የሀላባ ዞን መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ

የሀላባ ዞን መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ https://youtube.com/?si=0AgS5fdDK0fxiZF5
ለህዝብ ትክክለኛውን መረጃ በወቅቱ ማስተላለፍ ልዩ ምልክታችን ነወ።

የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ከድር የሴ የ2018 ዓ/ም ዕቅድ ክንውን ሪፖርት ለምክር ቤቱ እያቀረቡ ነው=====ነሀሴ 24/2018በሀላባ ዞን የዌራ ወረዳ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 7ኛ ዓመት የስ...
30/08/2026

የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ከድር የሴ የ2018 ዓ/ም ዕቅድ ክንውን ሪፖርት ለምክር ቤቱ እያቀረቡ ነው
=====

ነሀሴ 24/2018በሀላባ ዞን የዌራ ወረዳ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 7ኛ ዓመት የስራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ጉባኤ በሀላባ ሴራ አደራሽ እየተካሄደ ይገኛል።

እየተካሄደ ባለው የወረዳው ምክር ቤት ጉባኤ ላይ የዌራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ከድር የሴ የወረዳው ምክር ቤቱን የ2018 ዓ/ም ዕቅድ ክንውን ሪፖርት ለምክር ቤቱ እያቀረቡ ነው።

በጉባኤው ላይም የሀላባ ዞን ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ክቡርት ወይዘሮ ረውዳ ዜይኔ፣ የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ያድሶ ዱበለ፣ የወረዳው አመራሮች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባላት የወረዳ ምክር ቤት አባለት ተገኝተዋል።

በሹኩር ሀ/ሀሰን

ለተጨማሪ መረጃዎች በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተላሉን 👇

ቴሌግራም፦ https://t.me/+eIbzwXJYyQNlYjVk

ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/profile.php?id=100083958027668

በቲክቶክበ፦ tiktok.com/

በቲውተር፦ https://x.com/Halabazonecomun?t=jrF0ELvPbOBJOuLT6X3G1A&s=09

ዋትስአፕ፦ https://whatsapp.com/channel/0029Vb3YNPxJZg4GKKQ3Om3v

ዩቲዩብ፦ https://youtube.com/?si=SJOXf764DKjW1CUe

ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/halabazonecomunication?igsh=a3NwdTUwand6NWhn

ምርጫችሁ ስላደረጋችሁን እናመሰግናለን!!

የዌራ ዲጆ ወረዳ ምክር ቤት አባላት የ1ኛ ዙር 7ኛ ዓመት የስራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤ መካሄድ ጀመረ=====ነሀሴ 24/2018 በዌራ ዲጆ ወረዳ ምክር ቤት የ1ኛ ዙር 7ኛ ዓመት የስራ ዘመ...
30/08/2026

የዌራ ዲጆ ወረዳ ምክር ቤት አባላት የ1ኛ ዙር 7ኛ ዓመት የስራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤ መካሄድ ጀመረ
=====

ነሀሴ 24/2018 በዌራ ዲጆ ወረዳ ምክር ቤት የ1ኛ ዙር 7ኛ ዓመት የስራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤ መካሄድ ጀምረዋል።

የጉባኤ መድረኩን የወረዳው ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ የተከበሩ መሐመድ ጃተኖ መክፈቻ ንግግር በማድረግ፣የዕለቱን አጀንዳ በማቅረብ የ2018 ዓ.ም ቃለ ጉባዔ በምክር ቤቱ ሙሉ ድምፅ ጸድቋል።

በጉባኤው መድረክ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዲ አደም፣ የወረዳው የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ሱራጅ ጎድሶ፣ የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጎበና ሰማን፣ የወረዳው የመንግስት ረዳት ተጠሪና ፖለቲካ አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አ/ረህማን ጀማል፣ የወረዳው የመንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ ባሙድ ጡሚሶ፣የሀላባ ዞን ምክር ቤት ህግና ፍትህ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሁሴን ኢብራሂምን ጨምሮ የወረዳ አጠቃላይ አመራሮችና የዞንና የወረዳ ምክር ቤት አባላት ተገኝተዋል።

ነሃሴ 24/2018 በሸኖ፣(ዌራ ዲጆ ኮሚዩኒኬሽን)

የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ምክር ቤት 2ኛ ዙር 8ኛ ዓመት፣ 9ኛ መደበኛ ጉባዔ እየተካሄደ ነው=====ነሀሴ 24/2018 የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ምክር ቤት 2ኛ ዙር 8ኛ ዓመት፣ 9ኛ መደበኛ ጉባዔ እየተካ...
30/08/2026

የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ምክር ቤት 2ኛ ዙር 8ኛ ዓመት፣ 9ኛ መደበኛ ጉባዔ እየተካሄደ ነው
=====

ነሀሴ 24/2018 የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ምክር ቤት 2ኛ ዙር 8ኛ ዓመት፣ 9ኛ መደበኛ ጉባዔ እየተካሄደ ይገኛል።

በጉባዔው ላይ የምክር ቤቱ ዋና አፈጉባዔ የተከበሩ በርገና ዶቦጭ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በወረዳው በመሠረተ-ልማት ዘርፍ በመንገድና በውሃና በሌሎችም ማሕበራዊ ዘርፍ በትምህርት፣ በጤና፣ በባህልና ቱሪዝምና በሌሎችም ዘርፎች ስኬቶች መመዝገባቸውን ተናግረዋል።

ጉባዔው 7ኛው ሀገራዊ ክልላዊ ምርጫ በተካሄደበት፣ ሀገራዊ ምክክር በስኬት በተጠናቀቀበትና በዞናችን በርካታ ፕሮጀክቶች በተመረቁበት ዓመት መከበሩ ለየት እንደሚያደርገው ተናግረዋል።

በጉባዔው ላይ የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ኢንጅነር አ/ቃድር አማን የወረዳውን የ2019 አፈጻጸም ሪፖርት በዝርዝር እያቀረቡ ይገኛሉ።

በጉባዔው ላይ የሀላባ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈጉባዔ የተከበሩ መሐመድአሚን ሐጂ መህዲና የምክር ቤቱ የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች፣ ከዞን፣ ከወረዳና ከየቀበሌያቱ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የምክር ቤቱ አባላት ተገኝተዋል።

በሀላባ ዞን የዌራ ወረዳ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 7ኛ ዓመት የስራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ጉባኤ በሀላባ ሴራ አደራሽ መካሄድ ጀመረ=====ነሀሴ 24/2018በሀላባ ዞን የዌራ ወረዳ ምክር ቤት 4ኛ ...
30/08/2026

በሀላባ ዞን የዌራ ወረዳ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 7ኛ ዓመት የስራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ጉባኤ በሀላባ ሴራ አደራሽ መካሄድ ጀመረ
=====

ነሀሴ 24/2018በሀላባ ዞን የዌራ ወረዳ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 7ኛ ዓመት የስራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ጉባኤ በሀላባ ሴራ አደራሽ መካሄድ ጀምረዋል።

የጉባኤው መክፈቻ ንግግር የከፈቱት የዌራ ወረዳ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ኑረዲን ሪባቶ ቤቱ ከመቼውም ግዜ በላይ የወረዳውን የህብረተሰቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን እንዲፈቱ ይገኛል ብለዋል።

ምክር ቤቶች በክልሉ ህገ መንግስት ከተሰጣቸው ስልጣን አንዱ በየደረጃው ተፈፃሚ የሚሆኑ የተለያዩ ህጎችን በማውጣት እና በሚወጡ ህጎች መነሻ የተለያዩ ደንቦችንና መመሪያዎችን በማውጣት አፈጻጸማቸውን መከታተልና መቆጣጠር እንደሆነም ተናግረዋል።

የምክር ቤት ልማትና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች የህዝብ ተጠቃሚነት ይበልጥ እንዲረጋገጥ በትኩረት እንደሚሰራ አስገንዝበዋል።

በበጀት ዓመቱ የወረዳው የመንግስት አስፈፃሚ አካላት የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የተለያዩ ህጎችን በማውጣት፤ ከህዝብ የተሰጣቸውን ተልእኮ በብቃት እንዲፈፅሙ ድጋፍና ክትት ማድረጉን ገልጸዋል።

ምክር ቤት የህዝቡን ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሽጋገር መላውን ህዝብ በማንቀሳቀስ በርካታ ስራዎች መሰረታቸውን ገልጸዋል።

የምክር ቤቱ የወረዳ ያለፈው ዓመት ቃላ-ጉባዔ ረቂቅ እና የ2018 የምክር ቤቱ የስራ ዕቅድ፣ እንዲሁም የወረዳ አስተዳደር የ2018 ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እና የወረዳ ምክር ቤት 2019 የስራ ዘመን ዕቅድ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ይጸድቃል ተብለው ይጠበቃል።

