የሀላባ ዞን ፖሊስ መምሪያ

የሀላባ ዞን ፖሊስ መምሪያ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የሀላባ ዞን ፖሊስ መምሪያ, Government Official, Alaba K'ulito.
(1)

ኮማንደር ኑርዬ ከድር በወቅታዊና በሀገራዊ ጉደዮች ዙሪያ ከማኔጅመንት አባለት ጋር ውይይት አደረገ⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳ጳጉሜ 2/2018 ዓም ሀላባ ዞን ፖሊስ መምሪያ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክል...
07/09/2026

ኮማንደር ኑርዬ ከድር በወቅታዊና በሀገራዊ ጉደዮች ዙሪያ ከማኔጅመንት አባለት ጋር ውይይት አደረገ

⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳
ጳጉሜ 2/2018 ዓም ሀላባ ዞን ፖሊስ መምሪያ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በሀላባ ዞን በወቅታዊ ጉደዮች ዙሪያ፦ በቁሊቶ ከተማ ህገወጥ ግንባታ መከላከልን በተመለከተ፣ ፣በሀሰተኛ ሚዲያ፣የሀላባ ቁሊቶ ከተማ ፀጥታ በተመለከተ ፣መረጃ ከመሰብሰብና ክትትል በማድረግ ለሚመለከተው በወቅቱ ከማስተላለፍ ጋር በተመለከተ ከዞኑ ፖሊስ መምሪያ ማኔጅመንት አባለት ጋር ኮማንደር ኑርዬ ከድር ውይይት አድርገዋል።

በዞኑ ዋና ከተማ በሆነችዉ በቁሊቶ ከተማ የህገወጥ መሬት ወረራንና ህገወጥ ግንበታን ለመከላከልና ለመግታት ከዞኑንና ከክልል ከተወጣጡ ግብረ ሃይሎች ጋር ተቀናጅተው ወደ ስራ መግባታቸውን ኮማንደሩ ገልፀዋል።

ግብረሃይሉ ህገወጥ መሬት ወረራና ህገወጥ ግንባታ ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሚያደርገው ክትትልን ለመደገፍ በዞኑ መዋቅር ስር የሉ የፖሊስና የፀጥታ አካለት በግብረ ሃይሎች ሆኖ ድጋፍ እያደረጉ ስለመሆናቸው ተነግሯል።

ኮማንደሩ አክለው ህገወጥ የከተማ መሬት ወረራና ህገወጥ ግንባታ ለከተማው እድጋትና ለመሠረተ ልማት መስፋፋት አዳጋች መሆኑን በመግለፅ ህገወጥ ግንባታና ህገወጥ መሬት ወረራን ለመከላከል ሁሉም ባለድርሻ አካለት የበኩላቸውን እንድወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

ሀሰተኛ ሚዲያ፦ግለሰቦች የራሳቸውንና ግብረአበሮቻቸውን ጥቅምና የግል ፍላጎታቸውን ለመራመድ ሆን ብለው ሀሰተኛ ሚዲያ ወይም ጭንብል አካውንት ከፍተው የዞኑን መንግስትና ህዝብን ለማደናገር የፊት አመራሮችና አስተባባሪዎች ስም መጥፋትና ዛቻ እየተደረጉ መሆናቸውን ኮማንደሩ ተነግሯል።

በሀሰተኛ ሚዲያ መሰራጨትና በሀሰተኛ ሚዲያ ግለሰብን መስደብ ወይም በአሉባልታ ሰውን ስም መጥፋት ወንጀል መሆኑን ገልፀዋል።

በሀሰተኛ ሚዲያ በዞኑ ህዝብና መንግስት የተሰሩ በረከተ መሠረተ ልማቶችን ለመጥፋትና ስም ለማጠልሸት እንቅስቃሴ በሚያደርጉ አካለት ለይ እርምጃ ለመውሰድ ግብረሃይል ተቋቋመው ወደ ስራ መግባቱን ገልጾ በሀሰተኛ ሚዲያ እንደፈለጉ የሚሳደቡ ሃይሎች አደብ እንድገዙ ኮማንደሩ አሳስበዋል።

መረጃ፦መረጀ ህይወት ነው። መረጀ ለፖሊስ ደም ስር እንደሆነ ኮማንደር ኑርዬ ከድር አብራርተዋል።

ትክክለኛና ወቅቱን የጠበቀ መረጀ በመሰብሰብ ለሀገርና ለህዝብ ሠላም ቅድሚያ ተሰጥተው መስራት እንደሚገባ ኮማንደሩ ተነግሯል።

በመጨረሻም የሀገራችንና የህዝባችን ሠላም መጠበቅ የፖሊስና የፀጥታ አካለት ብቻ አለመሆኑን በመግለፅ የሀገርን ሠላምና ደህንነት መጠበቅ የሁሉም ነው ሁሉም ለሠላም ዘብ መቆም እንደለበት ኮማንደሩ አሳስበዋል።

ወንጀልን በጋራ እንከላከል!!

