በማዕ/ኢት/ክ/መንግስት የሀላባ ዞን ቁሊቶ ማረሚያ ተቋም

በማዕ/ኢት/ክ/መንግስት የሀላባ ዞን ቁሊቶ ማረሚያ ተቋም ይህ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀላባ ዞን ቁሊቶ ማረሚያ ተቋም የፌስቡክ ገጽ ነው ።

የሀላባ ቁሊቶ ማረሚያ ተቋም የሕግ ታራሚዎች የይቅርታ መልማይ ኮሚቴ በይቅርታ በሚፈቱ ታራሚዎች አፈፃፀም ዙሪያ ውይይት ተካሄደ*********ነሐሴ፣1/2018  የቁሊቶ ከተማ ማረሚያ ተቋም የይ...
07/08/2026

የሀላባ ቁሊቶ ማረሚያ ተቋም የሕግ ታራሚዎች የይቅርታ መልማይ ኮሚቴ በይቅርታ በሚፈቱ ታራሚዎች አፈፃፀም ዙሪያ ውይይት ተካሄደ
*********
ነሐሴ፣1/2018 የቁሊቶ ከተማ ማረሚያ ተቋም የይቅርታ ተጠቃሚ የሕግ ታራሚዎች ምልመላና መረጣ ኮሚቴ የይቅርታ ጥያቄ የተመለከቱ ተግባራት ላይ አፈጻጸም ላይ ውይይት ተካሄዷል።

ውይይቱ በተካሄደበት ወቅት እስካሁን ድረስ በታራሚዎች ምልመላና መረጠ ዙሪያ የተሰሩ ተግባራትን የቁሊቶ ማረሚያ ተቋም ኃላፊና መልማይ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ረዳት ኢንስፔክተር ሁሴን ጉንታ በዝርዝር አቅርበው የኮሚቴው አባላት በጉዳዩ ላይ ሰፋ ያለ ሀሳብ አንስተው ወይይት ተደርጓል።

የይቅርታ መልማይ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ገራሙ ሱንክቻ እንደገለጹት የይቅርታ ጥያቄ ምልመላና መረጣ ኮሚቴ በመመሪያ መሠረት ይቅርታን የተመለከቱ የህግ ማዕቀፎች ዋና ዓላማ በማረሚያ ተቋማት የሚታረሙ የህግ ታራሚዎች ይቅርታ የሚያሰጡ ዝርዝር መስፈርቶችን በመደንገግ እንዲሁም

በማረሚያ ተቋማት ውስጥ በመታረም ላይ የሚገኙ የህግ ታራሚዎች የሚያቀርቧቸውን የይቅርታ ጥያቄዎችን ተቀብሎ በመርመር በፍትሃዊነት የሕግ ታራሚዎችን የይቅርታ ጥያቄዎችን መርምሮ የይቅርታ የውሳኔ ሃሳብ ለክልሉ ፍትህ ቢሮ ለማቅረብ እንደሆነ ገልጸዋል።

በተሻሻለው አዋጅ መሰረት ይቅርታ የማያሰጡ ለአብነትም አስገድዶ መድፈር፣ጠለፋ፣ግብረሰዶም፣የግፍ ግ ዲያ።ከባድ ውንብድና የሙስና ወንጀሎች፣ህገወጥ የሰዎች ዝውውር፣ሀሰተኛ ሰነድ ማዘጋጀት፣በልማት አውታሮች ላይ ወንጀል መፈጸም፣

ይቅርታ አግኝቶ ዳግም ወንጀል ፈጽሞ ወደ ማረሚያ ተቋም የገባ፣ከማረሚያ ቤት ልያመልጥ የሞከረ ለማምለጥ የዲሲፕሊን ጥሰት መፈጸም በዐቃቤ ሕግ የይግባኝ ወይም የሰበር አቤቱታ የቀረበበት ታራሚ እነዚህ በዋነናነት ይቅርታን የማያሰጡ ወንጀሎች መሆናቸውን የኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ገረሙ ተናግረዋል ።

በመጨረሻም የቁሊቶ ማረሚያ ተቋም የሕግ ታራሚዎች የይቅርታ ጥያቄ መልማይ ኮሚቴ የ2018 1ኛ ዙር የይቅርታ ተጠቃሚ የህግ ታራሚዎች ምልመላና መረጣው በመስፈርቱ መሠረት መሆኑን በማረጋገጥ ለሚመለከተው ለክልሉ ፍትህ አካል እንዲተላለፍ በሙሉ ድምፅ ውሳኔ በማሳለፍ የዕለቱን ውይይት አጠናቋል።

እንኳን ደስ ያላችሁ እንኳን ደስ ያለን !የሀላባ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በፓርቲ  ሥራ  የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ አካላት እውቅና ሰጥቷል ።በዚህም መሠረት በ2...
06/08/2026

እንኳን ደስ ያላችሁ እንኳን ደስ ያለን !

