የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት/ Chagni town council

የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት/ Chagni town council የቻግኒ ከተማ ምክር ቤትንና ከተማዊ
አጠቃላይ እንቅስቃሴ እናደርሳለን፡፡
ለእውነተኛና ፈጣን መረጃዎች ይወዳጁን፤ ይከታተሉን!

‎የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ የተቋማት ክትትልና ቁጥጥር ስራ ዛሬም እንደቀጠለ ነው/////////////////////////////////////// ‎‎ነሀሴ  22/2018ዓ/ም የቻ/ከተ...
28/08/2026

‎የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ የተቋማት ክትትልና ቁጥጥር ስራ ዛሬም እንደቀጠለ ነው///////////////////////////////////////

‎ነሀሴ 22/2018ዓ/ም የቻ/ከተማ ምክር ቤት ጽ/ቤት

‎የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት የኢኮኖሚ ልማት በጀት ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የቻግኒ ከተማ አስተዳደር ከተማ መሰረተ ልማት ጽ/ቤትን የ2018 በጀት የ4ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈፃፀም ክትትልና ቁጥጥር አደረገ።

‎የቻግኒ ከተማ አስተዳደር ከተማ መሰረተ ልማት ጽ/ቤትም ቋሚ ኮሚቴ ባዘጋጀው ቼክሊስት መሠረት የ2018 በጀት የ4ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈፃፀማቸውን ሪፖርት በቻግኒ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና ከተማ መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ በሆኑት በአቶ ገበየሁ አልማው በኩል እንዲቀርብ ተደርጓል።
‎ በቀረበው ሪፖርት ላይ በቋሚ ኮሚቴዎች በኩል ማብራሪያ እንዲሁም ምላሽ የሚሹ ጥያቄዎች እንደሚከተሉት አንስተዋል
‎1. የኮሪደር ልማት ስራው በህብረተሰብ ተሳትፎ እንዲደገፍ በወቅቱና በጥራት ተሰርቶ እንዲጠናቀቅ የተቋሙ የክትትል ስራ ምን እንደሚመስል?
‎2.የከተማችን ደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ሰርዓት እንዲይዝ እና ከተማችን ጽዱ እንድትሆን እየተሰራ ያለ ስራ ምን ይመሰላል?
‎3.በከተማችን የሚሰሩ መሠረተ ልማቶች በጥራት እንዲሰሩ ክትትልና ቁጥጥር ምን ይመስላል ? የሚሉና ሌሎች ጥያቄዎች ተነስተው ውይይት ከተደረገባቸው በኋላ በተነሱ ጥያቄዎችና ሀሳቦች ላይ በማኔጅመንቱና በጽ/ቤት ኃላፊ በኩል በቂ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጧባቸው የክትትልና ቁጥጥር ስራ በተሳካ መንገድ ተጠናቋል።

‎‎በቻግኒ ከተማ ምክር ቤት ስር የሚገኙ  የቀበሌ ምክር  ቤቶች የነሀሴ  ወር ጉባኤ በዛሬው እለት ውይይት አካሄደዋል////////////////////‎‎ነሀሴ 20/2018 ዓ ም  (ቻግኒ ከተ...
26/08/2026


‎በቻግኒ ከተማ ምክር ቤት ስር የሚገኙ የቀበሌ ምክር ቤቶች የነሀሴ ወር ጉባኤ በዛሬው እለት ውይይት አካሄደዋል////////////////////

‎ነሀሴ 20/2018 ዓ ም (ቻግኒ ከተማ ምክርቤት)

