የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት-Halaba K'Ulito City Admin.Finance Office

  • Home
  • Ethiopia
  • Alaba K'ulito
  • የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት-Halaba K'Ulito City Admin.Finance Office

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት-Halaba K'Ulito City Admin.Finance Office Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት-Halaba K'Ulito City Admin.Finance Office, Public & Government Service, Alaba K'ulito.

This is an official page of Halaba Kullito city finance office, to get more information about the financial administrations & other related news, please follow the page!!

21/08/2026
“በፓርቲው መሪነት ህብረተሰቡን በማሳተፍ የተመዘገቡ ተጨባጭ ስኬቶች እንዳሉ ሁሉ፡ አሁንም ቢሆን ከህዝባችን ፍላጎትና ከሚቀርቡልን ተንከባላይ የቤት ሥራዎች አንጻር ብዙ መስራት ይጠበቅብናል”~...
20/08/2026

“በፓርቲው መሪነት ህብረተሰቡን በማሳተፍ የተመዘገቡ ተጨባጭ ስኬቶች እንዳሉ ሁሉ፡ አሁንም ቢሆን ከህዝባችን ፍላጎትና ከሚቀርቡልን ተንከባላይ የቤት ሥራዎች አንጻር ብዙ መስራት ይጠበቅብናል”

~ አቶ አብዲልመጂድ ፊጣሞ ~
(የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ የመንግሥት ዋና ተጠሪ)

በዛሬው ዕለት በተካሄደው የከተማ አስተዳደሩ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የ2018 ዓ/ም የሥራ አፈጻጸም ማጠቃለያና የ2019 በጀት ዓመት ፈጻሚ ማዘጋጃ መድረክ ላይ ከተናገሩት¦

በቁሊቶ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ፡ የፋይናንስ ቤተሰብ አደረጃጀት፡ በበጀት ዓመቱ የላቀ አፈጻጸም በማስመዝገብ የዋንጫና የሰርተፍኬት ተሸላሚ ሆነ።ነሃሴ 14/2018 ዓ/ምሀላባ ቁሊቶ“ሁሉ አቀፍ እ...
20/08/2026

በቁሊቶ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ፡ የፋይናንስ ቤተሰብ አደረጃጀት፡ በበጀት ዓመቱ የላቀ አፈጻጸም በማስመዝገብ የዋንጫና የሰርተፍኬት ተሸላሚ ሆነ።

ነሃሴ 14/2018 ዓ/ም
ሀላባ ቁሊቶ

“ሁሉ አቀፍ እድገት ለሁለንተናዊ ከፍታ” በሚል መሪ ቃል በዛሬው ዕለት በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት አዘጋጅነት በተካሄደው የ2018 ዓ/ም የሥራ አፈጻጸም ማጠቃለያ እና የ2019 በጀት ዓመት ፈጻሚ ማዘጋጃ መድረክ ላይ፡ የፋይናንስ ቤተሰብ የብልጽግና አደረጃጀት፡ በበጀት ዓመቱ የተሻለ አፈጻጸም በማምጣት የዋንጫና የሰርተፍኬት ተሸላሚ መሆን ችሏል።


◉◉◉◉◉◉
➔ በቴሌግራም ቻናላችን – https://t.me/halabakullitofinance

➔ በፌስቡክ ገፃችን – https://www.facebook.com/halabakullitofinance

“የተሻለ አፈጻጸም የውጤታማነት መለኪያ ብቻ ሳይሆን የጽኑ አደረጃጀትና የጠንካራ ህብረት ሕያው ማሳያ ነው” ፦ አቶ ሱልጣን ኢ/ሁሴንነሃሴ 14/2018 ዓ/ምሀላባ ቁሊቶ“ሁሉ አቀፍ እድገት ለሁ...
20/08/2026

“የተሻለ አፈጻጸም የውጤታማነት መለኪያ ብቻ ሳይሆን የጽኑ አደረጃጀትና የጠንካራ ህብረት ሕያው ማሳያ ነው” ፦ አቶ ሱልጣን ኢ/ሁሴን