የሀላባ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በፓርቲ ሥራ የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ አካላት እውቅና ሰጥቷል ።

በዚህም መሠረት በ2018 በጀት ዓመት በሀላባ ዞን ብልጽግና ፓርቲ አስተዳደር ህብረት ዘርፍ ካሉ ቤተሰቦች የሀላባ ዞን ማረሚያ ተቋም ብልጽግና ቤተሰብ #1ኛ ደረጀ በመዉጣት የሜዳሊያና የሰርቲፊኬት ተሸላሚ በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ ያለን።

የሀላባ ዞን ቁሊቶ ማረሚያ ቤተሰብ በ2018 በፓርቲ ስራዎች ከአስተዳደር የብልጽግና ህብረት ቤተሰቦች ውስጥ በልማት ትሩፋት ፣ በግቢ ኮሪደር ልማት ስራዎች ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት የላቀ ውጤት በማስመዝገብ 1ኛ ደረጃ በማውጣት የሜዳሊያና የሰርቲፊኬት ተሸላሚ በመሆን በበጀት ዓመቱ በርካታ ውጤቶችን አስመዝግቦ አልፏል ።

የተመዘገበው አኩሪና አስደሳች ውጤት ለቀጣዩ ሥራ ተነሳሽነት የሚፈጥር ትልቅ እገዛ ይሆነናል ።

የቁሊቶ ማረሚያ ተቋም ከጥልፍልፍ ችግር ወጥቶ ለዝህ ውጤት እንዲበቃ ትልቅ ድርሻ ለነበራቸው አካላት ምስጋና መቅረቡ ተገቢ በመሆኑ በመጀመሪያ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኮሚሽን፣ የሀላባ ዞን አስተዳደር የብልጽግና ህብረት አመራሮች፣ የሀላባ ዞን ምክር ቤት ፣የሀላባ ዞን ፍትህ መምሪያ ፣ የቁሊቶ ማረሚያ ተቋም ማኔጅመንት አካላትና መላው ታታሪ ፖሊስ አባላት ሠራተኞች እንድሁም የሕግ ታራሚዎች፣ አስተባባሪ ኮሚቴዎች ላቅ ያለ ምስጋና እናቀርባለን።
!!
!!

በሀላባ ዞን ቁሊቶ ማረሚያ ተቋም እና በስልጤ ዞን ማረሚያ ህግ ታራሚዎች እግር ኳስ ክለብ መካከል የወዳጅነት ጫዋታ ተካሄደ***************የሀላባ ዞን ቁሊቶ ማረሚያ የህግ ታራሚዎች እ...
05/08/2026

በሀላባ ዞን ቁሊቶ ማረሚያ ተቋም እና በስልጤ ዞን ማረሚያ ህግ ታራሚዎች እግር ኳስ ክለብ መካከል የወዳጅነት ጫዋታ ተካሄደ
***************
የሀላባ ዞን ቁሊቶ ማረሚያ የህግ ታራሚዎች እግር ኳስ ክለብ ከስልጤ ዞን ማረሚያ አቻው ጋር የወዳጅነት ጫዋታ በወረቤ ከተማ አካሄዷል።

በሁለቱ ማረሚያ ተቋማት የህግ ታራሚዎች እግር ኳስ ክለብ መካከል የተካሄደው ይህ የወዳጅነት ጨዋታ የአንድነትና የተስፋ መልዕክት ያስተላለፈ መሆኑ በመርሃግብሩ ላይ ተገልጿል።

በተካሄደው የወዳጅነት ጫዋታ ወራቤ ማረሚያ የህግ ታራሚዎች እግር ኳስ ቡድን የሀላባ ማረሚያ የህግ ታራሚዎችን ቡድን አሸንፏል።

ጨዋታው ከውጤቱ ባሻገር በህግ ታራሚዎች መካከል ወዳጅነትን፣ መከባበርን፣ መተባበርን እና የሰላማዊ አብሮነትን ለማጠናከር ትልቅ አስተዋፅኦ አበርክቷል።

በዝግጅቱ ላይ ስፖርት ለተሀድሶ፣ ለሥነ-ምግባር ግንባታ እና ለአዎንታዊ የሕይወት አመለካከት መጎልበት ያለውን ጠቀሜታ አሳይቷል። ሁለቱም ቡድኖች በአሳዩት ጨዋነታና የስፖርት መንፈስ እንኳን ደስ አላችሁ!!