እንዲሁም የወረዳ ፍርድ ቤት የ2018 ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርትና የ2019 የስራ ዕቅድ ለምክር ቤቱ ቀርበው ወይይት በማድረግ ማጽደቅ የመሳሰሉ አጀንዳዎችን መያዛቸውን ገልጸዋል።

በጉባኤው ላይም የዌራ ወረዳ ዋና አስተዳደር አቶ ከድር የሴ፤ የሀላባ ዞን ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ክቡርት ወይዘሮ ረውዳ ዜይኔ፣ የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ያድሶ ዱበለ፣ የወረዳው አመራሮች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባላት የወረዳ ምክር ቤት አባለት ተገኝተዋል።

በሹኩር ሀ/ሀሰን

ለተጨማሪ መረጃዎች በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተላሉን 👇

ቴሌግራም፦ https://t.me/+eIbzwXJYyQNlYjVk

ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/profile.php?id=100083958027668

በቲክቶክበ፦ tiktok.com/

በቲውተር፦ https://x.com/Halabazonecomun?t=jrF0ELvPbOBJOuLT6X3G1A&s=09

ዋትስአፕ፦ https://whatsapp.com/channel/0029Vb3YNPxJZg4GKKQ3Om3v

ዩቲዩብ፦ https://youtube.com/?si=SJOXf764DKjW1CUe

ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/halabazonecomunication?igsh=a3NwdTUwand6NWhn

ምርጫችሁ ስላደረጋችሁን እናመሰግናለን!!

የኢትዮጵያ የጤና መድኅን አገልግሎት አፈጻጸምን መሰረት ያደረገ የክፍያ ስርዓት (PBF) የሙከራ ትግበራን ገመገመ=====ነሀሴ 23/2018 የኢትዮጵያ የጤና መድኅን አገልግሎት በማዕከላዊ ኢት...
29/08/2026

የኢትዮጵያ የጤና መድኅን አገልግሎት አፈጻጸምን መሰረት ያደረገ የክፍያ ስርዓት (PBF) የሙከራ ትግበራን ገመገመ
=====

ነሀሴ 23/2018 የኢትዮጵያ የጤና መድኅን አገልግሎት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት- #በሀላባ ዞን ላይ በሙከራ ደረጃ እየተተገበረ የሚገኘውን አፈጻጸምን መሰረት ያደረገ የክፍያ ስርዓት (Performance-Based Financing - PBF) ትግበራ በሀዋሳ ከተማ በከፍተኛ አመራሮች፣ በባለድርሻ አካላት እና በጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ገመገመ።

በግምገማ መድረኩ ላይ የአገልግሎቱ ከፍተኛ አመራሮችና ስራ አስፈጻሚዎች፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ እና የሀላባ ዞን አመራሮች፣ የክላስተርና የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሀላፊዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም የኮርዴድ ኢትዮጵያ (Cordaid-Ethiopia) አባላት ተሳትፈዋል።

የመድረኩን መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ የጤና መድህን አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ወርቁ እንደገለጹት፤ አፈጻጸምን መሰረት ያደረገ የክፍያ ስርዓት (PBF) ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ በሱማሌ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስታት በሙከራ ደረጃ መጀመሩን አስታውሰዋል።

ፕሮጀክቱ የመደበኛ መንግስት በጀትን በመደገፍ የሕክምና አገልግሎት ጥራትን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ያለመ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም ፕሮጀክቱ በተጀመረባቸው አካባቢዎች ተጨባጭ ውጤት መመዝገቡን ገልጸው፣ የተገኙ መልካም አፈጻጸሞችን በማቀመር፣ በፋይናንስና በቴክኒክ የሚደረገውን ድጋፍ በማጠናከር ፕሮጀክቱ ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንዲሰፋና የበለጠ ስኬት እንዲመዘገብ አገልግሎቱ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ተናግረዋል።

የአገልግሎቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ጠዓመ አረዶም በበኩላቸው፤ "ውጤትን መሰረት ያደረገ የክፍያ ስርዓት በመዘርጋት የጤና መድህን ስርዓቱን እየደገፍን በሄድን ቁጥር ቀጣይነት ያለው የፋይናንስ ስርዓት መገንባት ይቻላል፤ በሌላ በኩል ደግሞ ጥራት ያለው የሕክምና አገልግሎት ለዜጎች ተደራሽ ማድረግ ይቻላል" ሲሉ የፕሮጀክቱን ስትራቴጂካዊ አስፈላጊነት አብራርተዋል።

የአገልግሎቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ያምሮት አንዱዓለም ቀደም ሲል በሐዋሳ ክላስተር በሙከራ ደረጃ ሲተገበር የነበረው የPBF ስርዓት የላቀ ውጤት የተመዘገበት መሆኑን ገልጸዋል።

አሁን ላይ ይህ የሙከራ ትግበራ ወደ ሆሳዕና ክላስተር ጽህፈት ቤት በሚሸጋገርበት ወቅት ከሐዋሳ ክላስተር የተገኙ ምርጥ ተሞክሮዎችን በመውሰድና በመተግበር የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የጤና ሚኒስቴር የስትራቴጂክ ጉዳዮች ሥራ አስፈጻሚ የጤና ፋይናንሲንግ ቡድን መሪ አቶ አንሙት አያሌው፤ ፕሮጀክቱ በሙከራ ደረጃ ሲጀመር ባለሙያዎችን በማሰልጠን እና የተሟላ ግንዛቤ በመፍጠር በመጀመሩ ምክንያት አበረታችና ተጨባጭ ውጤቶች ሊመዘገቡ መቻላቸውን ገልጸዋል።

አቶ ሀብቴ ገብረሚካኤል (የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ) ፕሮጀክቱ በክልሉ በሚገኙ የሙከራ አካባቢዎች በተሻለ ደረጃ በመፈጸሙ ውጤታማ ስራዎች ተከናውነዋል።

ዜጎች የሕክምና አገልግሎት ወጪ ሳያስጨንቃቸው በየደረጃው በሚገኙ የጤና ተቋማት ታክመው እንዲዳኑ ማስቻል መቻሉ ትልቅ ስኬት ነው።

አቶ ሙዲን ሁሴን (የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ)፦ ስርዓቱ በሀላባ ዞን በሙከራ ደረጃ መተግበር ከተጀመረ ወዲህ በዞኑ ይታዩ የነበሩ የበጀት ክፍተቶችን በመሙላት በጤና መድህን አገልግሎት የተያዙ ግቦች እንዲሳኩ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል።

በግምገማ መድረኩ ማጠናቀቂያ ላይ በሙከራ ትግበራው ወቅት የላቀ አስተዋጽኦ እና ከፍተኛ አፈጻጸም ላስመዘገቡት ለሐዋሳ ክላስተር ጽህፈት ቤት እና ለሀላባ ዞን የምስጋና እና የእውቀና ሰርተፊኬት ተበርክቶላቸዋል።

በተጨማሪም የPBF የሙከራ ትግበራ ስራውን የበለጠ ለማጠናከር እና ለማቀላጠፍ የሚያስችል የተሽከርካሪ ርክክብ በኢትዮጵያ የጤና መድህን አገልግሎትና በሆሳዕና ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት መካከል መካሄዱን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በሀላባ ዞን የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ምክር ቤት 2ኛ ዙር 8ኛ ዓመት የስራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤውን በወረዳው እየተሰሩ ባሉ ልማታዊ መስክ ምልከታ በማድረግ በይፋ አስጀመረ======ነሀሴ 23/2...
29/08/2026

በሀላባ ዞን የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ምክር ቤት 2ኛ ዙር 8ኛ ዓመት የስራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤውን በወረዳው እየተሰሩ ባሉ ልማታዊ መስክ ምልከታ በማድረግ በይፋ አስጀመረ
======

ነሀሴ 23/2018 የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ምክር ቤት 2ኛ ዙር 8ኛ ዓመት የስራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤውን በወረዳው እየተሰሩ ባሉ ልማታዊ መስክ ምልከታ በማድረግ በይፋ በዛሬው ዕለት አስጀምረዋል።

በዚህም የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር አ/ቃዲር አማን፣ የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ በርገና ዶቦጭ የተመራው የወረዳው ምክር ቤት አባላት ልኡክ 2ኛ ዙር 8ኛ ዓመት የስራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤውን በወረዳው እየተሰሩ ያሉ የተለየዩ ልማት ስራዎችን የመስክ ምልከታ አድርገዋል።

በመስክ ምልክታቸው በወረዳው በATI የተዘገዙ ትራክቴሮችን፣ በጉባ ጤና ጣቢያ ውስጥ ለውስጥ እየተሰራ ያለው የማህረሰብ ፋርማሲ፣ የጉባ ሃይስኩልን፣ አንደኛና ሁለተኛ ሀንሻ፣ የዬና ሸዋኮ ቀበሌዎች ሜጋ የበቆሎ ክላስተር ተመልክቷል።