ለመንገድ ትራፊክ ቁጥጥርና አድማን ለመበተን የሚያግዙ ተሽከርካሪዎች ርክክብ ተደረገ።‎***‎አዲስ አበባ፤ ጳጉሜ 02 ቀን 2018 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፡- የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መ...
07/09/2026

ለመንገድ ትራፊክ ቁጥጥርና አድማን ለመበተን የሚያግዙ ተሽከርካሪዎች ርክክብ ተደረገ።
‎***
‎አዲስ አበባ፤ ጳጉሜ 02 ቀን 2018 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፡- የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል አስራት ደኔሮ፣ የወንጀል መከላከል ም/ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ም/ኮሚሽነር ቶፊክ መድድ፣ የወንጀል ምርመራ ም/ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ም/ኮሚሽነር እርዚቅ ኢሳና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንዲሁም የማዕከል ዋና መምሪያ ኃላፊዎች በተገኙበት ነው የተሽከርካሪዎቹ ርክክብ የተከናወነው።

የዋና ጠቅላይ መምሪያው አዛዥ ሌ/ጀኔራል አስራት ደኔሮ በቁልፍ ርክክቡ ወቅት እንደገለፁት በተቋሙ እየተከናወኑ ካሉ ዘርፈ ብዙ የሪፎርም ስራዎች መካከል አንዱ ዘመናዊ ተሽከርካሪዎችን ለወንጀልና ትራፊክ መከላከልና ምርመራ ስራዎች መጠቀም መሆኑን ጠቁመው፤ ከተለያዩ ሀገራት ለሚመጡ መሪዎችና ለከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የአጀብ አገልግሎት ለመስጠት፤ የትራፊክ እንቅስቃሴዎችን ለማሳለጥና ለመቆጣጠር ይረዳ ዘንድ ዋና ጠቅላይ መምሪያው 10 ዘመናዊ የሞተር ሳይክሎችን ለትራፊክ ቁጥጥር ዋና መምሪያ እንዲሁም አንድ ለአድማ ብተና የሚውል በቴክኖሎጂ የዳበረ ተሽከርካሪን ለአድማ ብተና ም/ዋና መምሪያ ማስረከቡን ገልፀዋል።

ሌ/ጄነራል አስራት አክለውም ሞተር ሳይክሎቹ በአዲስ አበባ ከተማ የሚደርሰውን የመንገድ ላይ የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ፣ ትራፊክ ፖሊስ የማይደርስባቸውን አካባቢዎች ለመቃኘትና የሚታዩ የደንብ መተላለፎችን ለመቆጣጠር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው የገለጹ ሲሆን በተጨማሪም የአድማ ብተና ተሽከርካሪው በከተማችን የሚፈጠሩ ህገ ወጥ እንቅስቃሴዎችና አድማዎች ለመበተንና ለመቆጣጠር ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለው ተናግረዋል።

‎በቁልፍ ርክክቡ የተገኙት የዋና ጠቅላይ መምሪያው ከፍተኛ እና ስትራቴጂካዊ አመራሮች በበኩላቸው ሞተር ሳይክሎቹ ለትራፊክ አደጋ መቀነስ ትልቅ እገዛ የሚሰጡ ገልጸው የአድማ ብተናል ተሽከርካሪውም አድመኞችን በሦስት ቀለም በመለየትና በቁጥጥር ስር በማዋል ለወንጀል መከላከሉ ተግባር ትልቅ ድርሻ ይኖረዋልም ብለዋል።
*
ዘገባው:- ኢንስፔክተር እመቤት ሃብታሙ

06/09/2026

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጠቅላይ አዛዥ ክቡር ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል የሠራዊቱን ደም ስር ነው ፖሊስ መሪው/አዛዡን ይመስላል ስበል በምክንያት ነው❤🙏

