Lideta woreda 7 Communication Office

Lideta woreda 7 Communication Office ይህ የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ኮሙኒኬሽን ፔጅ ነው!!!
ፈጣን መረጃ እንዲደርስዎ ላይክ, ሼር ያድርጉ ለሌሎች ያጋሩ

ህፃናትን ለማሳደግ ምርጧ ከተማ አዲስ አበባ- የዓለም አቀፍ ሽልማቶች ሚስጥርአዲስ አበባ ያሸነፈቻቸው የዓለም አቀፍ ሽልማት ዋነኛ ሚስጥር የሚገኘው ከመሠረተ ልማትና ውጤታማ  ስራዎች ብቻ ሳይ...
04/09/2026

ህፃናትን ለማሳደግ ምርጧ ከተማ አዲስ አበባ- የዓለም አቀፍ ሽልማቶች ሚስጥር

አዲስ አበባ ያሸነፈቻቸው የዓለም አቀፍ ሽልማት ዋነኛ ሚስጥር የሚገኘው ከመሠረተ ልማትና ውጤታማ ስራዎች ብቻ ሳይሆን፣ ህፃናትን ለማሳደግ ምርጧ ከተማ ለማድረግ አጠቃላይ የሁለንተናዊ ብልፅግና ጉዞ ማዕከል በሆነው የሰብዓዊ ልማት እና ትውልድን በማነጽ ላይ በሰራችው ስር ነቀል ለውጥ ጭምር ነው።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ “የቀዳማይ ልጅነት ልማት ፕሮግራም”ን በብቃት በመምራታቸው በዓለም አቀፉ “አክት ፎር ኤርሊ ይርስ” (Act For Early Years) ኢኒሼቲቭ “የቅድመ ልጅነት ዕድገት ሻምፒዮን” ተብለው ተሸልመዋል። ይህ ትልቅ እውቅና ከተማዋን ለህፃናት የምትመች ከተማ እና ህፃናትን ለማሳደግ ምርጧ የአፍሪካ መዲና ለማድረግ የሰነቀችውን ራዕይ የሚያንፀባርቅ፣ እንዲሁም ለትውልድ ግንባታ የሚደረገው ኢንቨስትመንት ያመጣውን ለውጥ በጉልህ የሚያሳይ ነው።

የዚህ ስኬት እና የከተማዋ አስደናቂ እድገት ማሳያ የሆነው ከቁጥር በላይ የሆነው መረጃ የመጫወቻ ስፍራዎች እና የሕፃናት ማቆያዎች መስፋፋት ነው። 20 የመጫወቻ ስፍራዎች ብቻ የተነሳው የከተማዋ አስተዳደር በሦስት ዓመታት ውስጥ ብቻ 5 ሺህ 500 ማድረስ ችሏል። በሌላ በኩል 5 ሺህ 3 የሚሆኑት የልጆችን የዕድገት ደረጃና ሥርዓት ታሳቢ ያደረጉ የመጫወቻ ቦታዎችም ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ። በተጨማሪም የሕዝብ የሕፃናት ማቆያዎች ከ11 ብቻ ተነስተው በአሁኑ ሰዓት 1 ሺህ 100 ደርሰዋል። ይህ በተለያዩ ሞዴሎች የተደራጀው የማቆያ ቁጥር በጥቅሉ 1 ሺህ 155 የደረሰ ሲሆን፣ 27 ሺህ 302 ሕፃናት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ሆነዋል።

ይህ ስኬታማ የቀዳማይ ልጅነት ልማት ፕሮግራም በመዲናችን የሚገኙ 1.3 ሚሊዮን ገደማ ሕፃናትን፣ በተለይም 330 ሺህ አነስተኛ ገቢ ያላቸውን ታዳጊዎች ተደራሽ ለማድረግ ያለሙ አምስት አንኳር ጉዳዮችን ያካተተ ነው።