ነሃሴ 14/2018 ዓ/ም
ሀላባ ቁሊቶ

“ሁሉ አቀፍ እድገት ለሁለንተናዊ ከፍታ” በሚል መሪ ቃል በዛሬው ዕለት በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት አዘጋጅነት በተካሄደው የ2018 ዓ/ም የሥራ አፈጻጸም ማጠቃለያ እና የ2019 በጀት ዓመት ፈጻሚ ማዘጋጃ መድረክ ላይ፡ በከተማ አስተዳደሩ የኢኮኖሚ ዘርፍ ቁጥር-1 ህብረት የተሻለ አፈጻጸም በማስመዝገቡ፡ የ1ኛ ደረጃ የክብር ዋንጫ፣ የውጤታማነት ማረጋገጫ የእውቅና ሰርተፊኬት እና ለቀጣይ ጉዞ ስንቅ የሚሆኑ ልዩ ልዩ የሥራ ቁሳቁሶች ተሸላሚ መሆን ችሏል።

በመድረኩ ላይ ሽልማቱን የተቀበሉት የብልጽግና ህብረቷ ሰብሳቢ እና የማዘጋጃ ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሱልጣን ኢ/ሁሴን እንደተናገሩት፡ “​የተሻለ አፈጻጸም በድንገት የሚገኝ ሳይሆን የዕለት ተዕለት ትጋት ያልተቆጠበ ቁርጠኝነት እና የጠበቀ የቡድን ሥራ ያፈራው ጣፋጭ ፍሬ ነው” ብለዋል።

​ይህ ውጤት የሁሉም አባላት የአመራሮችና የመላው ኢኮኖሚ ቁጥር-1 ህብረት የጋራ የቅንጅት ፍሬ መሆኑን በመግለጽ ምስጋናቸውን ያቀረቡት አቶ ሱልጣን፡ የህብረቷ አባላትና አመራሮች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸውንም አስተላልፈዋል።

ይህም ለቀጣዩ ጉዞ ትልቅ ሞራልና ስንቅ በመሆኑ፡ በ2019 በጀት ዓመት ከዚህ የበለጠ ድንቅ ስኬት እንደሚያስመዝግቡ ያላቸውን ሙሉ ተስፋና እምነት ገልጸዋል።

❝ለላቀ አፈጻጸም የዕውቅናና የሽልማት መርሃ-ግብር❞‎‎በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ የፐብሊክ ሰርቫንቲ ግንባር የብልጽግና ህብረትና ቤተሰቦች የእውቅናና የሽልማት መርሃ ግብር...
20/08/2026

❝ለላቀ አፈጻጸም የዕውቅናና የሽልማት መርሃ-ግብር❞

‎በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ የፐብሊክ ሰርቫንቲ ግንባር የብልጽግና ህብረትና ቤተሰቦች የእውቅናና የሽልማት መርሃ ግብር ተካሄደ።

‎በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የ2018 ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም ማጠቃለያና የ2019 በጀት ዓመት ፈጻሚ ማዘጋጃ መድረክ በተሳካ ሁኔታ ተካሂዷል።

‎በመድረኩ የ2018 ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም በሰፊው የተገመገመ ሲሆን በዓመቱ የተመዘገቡ ውጤቶች የተስተዋሉ ጥንካሬዎች ያጋጠሙ ችግሮችና በቀጣይ የሚሻሻሉ የሥራ አቅጣጫዎች በጥልቀት ተዳስሰዋል።

‎በተጨማሪም የ2019 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም በተሻለ የአፈጻጸም ባህል በተጠናከረ የቡድን ሥራ በተጠያቂነትና በውጤት ተኮር አመራር ለመፈጸም የሚያስችሉ የትኩረት አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።

‎በዚህ መድረክ ከተለያዩ የሥራ መስኮች በላቀ ትጋት በተሻለ አፈጻጸምና በሚታይ ውጤት የተለዩ የፐብሊክ ሰርቫንቲ ግንባር የብልጽግና ህብረትና ቤተሰቦች ተለይተው ዕውቅናና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