የክልሉ ፍትህ ሴክተር ተቋማት በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በሀላባ ቁሊቶ ከተማ ያስገነቧቸውን ቤቶች ለባለቤቶቹ አስረከቡ ******ነሃሴ 30/2018)፣የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ሴክ...
05/09/2026

የክልሉ ፍትህ ሴክተር ተቋማት በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በሀላባ ቁሊቶ ከተማ ያስገነቧቸውን ቤቶች ለባለቤቶቹ አስረከቡ
******
ነሃሴ 30/2018)፣የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ሴክተር ተቋማት በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በሀላባ ቁሊቶ ከተማ ያስገነቧቸውን ሁለት የመኖሪያ ቤቶች ለባለቤቶች አስተላልፈዋል።

ተቋሟቱ የአቅመ ደካሞቹን የቤት ግንባታ ሀምሌ 14/2018 ማስጀመራቸው ይታወቃል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ኤርስኖ አቡሬ ተቋሙ የማህበራዊ ሀላፊነት ለመወጣት በርካታ ስራዎችን እየፈፀመ መሆኑን ተናግረዋል።

ደካሞችን ለመደገፍ የተጀመረውን ስራ በማጠናከር የበጎ ፈቃድ ስራዎችን ባህል ማድረግ ይገባል ያሉት ፕሬዝዳንቱ በዛሬው ዕለትም የፍትህ አካላትና የጠቅላይ ፍርድ ቤት በ1.2 ሚሊዮን ብር በጋራ የተገነባ የመኖሪያ ቤት አስረክቧል

የርዕሰ መስተዳድሩ ልዩ አማካሪ ንጉሴ አስረስ ዶ/ር በክልሉ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች በክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ በልዩ ትኩረት እየተመራ ተጨባጭ ውጤት እያመጣ ነው ብለዋል።

በክልሉ በሁሉም ዘርፍ በተሰራው ስራ እምርታ መጥቷል ያሉት ዋና አማካሪው የበጎ ተግባሩ ለዜጎች እፎይታን የሠጠና የመንግስትና የማህበረሰቡን ትስስርን እያጠናከረ መምጣቱን ተናግረዋል።

ህብረተሰቡ በጉልበቱ ፣በእውቀቱና በገንዘቡ ጠንካራ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ተናግረው እስካሁንም በክልሉ ከ13 ቢሊዮን በላይ ብር ተሳትፎ ማድረጉን ተናግረዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ ሀላፊ አቶ አክመል አህመድን በበኩላቸው የመረዳዳትና የመተጋገዝ አካል አንዱ የሆነውን ለአቅመ ደካማ ዜጎች የመኖሪያ ቤት ገንብቶ አስረክቧል ብለዋል።

ግንባታውን የፍትህ ቢሮ እና የማረሚያ ተቋማት በጋራ ያስገነቡት መሆኑን ገልፀው ለቤቱ የሚያስፈልጉ ሙሉ የቤት እቃዎች የተሟላለትና ለእናታችን ለስራ ማስጀመሪያ የሚሆን የ50 ሺ ብር ተጨማሪ ድጋፍ የተደረገላቸው መሆኑን ተናግረዋል።

‎ተግባሩ ዜጎች የተሻለ የኑሮ ሁኔታ እንዲኖራቸው ያደርጋል ያሉት አቶ አክመል በአጠቃላይ ለቤቱ ግንባታና የቤት ቁሳቁስ 1 ሚሊዮን 200ሺ ብር ወጪ መደረጉን ተናግረዋል።

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ገመዳ መሀመድ በበኩላቸው መንግስት በዜጋ ተኮር ስራዎች የተለያዩ ማህበራዊ ችግር ተጋላጭ የሆኑ አረጋዊያንና አቅመ ደካሞችን በመደገፍ ተጠቃሚ ማድረጉንና ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንም ተናግረዋል።

አባታቸውን በሞት ያጡ 4 ልጆችና 2 ወላጅ አልባ በድምሩ የ6 ልጆች አሳዳጊ የሆኑት ወ/ሮ መድሀኒት ሀይሉ መንግስት ያደረገላቸው የተሟላ ድጋፉ ለልጆቻቸውና ለራሳቸው ተስፋን እንደጨመረላቸው ተናግረዋል።

