13/08/2026
የእናቶችንና የህፃናትን ህመምና ሞት ለመቀነስ በተሰሩ የተቀናጁ ተግባራት ተጨባጭ ውጤት መመዝገቡን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ አስታወቀ።
ይህ የተገለጸው በዓለም የምግብ ፕሮግራም (WFP) ድጋፍ እየተተገበረ ያለውን የተቀናጀ የምግብ እጥረት ሕክምናና የምግብ ድጋፍ ፕሮግራም የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም በቡታጅራ ከተማ በተገመገመበት መድረክ ነው።
የጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የጤና ፕሮግራሞች ዘርፍ ኃላፊ አቶ አሸናፊ ጴጥሮስ እንደገለጹት፣የእናቶችና የህፃናት ጤናን ለማሻሻል በተሰራዉ ጠንካራ ስራ ተጨባጭ ውጤት መመዝገቡን ገልጸዋል፡፡
የእናቶችንና ህጻናትን ሞት ለመቀነስ እንደ ክልል ትልቅ ግብ ተጥሎ እየተሰራ መሆኑን ያነሱት አቶ አሸናፊ ቀደም ሲል ከ100,000 እናቶች 267 እናቶች የሚሞቱ ሲሆን፣ በ2018 በጀት ዓመት ይህ ቁጥር ወደ 140 በ100,000 መቀነሱን ገልጸዋል። የህፃናትና የጨቅላ ህፃናት ሞትም በከፍተኛ ደረጃ መቀነሱ ተገልጿል።
በተጨማሪም በተመረጡ ወረዳዎች ለነፍሰጡርና ለሚያጠቡ እናቶች እንዲሁም ለህፃናት የተመጣጠነ ምግብ ድጋፍ ተደርጓል።
ይህን ተግባር ከማገዝ አንፃር የአለም የምግብ ፕሮግራም በርካታ ድጋፎችን ሲያደርግ መቆየቱን ያነሱት አቶ አቨናፊ ህፃናት ፣ነብሰ ጡር እናቶች እንዲሁም የሚያጠቡ እናቶችን በምግብ እጥረት እንዳይጎዱ በተለይም በመካከለኛ የምግብ እጥረት የተጎዱ አካላትን የመደገፍ ስራዎች መሰራቱን ተናግረዋል ።
የልየታ ስራዉ ከሁለት ዓመት በታች ላሉ ህፃናት፣ አጥቢ እናቶችና ነብሰጡር እናቶች ለምግብ እጥረት ተጋላጭ እንዳይሆኑ 1780 እማ / አባወራ ድጋፍ እንዲያገኙ ተደርገዋል።
የክልሉ ጤና ቢሮ የእናቶች እና ህፃናት ጤናና ስርዓተ ምግብ አገ/ት ዳይሮክተሬት ዳይሬክተር አቶ ተስፉዬ ሌጅሶ በበኩላቸው
እንደሀገር ብልም እንደክልል የተረጅነት አመለካከትን በመቅረፍ ራስን የመቻል አቅምን ለማጠናከር የወስጥ አቅማችንን በማሳደግ በትኩረት መስራት ይገባል።
በአጠቃላይ፣ የእናቶችና የህፃናት ህመምና ሞትን ለመቀነስ የተጀመሩ ተግባራት በቀጣይም በተቀናጀ አሰራር ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ተጠቁሟል።
የወይይቱ ተሳታፊዎች እንደተናገሩት ዘላቂ አገልግሎት ለህብረተሰቡ ለማቅረብ ቅንጅታዊ አሰራርን ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆናቸውን አንስተዋል
በመድረኩ የዞን ጤና መምሪያ ሀላፊዎች ፣የወረዳ አስተዳዳሪዎችና ጤና ጽ/ቤት ሀለፊዎች፣የዞን የእናቶችና ህፃናት አስተባባሪዎችና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።