በሀላባ ዞን የአቶቲ ኡሎ ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Alaba K'ulito
  • በሀላባ ዞን የአቶቲ ኡሎ ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

በሀላባ ዞን የአቶቲ ኡሎ ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ይህ የአቶቲ ኡሎ ወረዳ መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ህጋዊ የሚዲያ ገፅ ሲሆን አጠቃላይ ወቅታዊና መደበኛ የመንግሥት ሥራዎች ዘወትር ይተላለፋል። ከታች ያለውን Follow በታን በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።

የዞኑ ትምህርት መምሪያ በዞኑ በአቶቲ ኡሎ ወረዳ በተለያዩ ትምህርት ቤቶች በመገኘት የ2019 የትምህርት ዘመን የተማሪዎችን የምዝገባ ሂደት ክትትል እያደረገ ነው=========ነሐሴ፣28/201...
03/09/2026

የዞኑ ትምህርት መምሪያ በዞኑ በአቶቲ ኡሎ ወረዳ በተለያዩ ትምህርት ቤቶች በመገኘት የ2019 የትምህርት ዘመን የተማሪዎችን የምዝገባ ሂደት ክትትል እያደረገ ነው
=========
ነሐሴ፣28/2018 የሀላባ ዞን ትምህርት መምሪያ በዞኑ በአቶቲ ኡሎ ወረዳ በተለያዩ ትምህርት ቤቶች በመገኘት የ2019 የትምህርት ዘመን የተማሪዎችን የምዝገባ የእስከአሁን ያለውን አፈጻጸም ክትትል አደረገ እያደረገ ይገኛል።

የዞኑ ትምህርት መምሪያ በወረዳው ያለውን የምዝገባ አፈጻጸም ሂደትን በተመለከተ ከወረዳው አስተባባሪ አመራሮች ጋር ወይይት ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

በክትትሉ የሀላባ ዞን የዋና አስተዳዳሪ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ አቶ ሁሴን ሮባና የዞኑ ትምህርት መምሪያ ሀላፊ ዶ/ር ኤፍሬም ዘለቀ እንዲሁም የወረዳው የትምህርት ጽ/ቤት አመራሮች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
የሀላባ ዞን መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ

የመልካም አስተዳደር ችግሮችን  ለመቅረፍ የተቋማት  አገልግሎቶችን የማዘመን ተግባር መከናወኑን የክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ገለፀ(ሆሳዕና፦ ነሐሴ /28/2018) የማዕከላ...
03/09/2026

የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ የተቋማት አገልግሎቶችን የማዘመን ተግባር መከናወኑን የክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ገለፀ

(ሆሳዕና፦ ነሐሴ /28/2018) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የ2018 አፈጻጸም እና በ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ዙሪያ የሚመክር የሴክተር ጉባኤ '' ሰው ተኮር አገልግሎት ለልህቀት'' በሚል መሪ ሀሳብ በሀላባ ቁሊቶ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ገብሬ ጋጌ እንደተናገሩት በበጀት ዓመቱ እንደ ክልልም ይሁን እንደ ተቋም በርካታ ውጤታማ ስራዎች ተሰርቷል።

የመንግስት ፖሊሲዎች እና ስትራቴጂዎች የሚፈፀሙት በየ ደረጃው በሚገኙ ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሆንም በለፉት ስርዓቶች ባህሪይ እና ተልዕኮ የተነሰ የህዝብን ፍላጎት ጥቅም ማሟላት አለመቻሉን ገልፀዋል።

የለውጡ መንግስት ቀደም ሲል አስተዋሉ የነበሩ ችግሮችን ለመፍታት የዲጂታል ሲቪል ሰርቪስ በመገንባት አገልግሎቶችንና ውሳኔዎችን የማቀላጠፍ ስራ እየተሰራ ነው ብለው በዚህም የህብረተሰብን የመልካም አስተዳደር ችግሮች እየተፈቱ ናቸው ብሏል።

በክልሉ በአሁኑ ወቅት 7 መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተመርቀው ለህዝብ እንግልትና እሮሮ ምንጭ ምክንያት የሆኑ ዋና ዋና አገልግሎቶች ተለይተው ለህዝቡ ተገቢውን አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

የህብረተሰቡን የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ የተቋማት አገልግሎቶችን የማዘመን ስራዎች ተሰርቷል በዚህም ተጨባጭ ውጤቶችን ማስመዝገብ ተችሏል።

የሀላባ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ ሀጂ ኑሪዬ ኡንታሌ እንደገለፁት ጥራት ቀልጣፋና ጥራት ያለውን አገልግሎት ለመስጠት የፐብሊክ ሰርቪስ ሚና ከፍተኛ ነው።