ሁለተኛው የቤት ድጋፍ የተደረገላቸው እናት ልጃቸው የሀገር መከላከያን እያገለገለ መሆኑን የተናገሩት ወ/ሮ አይነቴ ቦጪሶ ደግሞ ድጋፉ ከሰው ጋር እኩል መኖር እንዲችሉ ያስቻላቸው መሆኑን ገልፀዋል።
በቁልፍ ርክክቡ ወቅት የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችና የአካባቢው ነዋሪዎች የተገኙ ሲሆን ለቤቶቹ ግንባታ ስኬት ድጋፍ ያደረጉ አካላትን በሙሉ አመስግነዋል።

የማህበረሰባችን የቆዩ መልካም እሴቶችን በመጠቀም የሀገራችን ዘለቂ ሠላምና ልማትን መረጋገጥ እንደሚቻል ኮማንደር ኑርዬ ከድር ገለፃ። የማህበረሰባችንን ጠንካራ እሴቶችን በመጠቀም በሕዝቦች መካ...
04/09/2026

የማህበረሰባችን የቆዩ መልካም እሴቶችን በመጠቀም የሀገራችን ዘለቂ ሠላምና ልማትን መረጋገጥ እንደሚቻል ኮማንደር ኑርዬ ከድር ገለፃ።

የማህበረሰባችንን ጠንካራ እሴቶችን በመጠቀም በሕዝቦች መካከል መልካም ግንኙነትን፣ ትብብርንና ትስስርን በማጠናከር ሰላምን ማጎልበት እንደሚቻል ተነግሯል።

​ከፋፋይ ድርጊቶችን በመቃወም በዘር፣ በጎሳ ወይም በጥቅም ሰዎችን እርስ በእርስ በማነሳሳትና በማነቃቀስ የነበረውን መልካም ግንኙነት ማበላሸት፣ የሰዎችን ሰላማዊ ህይወትና ህልውና አደጋ ላይ ለመጣል መሞከር ባልተሰጠ ስልጣን ገብቶ የራስን ፍላጎት ለማሟላት የሚደረግ ከንቱ ልፋትና መንከራተት እንደሆነ አብራርቷል ።

​የተሰጠንን ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት በከንቱ ልፋት ከመጠመድ ይልቅ በተሰጠን ስልጣንና ኃላፊነት ወሰን ውስጥ ሆነን፣ ባሉን መልካም እሴቶችን በመጠቀም የህብረተሰባችንን ሰላም፣ ደህንነትና መልካም ግንኙነት ለማረጋገጥ ሊት ከቀን ሳንል በትጋት መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል

​ በጣም ድንቅና ታሪካዊ እሴቶቻችንን በመጠቀም በማህበረሰቡ መካከል መልካም ግንኙነት፣ ትብብርና ትስስር እንዲኖር፤ ሰላምም እንዲጎለብት ማድረግ እየተቻለ—በዘር፣ በጎሳና በጥቅም አንዱን በአንዱ ላይ በማነሳሳትና በማነቋቋር ያለውን መልካም ግንኙነት ማበላሸት እንዲሁም የሰላማዊ ሰዎችን ህይወት ለማጥፋት መሞከር ባልተሰጠን ስልጣን ገብተን የራስን ፍላጎት ለማሟላት የሚደረግ ከንቱ ልፋትና መንከራተት እንደሆነ ተነግሯል።

​ኮማንደሩ አያይዘውም በተሰጠን ስልጣንና ኃላፊነት ወሰን ውስጥ ሆነን፣ ባሉን መልካም እሴቶች ተጠቅመን የህብረተሰባችንን ሰላም፣ ደህንነትና መልካም ግንኙነት ለማረጋገጥ ቀን ከሌት ሳንታክት መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል።

​ባልተሰጠንም ሆነ በሌለን ነገር ላይ ትኩረት አድርገን ጊዜና ጉልበታችንን ከመጥፋት ይልቅ ባለን ነገር ላይ በማተኮር ዕድገትን እና ስኬትን በቀላሉ መምጣት እንደሚቻል ገልጸዋል።

​በተሰጠን ሃለፊነት በአግባቡ ከሰራን ግልጽነትን፣ ፍትህን እና ሰላምን መስፍን እንደሚቻል ገልፀዋል ።
​አላስፈላጊ ግጭትን ማስወገድ ባልተሰጠንም ሆነ በሌለን ጉዳይ ውስጥ ላለመግባት መጣጣር አላስፈላጊ ውዝግብን ይቀርፋል ብለዋል።