‎የጉባኤ አጀንዳ፡-
‎አጀንዳ1:- የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማና የ2019 ዕቅድ ትውውቅ በተመለከተ
‎ $.በምክር ቤት የተነሱ ጥያቄዎችና ሃሳቦች
‎1.የቆሻሻ አወጋገድ ስራዎች ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት አለበት ተብሏል ?
‎2.የጤና ስራዎች ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት አለበት ተብሏል?
‎3.የፀጥታ ስራዎች በትኩረት ተጠናክሮ እንዲሰራ ማለትም የሮንድ ጥበቃ በትኩረት እንዲሰራ፣የኬላ ፍተሻ በትኩረት እንዲሰራ በማለት የቀበሌ ምክር አባላት አስገነዘቡ።
‎4. ለስራ አጥ ወጣቶች የስራ ዕድል መፍጠሪያ ፀጋዎችን ለይቶ በትኩረት ለስራ ፈላጊዎች ስራ ዕድል መፍጠር አለበት ተብሏል?
‎5. የህግ ወጥ ግንባታና የህግ ወጥ አጥር ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት አለበት ተብሏል?
‎6. አገልግሎት አሰጣጥ በተመለከተ ለባለጉዳዮች ፈጣን ምላሽ በትኩረት መሰጠት አለበት በማለት ገለፁ።
‎7.የትምህርት ስራዎች ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት አለበት ተብሏል?
‎በአጠቃላይ የቀረበው ሪፖርት ላይ የቀበሌ ምክርቤቶች ሰፊ ማብራሪያና ውይይት አደርገው በዕለቱ በተገኙ የምክር ቤት አባላት በማፅደቅ ጉባኤውን አጠናቀዋል።


‎ለመላዉ የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1501ኛው የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፋ።‎‎ነሀሴ 19/2018 ዓ.ም (ቻግኒ ከተማ ምክር ቤት)‎‎​የቻግኒ ከተ...
25/08/2026

‎ለመላዉ የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1501ኛው የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፋ።

‎ነሀሴ 19/2018 ዓ.ም (ቻግኒ ከተማ ምክር ቤት)

‎​የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ተዋበ ምህረት እንኳን ለ1501ኛው የነቢዩ ሙሐመድ የልደት በዓል (መውሊድ) በሰላም አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡

‎ አፈ ጉባኤው እንደገለፁት በዓሉ የሠላም፣ የጤና፣የፍቅር፣ የመተሳሰብና የመደጋገፍ በዓል እንዲሆንላችሁ እየተመኘሁ ፤በዓሉ በሚከበርበት ጊዜ ደጋፊና ረዳት የሌላቸዉን ወገኖቻችንን በማሰብና በማገዝ በአሉን ማክበር ይኖርብናል በማለት አሳስበዋል

‎​በመጨረሻ አፈ ጉባኤው በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የልማትና የብልጽግና እንዲሆን በመመኘት፤ ለእስላምና እምነት ተከታዮች በሙሉ "እንኳን ለ1501ኛው የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ" ሲሉ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

‎1501ኛው የመውሊድ በዓል የሰላም፣ የጤና፣ የደስታ እና የበረከት እንዲሆን እመኛለሁ ብለዋል!!!!!

‎የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ የተቋማት የ2018 በጀት የ4ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈፃፀም  ክትትልና ቁጥጥር ስራ ዛሬም እንደቀጠለ ነው///////////////////////////////...
21/08/2026

‎የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ የተቋማት የ2018 በጀት የ4ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈፃፀም ክትትልና ቁጥጥር ስራ ዛሬም እንደቀጠለ ነው///////////////////////////////////////

‎ነሀሴ 15/2018ዓ/ም የቻ/ከተማ ምክር ቤት ጽ/ቤት

‎የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት የኢኮኖሚ ልማት በጀት ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የቻግኒ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ጽ/ቤትን የ2018 በጀት የ4ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈፃፀም ክትትልና ቁጥጥር አደረገ።

