የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Alaba K'ulito
  • የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት በመንግሥት መስሪያ ቤቶች ስለሚሠሩ ሥራዎች ለከተማው ህዝብ እንዲሁም የከተማውን ህዝብ ፍላጎቶችና ሁሉ ዓቀፍ መረጃዎችን የሚያበስር ገጽ ነው።
(3)

ከነገ ሰኞ ነሐሴ 11 ጀምሮ በዞኑ በሁሉም ት/ቤቶች የ2019 የተማሪዎች ምዝገባ በኦንላይን እንደሚጀምር ተገለፀ። የሀላባ ዞን ትምህርት መምሪያ የ2019 ዓ/ም የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ም...
16/08/2026

ከነገ ሰኞ ነሐሴ 11 ጀምሮ በዞኑ በሁሉም ት/ቤቶች የ2019 የተማሪዎች ምዝገባ በኦንላይን እንደሚጀምር ተገለፀ።
የሀላባ ዞን ትምህርት መምሪያ የ2019 ዓ/ም የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባን በማስመልከት መግለጫ ሰጥቷል።

መግለጫውን የሰጡት የሀላባ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ ዶ/ር ኤፍሬም ዘለቀ ከነገው ሰኞ ጀምሮ በቅድመ-አንደኛና በመደበኛ በሁሉም የትምህርት እርከን የተማሪዎች የ2019 የትምህርት ምዝገባ እንደሚጀመር ገልፀዋል።

በመሆኑም ሁሉም ባለድርሻ አካላት የምዝገባ አፈጻጸሙ በታቀደለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ በቅንጅት እንዲሰሩ ያሳሰቡ ሲሆን የተማሪ ወላጆችም በቅድመ አንደኛም ሆና በመደበኛ ትምህርት ልጆቻቸው ፈጥነው እንዲያስመዘግቡ አሳስበዋል።

አክለውም በትምህርቱ ዘርፍ የተጀመሩ የክረምት በጎ ስራዎች፣ የት/ቤቶች ዕድሳትና ጥገና፣ የት/ቤቶችን ውስጥ ገቢ በማሳደግ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ተጀመሩ ኢንሼቲቮችና የትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉም ጨምረው አሳስበዋል።

ከተለያዩ ምንጮች በሚገኘው ሀብትም የት/ቤቶችን ግብዓትን በማሟላት የት/ቤቶችን ደረጃ በማሻሻል ት/ቤቶች ለተማሪዎች ሳቢና ማራኪ እንዲሆኑ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

የተማሪዎች ምዝገባ ሂደቱ ከተያዘለት ጊዜ ቀደም ብሎ እንዲጠናቀቅ ሁሉም ባለድርሻ አካላትና የትምህርት አመራሩ በቅንጅት እንዲሰሩ አሳስበዉ በዞኑ በ2019 በአጠቃላይ 123,367 ተማሪዎችን ለመመዝገብ መታቀዱን ጨምረው ገልፃዋል።

ነሐሴ 10/2018 ሀላባ ቲቪ

የሀላባ ኮሚዩኒቲ ዓመታዊ የልጆች የአረንጓዴ አሻራ ለ5 ተከታታይ አመት አረንጓዴ አሻራ ችግኝ የተከሉ ቆንጆዎች እውቅና ሰጠነሀሴ 10/2018 የሀላባ ኮሚዩኒቲ ዓመታዊ የልጆች  የአረንጓዴ አሻ...
16/08/2026

የሀላባ ኮሚዩኒቲ ዓመታዊ የልጆች የአረንጓዴ አሻራ ለ5 ተከታታይ አመት አረንጓዴ አሻራ ችግኝ የተከሉ ቆንጆዎች እውቅና ሰጠ

ነሀሴ 10/2018 የሀላባ ኮሚዩኒቲ ዓመታዊ የልጆች የአረንጓዴ አሻራ ቆንጆዎቹ ችግኝ ተከለ እንደሚካሄድ ይታወቃል።

ለዚህም በዛሬው የሀላባ ኮሚዩኒቲ ዓመታዊ የልጆች የአረንጓዴ አሻራ ለ5 ተከታታይ አመት አረንጓዴ አሻራ ችግኝ የተከሉ ቆንጆዎች እውቅና ሰጥተዋል።

መርሀ-ግብሩ ዋና ዓላማው አባቶች ለልጆቻቸው በጎነትን በማስተማርና የተነጻ ትውልድ ለመቅረጽ ያለመ መሆኑን ተገልጿል።

በመጨረሻም በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር እድገት ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ ከዚህ በፊት የተተከለው ችግኝ ተዟዙረው ተመልክቷል።