አገልግሎቶችን ከወረቀት ነፃ በማድረግ የህብረተሰብ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ የተጀመሩ ስራዎች አበራታች እንደሆነም ገልፀዋል።

በመድረኩም የሴክተሩ ታችኛው መዋቅሮች የስራ ኃላፊዎች፣ ፈጻሚዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።

በአድነው አሰፋ

የዞኑ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ በ2018 ዓ.ም የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት እውቅና ሽልማ ተሰጠ=====ነሀሴ 27/2018 የሀላባ ዞን መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉ...
02/09/2026

የዞኑ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ በ2018 ዓ.ም የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት እውቅና ሽልማ ተሰጠ
=====

ነሀሴ 27/2018 የሀላባ ዞን መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ የ2018 በጀት አመት አፈጻጸም ሪፖርት ማጠቃለያ እና የ2019 ዕቅድ ዙሪያ ውይይት መድረክ ተካሄደዋል።

በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ መምሪያው በ2018 ዓ.ም የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ከ1ተኛ እስከ 3ተኛ ደረጃ ለወጡ የዞኑ ፎካል ፐርሳኖች፣ የመምሪያው ባለሙያዎች የኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤቶችን እውቅና ሽልማት ተሰጥተዋል።

በመድረኩ ላይ ድጋፍና ክትትል ወቅት በተገኙ በጥንካሬና በጉድለት በተነሱት ዋና ዋና ተግባራት ግብረ መልስና አፈጻጸም ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

በዚህ መሰረት፦ የአቶቲ ኡሎ ወረዳ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት በተደረገው #አንደኛ ደረጃ በመያዝ የዋንጫና ሰርተፍኬት ተሸላሚ መሆን ተችለዋል።

የዌራ ዲጆ ወረዳ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት #ሁለተኛ ደረጃ በማጠናቀቅ የዋንጫና ሰርተፍኬት አግኝተዋል።

የዌራ ወረዳ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት #ሶስተኛ ደረጃ በመውጣት የዋንጫና ሰርተፍኬት ተሸላሚ ሆነዋል።

#የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት በበጀት ባከናወናቸው የላቀ አፈጻጸም ልዩ ተሸላሚ ሆነዋል።

በሌላ በኩል የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ሚዲያ ዘርፍ፣ የሀላባ ቴለቪዥን፣ የዞን ማዕከል ፎካል ፐርሳኖች፣ ከ1ኛ- 3ተኛ የወጡ የመምሪያው ባለሙያዎች የእውቅና ሰርተፍኬት ተሰጥተዋል።

በዚህም የሀላባ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ መሀመድአሚን መሀዲ፣ የሀላባ ዞን መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ሀላፊ አቶ ሀሩና አህመድ እና የዞኑ ምክር ቤት ማህበራዊ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ የተከበሩ አቶ ሪባቶ ቤያጎ ጋር በመሆን የእውቅና ሽልማቱን አበርክተዋል።

መምሪያው የ2019 በጀት ዓመት የግብ ስምምነት ፊርማ ተከናወነ====ነሀሴ 27/2018 የዞኑ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ የ2019 በጀት ዓመት የግብ ስምምነት ፊርማ ተከናውነዋል።የሀላባ ዞ...
02/09/2026

መምሪያው የ2019 በጀት ዓመት የግብ ስምምነት ፊርማ ተከናወነ
====

ነሀሴ 27/2018 የዞኑ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ የ2019 በጀት ዓመት የግብ ስምምነት ፊርማ ተከናውነዋል።

የሀላባ ዞን መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ከታችኛው መዋቅር እና ከመምሪያው ዳይሬክተሮች ጋር የ2019 በጀት ዓመት የግብ ስምምነት ተፈራርመዋል።

በዚህ ወቅት የመምሪያው ሀላፊ አቶ ሀሩና አህመድ እንደገለጹት የግብ ስምምነቱ ዋና ዓላማ የ2019 በጀት ዓመት ዕቅዱን በተቀናጀና በውጤታማ መንገድ ለመፈጸም እና የስራ አፈጻጸምን ለማሻሻል ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

ታችኛው መዋቅርና የመምሪያ ዳይሬክተሮች እያንዳንዱ ዘርፍ የተሰጠውን ሀላፊነት በወቅቱና በጥራት እንዲያከናውን፣ ውጤት ተኮር ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ስራ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

ባለፈው አመት ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን በቅንጅት በመሰራቱ የታዩ አበረታች ስራዎችን ማጠናከር ያስፈልጋል ይገባል - የተከበሩ አቶ መሀመድአሚን መሀዲ =====ነሀሴ 27/2018 በማዕከላዊ ኢትዮጵያ...
02/09/2026