‎ የቻግኒ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ጽ/ቤትም ቋሚ ኮሚቴ ባዘጋጀው ቼክሊስት መሠረት የ2018 በጀት የ4ኛ ሩብ አመት የእቅድ አፈፃፀማቸውን ሪፖርት በቻግኒ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ጽ/ቤት ኃላፊ በሆኑት በአቶ ደሳለኝ ጌታቸው በኩል እንዲቀርብ ተደርጓል።
‎ሰለሆነም በቀረበው ሪፖርት ላይ በቋሚ ኮሚቴዎች በኩል ማብራሪያ እንዲሁም ምላሽ የሚሹ ጥያቄዎች እንደሚከተሉት
‎~አሽከርካሪዎችን በትኩረት ክትትልና ቁጥጥር ከማድረግ ላይ ያለው ሁኔታ ምን ይመስላል?
‎~ የመናኻሪያ ገቢን አሟጦ ለመሰብሰብ ተቋሙ የቀየሰው ስልት ካለ ይገለጽ?
‎~ የውስጥ ገቢ ለማሳደግ ገቢ የሚሰበሰብባቸውን አርስቶችን ከማስፋት አኳያ ምን ታስቦል?
‎~ የከተማ ታክሲ የቁጥጥር ስርዓቱ ሞቅ ቀዝቀዝ የሚልበት ሁኔታ አለ ክትትላችሁ ምንድንነው የሚመስለው?
‎~ የፓርኪንግ አገልገሎት የወሰዱ ተሽከርካሪዎች ለከተማ አስተዳደሩ የአገልግሎት ክፍያ ይከፍላሉ ወይ? የሚሉና ሌሎች ጥያቄዎች ተነስተው ውይይት ከተደረገባቸው በኋላ በተነሱ ጥያቄዎችና ሀሳቦች ላይ በማኔጅመንቱና በጽ/ቤት ኃላፊ በኩል በቂ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጧባቸው የክትትልና ቁጥጥር ስራ በተሳካ መንገድ ተጠናቋል።

‎የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት የኢኮኖሚ ልማት በጀት ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የቻግኒ ከተማ  አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤትን ክትትልና ቁጥጥር ስራ  ዛሬም እንደቀጠለ ነው //////...
21/08/2026

‎የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት የኢኮኖሚ ልማት በጀት ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የቻግኒ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤትን ክትትልና ቁጥጥር ስራ ዛሬም እንደቀጠለ ነው ////////////////

‎ነሀሴ 15/2018ዓ/ም የቻ/ከተማ ምክር ቤት ጽ/ቤት

‎የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት የኢኮኖሚ ልማት በጀት ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የቻግኒ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤትን የ2018 በጀት የ4ኛ ሩብ አመት የእቅድ አፈፃፀም ክትትልና ቁጥጥር አደረገ።

‎የቻግኒ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት በተዘጋጀው ቼክሊስት መሠረት የ2018 በጀት የ4ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈፃፀማቸውን ሪፖርትም በቻግኒ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ በሆኑት በአቶ ፈንታሁን ደማም በኩል ቀርቧል።

‎ በቀረበው ሪፖርት ላይ በቋሚ ኮሚቴዎች በኩል ማብራሪያ እንዲሁም ምላሽ የሚሹ ጥያቄዎች እንደሚከተሉት አንስተዋል
‎1. የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት ተቋሙ ምን ስራ ሰርታችኋል?
‎2. ሁሉም የንግድ ድርጅቶች ወቅታዊ የመሸጫ ዋጋ ዝርዝር ስለመለጠፋቸው እና በለጠፉት ዋጋ ዝርዝር መሰረት እየሸጡ ስለመሆናቸው ተቋሙ የሚከታተለው ስልት ምንድን ነው ይብራራ?
‎3.ያለአግባብ ዋጋ በመጨመር ኑሮ ውድነትን የሚያባብሱ አካላት ላይ እየተወሰደ ያለ እርምጃ ካለ ቢገለፅ?
‎4. የንግድ ምዝገባ ፈቃድ እድሳት ፣ ፈቃድ ማውጣት በወቅቱ እንዲከናወን የተቋሙ ክትትል ምን ይመስላል ?
‎5. የሰንበት ገበያን ወደ ተግባር በማስገባት ለኑሮ ውድነት ማረጋጋት የራሱን ድርሻ እንዲወጣ ከማድረግ አኳያ ተቋሙ የሰራው ስራ ቢገለፅ?
‎6.የሚመጣውን ናፍጣና ቤንዚን በአግባቡ እንዲሰራጭ እንዲሁም ስራ ላይ እንዲውል ተቋም እያደረገ ያለው የክትትልና ቁጥጥር ስራ ይብራራ? የሚሉና ሌሎች ጥያቄዎች በቋሚ ኮሚቴዎች በኩል ተነስተው በቂ ውይይት ከተደረገ በኋላ በጽ/ቤት ኃላፊና በማኔጅመንቱ አባላት በኩል ምላሽና ማብራሪያ ተሰጧበቸው ክትትልና ቁጥጥር ስራ ተጠናቋል ።