መርሀ-ግብሩ ላይ የሀላባ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የዞኑ ግብርና መምሪያ ሀላፊ አቶ ሀጂ ኑሪዬ፣ የሀላባ ኮሚዩኒቲ ማህበረሰብ እና የነገ ሀገር ተረከብ ቆንጆች ተገኝተው እውቅናቸውን ተቀብለዋል።

"የከተማ መሬት ከህገ ወጥ ወረራ ለመከላከል በዋናነት ከህብረተሰቡ ከባለድርሻ አካላት በመሆን በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ተገለጸ!!!ነሀሴ 10/2018 "ውስን የሆነውን የመሬት ሀብታችንን ከ...
16/08/2026

"የከተማ መሬት ከህገ ወጥ ወረራ ለመከላከል በዋናነት ከህብረተሰቡ ከባለድርሻ አካላት በመሆን በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ተገለጸ!!!

ነሀሴ 10/2018 "ውስን የሆነውን የመሬት ሀብታችንን ከሕገ-ወጥ ወረራና ምዝበራ በመከላከል፣ ፍትሐዊ የከተሞች ዕድገትን እናረጋግጣለን በሚል መሪ ቃል “የሀላባ ቁሊቶ ከተማ የህገወጥ መሬት ወረራን ለመከላከል የተዘጋጀ የንቅናቄ መድረክ" ተካሄደዋል።

በመድረኩ ላይ የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የቤት ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ አቶ ንጉሴ አቢሶ የንቅናቄ ሰነድ አቅርበዋል።

በዚህ ወቅት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ ሀላፊ አቶ አክመል አህመዲን እንደገለጹት መሬት ላይ የሚስተዋሉ ህገወጥና ብልሹ አሰራሮችን በጋራ መከላከል ይገባል ብለዋል።

መሬቱ በስርዓት እንዲመራ ለማስቻል በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላት መረባረብ እንደሚገባ አቶ አክመል አህመዲን አሳስበዋል።

የሀገርን እድገት በማረጋገጥና ህዝብን ከተረጅነት ለማላቀቅና መሬትን ህግ በሚፈቅደው መንገድ ብቻ መጠቀም እንደሚጠበቅባቸው ገልጸዋል።

ከተሞችን ከህገወጥ ወረራ ነጻ በመድረክ ለከተማችን እድገትና ልማት በትኩረት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ሙህዲን ሁሴን በበኩላቸው የመሬት ወረራ ተግባር በህዝብ ልማት ላይ የሚያመጠውን ተፅዕኖ የጎላ ነው ብለዋል።

እየተስፋፋ ያለውን ህገ-ወጥ የመሬት ወረራን በመለየት ህግ የማስከበር ስራን ለመስራት ህብረተሰብ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል።

ህግ ባለበት ከተማ ህገ-ወጦች ከተማችንን መውረር ስለማይገባቸው የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ህዝባችን ይህንን ለመከላከል ሀላፊነታችንን በአግባቡ መወጣት አለብን ብለዋል።

የህዝብና የመንግስት ሀብት የሆነውን መሬት የማቀረመት ስርዓት አልበኝነት ህግና ስርዓትን ተከትለን በቅንጅትና በቁርጠኝነት ሁሉም ባለድርሻ ሀላፊነቱን መወጣት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

መሬት ለእድገትና ለኢንቨስትመንት ፍሰት መሰረት መሆኑን ያሉት ዋና አስተዳዳሪው የመሬት ስርዓት የሚመራው በራሱ የሆነ የመንግስት አሰራር መኖሩን ገልጸዋል።

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ገመዳ መሀመድ እንደገለጹት የከተማ አስተዳደሩ ህገ-ወጦችን ስርዓት ለማስያዝ በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል።

የተጀመረው ህገወጥ የመሬት ወረራ የመከለል ሂደት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና የበኩላቸውን መወጣት እንደሚገባ አሳስበዋል።

የሀላባ ዞን ብልጽግና ቅ/ጽ/ቤት ሀላፊና የዞኑ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ መሀመድከማል ኑሪዬ፣ የከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አብዱልመጅድ ፍጣሞ፣ የሀላባ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ምክትልና የዋና ሀላፊ ተወካይ ኢንጂነር ሀቢስሰ፣ እና ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድ አካላት ተገኝተዋል።

