines - Ethiopia በማዕድንና ነዳጅ ዘርፍ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ለህዝብ ማስተዋወቅ

11/04/2026
መጭው የትንሳኤ በዓልን በማስመልከት   ማዕድ ማጋራት ተደረገ፡፡(መጋቢት 29 ቀን  2018፣ ማዕድን ሚኒስቴር)  ለማዕድን ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት ዝቅተኛ ደመወዝ ተከፋዮች  የትንሳኤ በ...
07/04/2026

መጭው የትንሳኤ በዓልን በማስመልከት ማዕድ ማጋራት ተደረገ፡፡
(መጋቢት 29 ቀን 2018፣ ማዕድን ሚኒስቴር) ለማዕድን ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት ዝቅተኛ ደመወዝ ተከፋዮች የትንሳኤ በዓልን በማስመልከት የማዕድ ማጋራት ተደረገ፡፡
የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለማዕድን ሚኒስቴር፣ ለኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት እና ለማዕድን ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ዝቅተኛ ደመወዝ ተከፋይ ሠራተኞች የማዕድ ማጋራት መርሐግብር ተካሂዷል፡፡
ለበለጠ መረጃ ማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችን በመከተል ይወዳጁን
Twitter፦ https://twitter.com/MinistryofMine_
Website ፦ www.mom.gov.et
Facebook፡- https://www.facebook.com/MinesandPetroleum/
Telegram: - https://t.me/+-aNetmkG-WY2YWM8

02/04/2026

#ፋና #ኢትዮጵያ

02/04/2026

#አንድጉዳይ #ፖድካስት #ፋናፖድካስት #እንግዳ #ፋናሚዲያኮርፖሬሽን #ፋና ሚዲያ ...

የኦፓል ማዕድን የግብይት አፈጻጸም ተገመገመ።(መጋቢት 19 ቀን 2018 ማዕድን ሚኒስቴር) የማዕድን ሚኒስቴር የኦፓል  የገበያ ግንባታ አፈጻጸም ያለበትን ደረጃ ከባለድርሻ አካላት ጋር ገመገመ...
28/03/2026

የኦፓል ማዕድን የግብይት አፈጻጸም ተገመገመ።
(መጋቢት 19 ቀን 2018 ማዕድን ሚኒስቴር) የማዕድን ሚኒስቴር የኦፓል የገበያ ግንባታ አፈጻጸም ያለበትን ደረጃ ከባለድርሻ አካላት ጋር ገመገመ፡፡
ግምገማው በከበሩ ማእድናት ዘርፍ ግብይትን በማዘመን ሀገር ማግኘት ያለባትን የውጪ ምንዛሪ ለማሳደግ እና የአምራቾችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው ፡፡ በውይይቱ የጌጣጌጥ ግብይትን ማዘመን አማራጭ የሌለው መሆኑ አጽንኦት ተሰጥቷል።

በግምገማው ላይ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ፣ የአማራ ክልል የማእድን ሀብት ልማት ቢሮና የወሎ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡ግብይቱን ለማዘመን የድርሻቸውን እንደሚወጡ ገልፀው በሚቀጥሉት ጥቂት ወራት ውስጥ የሚመለከታቸውን ቀሪ ስራዎችን በማጠናቀቅ ግብይቱን ለማስጀመር የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል። ለበለጠ መረጃ ማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችን በመከተል ይወዳጁን
Twitter፦ https://twitter.com/MinistryofMine_
Website ፦ www.mom.gov.et
Facebook፡- https://www.facebook.com/MinesandPetroleum/
Telegram: - https://t.me/+-aNetmkG-WY2YWM8

ኢ/ር ሃብታሙ ተገኘ ከአዘርባጃን የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን  ኤጀንሲ  ዋና ዳይሬክተር ዩሲፋ አብዱላየቭ ጋር  ተወያዩ፡፡ (መጋቢት 18 ቀን 2018 ማዕድን ሚኒስቴር) ኢ/ር ሃብታሙ ተገኘ ከአ...
27/03/2026