አዲስ አበባ ዛሬ አለምን ያስገረመችው እና የትኩረት ማዕከል የሆነችው በውብ የኮሪደር ልማቷ፣ በወንዝ ዳርቻዎቿ ውበት፣ ወይም በሌሎች ፕሮጀክቶቿ ብቻ አይደለም። ብሩህ አእምሮ ያለው ጤናማ ትውልድ በማፍራት፣ ህፃናትን ለማሳደግ ምርጧ ከተማ መሆኗን በተግባር በማሳየትና የዜጎችን በተለይም የሕፃናትን ሕይወት በሚቀይር የሰብዓዊ ልማት ሥራዋ ጭምር ነው። ይህ በሰብዓዊነት እና በትውልድ ላይ የተደረገው ጥልቅ ኢንቨስትመንት የመንግስትን የመደመር እሳቤ መሬት ያወረደ፣ ዜጎችን በአንድነት አስተባብሮ ከተማዋን እውነተኛ የብልፅግና ተምሳሌት ያደረጋት ሲሆን፣ ተደጋጋሚ ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን እንድትቀዳጅ ያስቻላት ዋነኛ ሚስጥርም ይኸው ነው።

🍂በልደታ ክፍለ ከተማ የአዲስ ዓመት በዓል ባዛርና ኤግዚቢሽን ተከፈተ መጪውን የ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት በዓል አስመልክቶ በልደታ ክፍለ ከተማ የተዘጋጀው የበዓል ባዛርና ኤግዚቢሽን ዛሬ በይ...
03/09/2026

🍂በልደታ ክፍለ ከተማ የአዲስ ዓመት በዓል ባዛርና ኤግዚቢሽን ተከፈተ

መጪውን የ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት በዓል አስመልክቶ በልደታ ክፍለ ከተማ የተዘጋጀው የበዓል ባዛርና ኤግዚቢሽን ዛሬ በይፋ ተከፍቷል።

በመክፈቻው ሥነ-ሥርዓት ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረት ሥራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ወ/ሮ ሽታዬ መሐመድ፣ ለመላው የከተማዋ ነዋሪዎች የአዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ኮሚሽነሯ በ11 ክፍለ ከተሞች የበዓል ባዛሮች በይፋ መከፈታቸውን ገልጸው፣ ሸማቾች ከትራንስፖርት እንግልት ነፃ በሆነ መልኩ በየአቅራቢያቸው ከሚገኙ የሸማቾች ሱቆችና የባዛር ማዕከላት መሰረታዊ የግብርናና የኢንዱስትሪ ፍጆታ ምርቶችን በበቂ መጠን ማግኘት እንደሚችሉ አስታውቀዋል።

የልደታ ክፍለ ከተማ ምክትል ሥራ አስፈጻሚና የሥራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አዳሙ በዛብህ በበኩላቸው፣ ነዋሪዎች አዲሱን ዓመት ሲቀበሉ እንደ አቅማቸው ጥራት ያለውን ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲገዙ ታስቦ በክፍለ ከተማው በ15 አካባቢዎች የበዓል ባዛር መዘጋጀቱን ገልጸዋል።

ባዛሩ ከነሐሴ 28 እስከ ጳጉሜ 5 ቀን ድረስ ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ የገለጹት አቶ አዳሙ፣ ነዋሪዎች በተዘጋጁት የግብይት ስፍራዎች በመገኘት ግብይታቸውን እንዲፈጽሙ ጥሪ አቅርበዋል።

የክፍለ ከተማው የንግድ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ተስፋነሽ ጋሻው፣ የበዓል ባዛሩ ዋና ዓላማ በበዓል ወቅት ሊከሰት የሚችለውን የኑሮ ውድነትና የገበያ ጫና ለማቃለል መሆኑን ገልጸዋል።

በባዛሩ መሰረታዊ የግብርናና የኢንዱስትሪ ፍጆታ ምርቶች በጥራት፣ በብዛትና በተመጣጣኝ ዋጋ ለሸማቾች መቅረባቸውን ወ/ሮ ተስፋነሽ አስታውቀዋል።