አቶ ባህሩ ከማል ለሀላባ ከነማ 10,000 ብር ገቢ አድርገዋል።የንግዱ ማህበረሰብ ሀላባ ከነማ ለመደገፍ ገቢ በማሰባሰብ እያደረገ ባለው አስተዋጽኦ አቶ ባህሩ ለሀላባ ከነማ 10,000 ብር ገ...
16/08/2026

አቶ ባህሩ ከማል ለሀላባ ከነማ 10,000 ብር ገቢ አድርገዋል።

የንግዱ ማህበረሰብ ሀላባ ከነማ ለመደገፍ ገቢ በማሰባሰብ እያደረገ ባለው አስተዋጽኦ አቶ ባህሩ ለሀላባ ከነማ 10,000 ብር ገቢ በማድረግ አጋርነታቸውን አሳይተዋል።

ከልብ እናመሰግናለን

የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የመምህራን፣ የወላጆች እና የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ ስራ ወሳኝ ነው፦ አቶ አብዲልቃድር ኢማም ሎላሶነሐሴ 10/2018 ዓ.ም የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ት...
16/08/2026

የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የመምህራን፣ የወላጆች እና የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ ስራ ወሳኝ ነው፦ አቶ አብዲልቃድር ኢማም ሎላሶ

ነሐሴ 10/2018 ዓ.ም የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት «የትምህርት ለትውልድ» ጥሪን መነሻ በማድረግ እና የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባን አስመልክቶ ሰፊ የንቅናቄ መድረክ አካሂዷል።

መድረኩን የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ እና የገቢዎች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብዲልቃድር ኢ/ሎላሶ፣ የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ብ/ፓ/ቅ/ጽ/ቤት ምክትልና የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሁሴን አብደላ እንዲሁም የትምህርት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኑረዲን ከድር በጋራ መርተዋል።

ትምህርት የነገ አገር ተረካቢ ትውልድ መገንቢያ መሠረት በመሆኑ የከተማችንን ትምህርት ቤቶች ማጠናከር የመላው ህብረተሰብ ኃላፊነት ሊሆን እንደሚገባ አቶ አብዲልቃድር ኢማም ሎላሶ ገልጸዋል።

የትምህርት ቤቶችን መሠረተ ልማት ለማሻሻልና ክፍተቶችን ለመሙላት የመንግሥት ጥረት ብቻውን በቂ እንደማይሆን ገልጸው ትምህርት ቤቶቹ ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት የውስጥ ገቢያቸውን ማጠናከርና ማስፋት እንደሚገባቸው አስረድተዋል።

ትውልድ የሚቀረጸው በትምህርት መሆኑን በመረዳት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ለትምህርት ዘርፍ ትኩረት ሰጥተን መረባረብ ይገባልም ብለዋል።

በከተማ አስተዳደሩ በፖለቲካዊ ቁርጠኝነት ታግዘን በትምህርት ጥራትና ተደራሽነት ላይ የተሻለ ለውጥ ማምጣት በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ የሀ/ቁ/ብ/ፓ/ቅ/ጽ/ቤት ምክትልና የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሁሴን አብደላ ገልጸዋል።

የትምህርት ሥራ የነገን ዕጣ ፈንታ የሚወስን ብሔራዊ አጀንዳ መሆኑን ጠቅሰው የፖለቲካና የሥራ አስፈፃሚ አካላት ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት ንቅናቄውን ወደ ታችኛው መዋቅር ወርዶ ውጤታማ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

በመድረኩ የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ኑረዲን ከድር ከመጪው ሰኞ ከነሐሴ 11/2018 ዓ.ም እስከ ጳጉሜ 5/2018 ዓ.ም ድረስ በሁሉም ትምህርት ቤቶች የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ እንደሚካሄድ ጠቁመዋል።

ኃላፊው አክለውም ዕድሜያቸው ከ4 ዓመት ጀምሮ ያሉ ሕፃናት፣ ለትምህርት የደረሱ ልጆች እንዲሁም በተለያየ ምክንያት ከትምህርት ገበታ ውጭ የሆኑ ተማሪዎች አስፈላጊውን መረጃ በማሟላት በወቅቱ እንዲመዘገቡ ጥሪ አቅርበዋል።

በተጨማሪም መምህራን በየትምህርት ቤቶቻቸው በመደበኛ የስራ ሰዓት ተገኝተው የምዝገባ ሂደቱን በጥብቅ ድሲፕሊን እንዲመሩ መመሪያ ተሰጥቷል።

