በሀላባ ዞን የዌራ ወረዳ ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት

በሀላባ ዞን የዌራ ወረዳ ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት ህገወጥ ንግድን በጋራ እንከላከል

ለግንባር ቀደም ባለሀብቶች የእውቅናና የሽልማት መርሃ-ግብር ተካሄደ!!!‎‎“ሁሉ አቀፍ እምርታ ለሁለንተናዊ ከፍታ”‎‎ በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር የባለሀብቶች ግንባር በፓርቲው የሥራ እን...
20/08/2026

ለግንባር ቀደም ባለሀብቶች የእውቅናና የሽልማት መርሃ-ግብር ተካሄደ!!!

‎“ሁሉ አቀፍ እምርታ ለሁለንተናዊ ከፍታ”

‎ በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር የባለሀብቶች ግንባር በፓርቲው የሥራ እንቅስቃሴዎች ላይ በመሳተፍ በሀብት በእውቀት በሙያና በሌሎች የድጋፍ መንገዶች ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ግንባር ቀደም ባለሀብቶች ልዩ የእውቅናና የሽልማት መርሃ ግብር ተካሂዷል።

‎በመርሃ ግብሩም ለከተማው የልማት እንቅስቃሴና ለፓርቲው የሥራ አፈጻጸም አንጸባራቂ ውጤት የራሳቸውን የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ባለሀብቶች የዋንጫ የሜዳሊያና የምስክር ወረቀት ና የእዉቅና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

‎የእውቅናና የሽልማት መርሃ ግብሩ ባለሀብቶች በከተማው የልማት ጉዞ ውስጥ ያላቸውን ሚና የበለጠ ለማጠናከር በቀጣይም በልማትና በፓርቲ ሥራዎች ላይ በተሻለ መንፈስ እንዲሳተፉ ለማበረታታት ያለመ ነው።

‎ባለሀብቶች የከተማውን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በማፋጠን የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ ሀብትን በማስፋፋትና ለልማት የሚያበረክቱትን ድርሻ በማጠናከር የከተማዋን የብልጽግና ጉዞ ለማስቀጠል ወሳኝ አጋሮች መሆናቸው በመድረኩ የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አ/መጅድ ፊጣሞ ገልጿል።

‎በ2018 ዓ.ም የተመዘገቡ ውጤቶችን በመጥቀስ በ2019 በጀት ዓመት የበለጠ ውጤታማ ተሳትፎአዊና ተጨባጭ የሆነ የሥራ አፈጻጸም ለማስመዝገብ የባለሀብቶች የፓርቲ አመራሩና የከተማው ማህበረሰብ ትብብር እንዲጠናከር ጥሪ ቀርቧል።

20/08/2026
20/08/2026
የዌራ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት እና የዌራ ወረዳ ንግድ ገበያ ልማት ጽ/ቤት የህገ-ወጥ የንግድ ቁጥጥር፣ኑሮ ማረጋጋት እና የታክስ ህግ ተገዢነት ለማረጋገጥ የሚደረግ የጋራ ንቅናቄ መድረክ አካሄዱ...
20/08/2026

የዌራ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት እና የዌራ ወረዳ ንግድ ገበያ ልማት ጽ/ቤት የህገ-ወጥ የንግድ ቁጥጥር፣ኑሮ ማረጋጋት እና የታክስ ህግ ተገዢነት ለማረጋገጥ የሚደረግ የጋራ ንቅናቄ መድረክ አካሄዱ

በሀላባ ዞን ዌራ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት እና ንግድ ገበያ ልማት ጽ/ቤት የህገ-ወጥ የንግድ ቁጥጥር፣ኑሮ ማረጋጋት እና የታክስ ህግ ተገዢነት ለማረጋገጥ የሚደረግ የጋራ ንቅናቄ መድረክ አካሄደዋል ።

በመድረኩ ላይ የገቢ እና የንግድ የ2018 ዕቅድ አፈጻጸም እና ቀጣይ የ2019 ዕቅድ ዝግጅት በሁለቱም ጽ/ቤት ሀላፊዎች አማካኝነት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጓል ።

