07/09/2026
የማንሰራራት ቀንን ምክንያት በማድረግ በሀላባ ዞን በቁሊቶ ከተማ የተሰሩ የመሰረተ ልማት ስራዎች ጉብኝት በማድረግ እየተከበረ ነው
=====
ጳጉሜ 2/2018 በሀላባ ዞን ጳጉሜ 2 "ዘላቂ ልማት ለሀገራዊ ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን የማንሰራራት ቀን ምክንያት በማድረግ የተሰሩ የመሠረተ ልማት ስራዎችን ጉብኝት በማድረግ እየተከበረ ይገኛል።
ከተጎበኙት መሰረተ ልማቶችን መካከል የሀላባ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ግንባታ፣ የሀላባ ዞን አስተዳደር ህጻን፣ በኢንዱስትሪ እና በጥቅል የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች የታዩትን ማንሰራራት ተመልክቷል።
የሀላባ ቁሊቶ ከተማ መሶብ አንድ አገልግሎት፣ ከሰንበት እስከ ሰንበት ገበያ ማዕከል ግንባታ፣ የሀላባ ቁሊቶ ከተማ ግርን ኤርያ፣ ጎበኝተዋል።
"የማንሰራራት ቀን" ሲከበር ሀገራችን ኢትዮጵያ ብሎም ክልላችን እና ዞናችን ከጎታች የእድገት ማነቆዎች ተላቅቃ ወደ ማንሠራራት ጉዞዋን ያፋጠነችበት ዓመት ለመሆኑ ማሳያ መሆኑን በጉብኝቱ ተመላክቷል።
በከተማ ስለተከናወኑ የልማት ስራዎች ስለተገኙ ውጤቶች ገለጻ ሰጥተዋል።
በከተማ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች የስራ እድል በመፍጠር እና የወረዳውን ኢኮኖሚ በማጠናከር የህዝቡን ኑሮ ለማሻሻል ያላቸው አስተዋጽኦ ተገልጿል።
ከተማ የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በማንሰራራት ጉዞዋ በርካታ ፕሮጀክቶችን ፈጽማለች፣ እያከናወነችም ትገኛለች ተብለዋል።
ከተማዋ በልማት የማንሰራራት ጉዞዋና በልማት ጉዞዋና በለውጥ አብሳሪ የቁርጥ ቀን ልጆቿ ጥረት ተደርገዋል ተብለዋል።
የተጀመሩ የልማት ሥራዎች በተጀመሩበት ፍጥነትና ጥራት እንዲጠናቀቁ እና ህዝብን በሰፊው ተሳትፎ የሀገር መንሰራራት ጉዞ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።
የመንሰራራት ቀን የተሰሩ ልማቶችን የምንገመግምበት፣ የተገኙ ስኬቶችን የምናጎለብትበት እና ለቀጣይ እድገት በጋራ ቁርጠኝነታችንን የምናረጋግጥበት ዕለት መሆኑም ተመልክቷል።
በዞኑ "የማንሰራራት ቀንን" ምክንያት በማድረግ የሀላባ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ መሀመድአሚን መሀዲ፣ የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ገመዳ መሀመድ፣ የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ምክትል የመንግስት ተጠሪዎች አቶ ራመቶ መሀመድ እና አቶ አደም ጀማል፣ ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል።
ሲል የሀላባ ዞን መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ዘግቧል።