‎የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ የተቋማት የ2018 በጀት የ4ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈፃፀም ክትትልና ቁጥጥር ስራ ዛሬም እንደቀጠለ ነው////////////////////////////////...
20/08/2026

‎የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ የተቋማት የ2018 በጀት የ4ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈፃፀም ክትትልና ቁጥጥር ስራ ዛሬም እንደቀጠለ ነው///////////////////////////////////////

‎ነሀሴ 14/2018 ዓ/ም የቻ/ከተማ ምክር ቤት ጽ/ቤት

‎የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት የኢኮኖሚ ልማት በጀት ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የቻግኒ ከተማ አስተዳደር ኢንዱሰትሪና ኢንቨስትመንት ጽ/ቤትን የ2018 በጀት የ4ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈፃፀም ክትትልና ቁጥጥር አደረገ ።

‎የቻግኒ ከተማ አስተዳደር ኢንዱሰትሪና ኢንቨስትመንት ጽ/ቤትም ቋሚ ኮሚቴ ባዘጋጀው ቼክሊስት መሠረት የ2018 በጀት የ4ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈፃፀማቸውን ሪፖርት በቻግኒ ከተማ አስተዳደር ኢንዱሰትሪና ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት ኃላፊ በሆኑት በአቶ አያና አድማስ በኩል እንዲቀርብ ተደርጓል።

‎ በቀረበው ሪፖርት ላይ በቋሚ ኮሚቴዎች በኩል ማብራሪያ እንዲሁም ምላሽ የሚሹ ጥያቄዎች እንደሚከተሉት አንስተዋል
‎1. የኢንዱስትሪ መንደር የመሰረተ ልማት ችግሮች እንዲፈቱ ከማድረግ ላይ የተሰራ ስራ ካለ ይገለጽ?
‎2. ከተማዋን የኢንቨስትመንት ፀጋዎች በመለየትና ለከተማው ማህበረሰብ ጠቃሚ የሆኑ የኢንቨስትመንት ዘርፎችን ላይቶ ከማስተዋወቅ አንፃር ተቋሙ የሰራው ስራ ካለ ይብራራ?
‎3.በከተማችን ፕሮጀክቶችን ለይቶ በመመልመል በኩል ያለው ሁኔታ ምን ይመስላል ?
‎4.ኢንቨስተሮችን ለመሳብ ያላችሁ ቅደመ ዝግጅት ምን ይመስላል?
‎5.ወደ ማምረት ለገቡት ኢንዱስትሪዎች የግብዓት ችግር ለመፍታት እየሄዳችሁበት እርቀት ካለ ቢገለፅ?
‎6.በስራ ላይ ያሉ አምራች ኢንዱስትሪዎችና ሌሎች ፕሮጀክቶች በገቡበት ውል መሰረት ለዜጎች የስራ ዕድል እየፈጠሩ ስለመሆናቸው ተቋሙ እንዴት ያረጋግጣል? የሚሉና ሌሎች ጥያቄዎች በቋሚ ኮሚቴዎች በኩል ተነስተው በቂ ውይይት ከተደረገ በኋላ በጽ/ቤት ኃላፊና በማኔጅመንቱ አባላት በኩል ምላሽና ማብራሪያ ተሰጧበቸው ክትትልና ቁጥጥር ስራ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።

‎የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ የተቋማት የ2018 በጀት የ4ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈፃፀም ክትትልና ቁጥጥር ስራ ዛሬም እንደቀጠለ ነው////////////////////////////////...
20/08/2026

‎የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ የተቋማት የ2018 በጀት የ4ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈፃፀም ክትትልና ቁጥጥር ስራ ዛሬም እንደቀጠለ ነው//////////////////////////////////////