በባዛሩ ይፋዊ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት የከተማ፣ የክፍለ ከተማና የወረዳ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ ነጋዴዎች፣ የነጋዴ ማኅበራት ተወካዮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
https://linktr.ee/worda7communication

በሀገራችን የመጀመሪያውን የተለየ የቤት መግዣ ብድር መልሶ ማጠናከሪያ ኩባንያ ለማቋቋም የሚያስችለውን ታሪካዊ የትብብር ማዕቀፍ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬ...
03/09/2026

በሀገራችን የመጀመሪያውን የተለየ የቤት መግዣ ብድር መልሶ ማጠናከሪያ ኩባንያ ለማቋቋም የሚያስችለውን ታሪካዊ የትብብር ማዕቀፍ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) መካከል ስምምነት ዛሬ አከናውነናል።

‎በ100 ቢሊዮን የኢትዮጵያ ብር ካፒታል የተቋቋመው እና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ደግሞ 200 ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ አስተዋፅኦ የሚያደርግበት ይህ ተቋም፤ በባንክ ዘርፋችን ውስጥ የጥሬ ገንዘብ ፍሰት አለመመጣጠንን የሚቀርፍ እና በመላው ኢትዮጵያ ተደራሽ የሚሆን የቤት መግዣ ብድር ፋይናንስን የሚያስገኝ ይሆናል።

‎ይህ አጋርነት በተመጣጣኝ ዋጋ የሚገነቡና የኢትዮጵያውያንን ክብር የጠበቁ 1.5 ሚሊዮን ቤቶችን ለማቅረብ እንዲሁም በፋይናንስ ሥርዓታችን ውስጥ የግል ዘርፉን ተሳትፎ ለማስፋት ያስቀመጥነውን ግብ የሚያሳካ ወሳኝ እርምጃ ነው።
‎ኢትዮጵያ ፈጣን፣ ጠንካራ እና ሁሉንም ያካተተ ኢኮኖሚ መገንባቷን ትቀጥላለች።

Today, I oversaw the signing of a landmark Framework for Cooperation between the National Bank of Ethiopia and the IFC to establish our country’s first dedicated Mortgage Refinance Company.

Capitalized at 100 Billion ETB, with the IFC set to contribute a minimum of $200 million, this wholesale institution will resolve long-standing liquidity mismatches in our banking sector and unlock accessible mortgage financing across Ethiopia.

This partnership is a critical step toward realizing our goal of delivering 1.5 million affordable, dignified homes for Ethiopian families while expanding private-sector participation in our financial system. Ethiopia continues to build a modern, resilient, and inclusive economy.

በልደታ ክ/ከተማ በከተማ ምግብ ዋስትና መርሃ ግብር በአካባቢ ልማት ሥራዎች ተሰማርተው የነበሩ ዜጎች ወደ ዘላቂ የኑሮ ማሻሻያ ተሸጋግረው በመረጡት የሥራ ዘርፍ በመሰማራት ማህበራዊና ኢኮኖሚያ...
03/09/2026

በልደታ ክ/ከተማ በከተማ ምግብ ዋስትና መርሃ ግብር በአካባቢ ልማት ሥራዎች ተሰማርተው የነበሩ ዜጎች ወደ ዘላቂ የኑሮ ማሻሻያ ተሸጋግረው በመረጡት የሥራ ዘርፍ በመሰማራት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ እየሆኑ መሆኑ ተገለጸ።

ተጠቃሚዎቹ ከመርሃ ግብሩ የተለቀቀላቸውን የግራንት ድጋፍና በቆጠቡት ገንዘብ በመጠቀም በመረጡት የሙያ ዘርፍ በመሰማራት የገቢ ምንጫቸውን ማሳደግ መቻላቸውን ገልጸዋል።

በመርሃ ግብሩ ተጠቃሚ ለሆኑ ዜጎች የሕይወት ክህሎት፣ የሂሳብ አያያዝና በመረጡት የሥራ ዘርፍ ላይ የሙያ ሥልጠና መሰጠቱም ተመላክቷል።