‎የእውቅናና የሽልማት መርሃ ግብሩ በሥራ የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ አካላትን ለማበረታታት ብቻ ሳይሆን ሌሎችም በተሻለ መንገድ እንዲሠሩ ተሞክሮ እንዲለዋወጡና የውጤት ባህልን እንዲያጎለብቱ የሚያነሳሳ እንደሆነ የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አ/መጅድ ፊጣሞ ገልጿል።

‎የተቋማትና የፓርቲ ሥራ አፈጻጸምን ወደተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር የአመራር የፐብሊክ ሰርቫንት የአባላትና የቤተሰቦች ትብብርና ተሳትፎ ወሳኝ ነውም ተብሏል።

በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር የ2018 በጀት ዓመት የኢንስፔክሽን ግኝቶች በጥንካሬና በጉድለት ቀርበው ውይይት ተደረገ።ነሃሴ 14/2018 ዓ/ምሀላባ ቁሊቶ‎‎በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ...
20/08/2026

በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር የ2018 በጀት ዓመት የኢንስፔክሽን ግኝቶች በጥንካሬና በጉድለት ቀርበው ውይይት ተደረገ።

ነሃሴ 14/2018 ዓ/ም
ሀላባ ቁሊቶ

‎በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ የ2018 በጀት ዓመት የኢንስፔክሽን ግኝቶች በጥንካሬና በጉድለት ተለይተው ቀርበው ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

‎የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ኢንስፔክሽን ኮሚሽን በ2018 በጀት ዓመት በተለያዩ የሥራ መስኮች ያከናወናቸውን የኢንስፔክሽን ሥራዎች ውጤትና ግኝቶች መነሻ በማድረግ የተገኙ ጠንካራ ጎኖችን እንዲሁም ማሻሻያ የሚፈልጉ ጉድለቶችን በመለየት ለመድረኩ አቀረበ።

‎የኢንስፔክሽን ግኝቶች ሪፖርት በአቶ አህመድ ሎብሶ በዝርዝር የቀረበ ሲሆን በሪፖርቱም በ2018 በጀት ዓመት በተከናወኑ የኢንስፔክሽን ሥራዎች የታዩ አፈጻጸሞች የተገኙ ጥንካሬዎች ክፍተቶችና ጉድለቶች በዝርዝር ቀርበዋል።

‎በ2018 በጀት ዓመት በሥራ አፈጻጸም የተሳኩ ተግባራትን በመለየት እንዲጠናከሩ ማድረግ የታዩ ክፍተቶችን በጋራ በመወያየት የመፍትሔ አቅጣጫ ማስቀመጥ እና በቀጣይ የሥራ ዘመን የተሻለ አፈጻጸም ማስመዝገብ የሚያስችሉ ማሻሻያዎችን ማስቀመጥ ላይ ኢንስፔክሽን ጽ/ቤቱ ትኩረት አድርጓል።

‎በሪፖርቱ የተገኙ ጥንካሬዎች በቀጣይ ሥራ እንዴት ሊጠናከሩ እንደሚችሉ የታዩ ጉድለቶችና ክፍተቶች ምን ምክንያት እንደተፈጠሩ እና በ2019 በጀት ዓመት እንዳይደገሙ ምን ዓይነት የማስተካከያ እርምጃዎች መወሰድ እንዳለባቸው በስፋት ዉይይት ተደርጓል።

20/08/2026
በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሀላፊ በአቶ አ/መጅድ ፊጣሞ የተመራው  ከተለያዩ አደረጃጀቶች የተውጣጡ ቡድን  የመስክ ምልከታ ጀምሯል!!!‎‎በሀላባ ቁሊቶ ከተማ የ...
20/08/2026

በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሀላፊ በአቶ አ/መጅድ ፊጣሞ የተመራው ከተለያዩ አደረጃጀቶች የተውጣጡ ቡድን የመስክ ምልከታ ጀምሯል!!!

