ጋሞ ዞን ቆጎታ ወረዳ ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት

ጋሞ ዞን ቆጎታ ወረዳ ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት Follow us on our official site

የ5 ሚሊየን ኢትዮጵያውያን ኮደሮች ኢንሸቲቭ" ተብሎ የተጀመረው ወጣቶች ላሳዩት ከፍተኛ ፍላጎትና ስኬት ምላሽ ለመስጠት እንዲሁም የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እቅዱን ለማፋጠን ግቡ ወደ 7 ሚሊየን...
16/08/2026

የ5 ሚሊየን ኢትዮጵያውያን ኮደሮች ኢንሸቲቭ" ተብሎ የተጀመረው ወጣቶች ላሳዩት ከፍተኛ ፍላጎትና ስኬት ምላሽ ለመስጠት እንዲሁም የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እቅዱን ለማፋጠን ግቡ ወደ 7 ሚሊየን አድጓል።

ኤዞ፦10/12/2018 ዓ.ም (የቆጎታ ወረዳ ኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ

ይህ የ7 ሚሊየን ኢትዮ ኮደርስ ኢንሸቲቭ በኢትዮጵያ መንግሥት እና በተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች መንግሥት መካከል በተደረገ ስትራቴጂካዊ ሁለተናዊ ትብብር የተጀመረ ነፃ የመስመር ላይ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ሥልጠና ፕሮግራም ነው።

መጀመሪያ ላይ "የ5 ሚሊየን ኢትዮጵያውያን ኮደሮች ኢንሸቲቭ" ተብሎ የተጀመረ ቢሆንም፣ የኢትዮጵያ ወጣቶች ላሳዩት ከፍተኛ ፍላጎትና ስኬት ምላሽ ለመስጠት እንዲሁም የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እቅዱን ለማፋጠን ግቡ ወደ 7 ሚሊየን አድጓል።

የሚሰጡ ነፃ የሥልጠና ዘርፎች በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚታወቀው Udacity ፕላትፎርም አማካኝነት የሚሰጡ ሲሆን አራት ዋና ዋና ዘርፎችን የኮዲንግ እና የፕሮግራሚንግ መሠረታዊ እውቀቶች ፣የመረጃ ትንተና ስታቲስቲክስ እና ዳታ ሳይንስ ፣ የሰው ሠራሽ አስተውሎት መሠረታዊ ፅንሰ ሐሳቦች እና የሞባይል መተግበሪያዎች ልማትን ያካተቱ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች አሏቸው።

ፍላጎቱ ያለው ማንኛውም ሰው በይፋዊው ድረ-ገጽ ethiocoders.et በመግባት በቀላሉ መመዝገብ እና ሥልጠናውን ወዲያውኑ መጀመር ይችላል።

ከታችኛው እስከ ከፍተኛ የት/ት ደረጃ እየተማሩ ያሉ ተማሪዎች የዲጂታል ፋይዳ መታወቂያ ባለቤት ሊሆኑ እንደሚገባ የቆጎታ ወረዳ ኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት አሳሰበ::ኤዞ፦01/12/2018 ዓ.ም...
07/08/2026

ከታችኛው እስከ ከፍተኛ የት/ት ደረጃ እየተማሩ ያሉ ተማሪዎች የዲጂታል ፋይዳ መታወቂያ ባለቤት ሊሆኑ እንደሚገባ የቆጎታ ወረዳ ኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት አሳሰበ::

ኤዞ፦01/12/2018 ዓ.ም (የቆጎታ ወረዳ ኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ

ከታችኛው እስከ ከፍተኛ የት/ት ደረጃ እየተማሩ ያሉ ተማሪዎች የዲጂታል ፋይዳ መታወቂያ ባለቤት ሊሆኑ እንደሚገባ የቆጎታ ወረዳ ኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ያሳሰበ ሲሆን በኢትዮጵያ ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም እና በትምህርት ሚኒስቴር በኩል አጽንኦት ተሰጥቶት እየተሰራበት ያለ አቅጣጫ ነው።

የጽ/ቤቱ ኃላፊ የሆኑት አቶ አማኑኤል አበበ እንደተናገሩት የዲጂታል ፋይዳ መታወቂያን ከአንደኛ ደረጃ እስከ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላሉ ተማሪዎች ተደራሽ ማድረግ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች አሉት ያሉ ሲሆን የትምህርት መረጃን ለማደራጀት የተማሪዎችን ውጤት፣ የትምህርት ቤት የተማሪዎች ቁጥር ፣ መጠነ መቋረጥ ፣ ዝውውር እና አጠቃላይ የትምህርት ታሪክ በአንድ ማዕከላዊ ሥርዓት አስተማማኝ በሆነ መንገድ ለመያዝ ይረዳል ብለዋል።

