የሀላባ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ

የሀላባ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ Government Organization

የእመርታ ቀን ሀገራችን ኢትዮጵያ ከአዝጋሚ የእድገት ጉዞ በመውጣት ያስመዘገበቻቸው ታሪካዊ ስኬቶች የምንዘክርበት ዕለት ነው። ክቡር አቶ ሙህዲን ሁሴን የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ!!!
05/09/2026

የእመርታ ቀን ሀገራችን ኢትዮጵያ ከአዝጋሚ የእድገት ጉዞ በመውጣት ያስመዘገበቻቸው ታሪካዊ ስኬቶች የምንዘክርበት ዕለት ነው።

ክቡር አቶ ሙህዲን ሁሴን የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ!!!

ጳጉሜ 1 የእምርታ ቀን ========== እምርታ ቀን በተመለከተ፦ በተለይም በኢኮኖሚክስ እና በግብርና ዕድገት ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ነጥቦችን ተዘርዝረዋል። በምስሉ ላይ የቀረቡት ዋና ዋና ነጥቦ...
05/09/2026

ጳጉሜ 1 የእምርታ ቀን
==========

እምርታ ቀን በተመለከተ፦

በተለይም በኢኮኖሚክስ እና በግብርና ዕድገት ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ነጥቦችን ተዘርዝረዋል።

በምስሉ ላይ የቀረቡት ዋና ዋና ነጥቦች ቀጥተኛ ትርጉም እና ማጠቃለያ እንደሚከተለው ቀርበዋል።

👉የኢትዮጵያ ምርትና ምርታማነት፣ በተለይም በግብርናው ዘርፍ ያለውን አቅም እንዲሁም አገሪቱ በምግብ ዋስትና ረገድ የምታደርገውን የፈጣንና የሽግግር ጉዞ ያሳያል።

👉 በሎጎው ላይ የሚታዩት የስንዴ ምርትና ትስስር በከፍታው ላይ የሚታዩት የስንዴ ሰብሎች ጥምረት የብልጽግናን፣ የባህል፣ የምርት ማደግ እና የህዝብን የኑሮ ትስስር እሴት ያመለክታል። የስንዴው ቅርፅ ከታች ተነስቶ ወደ ላይ መዘርጋቱ መሠረቱ ጠንካራ መሆኑን እና ወደፊት ዕድገት እንደሚቀጥል ያሳያል።

👉 ከዝቅተኛ ጉዞ ወደ ከፍተኛና ፈጣን ጉዞ መሸጋገር ይህም የኢኮኖሚ እድገትንና የመዋቅራዊ ሽግግርን ያሳያል።

👉 የልምላሜን፣ የእድገት፣ የግብርና መሰረት እና የተፈጥሮ ጸጋን ያሳያል።

👉 የበለጸገውን ምርት የጸሐይ ብርሃን እና የኢኮኖሚ ብልጽግናን ይመለከታል።

ስለሆነም በነገው ዕለትም "ጳጉሜን 1 – የእምርታ ቀን" በሚል መሪ-ቃል ይከበራል።

የእመርታ ቀን ሀገራችን ኢትዮጵያ ከአዝጋሚ የእድገት ጉዞ በመውጣት ያስመዘገበቻቸው ታሪካዊ ስኬቶች የምንዘክርበት ዕለት ነው። ክቡር አቶ ሙህዲን ሁሴን የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ
05/09/2026

የእመርታ ቀን ሀገራችን ኢትዮጵያ ከአዝጋሚ የእድገት ጉዞ በመውጣት ያስመዘገበቻቸው ታሪካዊ ስኬቶች የምንዘክርበት ዕለት ነው።

ክቡር አቶ ሙህዲን ሁሴን የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ

በዞኑ አምስቱን የጳጉሜ ቀናት በልዩ ድምቀት በተለየዩ መርሀ-ግብሮች ከነገ ጀምረው ይከበራል - አቶ ሀሩና አህመድ =====ነሀሴ 30/2018 በሀላባ ዞን አምስቱን የጳጉሜ ቀናት በልዩ ድምቀት...
05/09/2026