መድረኩም የንግድ ሥርዓትን ማስጠበቅ፣ የገበያ ቁጥጥርን ማጠናከርና የገቢ አሰባሰብን ማሻሻል በዋናነት ያለው ዓላማ መሆኑን ተገልጿል።

የውይይት መድረኩን የዌራ ወረዳ የመንግስት ዋና ተጠሪ እና የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ያድሶ ዱበላ እና የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪ እና የግብርና ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ጀማል ሚሀሌ ጋር በጋራ መርተዋል ።

የገቢ አሰባሰብ ከአመት አመት ተስፋ ሰጪ ለውጦችን እያስመዘገበ ነው ያሉት አቶ ያድሶ ዱበላ አሁንም ካለን የልማት ፍላጎት አንጻር የገቢ አሰባሰብ አቅም የበለጠ ከፍ ማድረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በርካታ የልማት ፍላጎቶችን ለመመለስ የገቢ አማራጮች አስፍቶ መስራት ይገባል ብለዋል።

‎በገቢ ስራ ላይ የቅንጅት ስራን በማጠናከር ካልተሰራ ውጤታማ መሆን ስለማይቻል የቅንጅቱ ላይ ልዩ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባም አቶ ያድሶ ያሳሰቡት።

የሕግ ወጥ የንግድ ቁጥጥር፣ የኑሮ ውድነትን ማረጋጋትና የታክስ ህግ ተገዥነት ለማረጋገጥ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅትና በትኩረት መስራት እንደሚገባ አያይዘው አስገንዝበዋል ።

‎የገቢ አሰባሰብ ስራችን በሚፈለገው መጠን ውጤታማ ለማድረግ በተለይ እንደ ወረዳ ባሉ የገቢ ማዕከላት ውስጥ ያሉን የገቢ አማራጮችን ለይቶ በማወቅ በወቅቱ ገቢ መሰብሰብ እንዳለበት አቶ ያድሶ ዱበላ አሳሰበዋል።

አቶ ጀማል ሚሀሌ በበኩላቸው በጠንካራ መረጃ የተደገፈ ገቢ አሰባሰብ ሥራ ውጤቱ የላቀ መሆኑን በማንሳት ጠንካራ ስራ መስራት ተገቢ እንደሆነ አንስተዋል።

ጊዜዉ በልማትም ይሁን በሌሎች ተግባራት የዉድድር መሆኑን በመግለፅ ጤናማ እና ዉጤታማ የሆነ ዉድድር በመፍጠር የተሻለ አፈፃፀም ማስመዝገብ ይጠበቃል ነዉ ያሉት።

የኑሮ ውድነት ለማረጋገጥ የተጀመረውን የሰንበት ገበያ መስፋፋት ፣የገበያ እጥረት መሙላት፣ምርት አቅርቦት፣የንግድ ትስስር መፍጠር እንደሚገባ ገልጸዋል።

አቶ ጀማል የንግድ ስርዓት በህጋዊ መንገድ ካልተመራ በማህበረሰቡ ላይ የሚያደረሰው ጫና ከፍተኛ በመሆኑ በህገወጥ ንግድ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።

የሕግ ወጥ የንግድ ቁጥጥርና የገቢ አሰባሰብ ስራው ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆን ሁሉም አመራርና ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡም ጥሪ ቀርበዋል።

በመድረኩ ማጠቃለያ ከተሳታፊዎች አስተያየት እና ጥያቄ ተነስተው ከመድረኩ ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት የጋራ ተደርጎና ቀጣይ የስራ አቅጣጫ በማስቀመጥ መድረኩ ተጠናቅቋል ።

በመድረኩ ላይ የዌራ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ምክትል እና ፖለቲካ ፣አቅም ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ጀማል አህመድ ፣የወረዳው ምክርቤት ዋና አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ ኑረዲን ሪባቶ፣የወረዳው ገቢዎች ጽ/ቤት ሀላፍ ወ/ሮ አምሪያ ሁሴን፣ የወረዳው ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት ሀላፍ አቶ ሙዜ ሽፋን ጨምሮ ሌሎችም የወረዳው አመራሮች እና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