ባለን እና በተሰጠን ጸጋና አቅም ላይ አክብረን እና ትኩረት ሰጥተን ብንሰራ ውጤቱ ለሁሉም የሚጠቅም እና የተቀደሰ እንደሚሆን ገልፀዋል ።

​ፈጣሪ ሁላችንንም ወደ ትክክለኛው፣ ወደ ፍቅርና ወደ አስተዋይነቱ መንገድ ይምራን በማለት መልካምና አባታዊ ምክር አስተላልፈዋል።

በሠላምና በፍቅር፤ በአብሮነት በመቻቻል በጋራ በመስራት ለሀገራችን ዘለቂ ሠላም እናረጋግጥ መልዕክታችን ነው!!

ነሐሴ 29/2018 ዓም ሀላባ ቁሊቶ

 !!የቅጥር ማስታወቂያየኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በ2019 በጀት ዓመት የተቋሙን የሰው ኃይል ለማጠናከር በሁሉም ክልሎችና በሁለቱ ከተማ አስተዳደር ውስጥ የሚገኙ ብሔር ብሔረሰብና ሕዝቦች፣ የጾ...
04/09/2026

!!

የቅጥር ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በ2019 በጀት ዓመት የተቋሙን የሰው ኃይል ለማጠናከር በሁሉም ክልሎችና በሁለቱ ከተማ አስተዳደር ውስጥ የሚገኙ ብሔር ብሔረሰብና ሕዝቦች፣ የጾታ ተዋፅዖን ከግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ ተመልምለው በተቋሙ ባሉት ልዩ ልዩ የሥራ ዘርፎች ተመድበው ማገልገል የሚፈልጉ ዕጩ ፖሊሶችን አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል።

ዕጩ ተመልማዮቹ ምልመላው ተጠናቆ ወደ ኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሥልጠና ማዕከል ገብተው ሥልጠና ከመጀመራቸው በፊት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 720/2004 እና ደንብ ቁጥር 268/2005 በሚያዘው መሠረት የ7 ዓመት የሥራ ውል ግዴታ በመግባት በማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ አማካይነት የሚሰጣቸውን ሥልጠና በሚገባ በመከታተል ማጠናቀቅ ይጠበቅባቸዋል፡፡
በሥልጠና ቆይታ ጊዜያቶችም በማሠልጠኛ ትምህርት ቤቱ በኩል የምግብ፣ የመኝታ፣ የሕክምና እና ለሥልጠናው የሚያስፈልጉ የአልባሳት፣ የትምህርት መርጃ መሳሪያዎችና የኪስ ገንዘብ ይሰጣል።

ሥልጠናው ሲጠናቀቅም እያንዳንዱ ተመራቂ በተቋሙ የደመወዝ ስኬል መሰረት ወርሃዊ ደመወዝና የቀለብ ሂሳብ የሚከፈለው ሆኖ በተቋሙ ልዩ ልዩ የስራ አልባሳት፣ ነፃ የሕክምና አገልግሎት፣ በካምፕ የጋራ መኖሪያ ቤት እንዲሁም የትራንስፖርት አገልግሎት ያገኛሉ።

ተመርቀው ፖሊሳዊ የሙያ አገልግሎት በሚያበረክቱባቸው ጊዜያትም በተቋሙ ውስጥ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ማቋቋሚያ አዋጅ፣ ደንብ እና የስልጠና መመሪያዎች መሠረት በሚወጡ መመዘኛዎች አማካኝነት በልዩ ልዩ የትምህርትና ሥልጠና ፕሮግራሞች በመወዳደር ተጠቃሚ የመሆን ሠፊ ዕድል የሚጠብቃቸው መሆኑን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በደስታ ይገለፃል።
የምልመላ መስፈርት (መመዘኛ)

1. ዜግነት ኢትዮጵያዊ የሆነ/የሆነች፣

2. ለሕገ-መንግስንቱና ለሀገሪቱ ሕጎች ተገዥና ታማኝ የሆነ/የሆነች፣

3. ከማናቸውም ደባል ሱሶች የፀዳ/የፀዳች እና መልካም ስነ-ምግባር ያለው/ያላት፣

4. በሚመለመልበት አካባቢ ነዋሪ ስለመሆኑ የቀበሌ መታወቂያ ወይም የፋይዳ መታወቂያ ማቅረብ የሚችል/የምትችል፣

5. ከሚኖርበት ቀበሌ አስተዳደር፣ ከአካባቢው ፖሊስ እና ከተማረበት ትምህርት ቤት የተዘጋጁ ቅፆችን በማስሞላት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል/የምትችል፤

6. በብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች እንዲሁም በሃይማኖት እኩልነት የሚያምን/የምታምን፣

7. ለፖሊስነት የሚያበቃ ሙሉ ጤናማ መሆኑን/መሆኗን በህክምና የተረጋገጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል/የምትችል፣

8. ዕድሜው/ዋ ከ18 እስከ 25 ዓመት ያላነሰና ያልበለጠ/ያልበለጠች፣

9. የማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት አባል ያልሆነ/ያልሆነች፣

10. የትምህርት ደረጃ 10ኛ ክፍል እና በላይ የሆነ/የሆነች እንዲሁም ትምህርት ያጠናቀቀበት ካርድ ዋናውንና የማይመለስ አንድ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችል/የምትችል፣

11. ብዝሃነትንና አካታችነትን ለማረጋገጥ ሲባል ያልተካተቱና አነስተኛ ቁጥር ባለባቸው ብሔሮች አካባቢ ለሚመለመሉ ወጣቶች ቢያንስ 6ኛ ክፍል እና በላይ የሆነ/የሆነች፣

12. ቁመት ለወንድ 1.65 ሜትር በላይ የሆነ፣ ለሴት 1.60 ሜትር በላይ የሆነች፣

13. የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 720/2004 እና ደንብ ቁጥር 268/2005 በተደነገገው መሠረት የ7 ዓመት የሥራ ውል ግዴታ በመግባት ሥልጠናው ሲጠናቀቅ በየትኛውም የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ተቋም የሥራ አከባቢ ተመድቦ/ተመድባ ለመሥራት ፈቃደኛ የሆነ/የሆነች፣
14. ከአሁን በፊት በወንጀል ተከሶ ያልተቀጣ/ያልተቀጣች ወይም የወንጀል ሪከርድ የሌለበት/የሌለባት የአሻራ

በሀላባ ዞን የዌራ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት የ2018 አጠቃላይ ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 መሪ ዕቅድ ዙሪያ ውይይት አደረገ የዌራ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት የ2018 አጠቃላይ ዕቅድ አፈጻጸም...
04/09/2026

በሀላባ ዞን የዌራ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት የ2018 አጠቃላይ ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 መሪ ዕቅድ ዙሪያ ውይይት አደረገ

የዌራ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት የ2018 አጠቃላይ ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 መሪ ዕቅድ ዙሪያ ውይይት አድርገዋል ።

መድረኩን የዌራ ወረዳ ፓሊስ ጽ/ቤት ሀላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ናስር አወል እና የዌራ ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ በረዲን ኬዳ በጋራ መርተዋል ።

የፖሊስ አባላትን የማስፈጸም አቅም በመገንባትና ከሌሎች የፍትህና የፀጥታ ሀይሎች ጋር ቅንጅት በመፍጠር የህብረተሰቡን ደህንነት አስተማማኝ ማድረግ እንደሚገባ አቶ በረዲን አሳስበዋል።

በጀት ዓመቱ የታዩ ጥንካሬዎችን ይበልጥ በማጎልበትና የተለዩ ውስንነቶችን በመቅረፍ በቀጣይ በ2019 በጀት አመት ይበልጥ አጠናክሮ በማስቀጠል ፖሊስ የተጣለብ አደራ በብቃት መወጣት እንዳለበት አሳስበዋል።

ምክትል ኢንስፔክተር ናስር አወል በበኩላቸው የፖሊስ ተቋም የማህበረሰቡ ተግባሩን በሰላም እንዲከውን ማስቻል እና ወንጀልን መከላከል ነው ብለዋል።

ይህን ተቋም የሚመጥን ተግባር በመፈጸም የተጣለብንን ሀላፊነት መወጣት እንደሚገባ በአጽኖት ገልጸዋል።

በተለይም የፖሊስ አባላት የተሰጣቸውን የህዝብ ኃላፊነትን በአቅም መወጣት እንደሚያስፈልግ ምክትል ኢንስፔክተር አያይዘው አሳስበዋል።

