New Code Enforcement

New Code Enforcement organized Addis Ababa since 2005 E.C

13/01/2026
13/01/2026
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ነዋሪዎችና አመራሮች የህዳሴ ግድቡ መጠናቀቁን አስመልክቶ በመስቀል አደባባይ እየተካሄደ ባለው የምስጋናና የድጋፍ ሰልፍ  እየተሳተፉ ይገኛሉ!!
14/09/2025

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ነዋሪዎችና አመራሮች የህዳሴ ግድቡ መጠናቀቁን አስመልክቶ በመስቀል አደባባይ እየተካሄደ ባለው የምስጋናና የድጋፍ ሰልፍ እየተሳተፉ ይገኛሉ!!



ፕረስ ሪሊዝየጳጉሜ 2 የህብር ቀንን በማስመልከት ለ50ሺህ ዜጎች ማዕድ ይጋራል::****************ጳጉሜ 1-2017ዓምበአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የጳጉሜ 2 የህብር ቀንን በማስመልከት ለ5...
06/09/2025

ፕረስ ሪሊዝ
የጳጉሜ 2 የህብር ቀንን በማስመልከት ለ50ሺህ ዜጎች ማዕድ ይጋራል::
****************
ጳጉሜ 1-2017ዓም
በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የጳጉሜ 2 የህብር ቀንን በማስመልከት ለ50ሺህ ድጋፍ ፈላጊ ዜጎች ማዕድ የሚያጋራ መሆኑን የክፍለ ከተማው ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበያ ጽ/ቤት ሃላፊ ወ/ሪት ሃብታሟ ቡልቻ አስታውቀዋል::

ለዘመናት የቆየው የመረዳዳትና የመተጋገዝ ኢትዮጵያዊ ባህላችን ተጠናክሮ እንዲቀጥል እየተሰራ መሆኑን የገለፁት ሃላፊዋ በነገው ፕሮግራም በፀጥታ ማስከበር ለተሰማሩ የፀጥታ አስከባሪ አካላት የበሬ ስጦታ የሚበረከት መሆኑን ገልፀዋል::


የጳጉሜ 1 የጽናት ቀንን ምክንያት በማድረግ "ፅኑ መሠረት ብርቱ ሀገር " በሚል መሪ ቃል የፓናል ውይይት ተካሄደ::****************የጳጉሜ 1-2017ዓ/ምየአዲስ ከተማ ክ/ከተማ አስ...
06/09/2025

የጳጉሜ 1 የጽናት ቀንን ምክንያት በማድረግ "ፅኑ መሠረት ብርቱ ሀገር " በሚል መሪ ቃል የፓናል ውይይት ተካሄደ::
****************
የጳጉሜ 1-2017ዓ/ም

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ አስተዳር "ፅኑ መሠረት ብርቱ ሀገር " በሚል መሪ ቃል የፅናት ቀንን የክፍለ ከተማው አስተባባሪ ኮሚቴዎች፣ አመራሮች፣ የፌደራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት፣ የደንብ ማስከበር አባላት እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው ህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበ ውይይት አካሂዷል ።

መድረኩን የመሩት የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ታረቀኝ ወርቅነህ እንዳሉት "ፅኑ መሠረት ብርቱ ሀገር " ስንል ከተማችንን ብሎም ክፍለ ከተማችንን ሰላሟ በአስተማማኝ ሁኔታ እንዲጠበቅ ሁሉም የፀጥታ አካላት የሀገር ወዳድነት በአርበኝነት ስሜት የሚጠብቅበትን ኃላፊነት በታማኝነት በማገልገል ሰላምን ማፅናት አለበት ሲሉ ተናግረዋል::

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘሪሁን ኮርሜ በበኩላቸው የዛሬዋን ቀን ፅናት ስንል ሀገራችን ከበርካታ ፈተናዎች አያቶቻችን በትልቅ ተጋድሎ ጀብድ በመሥራ አፅንተው ለዚህ ትውልድ አስተላልፈዋል፤ እኛም የአባት አያቶቻችንን ፈለግ በመከተል የሀገራችንን ሁለንተናዊ እድገት ብልፅግና ለመጎናፀፍ የተያዘውን የለውጥ ጉዞ ማስቀጠልና ማፅናት ይገባል ሲሉ ገለጸዋል::

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር ጥበቡ ደጀኔ በበኩላቸው እለቱን አስመልክቶ ስለሀገር ወዳድነትና ዘመኑን የዋጀ አርበኝነት ሰላማችንን እንዴት አድርገን ማፅናትና ማስቀጠል ለከተማች ብሎም ለክፍለ ከተማችን አስተማማኝ ሰላም እንዲሰፍን ትልቅ ተጋድሎ ማድረግ የሚጠበቅብን መሆኑን በተዘጋጀው አጭር ሰነድ ለተሳታፊዎች አቅርበዋል::