በዞኑ አምስቱን የጳጉሜ ቀናት በልዩ ድምቀት በተለየዩ መርሀ-ግብሮች ከነገ ጀምረው ይከበራል - አቶ ሀሩና አህመድ
=====
ነሀሴ 30/2018

በሀላባ ዞን አምስቱን የጳጉሜ ቀናት በልዩ ድምቀት በተለየዩ መርሀ-ግብሮች ከነገ ጀምረው እንደሚከበር - የዞኑ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ዋና ሀላፊ አቶ ሀሩና አህመድ ገለጹ።

በዚህ ወቅትም የሀላባ ዞን መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ዋና ሀላፊ አቶ ሀሩና አህመድ በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት ጳጉሜን ከአሮጌው ዓመት ወደ አዲሱ ዓመት የሚያሻግር የሽግግር ወቅት መሆኑን ገልጸዋል።

ያለፈውን ዓመት ስራና ውጤት ለመገምገም፣ የተገኙ ስኬቶችን ለማጠናከር፣ የታዩ ክፍተቶችን ለማረምና ለቀጣዩ ዓመት የተሻለ የስራ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ወሳኝ ነው ብለዋል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ዘርፈ-ብዙ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ድሎችን እያስመዘገበች፣ ውስብስብ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ተግዳሮቶችን በፅናት በመሻገር በአሁኑ ወቅት በማንሰራራት ምዕራፍ ላይ እንደምትገኝ አብራርተዋል።

ዞናችን ባለፉት ዓመታት ውስጥ ሁለንተናዊ ለውጦችን በማስመዘገብ በዚህ የማንሰራራት ምዕራፍ ውስጥ ግንባር ቀደም ተሳታፊና ተጠቃሚ መሆን የቻለ ዞን ነው ሲሉም ጠቁመዋል።

ወርሃ ጳጉሜ እንደሀገር ይሁን እንደዞናችን በኢኮኖሚ እና ማህበራዊ የተመዘገቡ ስኬቶች በሚመለከት ለህዝቡ ማስገንዘብ እና አጉልተን የምናሳይበት ወር መሆኑን አስገንዝበዋል።

በዘንድሮው አመት በአምስቱ የጳጉሜ ቀናት እያንዳንዳቸው በተሰጣቸው ስያሜና መሰራት በድምቀት እንደሚከበር ጠቁመዋል።

በ2018 ዓ.ም እንደ ሀገር አበረታች ስኬቶች የተመዘገቡበት እንደነበር የተናገሩት የመምሪያው ዋና ሀላፊ አቶ ሀሩና አህመድ በዞኑ በልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች አበራታች ስራዎች መሰራቱን አስረድተዋል።

የጳጉሜ ቀናት መርሀ-ግብር ዋነኛ ዓላማም ሀገራችን ኢትዮጵያ የጀመረችውን የብልጽግና ጉዞ ይበልጥ ለማሳካት እንደሆነ ገልጸዋል።

በተለይም የተከናወኑ ተግባራትን መገምገም እና የታዩ ለውጦችን ቀጣይነት ማረጋገጥ እና ህብረተሰቡ በልማት ስራዎች ላይ ያለውን ንቁ ተሳትፎ ይበልጥ ለማጠናከር ብለዋል።

የጳጉሜ ቀናት የተሰጣቸውን ስያሜዎች ሲያብራሩም
ጳጉሜን 1 – የእምርታ ቀን፣
ጳጉሜን 2 – የማንሰራራት ቀን፣
ጳጉሜን 3 – የጽናት ቀን፣
ጳጉሜን 4 – የኅብር ቀን፣
ጳጉሜን 5 – የነገ ቀን በሚሉ የተለያዩ መርሃ-ግብሮች የጳጉሜን ቀናት በልዩ ሁነቶችና በማንቀሳቀስ መርሀ-ግብሮች እንደሚከበሩ ገልጸዋል።