በሀላባ ቁሊቶ ከተማ «ተስፋን እንትከል» በሚል መሪ ቃል የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃግብር በቁሊቶ ማረሚያ ተቋም በታላቅ ድምቀት ተካሄደ የሀላባ ዞን ፖሊስ መምሪያ ፖ አመራሮችና አባለ...
03/08/2026

በሀላባ ቁሊቶ ከተማ «ተስፋን እንትከል» በሚል መሪ ቃል የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃግብር በቁሊቶ ማረሚያ ተቋም በታላቅ ድምቀት ተካሄደ

የሀላባ ዞን ፖሊስ መምሪያ ፖ አመራሮችና አባለት በጋር በመሆን በሀላባ ቁሊቶ ማረሚያ ተቋም «ተስፋን እንትከል» በሚል መሪ ቃል የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ፕሮግራም አካሄደዋል።

በችግኝ ተከላ መርሃግብር የሀላባ ዞን ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ኑርዬ ከድርና የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ማኔጅመንት አባለት እንዱሁም የቁሊቶ ከተማ አስተዳደር የማረሚያ ተቋም ሃላፊ ም/ኢንስፔክተር ሁሴን ጉንታ ተገኝተዋል።

ሀገራችንን አልምተን ለቀጣይ ትውልድ እናሻግራለን!!!

ሃምሌ 27/2018ዓም ሀላባ ቁሊቶ

የሀላባ ዞን ቁሊቶ ማረሚያ ተቋም በ2018 በጀት ዓመት የተሻለ የአፈፃፀም ውጤት ላስመዘገቡ የስራ ሂደቶችና ፖሊስ አባላት የዕውቅናና ማበረታቻ ሽልማት የምስክር ወረቀት ሰጠ***ሐምሌ 23/20...
30/07/2026

የሀላባ ዞን ቁሊቶ ማረሚያ ተቋም በ2018 በጀት ዓመት የተሻለ የአፈፃፀም ውጤት ላስመዘገቡ የስራ ሂደቶችና ፖሊስ አባላት የዕውቅናና ማበረታቻ ሽልማት የምስክር ወረቀት ሰጠ
***
ሐምሌ 23/2018ዓ.ም ቁሊቶ፤ የሀላባ ዞን ቁሊቶ ማረሚያ ተቋም የተጠናቀቀዉን የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማና በ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ዙሪያ የውይይትና ምክክር መድረክ በዛሬው ዕለት ያካሄደ ሲሆን በመድረኩ የተሻለ የስራ አፈፃፀም ውጤት ላስመዘገቡ ስራ ሂደቶችና ፖሊስ አባላት የዕውቅናና የማበረታቻ ሽልማት የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል።

የተቋሙ ኃላፊ ም/ኢንስፔክተር ሁሴን ጉንታ በስነስርዓቱ ላይ እንደተናገሩት በተቋሙ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በየስራ ክፍሉ ለማከናወን የታቀዱ ግቦችን ለማሳካት ሁሉም ዳይሬክቶሬት አስተባባሪዎች፣ የፖሊስ አባላት፣ ሰራተኞች፣ የማረሚያ ተቋሙ መምራህን፣ የህግ ታራሚ አቢይ ኮሚቴዎችና ሌሎች አደረጃጀቶች ያደረጉት ያለሰለሰ ጥረት እጅግ ውጤታማ እንደነበር ጠቁመዋል።

ኃላፊዉ ​አክለውም በ2018 በጀት ዓመት የህግ ታራሚዎችን በስነምግባር ለማረምና ማነጽ፣ በሙያና ትምህርት ስልጠና ለማብቃት፣ አስተማማኝ የደህንነትና ጥበቃ ስራዎችን ለማከናወን፣ ሰብዓዊ መብቶችን አክብሮ ለማስከበር፣ የመሠረታዊ ፍላጎትና አቅርቦትን ለማሟላት፣ የታራሚዎቹን ጤና ለመጠበቅ ተቋሙ ያስቀመጣቸው እቅዶች ግባቸውን እንዲመቱ የተጣለባቸውን ኃላፊነት በየተመደቡበት በብቃት ለተወጡ አባላት የተበረከተላቸው ይህ የእውቅናና ማበረታቻ ሰርቲፊኬት ለቀጣይ የበለጠ ማነቃቃትን የሚፈጥር መሆኑን ጠቁመው፤ የሚሰጡ ተልዕኮዎችን በውድድርና በፉክክር መንፈስ እንዲፈፀሙም ያስችላቸዋል ብለዋል።

በዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ዉይይት መድረኩ ላይ የተቋሙ ኃላፊ፣ የማኔጅመንት አባላት፣ የማረሚያ ተቋሙ የመጀ/2ኛ/ደ/ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር፣ የህግ ታራሚ አቢይ ኮሚቴዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ተገኝተዋል።