ይህም ዜጎች ከጊዜያዊ የድጋፍ ተጠቃሚነት በመሻገር በራሳቸው ጥረትና በተሰጣቸው ድጋፍ ዘላቂ የገቢ ምንጭ እንዲፈጥሩ እና የኑሮ ደረጃቸውን እንዲያሻሽሉ አድርጓል ተብሏል።

በከተማ ምግብ ዋስትና ሥራዎች ዜጎችን ወደ ዘላቂ የኑሮ ማሻሻያና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የማሸጋገር ስራ በትኩረት እየተሠራ መሆኑ ተጠቁሟል።
https://linktr.ee/worda7communication

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዓለም አቀፉ Act For Early Years  ኢኒሼቲቭ “የቅድመ ልጅነት እድገት ሻምፒዮን” ተብለው እውቅና ተሰጣቸው።ይህ እውቅና የከንቲባ አዳነች አቤቤ አመራራቸውንና...
02/09/2026

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዓለም አቀፉ Act For Early Years ኢኒሼቲቭ “የቅድመ ልጅነት እድገት ሻምፒዮን” ተብለው እውቅና ተሰጣቸው።

ይህ እውቅና የከንቲባ አዳነች አቤቤ አመራራቸውንና የከተማ አስተዳደሩ ለሕፃናት እድገት እያደረገ ያለውን ኢንቨስትመንት በተለይም በ"የአዲስ አበባ የወደፊት ተስፋ የቅድመ ልጅነት እድገት ተነሳሽነት" የተሰጠ እውቅና ነው።

ኢኒሼቲቩ ቀዳማይ ልጅነትን በመንግሥታት ፖሊሲዎች እና በዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንት አጀንዳ ማዕከል ላይ ለማስቀመጥ በትኩረት ይሰራል።

ይህ እውቅና የተሰጠው ከቀድሞው የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዓለም አቀፍ ትምህርት ልዩ መልዕክተኛ ጎርደን ብራውን በኩል የኢኒሼቲቭ አጋሮች በመወከል ሲሆን ፣ UNICEF እና UNESCOን ጨምሮ ከተለያዩ አጋር ተቋማት ጋር በመተባበር የተሰጠ ነው።

እውቅናው አዲስ አበባን በአፍሪካ የቀዳማይ ልጅነት እድገት የከተማ አመራር ተምሳሌት ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያጠናክረው ይታመናል።
https://linktr.ee/worda7communication

የጳጉሜን ወር አምስቱ ቀናት ስያሜዎችጳጉሜን 1 – “የእመርታ ቀን”ጳጉሜን 2 – “የማንሰራራት ቀን”ጳጉሜን 3 – “የጽናት ቀን”ጳጉሜን 4 – “የኅብር ቀን”ጳጉሜን 5 – “የነገ ቀን”
02/09/2026

የጳጉሜን ወር አምስቱ ቀናት ስያሜዎች

ጳጉሜን 1 – “የእመርታ ቀን”

ጳጉሜን 2 – “የማንሰራራት ቀን”

ጳጉሜን 3 – “የጽናት ቀን”

ጳጉሜን 4 – “የኅብር ቀን”

ጳጉሜን 5 – “የነገ ቀን”

ዛሬ 33ኛውን ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ “ብሩህ ነገን በዛሬ አዕምሮዎች” በሚል መሪ ቃል አስጀምረናል። ይህ ጉባኤ በየዓመቱ የምናካሂደው የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ፣ ተደራሽነትን ለማስ...
01/09/2026

ዛሬ 33ኛውን ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ “ብሩህ ነገን በዛሬ አዕምሮዎች” በሚል መሪ ቃል አስጀምረናል።