ቀናቱ በተሰጣቸው ስያሜና ጭብጥ መሰረት በተለያዩ መርሀ-ግብሮች ሌሎች በተለየዩ ተግባራት እንደሚከናወን ገልጸዋል።

ለዚህም እንደዞናችን የጳጉሜ ቀናት በተለያዩ ዝግጅቶች ለማክበር አስፈላጊው ዝግጅት ተጠናቀዋል ሲሉም ሀላፊው ገልጸዋል።

አምስቱ የጳጉሜ ቀናት መርሀ-ግብሮች የተሳኩ እንዲሆኑ የዞኑ ህብረተሰብ እና ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ አቶ ሀሩና አህመድ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በነገው ዕለትም "ጳጉሜን 1 – የእምርታ ቀን" እንደሚከበር የገለጹት ሀላፊው የዞኑ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ሀላፊ አቶ ሀሩና አህመድ ገልጸዋል።

በመጨረሻም በዞኑ አምስቱ የጳጉሜ ቀናት አከባበር ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ስራዎችን ወጥ የሆነው መልዕክት በማስተላለፍ የጳጉሜ ስያሜ የተሰጣቸው ቀናቶች ትኩረት ሰጥተው የሚከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ለማድረግ ሽፋን እንዲያገኙ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

የዞኑ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች

መጪዎቹን በዓላት ምክንያት በማድረግ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች ሳምንቱን ሙሉ አገልግሎት እንደሚሰጡና በዋጋ ጭማሪ ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚደረግ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር...
05/09/2026

መጪዎቹን በዓላት ምክንያት በማድረግ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች ሳምንቱን ሙሉ አገልግሎት እንደሚሰጡና በዋጋ ጭማሪ ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚደረግ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።

​(ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም)

መጪዎቹን የ2019 ዓ.ም የዘመን መለወጫ፣ የመስቀል እና የኢሬቻ በዓላትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ ከ2,300 በላይ የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች ሳምንቱን ሙሉ አገልግሎት እንደሚሰጡና በዓላትን በማሳበብ በሚደረግ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚደረግ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።

​የበዓል ወቅትን ምክንያት በማድረግ ሕገወጥ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ አካላት ላይ ከፌደራል እስከ ወረዳ ባለው የንግድ መዋቅር እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል የሚደረግ ሲሆን፣ ጥፋተኛ ሆነው በተገኙት ላይም ሕጋዊ እርምጃ ይወሰዳል።

​የገበያ ትስስርና የምርት አቅርቦትን በተመለከተ በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የሚገኙ የኅብረት ሥራ ማኅበራት፣ ዩኒየኖች እንዲሁም ከአምራቾችና ነጋዴዎች ጋር በተደረገ ትስስር የእርድ እንስሳትን ጨምሮ ለበዓሉ አስፈላጊ የሆኑ የኢንዱስትሪና የግብርና ምርቶች በስፋት እየቀረቡ ይገኛሉ።

​ለበዓላት አስፈላጊ የሆኑ ምርቶች በቅዳሜና እሁድ ገበያዎች፣ በተመቻቹ ኤግዚቢሽንና ባዛሮች እንዲሁም በሸማች ኅብረት ሥራ ማኅበራት ሱቆች አማካኝነት ለሸማቹ ማኅበረሰብ እየቀረቡ ይገኛሉ።

የክልሉ ፍትህ ሴክተር ተቋማት በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በሀላባ ቁሊቶ ከተማ ያስገነቧቸውን ቤቶች ለባለቤቶቹ አስረከቡ ******ነሃሴ 30/2018)፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ሴ...
05/09/2026