በ2ኛ ሀንሻ ቀበሌ እየተገነባ የሚገኘው የማህረሰብ ጤና ኬላ፣ በሴንቄሌ ቢጣና ቀበሌ በክላስተር እየለማ የሚገኘው የድንች ሰብል፣ በቁንጬ የዬ ቀበሌ የዶሮ መንደርን ተዟዙሮ ምልከታ አድርገዋል።

በወረዳው በተለያዩ ቀበሌዎች በመንግሥትና በህብረተሰብ ተሳትፎ እየተሰራ የሚገኘው የመንገድ ከፈታና ጠረጋ ስራዎች መመልከት ተችሏል።

በምልከታው ላይም የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ዋና አስተዳደሪ ኢንጂነር አብዱልቃድር አማን፣ የወረዳው የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ በክሪ አብደላ፣የወረዳው ምክርቤት ዋና አፈጉባኤ የተከበሩ በርገና ዶቦጭ፣ የወረዳው አመራሮች የምክርቤት አባላቶች ተገኝተዋል።

በመጨረሻም የወረዳው ምክር ቤት 2ኛ ዙር 8ኛ ዓመት የስራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤው ከነገ ጀምረው የወረዳው የአስፈጻሚ መስሪያ ቤት የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርበው ውይይት የሚደረገው ስሆን የ2019 በጀት ማጽደቅ፣ የቀጣይ የ2019 ዕቅድ ዙሪያ እንደሚመክር እንደዚሁም የተለያዩ አጀንዳዎች እንደሚኖሩም ተጠቁሟል።

ለተጨማሪ መረጃዎች በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተላሉን 👇

ቴሌግራም፦ https://t.me/+eIbzwXJYyQNlYjVk

ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/profile.php?id=100083958027668

በቲክቶክበ፦ tiktok.com/

በቲውተር፦ https://x.com/Halabazonecomun?t=jrF0ELvPbOBJOuLT6X3G1A&s=09

ዋትስአፕ፦ https://whatsapp.com/channel/0029Vb3YNPxJZg4GKKQ3Om3v

ዩቲዩብ፦ https://youtube.com/?si=SJOXf764DKjW1CUe

ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/halabazonecomunication?igsh=a3NwdTUwand6NWhn

ምርጫችሁ ስላደረጋችሁን እናመሰግናለን!!

በኢፌዲሪ በውሃ ሀብት ሚኒስትር በኩል በወርልድ ባንክ በተገኘ በጀት በኢትዮጵያ በሆርን ኦፍ አፍሪካ ድርጅት  በአቶቲ ኡሎ ወረዳ በፈልቃ ቀበሌ ለወራት ችግር ሆኖ የቆያሁን የመጠጥ ውሃ ችግር ...
29/08/2026

በኢፌዲሪ በውሃ ሀብት ሚኒስትር በኩል በወርልድ ባንክ በተገኘ በጀት በኢትዮጵያ በሆርን ኦፍ አፍሪካ ድርጅት

በአቶቲ ኡሎ ወረዳ በፈልቃ ቀበሌ ለወራት ችግር ሆኖ የቆያሁን የመጠጥ ውሃ ችግር ለመቅረፍ ይረዳን ዘንድ ከፌዴራል፥ ከዞንና ከወረዳው የተወጣጡ የጥናት ቡድን የውሃ ቁፋሮ ቦታ በመለየት

በጂኦፊዝክስ መሣሪያ የተደገፈ የጥናት ሥራ ዛሬ በቀን 23/12/2018 ዓ/ም የተሠራ ሲሆን በጥናት መረጃው መሠረት በቀጣይ ጊዜ ወደ ተግባር የሚገባ ይሆናል።

በወረዳው በፈልቃ ቀበሌ ለወራት ተቆርጦ የነበረው የውሃ ተቋምን አገልግሎት ለማስጀመር እየተሰራ እንደሚገኝ የወረዳው ዉሃ ጽ/ቤት አስታወቋል።

የማህበረሰቡን እንግልት ለመቅረፍ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ ተገልጸዋል።
መረጃው የወረዳው ዉሃ ማዕድን ኢነርጂ ጽ/ቤት ነው

በሀላባ ዞን በዌራ ወረዳ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 7ኛ ዓመት የስራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ጉባኤውን በወረዳው እየተሰሩ ባሉ ልማታዊ መስክ ምልከታ በማድረግ በይፋ አስጀመረ=====ነሀሴ 23/2018 ...
29/08/2026