ይህ ጉባኤ በየዓመቱ የምናካሂደው የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ፣ ተደራሽነትን ለማስፋት፣ የመማር ማስተማር ሂደቱን ጤናማ እና ውጤታማ ለማድረግ፣ በዘርፉ የተሰሩትን ጠንካራ ስራዎች ልምድ የምንቀምርበት፣ የሚታረሙትንም ለይቶ በጋራ መፍትሄ የምንሰጥበትና በጋራ እቅጣጫ የምንይዝበት ጉባኤ ነው ።

የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በከተማ አስተዳደራችን በልዩ ትኩረት ሰርተን የተማሪዎች ውጤት እየተሻሻለ መጥቷል። ዛሬ በከተማችን የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ውጤት ወደ 33 በመቶ መሻሻል አሳይቷል። ነገር ግን አሁንም ከፍ ያለ ውጤት እንጠብቃለን፤ ገና ብዙ መሥራት ይጠበቅብናል።

መምህራን፤ ባለድረሻ አካላት በእልህ ሰርተን መፍጠር የሚችሉ፣ ችግር የሚፈቱ፣ በሥነ ምግባር የታነፁ፣ እውቀት የታጠቁ ተማሪዎችን በብዛት ለመፍጠር መረባረብ ይጠበቅብናል።

ከተማ አስተዳደራችን ዋናውን ኢንቨስትመንት ትምህርት ላይ እናውል ብለን፣ ትልቁን በጀት ለትምህርት ዘርፍ እንዲሆን አድርገናል። ትውልድ ላይ ከመሰረቱ መስራት ወሳኝ በመሆኑ፣ ዋና የእዕምሮ እድገት በጨቅላ ህፃንነት ወቅት በመሆኑ ቀዳማይ ልጅነት ላይ እየሰራን እንገኛለን። በዚህ አግባብ ከመሰረቱ ጀምረን እየሰራን በአንደኛ ደረጃ እንዲሁም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ ከፍተኛ ውጤት እና በዲሲፕሊን የታነፀ ትውልድ እንጠብቃለን።

እስካሁን በተገኘው ውጤት ሁላችሁንም ከልብ እያመሰገንኩ፤ በቀጣይም በእውቀት የበለፀጉ፣ በስነምግባር የታነፁ፣ አልቀው የሚሰሩ ተማሪዎች ለመፍጠር ከልብ፣ ዋጋ ከፍለን ተባብረን እንድንሰራ አደራ እላለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ
https://linktr.ee/worda7communication

🍂ዛሬ የከተማ አስተዳደራችንን የቀጣይ አምስት ዓመታት እና የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ውይይት  መላው የከተማችን አመራሮች በተገኙበት አስጀምረናል። በስድስተኛው ዙር ሀገራዊ ምርጫ ህዝባችን ...
30/08/2026

🍂ዛሬ የከተማ አስተዳደራችንን የቀጣይ አምስት ዓመታት እና የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ውይይት መላው የከተማችን አመራሮች በተገኙበት አስጀምረናል።

በስድስተኛው ዙር ሀገራዊ ምርጫ ህዝባችን የሰጠንን ሃላፊነት መነሻ ያደረገ ስትራቴጂክ እቅድ ነድፈን ቃላችንን በተግባር ቆጥረን ፈፅመን የከተማችንን ህዝብ ተጠቃሚ እንዲሆን እንዲሁም ከተማችን ደግሞ ተወዳዳሪ እንድትሆን አድርገናል።

ይህንኑ መነሻ በማድረግ የከተማችን ነዋሪ እምነት አድሮበት ዳግም መርጦን ሀላፊነት ሰጥቶናል።
የዛሬው ውይይትም የከተማችን ነዋሪ የጣለብንን እምነት እና የሰጠንን ሀላፊነት መነሻ ያደረገ፣ በቀጣይ አምስት ዓመታት እና የ2019 በጀት ዓመት የእቅድ ዝርዝር ግቦች ላይ ተወያይተን በማዳበር የባለፉት አምስት ዓመታት አፈፃፀምን በእጥፍ ለማሳደግ ዝግጁነታችንን የምናረጋግጥበት መድረክ ነው።