የክልሉ ፍትህ ሴክተር ተቋማት በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በሀላባ ቁሊቶ ከተማ ያስገነቧቸውን ቤቶች ለባለቤቶቹ አስረከቡ
******
ነሃሴ 30/2018)፣

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ሴክተር ተቋማት በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በሀላባ ቁሊቶ ከተማ ያስገነቧቸውን ሁለት የመኖሪያ ቤቶች ለባለቤቶች አስተላልፈዋል።

ተቋሟቱ የአቅመ ደካሞቹን የቤት ግንባታ ሀምሌ 14/2018 ማስጀመራቸው ይታወቃል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ኤርስኖ አቡሬ ተቋሙ የማህበራዊ ሀላፊነት ለመወጣት በርካታ ስራዎችን እየፈፀመ መሆኑን ተናግረዋል።

ደካሞችን ለመደገፍ የተጀመረውን ስራ በማጠናከር የበጎ ፈቃድ ስራዎችን ባህል ማድረግ ይገባል ያሉት ፕሬዝዳንቱ በዛሬው ዕለትም የፍትህ አካላትና የጠቅላይ ፍርድ ቤት በ1.2 ሚሊዮን ብር በጋራ የተገነባ የመኖሪያ ቤት አስረክቧል

የርዕሰ መስተዳድሩ ልዩ አማካሪ ንጉሴ አስረስ ዶ/ር በክልሉ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች በክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ በልዩ ትኩረት እየተመራ ተጨባጭ ውጤት እያመጣ ነው ብለዋል።

በክልሉ በሁሉም ዘርፍ በተሰራው ስራ እምርታ መጥቷል ያሉት ዋና አማካሪው የበጎ ተግባሩ ለዜጎች እፎይታን የሠጠና የመንግስትና የማህበረሰቡን ትስስርን እያጠናከረ መምጣቱን ተናግረዋል።

ህብረተሰቡ በጉልበቱ ፣በእውቀቱና በገንዘቡ ጠንካራ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ተናግረው እስካሁንም በክልሉ ከ13 ቢሊዮን በላይ ብር ተሳትፎ ማድረጉን ተናግረዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ ሀላፊ አቶ አክመል አህመድን በበኩላቸው የመረዳዳትና የመተጋገዝ አካል አንዱ የሆነውን ለአቅመ ደካማ ዜጎች የመኖሪያ ቤት ገንብቶ አስረክቧል ብለዋል።

ግንባታውን የፍትህ ቢሮ እና የማረሚያ ተቋማት በጋራ ያስገነቡት መሆኑን ገልፀው ለቤቱ የሚያስፈልጉ ሙሉ የቤት እቃዎች የተሟላለትና ለእናታችን ለስራ ማስጀመሪያ የሚሆን የ50 ሺ ብር ተጨማሪ ድጋፍ የተደረገላቸው መሆኑን ተናግረዋል።

‎ተግባሩ ዜጎች የተሻለ የኑሮ ሁኔታ እንዲኖራቸው ያደርጋል ያሉት አቶ አክመል በአጠቃላይ ለቤቱ ግንባታና የቤት ቁሳቁስ 1 ሚሊዮን 200ሺ ብር ወጪ መደረጉን ተናግረዋል።

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ገመዳ መሀመድ በበኩላቸው መንግስት በዜጋ ተኮር ስራዎች የተለያዩ ማህበራዊ ችግር ተጋላጭ የሆኑ አረጋዊያንና አቅመ ደካሞችን በመደገፍ ተጠቃሚ ማድረጉንና ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንም ተናግረዋል።

አባታቸውን በሞት ያጡ 4 ልጆችና 2 ወላጅ አልባ በድምሩ የ6 ልጆች አሳዳጊ የሆኑት ወ/ሮ መድሀኒት ሀይሉ መንግስት ያደረገላቸው የተሟላ ድጋፉ ለልጆቻቸውና ለራሳቸው ተስፋን እንደጨመረላቸው ተናግረዋል።