በሀላባ ዞን በዌራ ወረዳ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 7ኛ ዓመት የስራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ጉባኤውን በወረዳው እየተሰሩ ባሉ ልማታዊ መስክ ምልከታ በማድረግ በይፋ አስጀመረ
=====

ነሀሴ 23/2018 የዌራ ወረዳ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 7ኛ ዓመት የስራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ጉባኤውን በወረዳው እየተሰሩ ባሉ ልማታዊ መስክ ምልከታ በማድረግ በዛሬው ዕለት በይፋ አስጀምረዋል።

በዚህም የዌራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ከድር የሴ እና የዌራ ወረዳ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ኑረዲን ሪባቶ የተመራው የወረዳው ምክር ቤት አባላት ልኡክ 4ኛ ዙር 7ኛ ዓመት የስራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ጉባኤውን በወረዳው እየተሰሩ ያሉ የተለየዩ ልማት ስራዎችን የመስክ ምልከታ አድርገዋል።

በመስክ ምልክታቸው በወረዳው የሙደ ኢሎለቃ ቀበሌ፣ ላይኛውና ታችኛው በደኔ ቀበሌ የገጠር ኮሪደር የቤቶች ግንባታ ያለበት ደረጃ ምልከታ ተዟዙሮ ተመልክቷል።

የአቦክቾ ከተማ ማዘጋጃ አዲሱ ህንፃ፣ የወረዳው የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ግቢ ውስጥ እያለማ የሚገኝ የፍራፍሬ ኢንሼቲቭ፣ በታችኛው አርሾ ቀበሌ ለበቆ የመንግስት ችግኝ ጣቢያ፣ በሙዳ በዊሻአሞ ቀበሌ የወተት መንደር ጽዱ መንደርና የአርሶአደር መሰልጠኛ ተቋም መመልከት ተችሏል።

የመስክ ምልከታው ላይ የምክር ቤቱ አባላት በሰጡት አስተያየት በወረዳው በሁሉም መስክ የሚሰሩ የልማት ስራዎች ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርግ በመሆኑ ተጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አንስተዋል።

በምልከታው ላይ የዌራ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ያድሶ ዱበላ፣ የዌራ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ እና የግብርና ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ጀማል ሚሀሌ፣ የሀላባ ዞን ምክርቤት ምክትል አፈጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ረውዳ ዘይኔ፣ የወረዳው አስተባባሪዎች፣ የወረዳው አመራሮችና የምክር ቤቱ አባላት እና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

በመጨረሻም የወረዳው ምክር ቤት 1ኛ ዙር 7ኛ ዓመት የስራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤው ከነገ ጀምረው የወረዳው የአስፈጻሚ መስሪያ ቤት የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርበው ውይይት የሚደረገው ስሆን የ2019 በጀት ማጽደቅ፣ የቀጣይ የ2019 ዕቅድ ዙሪያ እንደሚመክር እንደዚሁም የተለያዩ አጀንዳዎች እንደሚኖሩም ተጠቁሟል።

ለተጨማሪ መረጃዎች በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተላሉን 👇

ቴሌግራም፦ https://t.me/+eIbzwXJYyQNlYjVk

ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/profile.php?id=100083958027668

በቲክቶክበ፦ tiktok.com/

በቲውተር፦ https://x.com/Halabazonecomun?t=jrF0ELvPbOBJOuLT6X3G1A&s=09

ዋትስአፕ፦ https://whatsapp.com/channel/0029Vb3YNPxJZg4GKKQ3Om3v

ዩቲዩብ፦ https://youtube.com/?si=SJOXf764DKjW1CUe

ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/halabazonecomunication?igsh=a3NwdTUwand6NWhn

ምርጫችሁ ስላደረጋችሁን እናመሰግናለን!!

በክልሉ አነስተኛ የመስኖ ፕሮጀክቶችን በማስፋፋት የአርሶ አደሩን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለጸ ======ነሀሴ 23/2018 የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል መስኖ ተ...
29/08/2026

በክልሉ አነስተኛ የመስኖ ፕሮጀክቶችን በማስፋፋት የአርሶ አደሩን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለጸ
======

ነሀሴ 23/2018 የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል መስኖ ተቋማት ልማት አስተዳደር ኤጀንሲ አመራሮችና ባለሙያዎች በከምባታ ዞንና በሐዲያ ዞን እየተገነቡ የሚገኙ አነስተኛ የመስኖ ፕሮጀክችን ተዘዋውረው ምልከታ አድርገዋል።