ኢ/ር ሃብታሙ ተገኘ ከአዘርባጃን የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዩሲፋ አብዱላየቭ ጋር ተወያዩ፡፡
(መጋቢት 18 ቀን 2018 ማዕድን ሚኒስቴር) ኢ/ር ሃብታሙ ተገኘ ከአዘርባጃን የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዩሲፋ አብዱላየቭ ጋር በማዕድን ዘርፍ ያሉ የኢንቨስትመንት ዕድሎች እና የሁለትዮሽ ትብብርን ለማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ውይይት አድርገዋል።
በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ.ር) የተመራ ልኡክ ባለፈው በአዘርባጃን ባካሄደው የስራ ጉብኝት ሁለቱ ሃገራት በኢኮኖሚ እና በተለያዩ መስኮች በጋራ ለመስራት መምከራቸው እና አቅጣጫዎች መቀመጣቸው ይታወቃል፡፡
የዛሬው ውይይትም በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በማዕድን ዘርፉ በጋራ ለመስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ ነው፡፡
Twitter፦ https://twitter.com/MinistryofMine_
Website ፦ www.mom.gov.et
Facebook፡- https://www.facebook.com/MinesandPetroleum/
Telegram: - https://t.me/+-aNetmkG-WY2YWM8

ባለፉት 8 ወራት ከማዕድን ዘርፉ ከ3.5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ፡፡(መጋቢት 18 ቀን 2018 ዓ.ም) የማዕድን ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት ባለፉት 8 ወራት በማዕድን ዘርፍ የተከናወኑ...
27/03/2026

ባለፉት 8 ወራት ከማዕድን ዘርፉ ከ3.5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ፡፡

(መጋቢት 18 ቀን 2018 ዓ.ም) የማዕድን ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት ባለፉት 8 ወራት በማዕድን ዘርፍ የተከናወኑ አፈጻጸሞችን በጋራ ገምግመዋል፡፡

ባለፉት 8 ወራት ከወርቅ፣ከጌጣጌጥ ማዕድናት እና ኢንዱስትሪ ማዕድናት ከ3.5 ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ ተገኝቷል፡፡ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በመጠን 27 በመቶ በገቢ ደግሞ 92 በመቶ ብልጫ ተመዝግቧል፡፡

በበጀት አመቱ የተለያዩ የማዕድን ፕሮጀክቶች ተመርቀው ወደ ስራ የገቡ ሲሆን በወጭ ንግድ እና በተኪ ምርቶች ላይም የተሻለ ውጤት ተመዝግቧል፡፡በቀጣይ ቀሪ ወራትም በሂደት ላይ ያሉ ሜጋ ፕሮጀክቶች ወደ ስራ እንዲገቡ አስፈላጊው ድጋፍ የሚደረግ ሲሆን እየተመዘገቡ ያሉትን ውጤቶች ለማስቀጠል በሚቻልባቸው የትኩረት መስኮች ላይ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡
ለበለጠ መረጃ ማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችን በመከተል ይወዳጁን
Twitter፦ https://twitter.com/MinistryofMine_
Website ፦ www.mom.gov.et
Facebook፡- https://www.facebook.com/MinesandPetroleum/
Telegram: - https://t.me/+-aNetmkG-WY2YWM8

የተቋሙን የተሻለ አሰራር ለማረጋገጥ እየተሰሩ ያሉ የፕሮጀት ስራዎች ተገመገሙ፡፡(መጋቢት 16 ቀን 2018 ዓ.ም ማዕድን ሚኒስቴር) የማዕድን ሚኒስቴር ተቋሙን የበለጠ ለማዘመን ከአዲስ አበባ ...
25/03/2026

የተቋሙን የተሻለ አሰራር ለማረጋገጥ እየተሰሩ ያሉ የፕሮጀት ስራዎች ተገመገሙ፡፡
(መጋቢት 16 ቀን 2018 ዓ.ም ማዕድን ሚኒስቴር) የማዕድን ሚኒስቴር ተቋሙን የበለጠ ለማዘመን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር እየተሰሩ ያሉ የፕሮጀክት ስራዎችን ገምግሟል፡፡
የማዕድን ሚኒስቴር በዲጂታላይዜሽን፣ በፖሊሲ እና በህግ አገልግሎት ያሉ የተቋሙን አሰራሮች ለማዘመን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር የፕሮጀክት ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡ የተጀመሩት የፕሮጀክት ስራዎች ተቋሙን ዲጂታላይዝ ለማድረግ እና ለማዘምን የሚያስችሉ ናቸው፡፡
ፕሮጀክቶቹን በአጭር ጊዜ በማጠናቀቅ በተቋሙ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ወደተሻለ አሰራር ለማሸጋገር የሚያስችል መሆኑ በግምገማው ተነስቷል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ
Twitter፦ https://twitter.com/MinistryofMine_
Website፦ www.mom.gov.et
Facebook፡- https://www.facebook.com/MinesandPetroleum/
Telegram: - https://t.me/+-aNetmkG-WY2YWM8
Email: [email protected]