እነዚህን ዝርዝር ውይይቶች ስናደርግ 24/7 የመፈጸም ባህላችንን ይበልጥ በማሳደግ፣ አመራራችን ከፊት ሆኖ የበለጠ እየሮጠ ህዝባችንንና የልማት አጋሮቻችንን በማስተባበርና ተሞክሮዎችን በማስፋት በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት በሀገራዊ ማንሰራራት ውስጥ የአዲስ አበባን የብልፅግና ተምሳሌትነት ለማረጋገጥ እንተጋለን።

በተጨማሪም በክረምት የያዝናቸው የ90 ቀን ስራዎች ውስጥ የ60 ቀናት አፈፃፀማችንንም የምንገመግምበት የውይይት መድረክ ነው።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
https://linktr.ee/worda7communication

🍂739 ሚሊየን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙአዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2018 (ኤፍ ቢ ሲ) ከነሐሴ 14 እስከ 20 ቀን 2018 ዓ.ም በተደረገ ክትትል ከ739 ሚሊየ...
29/08/2026

🍂739 ሚሊየን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2018 (ኤፍ ቢ ሲ) ከነሐሴ 14 እስከ 20 ቀን 2018 ዓ.ም በተደረገ ክትትል ከ739 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተይዘዋል አለ የጉምሩክ ኮሚሽን ፡

የተያዙት እቃዎች አዳዲስና ልባሽ ጨርቆች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የግብርና ምርቶች፣ ጫት፣የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ የመዋቢያ እቃዎች፣ አደንዛዥ እጾች፣ መድኃኒት፣ ማዕድናት፣ ነዳጅና የውጭ ሀገር ገንዘቦች ናቸው፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች፣ በፌዴራል ፖሊስ፣ በክልል ፖሊስ አባላትና ሕብረተሰቡ ባደረጉት የጋራ ጥረት በፍተሻ፣ በጥቆማ እና ብርበራ ነው የተያዙት፡፡

የኮንትሮባንድ እቃዎቹን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 25 ተጠርጣሪዎች እና 17 ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውንም የኮሚሸኑ መረጃ አመልክቷል፡፡
https://linktr.ee/worda7communication

የልደታ ክ/ከተማ የ2019 በጀት ዓመት የፓርቲና የመንግስት ስራዎችን ዕቅድ የጋራ አደረገ የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የ2019 በጀት ዓመት የፓርቲና የመንግስት ስራዎችን በተቀናጀና በተና...
29/08/2026

የልደታ ክ/ከተማ የ2019 በጀት ዓመት የፓርቲና የመንግስት ስራዎችን ዕቅድ የጋራ አደረገ

የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የ2019 በጀት ዓመት የፓርቲና የመንግስት ስራዎችን በተቀናጀና በተናበበ መልኩ ለማከናወን ከክፍለ ከተማ እስከ ወረዳ ያሉ አመራሮች ጋር የዕቅድ ውይይት አካሂዷል።

በዕቅድ ውይይቱ የ2019 በጀት ዓመት በፓርቲና በመንግስት የሚከናወኑ ተግባራት በጋራ ተመልክተው የሚፈጸሙበት አቅጣጫ፣ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ የስራ መስኮችና የአፈጻጸም ሂደቶች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ በዕቅድ ውይይቱ ወቅት እንደገለፁት፣ በ2019 በጀት ዓመት የክፍለ ከተማውን ማህበረሰብ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት በላቀ ደረጃ ለማረጋገጥ የተደራጁና የተቀናጁ ተግባራት ይከናወናሉ ብለዋል።

በተለይም የኢንሼቲቭ ስራዎችን የበለጠ ማላቅ፣ የስራ ዕድል ፈጠራን ማስፋት፣ የኑሮ ውድነትን ለማርገብ ቀደም ሲል የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከር፣ የአገልግሎት አሰጣጥን በላቀ ደረጃ ማሻሻልና የዜጎችን እርካታ ማሳደግ በበጀት ዓመቱ ትኩረት ከሚሰጣቸው ዋና ዋና የስራ አቅጣጫዎች መካከል እንደሚገኙ ገልፀዋል።