በመስክ ምልከታው ላይ በሀዲያ ዞን በምዕራብ ባደዋቾ ወረዳ በሰጴራ ቀበሌ እየተገነባ የሚገኘው ደርጋሶ አነስተኛ መስኖ ፕሮጀክት እንዲሁም በከምባታ ዞን በቃጫቢራ ወረዳ በቡጌ መሰና ቀበሌ እየተገነባ የሚገኘው የአጃንቾ አነስተኛ መስኖ ፕሮጀክት የደረሰበት ደረጃ ምልከታ ተደርጓል።

በምልከታው ላይ ገለፃ ያደረጉት የክልሉ መስኖ ተቋማት ልማት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ካሳዬ ተክሌ ፕሮጀክቶቹ ከተጀመሩ ጥቂት ጊዜ ቢሆንም የግንባታ ሂደቱ በፍጥነት እየተከናወነ በመሆኑ አፈጻጸማቸው በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በዚሁም መሠረት የደርጋሶ አነስተኛ መስኖ ፕሮጀክት አፈጻጸሙ 75% ፐርሰንት መድረሱንና የአጃንቾ አነስተኛ መስኖ ፕሮጀክት አፈጻጸሙ 76% መጠናቀቁን ተናግረዋል።

በመሆኑም ፕሮጀክቶቹ ባጠረ ጊዜ አልቀው ለ2019 በጋ መስኖ ዝግጁ እንዲሆኑ ይደረጋል ያሉ ሲሆን ለዚህም በከፍተኛ ቁርጠኝነት የግንባታ ሂደቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

የኤጀንሲው ምክትል አስኪያጅና የግንባታ ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት ኢንጅነር መሐመድስራጅ አ/ቃድር በበኩላቸው ፕሮጀክቶቹ ለበጋ መስኖና ለዓሳ እርባታ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳላቸው ገልፀዋል።

አክለውም የደርጋሶ አነስተኛ መስኖ ፕሮጀክት 100 ሄ/ር ማልማት የሚችል እንደሆነና አጃንቾ አነስተኛ መስኖ ፕሮጀክት ከ70 በላይ ሄ/ር ማሳ ማልማት የሚችል መሆኑን ተናግረዋል።

ፕሮጀክቱ 700 አባወራዎችንና እማወራዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገልፀው ከዚህም የደርጋሶ አነስተኛ መስኖ ፕሮጀክት 400 አባወራዎችንና እማወራዎችን የአጃንቾ አነስተኛ መስኖ ፕሮጀክት ደግሞ 300 አባወራዎችንና እማወራዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑን ተናግረዋል።

ከመስኖ ፕሮጀክቶች ግንባታ መካከል የደርጋሶ አነስተኛ መስኖ ፕሮጀክት 127 እንዲሁም የአጃንቾ አነስተኛ መስኖ ፕሮጀክት 118 ሚሊዮን ብር የሚፈጁ ፕሮጀክቶች መሆናቸውን ጨምረው ተናግረዋል።

በፕሮጀክቶቹ ድልድዮችና የእግረኛ መንገዶች እንዲሁም ግንባታው እስኪጠናቀቅ በካምፕነት የሚያገለግሉ በኋላ ላይ ለመስኖ ውሃ ተጠቃሚ ማሕበራት ጽ/ቤት ሆነው የሚያገለግሉና ለቀበሌው ለተለያዩ አገልገሎቶች የሚውሉ ቢሮዎች ግንባታ መከናወናውንም ተናግረዋል።

በሀላባ ዞን በዌራ ዲጆ ወረዳ ምክር ቤት 1ኛ ዙር 7ኛ ዓመት የስራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤውን በወረዳው እየተሰሩ ባሉ ልማታዊ መስክ ምልከታ በማድረግ በይፋ አስጀመረ=====ነሀሴ 23/201...
29/08/2026

በሀላባ ዞን በዌራ ዲጆ ወረዳ ምክር ቤት 1ኛ ዙር 7ኛ ዓመት የስራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤውን በወረዳው እየተሰሩ ባሉ ልማታዊ መስክ ምልከታ በማድረግ በይፋ አስጀመረ
=====

ነሀሴ 23/2018 በሀላባ ዞን በዌራ ዲጆ ወረዳ ምክር ቤት 1ኛ ዙር 7ኛ ዓመት የስራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤውን በወረዳው እየተሰሩ ባሉ ልማታዊ መስክ ምልከታ በማድረግ በዛሬው ዕለት በይፋ አስጀምረዋል።