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የቀረበውን የመወያያ ሰነድ መሠረት አድርገው የሰላም ማፅናት ሥራ ሥምሪትን በአስተማማኝ ሁኔታ የክፍለ ከተማውንና አካባቢውን ከህብረተሰቡ ጋር እጅና ጓንት በመሆን በጋራ የሚሠሩ መሆኑን ገልፀዋል::

06/09/2025
የጳጉሜ 1 'የጽናት ቀን' በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል፡፡****************ጳጉሜ 1/13/2017 ዓ.ም (አዲስ ደንብ )"ጽኑ መሰረት ብርቱ ሀገር" በ...
06/09/2025

የጳጉሜ 1 'የጽናት ቀን' በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል፡፡
****************
ጳጉሜ 1/13/2017 ዓ.ም (አዲስ ደንብ )
"ጽኑ መሰረት ብርቱ ሀገር" በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ባለው 'የጽናት ቀን' የክፍለ ከተማው አስተባባሪ ኮሜዎቴዎች፣ አመራሮች፣ የፌደራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት፣ የደንብ ማስከበር አባላት እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው ህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት በድምቀት ተከብሯል፡፡

ኢትዮጵያ የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ተምሳሌት ናት ያሉት የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ታረቀኝ ወርቅነህ ሃገራችንን በፅኑ መሰረት ላይ ለማስቀመጥ የተከፈሉ መስዋትዕነቶችን በማስታወስ ቀኑን እያከበርን እንገኛለን ብለዋል፡፡

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ምክር ቤት ዋና አፈጉባኡ አቶ በቀለ ጉታ በበኩላቸው የሃገራችን ኢትዮጵያ የህዳሴ ጉዞ ለመላው አፍሪካም ሆነ ለዓለም ህዝቦች የጽናት ተምሳሌት ያደርጋታል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን ወደ መልካም እድል በመቀየር በጠንካራ መንፈስ ፀንታ የቆመች ሀገር ናት ያሉት የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ሃላፊ አቶ ዘሪሁን ኮርሜ መንግስታችን ለቀጣዩ ትውልድ ብሩህ ተስፋ ያለው የወደፊት ጊዜ ለመገንባት እየተጋ ይገኛል ብለዋል፡፡

በፕሮግራሙ በማርሽ ባንድ የታጀበ የሰንደቃላማ መስቀል ስነስርዓት የተካሄደ ሲሆን እለቱ በተለያዩ ዝግጅቶች መከበሩን ቀጥሏል፡፡
*************
መረጃን ከምንጭ በተለያየ አማራጭ
***************

ህገወጥ እርድ በፈፀመ እና ህገወጥ ንግድ ላይ በተሰማራው ግለሰብ ላይ ህጋዊ እርምጃ ተወሰደ*********23/12/2017 (አዲስ ደንብ )*****************በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ...
29/08/2025

ህገወጥ እርድ በፈፀመ እና ህገወጥ ንግድ ላይ በተሰማራው ግለሰብ ላይ ህጋዊ እርምጃ ተወሰደ

*********
23/12/2017 (አዲስ ደንብ )
*****************

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ቀጠና 2 ልዩ ቦታ ሎዛ ማርያም አከባቢ በቀን 23/12/2017 ከጠዋት 12:00 ሰዓት ላይ በህረተሰቡ ጥቆማ ህገወጥ እርድ በመፈፀም እና ህገወጥ ንግድ ላይ በተሰማራው ግለሰብ ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰድን የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ዳኜ ወርቁ ገለፁ።

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት በተደጋጋሚ ጊዜ በህገወጥ መንገድ እርድ የሚፈፅሙ ግለሰቦች ላይ ግንዛቤ በመፍጠርና ከህገወጥ ተግባራቸው እንዲመለሱ ማስጠንቀቂያ ቢሰጣቸውም ከችግር ውስጥ ባለመውጣቱ በአቶ ያዕቆብ ወዳጄ በተባለ ግለሰብ ላይ ህጋዊ እርምጃ ተወስዷል።

የጽ/ቤት ኃላፊ እንደገለፀው የእንስሳት ሀኪም ምርመራ ሳያደርጉ ህገወጥ እርድ በሚፈፅሙ ግለሰቡ ላይ እርምጃ በመውሰድ የህብረተሰቡን ጤና ለመጠበቅ ዝግጅ መሆኑን አሳስቧል ።

በዚህ 9 ሙሉ በሙሉ የተገፈፉ በጎችና 5 ያልታረዱ በጎችን በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ በማድረግ እና 15,000 ብር ደረሰኝ በመቁረጥ ይህን ተግባር ሲያደርግ የነበረውን ግለሰብ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የማሸግና በህግም ተጠያቂ በማድረግ የታረዱ በጎችንም ማስወገድ ተችሏል።

በመጨረሻም ህብረተሰቡ ህገወጥ ተግባራትን ሲመለከት ለፀጥታ አካላት በመጠቆም የተለመደ ትብብራቸሁን እንድታደርጉልን ሲል የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 13 ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዳኜ ወርቁ አስታውቀዋል።

በማጠቃለያቸውም ለዚህ ስራ ለተሳተፉ የግብረ ሀይል አባላት እና ለአመራሮች ምስጋና አቅርቧል።

ህገወጥነትን በጋራ እንከላከል!!