አያይዘው የብሔራዊና ክልላዊ የሚሰጡ ፈተናዎች ደህንነትን ለማስጠበቅ የ6ኛ፣ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ፈተናዎችን ያለምንም የማጭበርበር ስጋት ለማካሄድ እና ተፈታኞችን በትክክል ለመለየት የሚያስችል ሲሆን በወረዳችን ይህንን ተግባራዊ ለማድረግም ተማሪዎች ከታችኛው የት/ት ደረጃቸው ጀምሮ ፋይዳ ተጠቃሚ ሊሆኑ ይገባል ያሉ ሲሆን ለዚህም የተማሪ #ወላጆች ሚና ከፍተኛው ቦታ የሚይዝ ስለሆነ የተማሪ ወላጆች ልጆቻቸውን በአቅራቢያቸው ባሉ የፋይዳ መመዝገቢያ ጣቢያዎች በመውሰድ ማስመዝገብ እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

በቆጎታ ወረዳ ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ  ምዝገባ ፣ትግበራ  እና ስርጭት ተጠናክሮ ቀጥሏል። ኤዞ :- 30/11/2018 ዓ.ም (የቆጎታ ወረዳ ኢኖቬሽንበቆጎታ ወረዳ ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገ...
06/08/2026

በቆጎታ ወረዳ ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ፣ትግበራ እና ስርጭት ተጠናክሮ ቀጥሏል።

ኤዞ :- 30/11/2018 ዓ.ም (የቆጎታ ወረዳ ኢኖቬሽን

በቆጎታ ወረዳ ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ፣ትግበራ እና ስርጭት ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ይህ ብሔራዊ መታወቂያ የነዋሪዎችን ማንነት በዘመናዊ እና አስተማማኝ መንገድ ለማረጋገጥ የተዘረጋ ትልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክት ነው።

በዲጅታል ፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ ወቅት መረጃ አሰጣጥ ላይ ጥንቃቄ ማድረግ የሚገባ ሲሆን የሰጡት የስም፣ የትውልድ ቀን፣ አድራሻ ፣ ስልክ ቁጥር እና ሌሎች የሚጠየቁ መረጃዎች ትክክል መሆናቸውን የማረጋገጥ ስራ ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል፡፡

ዲጅታል ፋይዳ የተለያዩ የመንግስት አገልግሎቶች ላይ የትምህርት ተቋማት ተማሪ ምዝገባ ፣ እንደ ፓስፖርት፣ አርሶ አደር ማዳበሪያ ስርጭት ፣ ዘመናዊ የመሬት መረጃ አያያዝ ፣ መንጃ ፈቃድ ፣ የንግድ ፈቃድ እና ባንክ አገልግሎቶች የመሳሰሉትን ለማግኘት ፋይዳ መታወቂያን እንደ ቅድመ ሁኔታ ማስቀመጥ መጀመሩ ትልቅ አቅም የሚፈጥር ሲሆን ይህን ታሳቢ በማድረግ ቀሪ ማህበረሰብ አካላት የምዝገባ ሂደቱ ላይ ተሳታፊ በመሆን የመታወቂያው ባለቤት መሆን ይገባል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለኢትዮጵያ ወጣቶች ያቀረቡት ጥሪ**********************የኢትዮጵያ ወጣቶች በዚህ የክረምት ወቅት በነጻ በቀረበው የ5 ሚሊዮን ኮደርስ የስል...
05/08/2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለኢትዮጵያ ወጣቶች ያቀረቡት ጥሪ
**********************

የኢትዮጵያ ወጣቶች በዚህ የክረምት ወቅት በነጻ በቀረበው የ5 ሚሊዮን ኮደርስ የስልጠና መርኃ ግብር ላይ እንዲሳተፉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥሪ አቀረቡ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለኢትዮጵያ ወጣቶች ባስተላለፉት መልእክት፣ ይህ ክረምት በከንቱ እንዲያልፍ ሊፈቀድለት የማይገባ ትልቅ ዕድል ይዞ መጥቷል ብለዋል።

የ5 ሚሊዮን ኮደርስ ኮርሶች በነጻ የሚገኙ መሆናቸውን የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የሚሰጠው የምስክር ወረቀትም ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያለው መሆኑን ገልፀዋል።

5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ቀድመው ወስነዋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ አሁን ደግሞ ተራው የእናንተ ነው ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ወጣቶች በዚህ የስልጠና መርኃ ግብር ላይ ለመሳተፍ በ ethiocoders.et ላይ መመዝገብ እንደሚችሉም ተመላክቷል፡፡

25/07/2026

በአንድ ስልክ ቁጥር ከአንድ በላይ ሰው ተመዝግበው የፋይዳ ቁጥር ለማስላክ ተቸግረዋል?