በምግብ ራስን ለመቻል እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን በበለጠ ማጠናከር፣ የምርት አቅርቦትን ማሳደግ፣ የዜጎችን የኑሮ ጫና ለማቃለል በተቀናጀ መልኩ መስራት እንደሚገባም ዋና ስራ አስፈፃሚዋ አስገንዝበዋል።

የክፍለ ከተማው አመራር በሚያከናውናቸው ተግባራት የዜጎችን ተጠቃሚነት በቀጥታ ሊያሳድጉ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ ሊያተኩሩ እንደሚገባ ወ/ሮ ልዕልቲ ጠቁመው፣ ዜጎች የሚያነሷቸውን የመልካም አስተዳደር ችግሮች ደረጃ በደረጃ በመፍታት ዘላቂ ተጠቃሚነትንና እርካታን ለማረጋገጥ አስተዳደሩ በትኩረት እንደሚሰራም ገልፀዋል።

የክፍለ ከተማው የብልፅግና ፓርቲ ኃላፊ አቶ ዘመኑ ደሳለኝ በበኩላቸው፣ በ2019 በጀት ዓመት የፓርቲና የመንግስት ስራዎችን በተቀናጀና በተናበበ መልኩ በመስራት የዜጎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ስራ ይከናወናል በማለት ገልፀዋል።

አቶ ዘመኑ እንዳሉት፣ የፓርቲው ተግባራት ከመንግስት የልማትና የአገልግሎት ስራዎች ጋር በማቀናጀት በማኅበረሰቡ ዘንድ ተጨባጭ ለውጥ የሚያመጡ ስራዎችን በትኩረት ማከናወን ይገባል ብለዋል።

“ብልፅግና ፓርቲ የሚያከናውናቸውን ሰው ተኮር ተግባራት በላቀ ደረጃ በማከናወን ለዜጎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እፎይታን ለማረጋገጥ ከምንጊዜውም በላይ በትጋትና በቁርጠኝነት እንሰራለን” ሲሉም ገልፀዋል።

የክፍለ ከተማው ምክትል ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አዳሙ በዛብህ በበኩላቸው፣ በ2019 በጀት ዓመት የድህነት ቅነሳና የስራ ዕድል ፈጠራ ተግባራትን በላቀ ደረጃ በመተግበር የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊ አቅም ለማሳደግና ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ ይሰራል ብለዋል።

በተለይም በስራ ዕድል ፈጠራ ስራዎች ወጣቶችን፣ ሴቶችንና ሌሎች ስራ ፈላጊ ዜጎችን በማሳተፍ ወደ ተጨባጭ የገቢ ምንጭ ሊቀየሩ የሚችሉ ዕድሎችን ማስፋት ላይ ትኩረት እንደሚደረግ ጠቁመዋል።

ለዕቅዱ ስኬታማ አፈጻጸም ከክፍለ ከተማ እስከ ወረዳ ያሉ አመራሮች፣ ተቋማትና ማህበረሰቡ በተቀናጀ መልኩ የድርሻቸውን መወጣት እንደሚገባም ገልፀዋል።

በዕቅድ ውይይቱ በ2019 በጀት ዓመት በተለይም የስራ ዕድል ፈጠራን ማስፋት፣ የኑሮ ውድነትን ማርገብ፣ የምግብ ራስን መቻልን ማጠናከር፣ የአገልግሎት ጥራትን ማሻሻል፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታትና የዜጎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማሳደግ የበጀት ዓመቱ ዋና የትኩረት መስኮች እንደሚሆኑ ተገልጿል።

Address

Addis Abeba

Telephone

+251973027010

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Lideta woreda 7 Communication Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Lideta woreda 7 Communication Office:

Shortcuts

Share