‎በሀላባ ቁሊቶ ከተማ የ2018 ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም ማጠቃለያ እና የ2019 ዓ.ም የፈጻሚ ማዘጋጃ መድረክ አስመልክቶ የመስክ ምልከታ ተጀምሯል

‎በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር የብልጽግና ፓርቲ የ2018 ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም ማጠቃለያ እና የ2019 ዓ.ም የፈጻሚ ማዘጋጃ መድረክ እየተካሄደ ሲሆን በመድረኩ አካል በከተማዋ የተከናወኑ የተለያዩ የልማት ሥራዎች የመስክ ምልከታ እየተደረገ ይገኛል።

‎በመስክ ምልከታው የ2018 ዓ.ም በከተማዋ የተከናወኑ የልማት ፕሮጀክቶችና የሕዝብን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል የተደረጉ የተለያዩ ጥረቶች በተግባር እየተጎበኙ ነው።

‎የመስክ ምልከታው ከ2018 ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም የተገኙ ልምዶችን በመውሰድ፣ በ2019 ዓ.ም የታቀዱ ሥራዎች በተሻለ አፈጻጸም እንዲመሩ አቅጣጫ ለማስቀመጥም ያግዛል።

የህዝብ ድምፅ በመሆን የላቀ ውጤት ያስመዘገበው የሀላባ ቁሊቶ ከተማ ምክር ቤት የዋንጫ ተሸላሚ ሆነ!!!ለተከታታይ ሁለት ቀናት ስካሄድ የቆየው የሀላባ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 11ኛ ዓመት የ...
19/08/2026

የህዝብ ድምፅ በመሆን የላቀ ውጤት ያስመዘገበው የሀላባ ቁሊቶ ከተማ ምክር ቤት የዋንጫ ተሸላሚ ሆነ!!!

ለተከታታይ ሁለት ቀናት ስካሄድ የቆየው የሀላባ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 11ኛ ዓመት የስራ ዘመን 21ኛ መደበኛ ጉባኤ ዛሬ ተጠናቋል።

በዚህ ታሪካዊ ጉባኤ ላይ የሀላባ ቁሊቶ ከተማ ምክር ቤት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ባስመዘገበው አንጸባራቂ የሥራ አፈጻጸም በዞኑ ከሚገኙ ምክር ቤቶች ቀዳሚ በመሆን የ1ኛ ደረጃን በመያዝ የዋንጫና የምስክር ወረቀት (ሰርተፍኬት) ተሸላሚ ለመሆን በቅቷል።

ይህ ደማቅ ውጤት በአጋጣሚ የመጣ ሳይሆን ምክር ቤቱ የህዝብ ድምፅ መሆን በመቻሉ የተገኘ ነው።

በተለይም ህዝባችን የሚያነሳቸው መሰረታዊ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ እንዲያገኙ ምክር ቤቱ ከከተማ አስተዳደሩ እና ከከተማው ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ጋር በፈጠረው ጠንካራ ቅንጅትና መናበብ እጅግ አበረታችና ውጤታማ ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል።

ይህን እውቅና ተከትሎ የምክር ቤቱ ዋና አፈ-ጉባኤ የተከበሩ አህመዲን ሁሴን ባስተላለፉት መልዕክት ለዚህ ስኬት መገኘት የድርሻቸውን ላበረከቱ አካላት ሁሉ ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበው ይህ የተሰጠን ክብርና ሽልማት በቀጣይ ለህዝባችን የተሻለ ስራ እንድንሰራና ሌት ተቀን በትጋት እንድናገለግል ትልቅ አቅምና የሞራል ስንቅ እንደሚሆንና ለበለጠ ስራም ዝግጁ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

የሀላባ ዞን ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት አጸደቀ።ነሀሴ 13/2018 ዓ/ምየሀላባ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 11ኛ የስራ ዘመን 21ኛ...
19/08/2026