በሀላባ ዞን የዌራ ወረዳ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት

ዶ/ር ሀቢብ በሽር ፋማ ክሊኒክ ለሀላባ ከነማ 150,000 ብር ገቢ አድርገዋል።‎‎የንግዱ ማህበረሰብ  #ሀላባ ከነማ ለመደገፍ ገቢ በማሰባሰብ እያደረገ ባለው አስተዋጽኦ ዶክተር ሀቢብ ለሀላባ...
19/08/2026

ዶ/ር ሀቢብ በሽር ፋማ ክሊኒክ ለሀላባ ከነማ 150,000 ብር ገቢ አድርገዋል።

‎የንግዱ ማህበረሰብ #ሀላባ ከነማ ለመደገፍ ገቢ በማሰባሰብ እያደረገ ባለው አስተዋጽኦ ዶክተር ሀቢብ ለሀላባ ከነማ 150,000 ብር ገቢ በማድረግ አጋርነታቸውን አሳይተዋል።

‎ ከልብ እናመሰግናለን👌👌👌

አቶ አክረም ሀጂ መርጃን ለሀላባ ከነማ 300,000 ብር ገቢ አድርገዋል።‎‎የንግዱ ማህበረሰብ ሀላባ ከነማ ለመደገፍ ገቢ በማሰባሰብ እያደረገ ባለው አስተዋጽኦ አቶ አክረም ሀጂ መርጃን ለሀላ...
19/08/2026

አቶ አክረም ሀጂ መርጃን ለሀላባ ከነማ 300,000 ብር ገቢ አድርገዋል።

‎የንግዱ ማህበረሰብ ሀላባ ከነማ ለመደገፍ ገቢ በማሰባሰብ እያደረገ ባለው አስተዋጽኦ አቶ አክረም ሀጂ መርጃን ለሀላባ ከነማ 300,000 ብር ገቢ በማድረግ አጋርነታቸውን አሳይተዋል።

‎ ከልብ እናመሰግናለን!!!

የሀላባ ዞን ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት አጸደቀ=====ነሀሴ 13/2018 የሀላባ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 11ኛ የስራ ዘመን 21...
19/08/2026

የሀላባ ዞን ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት አጸደቀ
=====

ነሀሴ 13/2018 የሀላባ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 11ኛ የስራ ዘመን 21ኛ መደበኛ ጉባዔ የሀላባ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ሀላፊ ወወይዘሮ ዙበይዳ ገለቶ እና የዞኑ ምክር ቤት የኢኮኖሚ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በተከበሩ አቶ አህመዲን መሀመድ አማካይነት የዞኑ አስተዳደር የ2018 በጀት ዓመት የበጀት ረቂቅ አዋጅ እና የበጀት መግለጫ ለዞኑ ምክር ቤት ቀርበዋል።

በዚህም የዞኑን 2019 በጀት አመት የልማትና የመልካም አስተደደር ማስፈፀሚያ የምሆን በጀት ከክልል ግምጃ ቤት እና ከሁሉም የገቢ ምንጮች የተገኘ 3,293,518,873 ብር በጀት አጽድቋል፡፡

የ2019 በጀት ዓመት ዞናዊ ተቋማትና ዞናዊ ፕሮጀክቶች 3ቱም ወረዳዎችና የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር በቀመር በጀት ክፍፍል ተደርገዋል።

ዞናዊ ተቋማት፦ የሀላባ ቁሊቶ አጠቃላይ ሆስፒታል፣ የበሸኖ የመጀመሪያ ሆስፒታል እና የቡራቲቾ አዳሬ ት/ቤት እና ሌሎችም ዞናዊ ፕሮጀክቶች እንድሁም የዞን ማዕከል መምሪያዎች የበጀት ድርሻ በየደረጃው ባሉ ባለድርሻ አካለት የቀመር መረጃን መሰረት በማድረግና ልማትን በሚያፈጥኑ ዘርፎች ትኩረት በመስጠት ክፍፍል የተደረገ ተደርጎበታል።

ለሁሉም ዜጎች የበጀት ፍትሃዊነትና ግልፀኝነት ማሳወቅ ስለሚያስፈልግ እንድሁም በሚተገበሩ የልማት ስራዎች ዜጎች የነቀ ተሳትፎ ማድረግ ስላለባቸው የበጀት መግለጫው እንደሚከተለው ቀርበል።