‎ነሀሴ 14/2018ዓ/ም የቻ/ከተማ ምክር ቤት ጽ/ቤት

‎የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት ማህበራዊ ሴቶችና ህፃናት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የቻግኒ ከተማ አስተዳደር ባህል ቱሪዝም ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤትን የ2018 በጀት የ4ኛ ሩብ አመት የእቅድ አፈፃፀም ክትትልና ቁጥጥር አደረገ። የቻግኒ ከተማ አስተዳደር ባህል ቱሪዝም ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤትም ቋሚ ኮሚቴ ባዘጋጀው ቼክሊስት መሠረት የ2018 በጀት የ4ኛ ሩብ አመት የእቅድ አፈፃፀማቸውን ሪፖርት በቻግኒ ከተማ አስተዳደር ባህል ቱሪዝም ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ በሆኑት በአቶ ቁምላቸው አስፋው በኩል ቀርቧል።
‎ሰለሆነም በቀረበው ሪፖርት ላይ በቋሚ ኮሚቴዎች በኩል ማብራሪያ እንዲሁም ምላሽ የሚሹ ጥያቄዎች እንደሚከተሉት አንስተዋል
‎1.በስፖርት ኢንቨስትመንት ዘርፍ የባለሀብቶች ተሳትፎ ያለበት ሁኔታ ምን ደረጃ ላይ ነው?
‎2. ስፖርቱ ህዝባዊ መሰረት እንዲኖረው በየቀበሌው ከማህበረሰብ ጋር መድረክ ፈጥሮ ውይይት በማድረግ በኩል እየተሰራ ስራ ካሉ ?
‎ 3.የህዝብ ቤተ መጽሀፍት ያለበት ደረጃና በሁሉም ቀበሌዎች የንባብ ቤቶችን በማቋቋም በኩል ተቋሙ ያለበት ደረጃ የዋይፋይ አገልግሎቱ ያለበት ደረጃ?
‎4.የታዳጊ ህፃናት ፕሮጀከቶች ያለበት አሁናዊ ቁመና ምን ደረጃ ላይ ናቸው?
‎ 5.የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንደ ከተማ እንዴት ነው እየሰራችሁ ያላችሁት?
‎6.በሆቴል ቱሪዝም ዘርፍ ላይ አገልግሎት ሰጪ መስተንግዶ ቤቶች ድጋፍና ክትትላችሁ ምን ይመስላል፣ በዘርፉ ባለሀብቶች እንዲሰመሩ ከማድረግ አኳያ ምን ታስቦል?
‎7.በስፖርት ኢንቨስትመንት ዘርፍ የባለሀብቶች ተሳትፎ ያለበት ሁኔታ ምን ደረጃ ላይ ነው? የሚሉና ሌሎች ጥያቄዎች በቋሚ ኮሚቴዎች በኩል ተነስተው በጽ/ቤት ኃላፊና በማኔጅመንቱ አባለት ምላሽና ማብራሪያ ተሰጧበቸው ክትትልና ቁጥጥር ስራ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል ።።

‎የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት የኢኮኖሚ ልማት በጀት ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የቻግኒ ከተማ  አስተዳደር ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅትን ክትትልና ቁጥጥር ስራ ዛሬም እንደቀጠለ ነው//////...
20/08/2026

‎የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት የኢኮኖሚ ልማት በጀት ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የቻግኒ ከተማ አስተዳደር ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅትን ክትትልና ቁጥጥር ስራ ዛሬም እንደቀጠለ ነው///////////////

‎ነሀሴ 14/2018ዓ/ም የቻ/ከተማ ምክር ቤት ጽ/ቤት

‎የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት የኢኮኖሚ ልማት በጀት ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የቻግኒ ከተማ አስተዳደር ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ጽ/ቤትን የ2018 በጀት የ4ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈፃፀም ክትትልና ቁጥጥር እየደረገ ይገኛል።