ባለፈው አመት ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን በቅንጅት በመሰራቱ የታዩ አበረታች ስራዎችን ማጠናከር ያስፈልጋል ይገባል - የተከበሩ አቶ መሀመድአሚን መሀዲ
=====

ነሀሴ 27/2018 በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የሀላባ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ የ2018 ዓ.ም አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 ዓ/ም ዕቅድ ዝግጅት መድረክ ተካሄደዋል።

በዚህ ወቅት የሀላባ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ መሀመድአሚን መሀዲ እንደገለጹት ባለፈው አመት ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን በቅንጅት በመሰራቱ የታዩ አበረታች ስራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ ገልጸዋል።

ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን በህዝብና በመንግስት የሚከናወኑ ማናቸውም ተግባራት በሚዲያ ተደራሽ በማድረግ የላቀ አስተዋፅኦ ያለው መሆኑን ጠቅሰዋል።

ሚዲያና ኮሙኒኬሽን መረጃ ለሕዝብ ከማድረስ ባሻገር በዞኑ ሰላም ቀጣይነት እንዲኖር መረጋጋትና ልማት እንዲሰፍን ታሪካዊ ሚና እየተወጣ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

​በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ተግባራት የዘርፉን በተግባር ያረጋገጡ እንደነበሩ ዋና አፈ ጉባኤው ገልጸዋል።

እነዚህ ስራዎች የህዝቡን የልማት እንቅስቃሴ የሚያፋጥኑ፣ እውነትን የሚያጎሉና የዞኑን መልካም ገጽታ በመገንባት ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደነበር ገልጸው ቀጣይነት እንዲኖር መስራት ይገባል ብለዋል።

ዞናችን ከለውጡ ወዲህ በሁሉም ዘርፍ ከፍተኛ የሆኑ ለውጦች መታየቱን በመጠቆም ይህም በሚዲያ ሲደገፍና ሲተዋወቅ እንደነበርና ተጠናክሮ ሊመራ እንደሚገባም ገልጸዋል።

ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ተቋማት ወቅታዊና ሚዛናዊ መረጃዎች ተደራሽ ለማድረግ የበኩላቸውን ድርሻ ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ተቋማት በጥራት፣ በይዘትና ዓላማ ተኮር ስራ በመስራት ተወዳዳሪ መሆን እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ኮሙኒኬሽን ተቋማት ጠንካራ አቅም ለመፍጠር ከማህበረሰብ እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀራርበውና ተቀናጅተው መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

የሚዲያ ተቋም ሌላውን ለመቅደም በሚያደርገው ችኮላ የሚለቃቸው የማህበራዊ ሚዲያ ዘገባዎችም ጥንቃቄ ሊደረግባቸው እንደሚገባ ገልጸዋል።

ስራዎችን መድረክ ተኮር ከማድረግ ይልቅ ይዘት ላይ ተመስርቶ ተግባር ተኮር በማድረግ ህብረተሰቡ ጋር ወርዶ መስራት ይገባልም ብለዋል።

በአመቱ የታዩ ጥንካሬዎች በማስቀጠል በቀጣይ በጀት አመት ደግሞ ከዚህ በበለጠ ተቋሙ የሚዲያ ተደራሽነትን አጠናክሮ ማከማከናን ይገበዋል ብለዋል።

ማህበራዊ ሚዲያውን ለበጎ አላማ በማዋል የሀሰትና አፍራሽ የዘገባ ተልዕኮዎችን ለህብረተሰቡ አጋልጦ መስጠት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የሀላባ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ሀላፊ አቶ ሀሩና አህመድ በበኩላቸው ወቅቱን ያገናዘበና የሚዲያ ስራ ከመቸውም ጊዜ በላይ መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል።

በዘንድሮው አመት በስፖርታዊ ውድድሮች፣ የሀላባ ሴራ በዓል ለማስተዋወቅ፣ የሀላባ ኢንተርናሽናል ስታዲየም፣ የዞኑ አስተዳደር ጽ/ቤት ህንጻ፣ የልማት ስራዎች በመመረቅና የሚዲያ ቱሩ ጨምረው በመጎብኘት በርካታ ስራዎች መከናወኑ ጠቁመዋል።

በዞኑ የሚዲያና ኮሙዩናኬሽን ዘርፉ የምርጫ ስራዎች በሂደቱ ፍትሃዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ አሳታፊና በተዋናዮች ዘንድ ተዓማኒነት ያለው እንዲሆን የተለያዩ ሁነቶችን በወረዳ፣ በዞንና በክልል የፓርቲው ሚዲያ ከፍተኛ ሽፋን በመስጠት አመርቂ ውጤት ማሳየቱም ተናግረዋል።

የሚዲያ ተቋማት በመንግስት በኩል የተከናወኑ የልማት ስራዎች እንዲሁም በህብረተሰቡ ዘንድ የሚነሱ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች የሚዳሰሱበት መሆኑን ጠቁመዋል።