የዞን ማዕከል ዞናዊ ተቋማትን፣ ዞናዊ ፕሮጀክቶችንና ሴክተር መስሪያ ቤቶች ጨምሮ 1,175,622,598 ብር

1. የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር የበጀት ድርሻ 1,011,844,596 ብር

2. የዌራ ወረዳ የበጀት ድርሻ 442,872,559 ብር፤

3. የዌራ ዲጆ ወረዳ የበጀት ድርሻ 361,129,215 ብር፤

4. የአቶቲ ኡሎ ወረዳ የበጀት ድርሻ 302,049,926 ብር በመሆን ድርሻቸውን አውቀዋል።

የሀላባ ዞን ዋና አስተዳደር የተከበሩ አቶ ሙህድን ማጠቃለያ ባደረጉት ወቅት ህብረተሰቡ በአንድም በሌላ የሚያነሳቸውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዲፈታ የውስጥ ገቢ ማሳደግ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ መስረት እንደሚገባ ገልጸዋል።

የዞኑን የውስጥ ገቢ አሟጦ በመሰብሰብ የሕዝባችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል።

አክለውም የተመደበው ውስን የመንግስት በጀት ለታለመለት ዓላማ ብቻ ሊውል እንደሚገባ ዋና አስተዳዳሪው አስገንዝበዋል።

በጉባኤው ላይ የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሀላፊና የዞኑ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ መሀመድከማል ኑሪዬ፤የሀላባ ዞን ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ክብርት ወይዘሮ ረውዳ ዘይኔ፣ የክልሉ ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ ወይዘሮ ዘቢባ መሀመድናስር፣ የዞኑ ምክትል አባላትና ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

እንኳን ደስ አላችሁ የዌራ ወረዳ ምክር ቤት በላቀ አፈጻጸም ከዞኑ ከሉ መዋቅሮች 2ኛ ደረጃ  በማውጣት የዕውቅና ሰርተፍኬት ተበረከተ በሀላባ ዞን የዌራ ወረዳ ምክር ቤት በ2018 በጀት ዓመት...
19/08/2026

እንኳን ደስ አላችሁ

የዌራ ወረዳ ምክር ቤት በላቀ አፈጻጸም ከዞኑ ከሉ መዋቅሮች 2ኛ ደረጃ በማውጣት የዕውቅና ሰርተፍኬት ተበረከተ

በሀላባ ዞን የዌራ ወረዳ ምክር ቤት በ2018 በጀት ዓመት ባከናወናቸው ተግባራት የተሻለ አፈጻጸም በማስመዝገብ በዞኑ ከሚገኙ ምክር ቤቶች 2ኛ በመውጣት የዕውቅና ሰርተፊኬት ተሸላሚ ሆኗል።

የዕውቅና ሽልማቱ ቀጣይ ከዚህ የተሸላ ህዝብን ለመገልጋል የሚያናሰሳ ስለሆነ ለተበረከተው የእውቅና ሽልማት ምስጋና አቅርባዋል ።

በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ ደስ አለን !!

በሀላባ ዞን ዌራ ወረዳ አቦክቾ ከተማ ህገወጥ የመሬት ወረራን ለመከላከል የተዘጋጀው የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው በዌራ ወረዳ አቦክቾ ከተማ ህገወጥ የመሬት ወረራን ለመከላከል የተዘጋጀው ...
19/08/2026

በሀላባ ዞን ዌራ ወረዳ አቦክቾ ከተማ ህገወጥ የመሬት ወረራን ለመከላከል የተዘጋጀው የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው

በዌራ ወረዳ አቦክቾ ከተማ ህገወጥ የመሬት ወረራን ለመከላከል የተዘጋጀው የንቅናቄ መድረክ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል

ለመድረኩ የተዘጋጀውን ሰነድ የዌራ ወረዳ ከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሰልማን ጡሜቦ እየቀረቡ ይገኛሉ

በመድረኩ ላይ የዌራ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ምክትል እና ፖለቲካ፣ አቅም ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ጀማል አህመድ እና ሌሎችም ባለድርሻ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ ።

Address

Alaba K'ulito

Telephone

+251945849548

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when በሀላባ ዞን የዌራ ወረዳ ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share