‎ የቻግኒ ከተማ አስተዳደር ዉሃ ጽ/ቤትም ቋሚ ኮሚቴ ባዘጋጀው ቼክሊስት መሠረት የ2018 በጀት የ4ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈፃፀማቸውን ሪፖርት በቻግኒ ከተማ አስተዳደር ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ኃላፊ በሆኑት በአቶ ታደሰ አዱኛ በኩል እንዲቀርብ ተደርጓል።
‎ሰለሆነም በቀረበው ሪፖርት ላይ በቋሚ ኮሚቴዎች በኩል ማብራሪያ እንዲሁም ምላሽ የሚሹ ጥያቄዎች እንደሚከተሉት ተነስተዋል።
‎1.የውሃ እጥረትን በጊዜያዊነትና በቋሚነት ለመፍታት ተቋሙ የቀየሰው ስልት ምንድነው ?
‎2. ተቋሙ የንፁህ መጠጥ ውሃ እጥረትን ለመቅረፍ እየተወሰደ እርምጃ ካለ ይገለጽ?
‎3. አዳዲስ ሰፈሮች የንፁህ የውሃ መሰመሮችን ህብረተሰቡን በማሳተፍ በአዲስ እንዲተኩ በማድረግ በኩል የተሰራ ሰራ ይገለጽ?
‎4.የውሃ ብክነትን ለመቀነስና የተመረጠው ውሃ ለተጠቃሚዎች እንዲደርስ የተቋሙ አሰራር ስልት ምንድነው ?
‎5.የውሃ ንፅህና ቁጥጥር በማድረግ ከእነእጥረቱም ቢሆን ጥራቱ የተጠበቀ ውሃ ለተጠቃሚዎች እንዲደርስ የሚከናወን ተግባር ቢገለጽ?
‎6. የውሃ ፍጆታ ሒሳብ በወቅቱ የማይከፍሉ ደንበኞችን ቁጥር ለመቀነስ እንዲሁም ውዝፍ በአግባቡ እንዲሰበሰብ ተቋሙ የወሰደው እርምጃ ምን ይመስላል ?
‎7. የመስመር መቆራረጥ ችግርን እንዴት ነው እየፈታችሁ ነው ያላችሁ? የሚሉና ሌሎች ጥያቄዎች በቋሚ ኮሚቴዎች በኩል ተነስተው በቂ ውይይት ከተደረገ በኋላ በጽ/ቤት ኃላፊና በማኔጅመንቱ አባላት በኩል ምላሽና ማብራሪያ ተሰጧበቸው ክትትልና ቁጥጥር ስራ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል ። ።

‎የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት ማህበራዊ ሴቶችና ህፃናት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የቻግኒ ከተማ  አስተዳደር ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤትን ክትትልና ቁጥጥር ስራ ዛሬም እንደቀጠለ ነው/////...
20/08/2026

‎የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት ማህበራዊ ሴቶችና ህፃናት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የቻግኒ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤትን ክትትልና ቁጥጥር ስራ ዛሬም እንደቀጠለ ነው/////////////////////////

‎ነሀሴ 14/2018ዓ/ም የቻ/ከተማ ምክር ቤት ጽ/ቤት

‎የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት ማህበራዊ ሴቶችና ህፃናት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የቻግኒ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤትን የ2018 በጀት የ4ኛ ሩብ አመት የእቅድ አፈፃፀም ክትትልና ቁጥጥር እየደረገ ይገኛል ።
‎የቻግኒ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤትም ቋሚ ኮሚቴ ባዘጋጀው ቼክሊስት መሠረት የ2018 በጀት የ4ኛ ሩብ አመት የእቅድ አፈፃፀማቸውን ሪፖርት በቻግኒ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ በሆኑት በወ/ሮ ፈንታነሽ እንዳለው በኩል ቀርቧል።
‎ በቀረበው ሪፖርት ላይ በቋሚ ኮሚቴዎች በኩል ማብራሪያ እንዲሁም ምላሽ የሚያስፈልጉ ጥያቄዎች እንደሚከተሉት ተነስተዋል።
‎~ ለችግር ተጋላጭ የሆኑ ወጣቶች በግልና በመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የነጻ ትምህርት ዕድል እንዲያገኙ ከማድረግ ላይ ምን ይመስላል?
‎~ በሴቶች ጥቃትና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች የአቅም ግንባታ ስልጠና ከመስጠት ላይ ያለው ሁኔታ ምን ይመስላል?
‎~ ለሴት አደረጃጀት አመራሮች ክፍተት የለየ ስልጠና ከመስጠት ምን ይመስላል?
‎~ ከተማችን ላይ ለምኖ አዳሪ በዝተዋል ማስተካከል አይቻልም ወይ?
‎~ በስርዓተ ፆታ ዙሪያ የተዘባ አመለካከት ያለውን ማህበረሰብ አመለካከቱን በሚቀይር መንገድ በየደረጀው የተሰጡ ስልጠናዎች ካሉ ቢገለፅ?
‎~ ቀበሌ ላይ ያሉ የሴቶች መዋቅር ድጋፍና ክትትል ምን ይመስላል?
‎~ ለአካል ጉዳተኞች ለአረጋዊያን ለድሀድሀ ሴቶች ለተጋላጭ የማህበረሰብ ክፍሎች ድጋፍና ክትትል ከማድረግ ላይ ያለው ሁኔታ ምን ይመስላል? የሚሉና ሌሎች ጥያቄዎች ተነስተው በጽ/ቤት ኃላፊና በማኔጅመንቱ አባለት ምላሽና ማብራሪያ ተሰጧበቸው ክትትልና ቁጥጥር ስራ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል ።

