KrIkose worda 07 prosperity party

KrIkose worda 07 prosperity party political party

13/01/2024
13/01/2024
11/01/2024

መደመር በለውጥ መንገድ ላይ የተወለደ የአተያይ ፓራዳይም ነው።

መደመር በለውጥ መንገድ ላይ የተወለደ የአተያይ ፓራዳይም ነው፤ ቁስሎች እንዲጠገኑ፣ ሕመሞች እንዲድኑ፣ ችግሮች እንዲፈቱ፣ ፈተናዎች እንዲታለፉ፣ ያለፈውን ጉዟችንን መመልከቻና የቀጣይ ጉዟችን ጠቋሚ፤ አዲስ የእሳቤ ማዕቀፍ ነው፡፡

ከመደመር ትውልድ መጽሀፍ ገጽ v የተወሰደ

ዶ/ር ብሩክ ከድርየቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ እንኳን ደህና መጣህ
03/09/2022

ዶ/ር ብሩክ ከድር
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ እንኳን ደህና መጣህ

የኢትዮጵያ መንግስት ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት ለማቆም ስለመወሰኑ የወጣ መግለጫየኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል ለሚገኙ የሰብዓዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦቱ የተሳ...
24/03/2022

የኢትዮጵያ መንግስት ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት ለማቆም ስለመወሰኑ የወጣ መግለጫ

የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል ለሚገኙ የሰብዓዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦቱ የተሳለጠ እንዲሆን የተለያዩ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ይገኛል። በዚህም መሰረት የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ እርዳታ የአየር በረራዎች ቁጥር እንዲጨምር እንዲሁም ለእርዳታ አቅራቢ ድርጅቶች የነዳጅ እና የጥሬ ገንዘብ የሚቀርብበትን ስርዓት የተሳለጠ እንዲሆን ተደርጓል። ከዚህ ጋር በተያያዘም የአለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ፣ የአለም ጤና ድርጅት እና የአውሮፓ ህብረት የሰብዓዊ እርዳታዎችን ማደረስ እንዲችሉ የአየር በረራ ተመቻችቷል።ከዚህ በተጨማሪም የኢትዮጵያ መንግስት በአብአላ-መቀሌ የየብስ ትራንስፖርት መስመር በኩል የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት መድረስ እንዲችል አስፈላጊውን ሁሉ እያደረገ ይገኛል።

ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት በሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ክልል ነዋሪዎች የሰብዓዊ እርዳታን ፍለጋ ወደአጎራባች ክልሎች እየተጓዙ መሆኑ እየተስተዋለ ነው። በዚህም በትግራይ አጎራባች ክልሎች የሚኖሩ ዜጎች ከትግራይ ክልል የሚመጡ የሰብዓዊ እርዳታ ፈላጊ ዜጎችን ተቀብሎ በማስተናገድ እያሳዩ ያለው በጎ ተግባር በህዝቦች መካከል ያለውን የወንድማማችነት እና የአንድነት መንፈስ የሚያሳይ ነው። መንግስት እነዚህ ዜጎች የሰብዓዊ እርዳታው ከቀያቸው ሳፈናቀሉ ባሉበት እንዲርሳቸው ቢደረግ እንግልታቸውን እንድሚቀንስ በጽኑ ያምናል።

በመሆኑም መንግስት በከፍተኛ ችግር ውስጥ የሚገኙ ዜጎቹን ችግር በአፋጣኝ የመፍታት ኃላፊነቱ ከምንም ነገር በላይ ቅድሚያ የሚሰጠው መሆኑን በመረዳት የአስቸኳይ የሰብዓዊ አቅርቦቶች ወደትግራይ ክልል በበቂ ሁኔታ መድረስ የሚችሉበትን ሁኔታ ለማሳካት የተቻለውን ሁሉ ጥረቶች ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን ለመግለጽ ይወዳል።
በዚህም መሠረት በከፍተኛ ችግር ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ህይወት ለመታደግ እና የዜጎችን እንግልት ለመቀነስ ይቻል ዘንድ ከተለመደው የተለዩ እርምጃዎችን መውሰድ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ መንግስት ይህ ውሳኔ ከወጣበት ሰዓት ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት የማቆም ውሳኔ አስተላልፏል። በዚህ አጋጣሚ መንግስት ዓለም ዓቀፉ የለጋሾች ማህበረሰብ እያቀረበ ያለውን ድጋፍ እና እርዳታ በከፍተኛ መጠን እንዲጨምር ጥሪ ያቀረባል።

የሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦቱ በተሳለጠ ሁኔታ መድረስ እንዲችል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተባብሮ ለመስራት ያለውን ቁርጠኝነት በድጋሚ ያረጋግጣል። ይህ የመንግስት ጥረት እና ቁርጠኝነት የሰብዓዊ ሁኔታውን በማሻሻል ረገድ የሚኖረው ስኬት የሚረጋገጠው በሌላኛው ወገን የሚገኘው አካል በተመሳሳይ ለዚህ አላማ በሚኖረው ቁርጠኝነት ልክ መሆኑን መንግስት ያምናል። ይህ በመንግስት በኩል የተላለፈው ውሳኔ አላማው የአስቸኳይ የሰብዓዊ ድጋፍ በነጻነት ተጓጉዞ ለእርዳታ ፈላጊ ዜጎች ለመድረስ እንዲችል ነው። በመሆኑም ለሰብኣዊነት ግጭት የማቆም ውሳኔ የተፈለገውን ውጤት ማምጣት እንዲችል መንግስት በትግራይ ክልል የሚገኙ አማጺያን ከማንኛውም የጥቃት እንቅስቃሴ እንዲታቀቡ እና ን በጉልበት ከያዟቸው የአጎራባች ክልል አካባቢዎችእንዲወጡ ይጠይቃል።

የኢትዮጵያ መንግስት ይህ ለሰብኣዊነት ግጭት የማቆም ውሳኔ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን የሰብዓዊ ሁኔታ በእጅጉ ሊያሻሽል እንደሚችል ብሎም በቀጣይ ያለተጨማሪ ደም መፋሰስ ለግጭቱ መፍትሔ ሊያመጣ እንደሚችል ተስፋ ያደርጋል።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

የህዝባችንን ሃሳብ በአግባቡ እናደምጣለን!!በፍላጎቱ እንመራለን!!!በዛሬው  እለት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በ10ሩም ወረዳዎችና በክፍለ ከተማ ደረጃ   የሚከናወነው የህዝብ ውይይት መድረክ  ከጥ...
23/03/2022

የህዝባችንን ሃሳብ በአግባቡ እናደምጣለን!!
በፍላጎቱ እንመራለን!!!

በዛሬው እለት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በ10ሩም ወረዳዎችና በክፍለ ከተማ ደረጃ የሚከናወነው የህዝብ ውይይት መድረክ ከጥቂት ደቂቃዎች በሀላ ይጀምራል።

በቅድመ ዝግጅቱም በክፍለ ከተማ በአራት ዓመታት የተሰሩ ስራዎች በፎቶ ኤግዝብሽን መልኩ ተከፍቶ ለህዝብ ክፍት ሆኗል።

በአዲስ አበባ በከተማ ደረጃ የሚካሄደው የህዝብ የውይይት መድረክ ተጀምሯል።የብልጽግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ እና የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ህዝብ ለማወያየት በ...
23/03/2022

በአዲስ አበባ በከተማ ደረጃ የሚካሄደው የህዝብ የውይይት መድረክ ተጀምሯል።

የብልጽግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ እና የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ህዝብ ለማወያየት በመድረኩ ተገኝተዋል

ከአንድ ሺህ በላይ የሚሆኑ ከተለያዩ ማህበረሰብ ክፍሎች የተወጣጡ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችም በመድረኩ ታድመዋል።

የህዝባችንን ሃሳብ በአግባቡ እናዳምጣለን፤ በፍላጎቱ እንመራለን!!የህባችን ሀሳብ ለሀገራችን ብልፅግና ወሳኝ ነው!!የወረዳ 07 አስተዳደር የህዝብ ውይይት እየተደረገ ይገኛልመጋቢት14/2014ዓ...
23/03/2022

የህዝባችንን ሃሳብ በአግባቡ እናዳምጣለን፤ በፍላጎቱ እንመራለን!!
የህባችን ሀሳብ ለሀገራችን ብልፅግና ወሳኝ ነው!!
የወረዳ 07 አስተዳደር የህዝብ ውይይት እየተደረገ ይገኛል
መጋቢት14/2014ዓ.ም
ወረዳ 07 ብልፅግና ፓርቲ ሚዲያ

Address

Adis

Telephone

+251912710260

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when KrIkose worda 07 prosperity party posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share