04/09/2026
የዌራ ዲጆ ጤና ጽ/ቤት የጤና ቤተሰብ አባላት የነሐሴ ወር ውይይት በልሳነ-ማዕከላዊ 1ኛ ዓመት ቁጥር 5 የአባላት አጀንዳ ላይ የቤተሰብ ውይይት አደረጉ
ነሐሴ 29/2018 ዓ/ም | በሸኖ
የዌራ ዲጆ ጤና ጽ/ቤት የጤና ቤተሰብ አባላት በነሐሴ ወር ልሳነ-ማዕከላዊ የአባላት መወያያ "ለጠንካራና ቅቡልነት ያለው ዘላቂ አገረ-መንግስት ግንባታ " በሚል አጀንዳ ላይ የአባላት ውይይት ተደረገ::
ሀገራችን ኢትዮጵያ ጠንካራና ቅቡልነት ያለው አገረ መንግሥት ለመመስረትና ለመገንባት የተለያዩ ተግባራትንና የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እየሰራች እንዳለ የሚታወቅ ሲሆን በማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ፓለቲካዊ ዘርፎች ተጨባጭ ለውጥ በማምጣት ሀገራችንን የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ ቀንና ማታ እየሰራ እንዳለ ከውይይቱ መረዳት ተችሏል ፡፡
የሀገራችን ዜጎች በአካታችና በአቃፊ የፖለቲካ ምህዳር ውስጥ በሁሉም የልማትና ዕድገት አጀንዳዎች ላይ የራሳቸውን አሻራ ለማሳረፍ በሁሉም አጋጣሚዎች አይተኬ ሚናቸውን ማሳረፍ እንደሚገባም በመድረኩ ተነስቷል፡፡
በአጠቃላይ ለአንድ አገር ጠንካራና በሁሉም የልማትና የዕድገት መንገዶች ፊት የወጣ የመንግሥት አደረጃጀት መኖር ለዜጎች ዋስትና ስለሆነ የቤተሰቧ አባላት ለዚህ ሁሉ አቀፍና አካታች የፖለቲካ ሥርዓት መገንባት ኃላፊነቱን መወጣት እንደሚገባ የቤተሰቧ አባላት ተናግረዋል ፡፡