የፖሊስ አባላት ተግባራትን በጥበብ በመምራት የወንጀል ድርጊቶችን ቀድመው በመከላከል የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ ቅንጅታዊ ስራን ማጠናከር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በውይይቱ ማጡቃለያ የ2019 መሪ ዕቅድ ዙሪያ ውይይት አድርገው በበጀት ዓመቱ ያለቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የፖሊስ አባላት ዕውቅና በመስጠት መድረከ ተጠናቋል ።

ከመንግስት ሆስፒታል መድኃኒትን የሰረቀዉ ባለሙያ  በቁጥጥር ስር ዋለ።ወንጀሉ የተፈፀመዉ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን በማሌ ወረዳ የኮይቤ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ዉስጥ ነዉ።በ...
04/09/2026

ከመንግስት ሆስፒታል መድኃኒትን የሰረቀዉ ባለሙያ
በቁጥጥር ስር ዋለ።

ወንጀሉ የተፈፀመዉ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን በማሌ ወረዳ የኮይቤ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ዉስጥ ነዉ።

በደቡብ ኦሞ ዞን በማሌ ወረዳ የኮይቤ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለሕዝብ አገልግሎት የተመደበ የመንግሥት መድኃኒትን ከሆስፒታሉ ግቢ ለማስወጣት ሲሞከር አንድ የፋርማሲ ባለሙያ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የማሌ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ገለጸ።

ነሐሴ ቀን 27 /12/ 2018 ዓ.ም ምሽት 2፡00 ሰዓት ገደማ በሆስፒታሉ የፋርማሲ ባለሙያ የሆኑት አቶ ዳግማዊ ዳንኤል የመንግሥት ንብረት የሆኑ መድኃኒቶችን በሁለት ካርቶን በማሸግና በመደራረብ ከሆስፒታሉ ግቢ ለማስወጣት ሲሞክሩ በጥበቃ አባል ክትትል ተይዘዋል ተብሏል።

በወቅቱ የተያዙት መድኃኒቶች
Coartem (6×4) — 15 ስትሪፕ
Coartem (6×2) — 30 ስትሪፕ
Primaquine (7.5 mg) — 20 ስትሪፕ
ጠቅላላ — 65 ስትሪፕ
የሆስፒታሉ ጥበቃ አባል አቶ ናሆም ሶንቤ በወቅቱ ያደረጉት ንቁ ክትትል መድኃኒቶቹ ከሆስፒታሉ ግቢ እንዳይወጡ ለማድረግ የጎላ ሚና እንደነበረው ፖሊስ ጽ/ቤቱ ገልጿል።

ተጠርጣሪው በአሁኑ ወቅት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሲሆኑ፣ በጉዳዩ ላይ ዝርዝር ምርመራ እየተካሄደ ነው። ምርመራው እንደተጠናቀቀም የምርመራ መዝገቡ ለሕግ አካል እንደሚቀርብ ተገልጿል።

የማሌ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ም/ኢ/ር መክት መስፈን በበኩላቸው፣ የተሰጠን ሙያዊ ኃላፊነትና አደራ በመወጣት ለሕዝብ የተመደበን ሀብት ለግል ጥቅም ለማዋል የሚደረጉ ሕገወጥ ተግባራትን ማስቆም እንደሚገባ ጠንካራ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ፖሊስ የሕዝብና የመንግሥት ሀብትን ከሚያባክኑ እና ከሚያለያዩ ተግባራት ለመጠበቅ የሚደረገው ሥራ ከሁሉም የሚጠበቅ የጋራ ኃላፊነት መሆኑን አሳስቧል።ዘገባ፡ የማሌ ወረዳ ህዝብ ግንኙነት ነዉ።

የውንብድና ወንጀል የፈፀሙ ሦስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ።***አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 28 ቀን 2018 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ አባይነህ ሙሉዬ፣ ሹሙየ መልኬ፣ ዮሀንስ አለማየው የተባሉ ግ...
04/09/2026

የውንብድና ወንጀል የፈፀሙ ሦስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ።
***
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 28 ቀን 2018 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ አባይነህ ሙሉዬ፣ ሹሙየ መልኬ፣ ዮሀንስ አለማየው የተባሉ ግለሰቦች የወንጀል ድርጊቱን የፈፀሙት ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ/ም በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ልዩ ቦታው የአዳም ዘውድ ሆቴል አካባቢ ከሌሊቱ 6:00 ሠዓት ገደማ ነው።