የሀላባ ዞን ቁሊቶ ማረሚያ ተቋም የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
30/07/2026

የሀላባ ዞን ቁሊቶ ማረሚያ ተቋም የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

27/07/2026
የሀላባ ዞን ፀጥታ ተቋማት በሀላባ ቁሊቶ ከተማ የክረምት በጎ ፈቃድ ተግባራት አካል የሆነውን የጽዳት ዘመቻ አካሄዱ ******ሐምሌ፣18/2018የሀላባ ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙ...
25/07/2026

የሀላባ ዞን ፀጥታ ተቋማት በሀላባ ቁሊቶ ከተማ የክረምት በጎ ፈቃድ ተግባራት አካል የሆነውን የጽዳት ዘመቻ አካሄዱ
******
ሐምሌ፣18/2018የሀላባ ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙደስር ጉታጎ ጽዱ ከተማን ለመፍጠር በሚደረገው ሂደት የፀጥታ ተቋማት ለህብረተሰቡ አጋር በመሆን እየሰሩ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

የጽዳት ዘመቻው የከተማዋን ውበትንና ገጽታን በመጠበቁ ረገድ ትልቅ ሚና እንዳለው የገለጹት አቶ ሙደስር የጸጥታ ተቋማት የህዝቡን ሰላምና ደህነነት ከመጠበቅ ባለፈም በጽዳት ዘመቻ በመሳተፍ ገጽታውን የሚጠብቁ ስለመሆናቸው ተናግረዋል።

በተቀናጀ መልኩ የተጀመሩትን የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራትን ሁሉንም የፀጥታ ተቋማትን ባሳተፈ መልኩ የሚቀጥሉ መሆናቸውን ኃላፊው አመላክተዋል።

በመጨረሻም በጽዳት ዘመቻ መርሐግብሩ የክልሉ አድማ በታኝ፣ የዞን ማዕከል ፖሊስ አባላት፣የከተማ አስተዳደር ፖሊስ አባላትና የቁሊቶ ማረሚያ ተቋም አባላት ተሳታፊ ሆነዋል።

ስል የሀላባ ዞን መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ዘግቧል።

ፖሊስነትና ቅንነትፖሊስነት የደንብ ልብስ መልበስና ሕግ ማስከበር ብቻ አይደለም፤ የሕዝብ አለኝታነትና ታላቅ የሰብአዊነት ኃላፊነት እንጂ። የዚህ ታላቅ ሙያ እውነተኛ ውበቱና ኃይሉ ደግሞ የሚጎ...
24/07/2026

ፖሊስነትና ቅንነት

ፖሊስነት የደንብ ልብስ መልበስና ሕግ ማስከበር ብቻ አይደለም፤ የሕዝብ አለኝታነትና ታላቅ የሰብአዊነት ኃላፊነት እንጂ። የዚህ ታላቅ ሙያ እውነተኛ ውበቱና ኃይሉ ደግሞ የሚጎላው በቅንነት ሲታጀብ ነው።

ቅን ፖሊስ፡

ሕግን በፍትሕ ያስከብራል፡ ፍርሃትን ሳይሆን አክብሮትንና እምነትን በሕዝቡ ልብ ውስጥ ይዘራል፤

ለተበደሉ አለኝታ ነው፡ ደካሞችንና ተበዳዮችን በፍቅርና በርህራሄ ያዳምጣል፤

ሰላምን በጥበብ ይጠብቃል፡ በሃይል ከማስገደድ ይልቅ በቅንነትና በምክንያታዊነት ሰላምን ያሰፍናል።

በስተመጨረሻም፤ ሕግ አስከባሪነት የሰውነት ደረጃ እንጂ የሥልጣን ወንበር አይደለም። ቅንነት የተላበሰ ፖሊስ የአንድን ሀገር ሕግ ብቻ ሳይሆን የሕዝቡን ልብና ሰላም የሚያስከብር እውነተኛ የሕዝብ አለኝታ ነው!

በሀላባ ዞን ቁሊቶ ማረሚያ ተቋም የለማ ጎመን ለፖሊስ አባላትና ለሰራተኞች፣ ለህግ ታራሚዎች እና ለባለጉዳዮች በቅናሽ ዋጋ እየተሸጠ ይገኛል።
23/07/2026

በሀላባ ዞን ቁሊቶ ማረሚያ ተቋም የለማ ጎመን ለፖሊስ አባላትና ለሰራተኞች፣ ለህግ ታራሚዎች እና ለባለጉዳዮች በቅናሽ ዋጋ እየተሸጠ ይገኛል።

Address

Alaba Kulito
Alaba K'ulito

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when በማዕ/ኢት/ክ/መንግስት የሀላባ ዞን ቁሊቶ ማረሚያ ተቋም posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share