አሁን ያለንበት ዘመን በቴክኖሎጂ እድገት የረቀቁ በመሆኑ ፈጣንና ትክክለኛ መረጃን በወቅቱ ለህብረተሰቡ ለማድረስ የሚረዳ ቴክኖሎጂን ለመጠቀም ተቋም መደገፍ እጅግ አስፈላጊ ነው ብለዋል።

የጠነከረ ግንኙነት በመፍጠር የመንግስትን ፖሊሶች፣ አጀንዳዎች፣ እቅዶች እና ትኩረት አቅጣጫዎችን የማሳወቅ ስራዎች እንደሚጠናከር ገልጸዋል።

የሚሰሩ ስራዎችን በሚገባ በሚዲያዎች ማስተላለፍ እንደሚገባ ገልፀው ሀሰተኛ ማህበራዊ ሚዲያዎችን መመከት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ኮሙዩኒኬሽን የሚዲያ ተግባራት በተቀናጀ መልኩ እንዲሰሩ የሚዲያ ባለድርሻዎች የበኩላቸውን ድርሻ ሊወጡ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በቀጣይም የሚከናወኑ ተግባራት የትኩረት አቅጣጫዎች ተቀምጠው መስራት ከሁላችን ይጠበቃል ሲሉም አሳስበዋል።

በ2018 ዓ/ምየተከናወኑ ተግባራት ሪፖርት በመምሪያው የእቅድ ዝግጅትና በጀት ክትትል ባለሙያ ስሆን የቀረበውን ሪፖርት መሰረት በማድረግ የውይይቱ ተሳታፊዎች ሀሳብና አስታያየት ሰጥተዋል።

በመድረኩ ላይ የሀላባ ቴሌቪዥን ምክትል ስራአስኪያጅ አቶ አብዲ ጌቻራ፣ የዞኑ ፓርቲ ሚዲያና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ሀላፊ አቶ በድሩ ከድር፣ የአራቱም መዋቅር ኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት ሀላፊዎች፣ ማኔጅመንት አባላት፣ ፎካል ፐርሳኖች፣ ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

የሀላባ ዞን መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ

02/09/2026
በድጅታል መታወቂያ የእስካሁኑ አፈጻጸምና የቀጣይ አቅጣጫ ዙርያ ከባለድርሻ ተቋማት ጋራ ውይይት ተደረገ።ውይይቱን የመሩት አቶ ጀማል ቤያ የአስ/ር ጽ/ቤት ኃለፍና በድሩ ሙናቴ የፐብሊክ ሰርቪስ...
02/09/2026

በድጅታል መታወቂያ የእስካሁኑ አፈጻጸምና የቀጣይ አቅጣጫ ዙርያ ከባለድርሻ ተቋማት ጋራ ውይይት ተደረገ።

ውይይቱን የመሩት አቶ ጀማል ቤያ የአስ/ር ጽ/ቤት ኃለፍና በድሩ ሙናቴ የፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ስሆን ባለድርሻ ተቋማት በተገኙበት መድረኩ ተካሂዷል።

ነሐሴ፣27/2018 ዓ.ም)ጉባ አቶቲ ኡሎ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን

02/09/2026
02/09/2026

የአቶቲ ኡሎ ወረዳ በበጀት አመቱ የላቀ አፈጻጸም በማስመዝገብ ከዞኑ #1ኛ

1ኛ ደረጃ እንኳን ደስ አላችሁ/አለንየአቶቲ ኡሎ ወረዳ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን በዞኑ ካሉ ከኮሚዩኒኬሽን  መዋቅሮች 1ኛ ደረጃ በመውጣት የዋንጫና የሰርተፍኬት ተሸላሚ ሆነየአቶቲ ኡሎ ወረዳ መን...
02/09/2026

1ኛ ደረጃ እንኳን ደስ አላችሁ/አለን
የአቶቲ ኡሎ ወረዳ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን በዞኑ ካሉ ከኮሚዩኒኬሽን መዋቅሮች 1ኛ ደረጃ በመውጣት የዋንጫና የሰርተፍኬት ተሸላሚ ሆነ

የአቶቲ ኡሎ ወረዳ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን በዞናዊ በኮሚዩኒኬሽን በ2018 ዓ.ም አፈፃፀም ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ በዞኑ ካሉ በወረዳና ከተማ አስተዳደር መዋቅሮች 1ኛ ደረጃ በመውጣት የዋንጫና የሰርተፍኬት ተሸላሚ ሆኗል።

እንኳን ደስ አላችሁ

Address

Atoti Ullo Guba
Alaba K'ulito

Telephone

+251916268290

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when በሀላባ ዞን የአቶቲ ኡሎ ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share