የግል ተበዳይ ሲዝናና ቆይቶ ወደ ቤቱ በሚሄድበት ወቅት ተጠርጣሪዎቹ ሲከታተሉት ቆይተው ከኋላው አንገቱን በማነቅና በመደብደብ ራሱን እንዲስት ካደረጉት በኋላ በኪሱ የነበረ 8ሺ ብር፣ ግምቱ 18ሺ 5መቶ የሆነ ሳምሠንግ ስልክና አይፎን ስማርት ሠዓት ወስደውበት ተሠውረዋል።

የግል ተበዳይም እራሱን ስቶ ከወደቀበት ቦታ በመነሳት ንብረቱ እንደተወሰደበት ሲያረጋግጥ ወደ አራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የራስ ደስታ አካባቢ ፖሊስ መምሪያ በመሄድ የተፈፀመበትን የውንብድና ወንጀል ያመለክታል።

ፖሊስም የተሠጠውን ጥቆማ መነሻ በማድረግ ባደረገው ብርቱ ክትትል ወንጀሉ በተፈፀመ በሁለት ሰዓታት ውስጥ ተጠርጣሪዎቹን ከነ ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር ሊያውላቸውም ችሏል።

ተጠርጣሪዎቹ ከተያዙ በኋላ በተደረገባቸው የአካል ፍተሻም ከግል ተበዳይ የወሠዱት ንብረትና ጩቤ ጭምር የተያዘ ሲሆን መዝገብ ተደራጅቶባቸው በምርመራ ላይ እንደሚገኙም የራስ ደስታ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።

የዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ ህገወጦች እንደይጭባረብሩ ጥንቃቄ መደረግ እንደለበት ተገለፀ።በግብይት ወቅት ህብረተሰቡ በህገ-ወጦች እንዳይጭበረበር ጥንቃቄ ማደረግ እንደለበት የሀላ...
03/09/2026

የዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ ህገወጦች እንደይጭባረብሩ ጥንቃቄ መደረግ እንደለበት ተገለፀ።

በግብይት ወቅት ህብረተሰቡ በህገ-ወጦች እንዳይጭበረበር ጥንቃቄ ማደረግ እንደለበት የሀላባ ዞን ፖሊስ መምሪያ አሳስበዋል።

ከፊታችን መስከረም 1 ቀን 2019 ዓ.ም የሚከበረዉን የዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ ህገ_ወጦች ህብረተሰቡን በህገወጥ ገንዘብ ኖቶች በተለያዩ ባዕድ ነገሮች ለማጭበርበር አቅደው ሊወጡ ስለሚችሉ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ በማድረግ እራሱንና ሌሎችንም መጠበቅ እንደሚገባ መምሪያው አሳስበዋል።

በበዓላት ወቅት የሚስተዋሉ እና ህብረተሰቡ ትኩረት በሚያደርገው ግብይቶች ለይ እንደ ዶሮ ተራ፣ ሽንኩርት ተራ፣ በቅቤ ተራ፣ ለይ ጥንቃቄ በማድረግ አጠራጠሪ ነገሮች ከገጠሙ በአከባቢ ለሚገኘው ፖሊስና ለፀጥታ አካለት ርፖርት ማድርግ እንደምገባ የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አሳስበዋል።

በዓሉን ምክንያት በመድረግ የሰዉ በግ፣ፍየል፣ዶሮ ፣በሬ የመሳሰሉ የቤት እንስሳትን ሌቦች ሰርቀዉ ሊየመጡ ስለሚችሉ ግዥ ሲፈፅሙ አጣርተዉ መግዛት እንዳለበት ተገልፆዋል

በበዓል ጊዜ የተሽከርካሪ መብዛት ስለሚኖር አሽከርካሪዎች ለእግረኛ ቅድሚያ በመስጠት፣ርቀትን በመጠበቅና ፍጥነትን በመቀነስ መሽከርከር እንደለበት ፖሊስ መምሪያው አሳስበዋል

ለበዓሉ ዝግጅት ተብሎ የሚጠቀሙ ማንኛውም ነገር ጥንቃቄ መድረግ እንደሚገባ ለምሳሌ የኤሌክትሪክ መሣሪያ የእንጄራ ምድጃ፣ እስቶፊ የኤሌክትሪክ መስመር ተያያዥ ነገሮችን በጥንቃቄ መደረግ እንደለበት አሳስበዋል።

ነሐሴ 28/2018 ዓም ሀላባ ቁሊቶ

Address

Alaba K'ulito

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የሀላባ ዞን ፖሊስ መምሪያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share