በመድረኩ ላይ የሀላባ ቁሊቶ ከተማ ምክር ቤት አፈጉባኤ የተከበሩ አህመዲን ሁሴን፣ የከተማ አስተዳደሩ መካከለኛ አመራሮች፣ የቀጠና ሊቀመንበሮች፣ ሥራ አስኪያጆች፣ የትምህርት ጽሕፈት ቤት ማኔጅመንትና የትምህርት ዘርፍ አመራሮች ተገኝተዋል።

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ የህገወጥ መሬት ወረራን ለመከላከል የተዘጋጀ የንቅናቄ የውይይት መድረክ እየተደረገ ይገኛል!!!ነሀሴ 10/2018 "ውስን የሆነውን የመሬት ሀብታችንን ከሕገ-ወጥ ወረራና ም...
16/08/2026

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ የህገወጥ መሬት ወረራን ለመከላከል የተዘጋጀ የንቅናቄ የውይይት መድረክ እየተደረገ ይገኛል!!!

ነሀሴ 10/2018 "ውስን የሆነውን የመሬት ሀብታችንን ከሕገ-ወጥ ወረራና ምዝበራ በመከላከል፣ ፍትሐዊ የከተሞች ዕድገትን እናረጋግጣለን በሚል መሪ ቃል “የሀላባ ቁሊቶ ከተማ የህገወጥ መሬት ወረራን ለመከላከል የተዘጋጀ የንቅናቄ መድረክ" ከከተማው ህብረተሰብ ክፍል ጋር የውይይት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

የውይይት መድረኩን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ ሀላፊ አቶ አክመል አህመዲን፣ የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ሙህዲን ሁሴን እና የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ገመዳ መሀመድ በጋራ እየመሩ ይገኛሉ።

በመድረኩ ላይ የሀላባ ዞን ብልጽግና ቅ/ጽ/ቤት ሀላፊና የዞኑ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ መሀመድከማል ኑሪዬ፣ የከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አብዱልመጅድ ፍጣሞና የሀላባ ቁሊቶ ከተማ ምክር ቤት አፈጉባኤ የተከበሩ አህመዲንን ሁሴንን ጨምሮ ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

“የሀላባ ቁሊቶ ከተማ የህገወጥ መሬት ወረራን ለመከላከል የተዘጋጀ የንቅናቄ መድረክ" እየተካሄደ ነው====ነሀሴ 10/2018 "ውስን የሆነውን የመሬት ሀብታችንን ከሕገ-ወጥ ወረራና ምዝበራ በ...
16/08/2026

“የሀላባ ቁሊቶ ከተማ የህገወጥ መሬት ወረራን ለመከላከል የተዘጋጀ የንቅናቄ መድረክ" እየተካሄደ ነው
====

ነሀሴ 10/2018 "ውስን የሆነውን የመሬት ሀብታችንን ከሕገ-ወጥ ወረራና ምዝበራ በመከላከል፣ ፍትሐዊ የከተሞች ዕድገትን እናረጋግጣለን በሚል መሪ ቃል “የሀላባ ቁሊቶ ከተማ የህገወጥ መሬት ወረራን ለመከላከል የተዘጋጀ የንቅናቄ መድረክ" እየተካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ሙህዲን ሁሴን፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ ሀላፊ አቶ አክመል አህመዲን፣ የሀላባ ዞን ብልጽግና ቅ/ጽ/ቤት ሀላፊና የዞኑ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ መሀመድከማል ኑሪዬ፣ የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ገመዳ መሀመድ፣ የከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አብዱልመጅድ ፍጣሞ ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድ አካላት ተገኝተዋል።

በመድረኩ ላይ የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የቤት ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ አቶ ንጉሴ አቢሶ የንቅናቄ ሰነድ እየቀረበ ይገኛል።

ፍርዳውስ ዳቦ ኢንተርፕራይዞች ለሀላባ ከነማ 10,000 ብር ገቢ አድርገዋል።የንግዱ ማህበረሰብ ሀላባ ከነማ ለመደገፍ ገቢ በማሰባሰብ እያደረገ ባለው አስተዋጽኦ ፍርዳውስ ዳቦ ኢንተርፕራይዞች ...
16/08/2026

ፍርዳውስ ዳቦ ኢንተርፕራይዞች ለሀላባ ከነማ 10,000 ብር ገቢ አድርገዋል።

የንግዱ ማህበረሰብ ሀላባ ከነማ ለመደገፍ ገቢ በማሰባሰብ እያደረገ ባለው አስተዋጽኦ ፍርዳውስ ዳቦ ኢንተርፕራይዞች ለሀላባ ከነማ 10,000 ብር ገቢ በማድረግ አጋርነታቸውን አሳይተዋል።

ከልብ እናመሰግናለን

15/08/2026

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር የንግዱ ማህበረሰብ የሀላባ ከነማ እግርኳስ ክለብን በፋይናንስ ለመደገፍ የለው ተነሳሽነት!!!