የሀላባ ዞን ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት አጸደቀ።

ነሀሴ 13/2018 ዓ/ም

የሀላባ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 11ኛ የስራ ዘመን 21ኛ መደበኛ ጉባዔ የሀላባ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ሀላፊ ወወይዘሮ ዙበይዳ ገለቶ እና የዞኑ ምክር ቤት የኢኮኖሚ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በተከበሩ አቶ አህመዲን መሀመድ አማካይነት የዞኑ አስተዳደር የ2018 በጀት ዓመት የበጀት ረቂቅ አዋጅ እና የበጀት መግለጫ ለዞኑ ምክር ቤት ቀርበዋል።

በዚህም የዞኑን 2019 በጀት አመት የልማትና የመልካም አስተደደር ማስፈፀሚያ የምሆን በጀት ከክልል ግምጃ ቤት እና ከሁሉም የገቢ ምንጮች የተገኘ 3,293,518,873 ብር በጀት አጽድቋል፡፡

የ2018 በጀት ዓመት ዞናዊ ተቋማትና ዞናዊ ፕሮጀክቶች 3ቱም ወረዳዎችና የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር በቀመር በጀት ክፍፍል ተደርገዋል።

ዞናዊ ተቋማት፦ የሀላባ ቁሊቶ አጠቃላይ ሆስፒታል፣ የበሸኖ የመጀመሪያ ሆስፒታል እና የቡራቲቾ አዳሬ ት/ቤት እና ሌሎችም ዞናዊ ፕሮጀክቶች እንድሁም የዞን ማዕከል መምሪያዎች የበጀት ድርሻ በየደረጃው ባሉ ባለድርሻ አካለት የቀመር መረጃን መሰረት በማድረግና ልማትን በሚያፈጥኑ ዘርፎች ትኩረት በመስጠት ክፍፍል የተደረገ ተደርጎበታል።

ለሁሉም ዜጎች የበጀት ፍትሃዊነትና ግልፀኝነት ማሳወቅ ስለሚያስፈልግ እንድሁም በሚተገበሩ የልማት ስራዎች ዜጎች የነቀ ተሳትፎ ማድረግ ስላለባቸው የበጀት መግለጫው እንደሚከተለው ቀርበል።

የዞን ማዕከል ዞናዊ ተቋማትን፣ ዞናዊ ፕሮጀክቶችንና ሴክተር መስሪያ ቤቶች ጨምሮ 1,175,622,598 ብር

1. የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር የበጀት ድርሻ 1,011,844,596 ብር

2. የዌራ ወረዳ የበጀት ድርሻ 442,872,559 ብር፤

3. የዌራ ዲጆ ወረዳ የበጀት ድርሻ 361,129,215 ብር፤

4. የአቶቲ ኡሎ ወረዳ የበጀት ድርሻ 302,049,926 ብር በመሆን ድርሻቸውን አውቀዋል።

የሀላባ ዞን ዋና አስተዳደር የተከበሩ አቶ ሙህድን ማጠቃለያ ባደረጉት ወቅት ህብረተሰቡ በአንድም በሌላ የሚያነሳቸውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዲፈታ የውስጥ ገቢ ማሳደግ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ መስረት እንደሚገባ ገልጸዋል።

የዞኑን የውስጥ ገቢ አሟጦ በመሰብሰብ የሕዝባችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል።

አክለውም የተመደበው ውስን የመንግስት በጀት ለታለመለት ዓላማ ብቻ ሊውል እንደሚገባ ዋና አስተዳዳሪው አስገንዝበዋል።

በጉባኤው ላይ የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሀላፊና የዞኑ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ መሀመድከማል ኑሪዬ፤የሀላባ ዞን ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ክብርት ወይዘሮ ረውዳ ዘይኔ፣ የክልሉ ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ ወይዘሮ ዘቢባ መሀመድናስር፣ የዞኑ ምክትል አባላትና ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

Address

Alaba K'ulito

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት-Halaba K'Ulito City Admin.Finance Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share