25/08/2026
ክብርት ወ/ሮ ሒክማ ከይረዲን የኢፌዴሪ የሴቶችና ህፃናት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ!ከሀላባ ዞን ቡራቲቾ አዳሪ ትምህርት ቤት ለተመዘገበው 🌟 ታሪካዊ ድል የእንኳን ደስ አላችሁ! መልእክት አስተላልፏል🎉
እንኳን ደስ አለን! እንኳን ደስ አላችሁ! 🎉
🌟 ታሪካዊ ድል ከሀላባ ዞን ቡራቲቾ አዳሪ ትምህርት ቤት!
ዛሬ የምንገልጸው ደስታ የአንድ ትምህርት ቤት ውጤት ብቻ አይደለም,,,, የትጋት,,, የትዕግሥት,,, የትብብር እና ለትውልድ የሚተላለፍ ትልቅ ስንቅ ነው, ,,,,!
ትምህርት የሕይወት ለውጥማምጫ ,,, የብሩህ ነገ መሠረትና የሁሉም ዕድገት መክፈቻ ቁልፍ ነው,,,,,,የሕዝባችንን ብሎም የሀገራችንን ቀጣይ ዕጣ ፈንታ የሚወስኑ የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልዶች መፍለቂያ የሆነው,,,,, የቡራቲቾ አዳሪ ትምህርት ቤት ሚስጥር ነው,,,,ተከታታይ ዓመታት 100% ተማሪዎቹን ያሳለፈበትን ታሪካዊና አኩሪ ውጤት በግንባር ቀደምትነት አሻራውን በታሪክ መዝገብ ውስጥ ተፅፏል, ,,,
የሀላባ ቡራትቾ አዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪዎች፣ መምህራንና አመራሮች፣ የዞኑ አመራሮች፣ የሀላባ ልማት ማህበር እንዲሁም የተማሪዎቻችሁ ወላጆች፤
የሀላባ ቡራትቾ አዳሪ ትምህርት ቤት ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ 100% የተማሪዎች ማለፍ ማስመዝገቡ በእውነት የሀላባ ህዝብ የሚኮራበት ታላቅ ስኬት ነው። 🇪🇹❤️
ውድ ተማሪዎች፣ ይህ ውጤት የእናንተ ትጋት ፍሬ ነው,,,, ዛሬ ያገኛችሁትን ስኬት የመጨረሻ መዳረሻ ሳይሆን ወደ ትልቅ ህልም የሚያሻግራችሁ መነሻ አድርጉት,,, የሀላባ ልጆች በትምህርት አውራ ንግስቶች ሆናችሁ ለኢትዮጵያ ተማሪዎች አሳይታችኋል,,,,🇪🇹❤️
ውድ መምህራንና የትምህርት ቤቱ አመራሮች,, ከማስተማር በላይ ተማሪዎቻችሁን ለስኬት አዘጋጅታችኋል,,, የዛሬው 100% ውጤት በእናንተ ላይ የተጣለውን ኃላፊነት በትጋት መወጣታችሁን የሚያረጋግጥ ታላቅ ምስክር ነው, ,,❤️
ለዞኑ አመራሮች,,,,, ለሀላባ ልማት ማህበር,,, ትምህርት ቤትን መደገፍ ማለት የዛሬን ተማሪ ብቻ መደገፍ ሳይሆን የነገን ሀገር መገንባት ነው,,,,ለትምህርት እና ለተማሪዎች የሰጣችሁት ትኩረት ዛሬ በውጤት ምላሽ አግኝታችኃል በርቱ ድጋፋቹ ተጠናክሮ ይቀጥል, ,,,
ውድ ወላጆች,,, የልጆቻችሁን ህልም ከራሳችሁ ህልም አስበልጣችሁ ደግፋችኋል,,, ዛሬ የምትደሰቱበት ውጤት የእናንተም ድርሻ ያለበት ድል ነው ,,ልጆችን ኮትኩቶ ማብቃት የዘራችሁትን በውጤት አንስታችኃል!
በትምርት ቤቱ ላይ ድጋፍ ስታደርጉ ለነበራችሁ ሁሉ ባለድርሻ አካላት በሙሉ የላቀ ምስጋናዬን እያቀረብኩ፤
መላው የዞናችን ህዝብ እንኳን ደስ አለን! እንኳን ደስ አላችሁ!!❤
ክብርት ሒክማ ከይረዲን፦የሴቶችና ህፃናት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ!!ያስተላለፉት መልእክት ከማህበራዊ የትስስር ገጻቸው የተወሰደ፣