‎የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ የተቋማት የ2018 በጀት የ4ኛ ሩብ አመት የእቅድ አፈፃፀም ክትትልና ቁጥጥር ስራ ዛሬም እንደቀጠለ ነው///////////////////////////////...
19/08/2026

‎የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ የተቋማት የ2018 በጀት የ4ኛ ሩብ አመት የእቅድ አፈፃፀም ክትትልና ቁጥጥር ስራ ዛሬም እንደቀጠለ ነው///////////////////////////////////////

‎ነሀሴ 13/2018ዓ/ም የቻ/ከተማ ምክር ቤት

‎ የኢኮኖሚ ልማት በጀት ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የቻግኒ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤትን የ2018 በጀት የ4ኛ ሩብ አመት የእቅድ አፈፃፀም ክትትልና ቁጥጥር አደረገ።

‎ የቻግኒ ከተማ ስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በተዘጋጀው ቼክሊስት መሠረት የ2018 በጀት የ4ኛ ሩብ አመት የእቅድ አፈፃፀማቸውን ሪፖርት በቻግኒ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ኃላፊ በሆኑት በወ/ሮ ደብሪቱ ደስየ በኩል እንዲቀርብ ተደርጓል።

‎ሰለሆነም በቀረበው ሪፖርት ላይ በቋሚ ኮሚቴዎች በኩል ማብራሪያ እንዲሁም ምላሽ የሚሹ ጥያቄዎች እንደሚከተሉት አንስተዋል
‎1. የበጀት አስተዳደሩን ዘመናዊ በማድረግ በጀቱ ለታለመለት ዓላማ እንዲውል ተቋማት የበጀት ዝውውር እንዳያበዙ ድጋፍ ከማድረግ አኳያ የተሰራ ስራ ይብራራ?
‎2. ተቋማትን የበጀት አጠቃቀማቸውን በተቀመጠለት የጊዜ ሰሌዳ በማሳወቅ የፋይናንስ ግልፀኝነትና ተጠያቂነት ለማህበረሰቡ በመፍጠር በኩል የተሰራ ስራ ይገለጽ ?
‎3.የግዥ ስርዓቱ ወቅታዊና ጥራት ያለው እንዲሆን እንዲሁም ሴ/ መ /ቤቶች በእቅድና በግዥ ፍላጎት ያሳወቁት ዕቃ እንዲገዛ ከማድረግ አንፃር ተቋሙ ምን ስልት የተሰራባቸው ካርኒዎች እና ሰነዶች በአግባቡ ስለመያዛቸው ይገለጽ?
‎4. ንብረት ከብክነትና ከጉዳት ለማዳን ታስቦ ተግባራዊ የተደረገው ቴክኖሎጂ ምን ደረጃ ላይነው የመጣ ለውጥ ካለ ይገለጽ?
‎5. የኦዲት አፈፃፀም ምን ደረጃ ላይነው የተሰጠ የሙያና ምክር አገልግሎት ለኦዲት ግኝት መቀነስ ያደረገው አስተዋፅኦ ምንድነው ?
‎6. ካፒታል በጀት በወቅቱ ስራ ላይ እንዲውል የተቋሙ ሚና ምንድን ነው ?የሚሉና ሌሎች ጥያቄዎች በቋሚ ኮሚቴዎች በኩል ተነስተው በቂ ውይይት ከተደረገ በኋላ በጽ/ቤት ኃላፊና በማኔጅመንቱ አባላት በኩል ምላሽና ማብራሪያ ተሰጧበቸው የክትትልና ቁጥጥር ስራ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።

Address

Chagni
Amhara Region

Telephone

+251582250761

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የቻግኒ ከተማ ምክር ቤት/ Chagni town council posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share