05/09/2026
ካለን ላይ ...........አካፈልን!!!!
በጎነት የሌላን ሰዉ ችግር እንደራሳችን በመመልከት መፍትሄ ለማምጣት መረባረብ ነዉ::
ነሐሴ 30/2018
የሀላባ ዞን ገቢዎች መምሪያ ብልፅግና ቤተሰብ በክረምት በጎ ፍቃድ ለአንድ ቤተሰብ የመኝታ አልጋ ከነፍራሹና ፍራሽ ልብሱ አበረከተ:: # # # # # # # # #
የሀላባ ዞን ኢኮኖሚ ቁጥር 2 ህብረት እንደ ህብረት በክረምት በጎ ፍቃድ ለአንድ ቤተሰብ ቤት ማስገንባቱ ይታወቃል::የሀላባ ዞን ገቢዎች መምሪያ ብልፅግና ቤተሰብ እንደህብረት ባስገነባነዉ ቤት እንደ ቤተሰብ የመኝታ ቤቱን ኮታ ሸፍነናል:: በርክክቡ ወቅት የምሪያዉ ኃላፊ ወ/ሮ ፋጤ ዩሐንስ እንደገለፁት ዛሬ በትንሿ ነገር በጎ የዋልነዉ ተግባር ነገ በማህበረሰብ በጎ መዋልን ለማስተማር ከትንሿ ስጦታ በላይ በጎ የሚዉል ማህበረሰብ ግንባታ ላይ ትልቅ አስተዋፅኦን ያበረክታል ብለዋል::
በርክክቡ የሀላባ ዞን ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ፋጤ ዩሐንስን ጨምሮ የመምሪያዉ ማኔጅመንት አባላት ተገኝተዋል::
"በጎነት ለኢትዮጲያ ከፍታ"
የሀላባ ዞን ገቢዎች መምሪያ