ሁለተኛው የቤት ድጋፍ የተደረገላቸው እናት ልጃቸው የሀገር መከላከያን እያገለገለ መሆኑን የተናገሩት ወ/ሮ አይነቴ ቦጪሶ ደግሞ ድጋፉ ከሰው ጋር እኩል መኖር እንዲችሉ ያስቻላቸው መሆኑን ገልፀዋል።

በቁልፍ ርክክቡ ወቅት የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችና የአካባቢው ነዋሪዎች የተገኙ ሲሆን ለቤቶቹ ግንባታ ስኬት ድጋፍ ያደረጉ አካላትን በሙሉ አመስግነዋል።

ሀላባ ቲቪ

ገበያው ላይ በቂ የሆነ የቁም እንስሳት፣ የእንስሳት ተዋጽኦ፣ የፋብሪካ ምርቶች፣ አትክልት እና ሌሎችም ለበዓሉ የሚያስፈልጉ አቅርቦቶች መኖራቸው ተገለፀ ==============ነሐሴ 30 ፣ 2...
05/09/2026

ገበያው ላይ በቂ የሆነ የቁም እንስሳት፣ የእንስሳት ተዋጽኦ፣ የፋብሪካ ምርቶች፣ አትክልት እና ሌሎችም ለበዓሉ የሚያስፈልጉ አቅርቦቶች መኖራቸው ተገለፀ
==============
ነሐሴ 30 ፣ 2018 ዓ.ም

የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ ባዩሽ ተስፋዬ (ዶ/ር) ከፊታች ለሚከበረው የዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦትና ህገ-ወጥ ንግድን መከላከልና መቆጣጠር በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል።

ቢሮ ኃላፊዋ ባዩሽ ተስፋዬ (ዶ/ር) የአዲስ ዓመት በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰትና ሕገ ወጥ ግብይትን ለመቆጣጠር አስፈላጊው የቅድመ ዝግጅት
ስራ መሰራቱን ጠቁመዋል።

በተለይም በበዓሉ ወቅት ከፍተኛ የሆነ የገበያ ፍላጎትን መነሻ በማድረግ ሊከሰቱ የሚችሉ የዋጋ ጭማሪ፣ የምርት እጥረትና ሕገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴን ለመከላከል ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሠራ መሆኑን ገልጸዉ በሁሉም የሰንበት ገበያዎች ምርት በበቂ ሁኔታ እየቀረበ እንደሚገኝ አስታዉቀዋል።

ገበያው ላይ በቂ የሆነ የቁም እንስሳት፣ የእንስሳት ተዋጽኦ፣ የፋብሪካ ምርቶች፣ አትክልት እና ሌሎችም ለበዓሉ የሚያስፈልጉ አቅርቦቶች መኖራቸውን የገለጽት ኃላፊዋ በበዓሉ ወቅት ሰው ሠራሽ የምርት እጥረት በሚፈጥሩ፣ በምግብ በምርት ላይ ባእድ ነገር ቀላቅለው የሚሸጡ ዋጋ በሚጨምሩ ሕገ ወጥ ነጋዴዎች ላይ ቁጥጥር በማድረግ አስፈላጊውን አስተዳደራዊና ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ አሳስበዋል።

በተጨማሪም ከአጎራባች አካባቢዎች ጋር ትስስር በመፍጠር ለበዓል ግብአት የሚሆኑ አትክልት እና ሌሎችም የግብርና ምርቶች ወደ ሰንበት ገበያዎች እና መደበኛ ገበያዎች እየገባ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ በዓልን ምክንያት በማድረግ ሊከሰት የሚችል ህገ-ወጥ ንግድን ለመከላከል በሚሰራቸው ስራዎች ባለድርሻ አካላትም የድርሻቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ህብረተሰቡ ለሚገዛቸው ምርቶች ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባው ያመላከቱት ቢሮ ኃላፊዋ ማንኛውም ህገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ ሲያጋጥመው አቅራቢያው ላለው የንግድ መዋቅር እንዲሁም በቢሮው ነፃ የስልክ መስመር 9348 ደውሎ ጥቆማ በመስጠት የድርሻውን እንዲወጣ አስታውቀዋል፡፡

የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ

ምሁራን የሃሳብ ልዩነታቸውን በጠረጴዛ ዙሪያ በመፍታት ለሃሳብ የበላይነት የሚገዙና አዳዲሰ ነገሮችን የሚፈጥሩ ሊሆኑ ይገባል-  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
04/09/2026

ምሁራን የሃሳብ ልዩነታቸውን በጠረጴዛ ዙሪያ በመፍታት ለሃሳብ የበላይነት የሚገዙና አዳዲሰ ነገሮችን የሚፈጥሩ ሊሆኑ ይገባል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

"የኢትዮጵያ ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል የጳጉሜን ወር አከባበር ላይ የዞኑ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ Zoom ቴክኖሎጂን በመጠቀም ለሚዲያ ኦራንቴሽ ሰጠ=====ነሀሴ 29/2018 የሀላባ ...
04/09/2026

"የኢትዮጵያ ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል የጳጉሜን ወር አከባበር ላይ የዞኑ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ Zoom ቴክኖሎጂን በመጠቀም ለሚዲያ ኦራንቴሽ ሰጠ
=====
ነሀሴ 29/2018

የሀላባ ዞን መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ "የኢትዮጵያ ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል የጳጉሜን ወር አከባበር ላይ የዞኑ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ Zoom ቴክኖሎጂን በመጠቀም ለሚዲያ ኦራንቴሽ ሰጥተዋል።

ለሚዲያ ኦራንቴሽን በሰጡበት ወቅት የሀላባ ዞን መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ እንደገለጹት ኢትዮጵያ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ዘርፈ-ብዙ ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ድሎችን እያስመዘገበች፣ ውስብስብ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ተግዳሮቶችን በፅናት በመሻገር በአሁኑ ወቅት በማንሠራራት ምዕራፍ ላይ ትገኛለች ብለዋል።

​ዞናችን ባለፉት ዓመታት ውስጥ ሁለንተናዊ ለውጦችን በማስመዝገብ በዚህ የማንሰራራት ምዕራፍ ውስጥ ግንባር ቀደም ተሳታፊና ተጠቃሚ መሆን መቻሉን ገልጸዋል።

ወርሃ ጳጉሜ እንደሀገር ይሁን እንደዞናችን በኢኮኖሚ እና ማህበራዊ የተመዘገቡ ስኬቶች በሚመለከት ለህዝቡ ማስገንዘብ እና አጉልተን የምናሳይበት ነው ሲሉም ገልጸዋል።

• ጳጉሜን 1 – የእምርታ ቀን

• ጳጉሜን 2 – የማንሰራራት ቀን

• ጳጉሜን 3 – የጽናት ቀን

• ጳጉሜን 4 – የኅብር ቀን

• ጳጉሜን 5 – የነገ ቀን

በሚሉ የተለያዩ መርሀ-ግብሮች የጳጉሜን ቀናት በልዩ ሁነቶችና በማንቀሳቀስ መርሀ-ግብሮች እንደሚከበሩ አስረድተዋል።

ለዚህም ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ስራዎችን ከወትሮው በተለያ መልኩ ወጥ በሆነው በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ሀላፊው አሳስበዋል።

በዞኑ አምስቱ የጳጉሜ ቀናት አከባበርን በማስመልከት ወጥ የሆነው መልዕክት ለማስተላለፍ ከሚዲያ ኮሙዩኒኬሽን፥ በአምስቱም የጳጉሜ ቀናት የሚከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ማድረግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ የጋራ አቅጣጫ አስቀምጧል።

Address

Alaba K'ulito

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የሀላባ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to የሀላባ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ:

Shortcuts

Share