ወደ *9779 # ሲደውሉ የአንደኛው ሰው የፋይዳ ቁጥር ብቻ እየመጣብዎት ከሆነ በቀላሉ:

1. ወደ ቴሌግራም ቦት ይግቡ።
2. ከሚመጡት አማራጮች ውስጥ "የፋይዳ ቁጥር ለማስላክ" የሚለውን ይምረጡ።
3. ባለ 29 አኃዝ የምዝገባ ቁጥርዎን (በአጭር የጽሁፍ መልዕክት (SMS) የደረሰዎትን ወይም በምዝገባ ወቅት የተሰጥዎትን ወረቀት ላይ ያለውን) በጥንቃቄ ያስገቡ።
በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ የፋይዳ ቁጥርዎ በስልክዎ ይደርስዎታል!

የዲጅታል ፋይታ መታወቂያ ምዝገባ ሂደት በቆጎታ ወረዳ:-
19/07/2026

የዲጅታል ፋይታ መታወቂያ ምዝገባ ሂደት በቆጎታ ወረዳ:-

11/07/2026

"ህጻናት ለምን ፋይዳ መታወቂያ ይመዘገባሉ?" የሚለው በተደጋጋሚ ለሚነሳ ጥያቄ የሚከተለውን ገለፃ ይመልከቱ፦

የድሮን ትርኢት - ከገበታ ለትውልድ - አርባምንጭ በአርባምንጭ ኮንፍረንስ ሪዞርት የተካሄደው የድሮን ትርኢት የገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገር እና ገበታ ለትውልድ ፕሮጀክቶችን በዘመናዊ የድሮን...
03/07/2026

የድሮን ትርኢት - ከገበታ ለትውልድ - አርባምንጭ

በአርባምንጭ ኮንፍረንስ ሪዞርት የተካሄደው የድሮን ትርኢት የገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገር እና ገበታ ለትውልድ ፕሮጀክቶችን በዘመናዊ የድሮን ቴክኖሎጂ በሰማይ ላይ በማሳየት የኢትዮጵያን የልማት ጉዞ እና የሀገር ግንባታ ራዕይ በልዩ መልኩ አስተዋውቋል።

በቆጎታ ወረዳ ፋይዳ ዲጅታል መታወቂያ ምዝገባ ሂደት ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ኤዞ፦25/10/2018 ዓ.ም (ቆጎታ ወረዳ ኢኖቬሽን ቴክኖሎጂበቆጎታ ወረዳ ፋይዳ ዲጅታል መታወቂያ ምዝገባ ሂደት ተጠናክ...
02/07/2026

በቆጎታ ወረዳ ፋይዳ ዲጅታል መታወቂያ ምዝገባ ሂደት ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

ኤዞ፦25/10/2018 ዓ.ም (ቆጎታ ወረዳ ኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ

በቆጎታ ወረዳ ፋይዳ ዲጅታል መታወቂያ ምዝገባ ሂደት ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የፋይዳ መታወቂያ ለተለያዩ የመንግሥትና የግል አገልግሎቶች በተለይም ለባንክ አካውንት መክፈትና ማንነትን ለማረጋገጫ በግዴታነት መተግበር በመጀመሩ የምዝገባው ሂደት በሰፊው እንዲካሄድ በር ከፍቶለታል።

ምዝገባው በቆጎታ ወረዳ ወጣቶች ስብዕና ግንባታ ማዕከል፣
በኢትዮ ቴሌኮም ኤዞ ቅርንጫፍ ማዕከል እና እትዮጵያ ንግድ ባንክ ኤዞ ቅርንጫፍን ማዕከል በማድረግ በ3 ማዕከላት እየተከናወነ ይገኛል፡፡

የፋይዳ መታወቂያ የዘመናዊነት መገለጫ ከመሆኑም በላይ በየቀኑ የምናከናውናቸውን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች የተደራጀ መረጃ በመንግሥት ለሕዝብ የሚያስፈልጉ እንደ ጤና፣ ትምህርት እና መሠረተ ልማት (ውሃ፣ መንገድ፣ መብራት) ያሉ የልማት ዕቅዶችን በትክክለኛ የሕዝብ ቁጥርና ፍላጎት ላይ ተመስርቶ ለማቀድ ይረዳዋል።