የዌራ ዲጆ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዲ አደም እና የዌራ ዲጆ ወረዳ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ መሀመድ ጀተኖ የተመራው የወረዳው ምክር ቤት አባላት ልዑክ 1ኛ ዙር 7ኛ ዓመት የስራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤውን በወረዳው እየተሰሩ ያሉ የተለየዩ ልማት ስራዎችን የመስክ ምልከታ አድርገዋል።

በዚህም መስክ ምልክታቸው በሲንቢጣ ቀበሌ በትምህርት ቤት ማሳ ለውስጥ ገቢ የተዘራው የቺያ-ሲድ ሰብል፣ በቁሉቢ ቀበሌ በአርሶአደሩ ማሳ በመደበኛ በልግ አዝመራ በክላስተር በመልማት ላይ የሚገኝ የበቆሎ ክላስተር ተመልክቷል።

በአጆና ጢጣሊ-ብጦራ ቀበሌዎች ላይ ለተረጂዎች መጠባበቂያ የተዘራው የስንዴ ሰብል የደረሰበት ደረጃ፣ በጮባሬ ሜዕኖ ቀበሌ ላይ አዲሱን የፍራፍሬ መንደር፣ የሌማት ቱሩፋት አካል የሆነውን የዶሮ መንደር ምልከታ አድርገዋል።

በጮባሬ ሜዕኖ ቀበሌ በመደበኛ በልግ አዝመራ በአርሶአደሩ ማሳ በክላስተር በመልማት ላይ የሚገኝ የበቆሎ የተመለከቱ ስሆን በተለይም በጮባሬ ሜዕኖ ቀበሌ በአርሶአደሩ ማሳ በክላስተር ተዘርተው የደረሰውን የቅድመ በልግ በቆሎ ያለበት ደረጃ ተመልክቷል።

የምክር ቤት አባላት በወረዳው በበጀት አመቱ በተግባር የተከናወኑ የተለያዩ መሰረተ ልማት ስራዎችን ተዟዙረው ተመልክቷል።

በበሸኖ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግቢ ውስጥ እየለሙ የሚገኙ የተለያዩ የግብርና ልማት ስራዎችን ተዟዙረው መመልከት ችለዋል።

የመስክ ምልከታው ላይ የምክር ቤቱ አባላት በሰጡት አሰተያየት የህብረተሰቡን የልማት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚሰሩ ስራዎች መጠናከር አለባቸው ብለዋል።

በወረዳው በሁሉም መስክ የሚሰሩ የልማት ስራዎች ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ መሆኑን በማንሳት ይህ የተጀመረው ስራ ቀጣይነት ሊኖረው ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

በምልከታው ላይ የዌራ ዲጆ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዲ አደም፣ የዌራ ዲጆ ወረዳ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ መሀመድ ጀተኖ፣ የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሱራጅ ጎድሶ፣ የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ጎበና ሰማን፣ የወረዳው ምክር ቤት አባላት፣ የወረዳው ካቢኔ አመራሮች፣ ጥሩ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የወረዳው ምክር ቤት 1ኛ ዙር 7ኛ ዓመት የስራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤው ከነገ ጀምሮ የወረዳው የአስፈጻሚ መስሪያ ቤት የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርበው ውይይት የሚደረገው ስሆን የ2019 በጀት ማጽደቅ፣ የቀጣይ የ2019 ዕቅድ ዙሪያ እንደሚመክር እንደዚሁም የተለያዩ አጀንዳዎች እንደሚኖሩም ለማወቅ ተችሏል።

ለተጨማሪ መረጃዎች በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተላሉን 👇

ቴሌግራም፦ https://t.me/+eIbzwXJYyQNlYjVk

ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/profile.php?id=100083958027668

በቲክቶክበ፦ tiktok.com/

በቲውተር፦ https://x.com/Halabazonecomun?t=jrF0ELvPbOBJOuLT6X3G1A&s=09

ዋትስአፕ፦ https://whatsapp.com/channel/0029Vb3YNPxJZg4GKKQ3Om3v

ዩቲዩብ፦ https://youtube.com/?si=SJOXf764DKjW1CUe

ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/halabazonecomunication?igsh=a3NwdTUwand6NWhn

ምርጫችሁ ስላደረጋችሁን እናመሰግናለን!!

Address

Alaba K'ulito

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የሀላባ ዞን መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to የሀላባ ዞን መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ:

Shortcuts

Share