የሀላባ ከነማ ስፖርት ክለብ የዞኑ መገለጫ፣ የወጣቶች ተስፋ እና የማህበረሰቡ አንድነት ማጠናከሪያ ነው፦ አቶ ሐጂ ኑሪዬየሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር በመሆን ለሀላባ ...
15/08/2026

የሀላባ ከነማ ስፖርት ክለብ የዞኑ መገለጫ፣ የወጣቶች ተስፋ እና የማህበረሰቡ አንድነት ማጠናከሪያ ነው፦ አቶ ሐጂ ኑሪዬ

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር በመሆን ለሀላባ ከነማ እግር ኳስ ክለብ የሀብት ማሰባሰቢያ የውይይት መድረክ አካሄዷል።

የውይይቱ ዓላማ ክለቡን ህዝባዊ መሠረት በማስያዝ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውስጥ ጠንካራ እና ውጤታማ ተፎካካሪ ለማድረግ ያለመ ነው።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የሀላባ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የዞኑ ግብርና መምሪያ ሃላፊ እና የክለቡ ፕሬዝዳንት አቶ ሐጂ ኑሪዬ እንዲሁም የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባና የክለቡ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ገመዳ መሀመድ ውይይቱን በጋራ መርተዋል።

ሀላባ በታዋቂው የበርበሬ ምርቷ ብቻ ሳይሆን በስፖርቱም ዘርፍ ገናና ስሟን ከፍ ለማድረግ የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አቶ ሐጂ ኑሪዬ ገልጸዋል።

የሀላባ ከነማ የፕሪሚየር ሊግ ተሳትፎ የረጅም ጊዜ ህልም እውን የሆነበት እንደመሆኑ መጠን ህዝቡ አንድነቱን አጠናክሮ ከክለቡ ጎን ሊቆም እንደሚገባ ጥሪ አቅርበው ክለቡ ስኬታማ ሆኖ እንዲቀጥል የዞኑ እና የከተማዋ ነጋዴዎች የሚያደርጉት ድጋፍ ወሳኝ ሚና ይጫወታል ብለዋል።

ስፖርት ከመዝናኛነት ባለፈ ለአንድ ከተማ ሁለንተናዊ ዕድገት የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች በከተማችን ሲካሄዱ እንግዶችና ስፖርት ወዳዶች ወደ ሀላባ ስለሚመጡ የሆቴል፣ የትራንስፖርት፣ የንግድና የአከባቢ ምርቶች ገበያ እንዲነቃቃ የሚያደርግ በመሆኑ ህብረተሰቡ ከስፖርቱ ጎን ልሆን ይገባል ብለዋል።

ዛሬ የሚደረገው የገቢ ማሰባሰብ ድጋፍ ብቻ ሳይሆን በከተማዋ ወጣቶች እና በንግድ እንቅስቃሴው ላይ የሚደረግ የረጅም ጊዜ ኢንቨስትመንት እንደሆነም ጠቁመዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ገመዳ መሀመድ በበኩላቸው ስፖርት ህዝብን የሚያቀራርብ፣ የወንድማማችነት ስሜትን የሚያጠናክርና የጋራ ህልምን የሚያካፍል ታላቅ የህዝብ ኃይል ነው ብለዋል።

የስፖርቱን መሰረት ለማስፋት የተገነባውን ዓለምአቀፍ ስታዲየም የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ የክለቡን ቀጣይነት ማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን በመጥቀስ የንግዱ ማህበረሰብ የበኩሉን አስተዋጽኦ ማድረግ እንደሚገባው ገልጸዋል።

ክለባችን በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚያደርጋቸው ጨዋታዎች የሀላባን መልካም ገጽታ፣ ባህልና እሴት ለኢትዮጵያ ህዝብ በማስተዋወቅ ረገድ ትልቅ ሚና እንደሚጫወት አስረድተዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በክለቡ ውጤት የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው ከመድረኩ ሳይወጡ ወደ ክለቡ ባንክ አካውንት ገቢ በማድረግ አጋርነታቸውን በተግባር አሳይተዋል።

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

Address

Halaba
Alaba K'ulito

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት:

Shortcuts

Share