ኢንጅነር ሃብታሙ ተገኘ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ጋር ተወያዩ፡፡(መጋቢት 15 ቀን 2018) ኢንጅነር ሃብታሙ ተገኘ  በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ጋር...
24/03/2026

ኢንጅነር ሃብታሙ ተገኘ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ጋር ተወያዩ፡፡
(መጋቢት 15 ቀን 2018) ኢንጅነር ሃብታሙ ተገኘ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ጋር ተወያዩ፡፡ ውይይቱ በማዕድን ዘርፍ ያሉ የኢንቨስትመንት እድሎችን እና የትብብር መስኮች ዙሪያ ያተኮረ ነው፡፡ ይህም በማዕድን ዘርፍ የሚገኙ አዳዲስ እድሎችን ለመጠቀም አስፈላጊ መሠረት እንደሚፈጥር ተጠቁሟል።
ለተጨማሪ መረጃ
Twitter፦ https://twitter.com/MinistryofMine_
Website፦ www.mom.gov.et
Facebook፡- https://www.facebook.com/MinesandPetroleum/
Telegram: - https://t.me/+-aNetmkG-WY2YWM8
Email: [email protected]

የማዕድን ፕሮጀክቶችን በአጭር ጊዜ ማጠናቀቅ የስራ ባህልን የቀየረ መሆኑ ተገለጸ ፡፡ (መጋቢት 14 ቀን 2018 ዓ.ም ማዕድን ሚኒስቴር) የኢንዱስትሪ እና ማዕድን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ...
23/03/2026

የማዕድን ፕሮጀክቶችን በአጭር ጊዜ ማጠናቀቅ የስራ ባህልን የቀየረ መሆኑ ተገለጸ ፡፡
(መጋቢት 14 ቀን 2018 ዓ.ም ማዕድን ሚኒስቴር) የኢንዱስትሪ እና ማዕድን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት የባይጃ ሴራሚክ ፋብሪካን የግንባታ ሂደት ጎበኙ፡፡ የፋብሪካው ግንባታ ሂደት በአጭር ጊዜ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱ የስራ ባህልን የቀየረ መሆኑን የቋሚ ኮሚቴው አባላት ተናግረዋል፡፡
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ ኢንዱስትሪ እና ማዕድን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት የባይጃ ሴራሚክስ የግንባታ ሂደትን ጎብኝተዋል፡፡ ፋብሪካው የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባውን በአጭር ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ ወደ ምርት ለመግባት በሚችልበት ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡
የፋብሪካው መገንባት ከውጭ ሲገባ የነበረውን ምርት ሙሉ በሙሉ በሃገር ውስጥ ለመተካት ከሚያስችሉ ፕሮጅክቶች አንዱ ነው፡፡ የሃገርን ሃብት ለሃገር ለመጠቀም የሚያስችል ፋብሪካ በመሆኑ አባላቱ ድጋፋቸውን እንደሚያደርጉም ገልጸዋል፡፡
የማዕድን እና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሰቢ የተከበሩ ፍቃዱ መንግስቱ(ዶ.ር) መንግስት ለማዕድን ከፍተኛ ትኩረት የሰጠበት መሆኑን ገልጸው ሚኒስር መስሪያቤቱም በተኪ ምርቶች ላይ በልዩ ትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ በድጋፋቸው መመልከታቸውን ተናግረዋል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ
Twitter፦ https://twitter.com/MinistryofMine_
Website፦ www.mom.gov.et
Facebook፡- https://www.facebook.com/MinesandPetroleum/
Telegram: - https://t.me/+-aNetmkG-WY2YWM8
Email: [email protected]

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በሠላም አደረሳችሁ!!
19/03/2026

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በሠላም አደረሳችሁ!!

Address

0116675480
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 08:30 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30
Thursday 08:30 - 15:30
Friday 08:30 - 17:30

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ministry of Mines - Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Ministry of Mines - Ethiopia:

Share