በቀጣይ በከተማችን አዲስ አበባ እና በክፍለ ከተማችን የሚከናወኑ የተለያዩ ኩነቶች፣ ኃይማኖታዊና ህዝባዊ በዓላት ያለ ምንም የጸጥታ ችግር እንዲከናወኑ ዝግጅቱን አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን የአ...
29/08/2025

በቀጣይ በከተማችን አዲስ አበባ እና በክፍለ ከተማችን የሚከናወኑ የተለያዩ ኩነቶች፣ ኃይማኖታዊና ህዝባዊ በዓላት ያለ ምንም የጸጥታ ችግር እንዲከናወኑ ዝግጅቱን አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ሃላፊ እና አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ድንብ ማስከበር ጽ/ቤት ሃላፊ አስተዋወቁ ።

ነሐሴ 22/12/2017 ዓ/ም (አዲስ ደንብ)፦

የሀገራችንን የከተማችንን ብሎም የክፍለ ከተማችንን ሠላም፣ደህንነት እና ህገወጥ ተግባራትን ለማረጋገጥ በጋራ ባከናወነው ጠንካራ ህግን የማስከበር ተግባር ውጤት ተመዝግቧል።

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ከመርካቶ ፖሊስ ጣቢያ ፣ከፌደራል ፖሊስ ከደንብ ማስከበር ኦፊሰር ጋር በጋራ በመሆን በመርካቶ ዙሪያ ከቀኑ 8:00 ሰዓት እሰከ ቀኑ 11:00 ሰዓት ድረሰ በሁለት አቅጣጫ በአዋኪ ተግባር ተጋላጭ የሆኑና እና የወንጀል ሰጋት የሆኑ ቀጠናዎች ላይ የአሰሳ ስራ በመስራት ወረዳ 01 ልዩ ቦታው አሜሪካን ግቢ ውሰጥ ከቀኑ 9:00 ሰዓት ሲሆን የወንጀል መንሰኤ ሺሻ እና አደንዛዥ እፅ በፍተሻ የተገኙ ናቸው። በዝርዝር በተመለከተ:-23 የሺሻ ጠርሙሰ፣23 ገመድ፣24 ቡሬ፣10 ዘንግ፣4 መቆንጠጫ፣3ላሰትሮ ፕላሰተር፣አዲሱ የመከላኪያ የደንብ ልብሰ ሸሚዝ፣ የሰላም ሰራዊት ፒፒሰ እና የበጎ ፍቃደኛ ፒፒሰ ናቸው

የከተማችንን ሠላም፣ ደህንነት ህገወጥነት ለማረጋገጥ ባለፈው ሁለት ወር ከተከናወኑት ተግባራት መልካም ተሞክሮን በመቅሰም በቀጣይ አንድ ወር በከተማዋ የሚከናወኑ ኃይማኖታዊ፣ ህዝባዊና ብሔራዊ በዓላትን ጨምሮ የተለያዩ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ኩነቶች እንዲሁም በቅርቡ የሚከናወኑ የጳጉሜ ቀናት መርሀ ግብሮች፣ የአዲስ ዓመት እንዲሁም የእሬቻና የመስቀል በዓላትን በማስመልከት የሚከናወኑ ፀጥታን የማስከበርና ሠላምን የማስጠበቅ ተግባራትን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።

የከተማችንን ሠላምና ፀጥታን በዘላቂነት ለማስቀጠል የሚከናወኑ ጠንካራ ህግን የማስከበር ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ እና የህብረተሰቡን ተባባሪነት በተጠናከረ መልኩ መጠቀም እንደሚገባ የተገለጸ ሲሆን የመንግስት ሠራተኞችን ኑሮ ለመደጎም ታስቦ የሚደረገውን የደሞዝ ጭማሪ ምክንያት በማድረግ በአንዳንድ ህገ ወጥ ነጋዴዎች የሚስተዋሉ ሸቀጦችን የመሸሸግና የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉና የተለያየ ህገወጥ ተግባር ለመፈፀም በሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች ላይ የማያዳግም እርምጃ የሚወሰድ ሲሆን ማንኛውንም ዓይነት አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙም በ991ነጻ የፖሊስ የመረጃ ስልክ እንዲሁም በ9995 ነፃ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ላይ መረጃ መስጠት እንደሚገባም አሳስቧል።

“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
``ህገወጥን በጋራ እንከላከል''

Address

Addis Ababa
Addis Abeba

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when New Code Enforcement posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share