ፋይዳ ዲጅታል የመንግሥት ድጋፎችን ለትክክለኛ ተጠቃሚዎች ማድረስ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች ያሉት ሲሆን ለአርሶ አደር ይዞታ ማረጋገጫ ተጠቅሞ የተለያዩ ማግኘት የሚገቧቸውን ጥቅማ ጥቆሞችን ለማግኘት፣ እንደ ማዳበሪያ ግዢ፣ የሴፍቲኔት ፕሮግራሞች፣ እና ሌሎች የመንግሥት ድጋፎች በቀጥታ ለሚገባቸው ዜጎች ብቻ እንዲደርሱ ያደርጋል።

💻 በላፕቶፕ እና ስልክ ቻርጀር ገመዶች ላይ የሚገኘው ያበጠው ሲሊንደር ሚስጥር፤ ለጌጥ ወይስ ለደህንነት? 🔌በላፕቶፕ እና ስልክ ቻርጀር ገመዶች ላይ ወደ ጫፉ አካባቢ ያበጠ ክብ ሲሊንደር ነገ...
30/06/2026

💻 በላፕቶፕ እና ስልክ ቻርጀር ገመዶች ላይ የሚገኘው ያበጠው ሲሊንደር ሚስጥር፤ ለጌጥ ወይስ ለደህንነት? 🔌

በላፕቶፕ እና ስልክ ቻርጀር ገመዶች ላይ ወደ ጫፉ አካባቢ ያበጠ ክብ ሲሊንደር ነገር አስተውለው ያውቃሉ? ብዙዎቻችን ይህንን ሲሊንደር ስናይ ዝም ብሎ ገመዱ እንዳይቋጠር ማድረጊያ ወይም ለጌጥ የተደረገ ይመስለን ይሆናል።

ነገር ግን እውነታው ከዚያ የራቀ ሲሆን፣ ይህ ያበጠ ሲሊንደር የላፕቶፕዎን እና የስልክዎን ዕድሜ የሚቀጥል፣ ከከፍተኛ የኤሌክትሪክ መናጋት የሚጠብቅ እጅግ ወሳኝ የቴክኖሎጂ አካል ነው።

በሳይንሱ አጠራር ፌራይት ቢድ (Ferrite Bead ወይም Ferrite Core) በመባል የሚጠራው ይህ ሲሊንደር፣ ዝም ብሎ የተቀመጠ ሳይሆን የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በአግባቡ የሚያገለግል ስውር የደህንነት ዘበኛ ነው።

ማንኛውም የኤሌክትሮኒክስ ዕቃ ውስጥ የኤሌክትሪክ ኃይል በገመድ ውስጥ ሲያልፍ፣ ገመዱ ሳያውቀው እንደ አንቴና ያገለግላል። ይህም ማለት በአየር ላይ ያሉትን የራዲዮ ሞገዶች፣ የዋይፋይ እና የሌሎች ማሽኖች የኤሌክትሮማግኔቲክ ሞገዶችን ወደ ራሱ ይስባል።

ይህ አላስፈላጊ የሞገድ ረብሻ (Noise) ወደ ላፕቶፕዎ ወይም ስልክዎ በቀጥታ ከገባ፣ ስሱ የሆኑትን የውስጥ ክፍሎች ያናጋል፣ ስክሪኑ እንዲርገበገብ ያደርጋል፣ እንዲሁም የባትሪውን ዕድሜ ያሳጥራል።

በዚህ ሲሊንደር ውስጥ ያለው ቁስ ፌራይት የሚባል መግነጢሳዊ የብረት ኦክሳይድ ስብስብ ሲሆን፣ ገመዱ ከአየር ላይ የሳባቸውን አደገኛ እና አላስፈላጊ የኤሌክትሮማግኔቲክ ሞገዶች ወደ ማሽኑ ሳይገቡ በመያዝ ወደ ሙቀት ኃይል በመቀየር ያስወግዳቸዋል።

በዚህም ምክንያት የላፕቶፕዎ ሲስተም ያለምንም መቆራረጥ እና መዘጋት በጥራት እንዲሰራ ያደርጋል። ባጭሩ ያ ያበጠው ሲሊንደር ለጌጥ ሳይሆን ላፕቶፕዎ እና ስልክዎ በአደገኛ ሞገዶች ተመትተው እንዳይበላሹ የሚጠብቅ ድምፅ አልባ የሞገድ ማጣሪያ ነው።

እናንተስ ከዚህ በፊት በቻርጀራችሁ ላይ ይህንን አይታችሁ ምን መስሏችሁ ነበር? መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ሼር አድርጉት!

Address

ቆጎታ ኤዞ
Arba Minch'

Telephone

+251923827614

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ጋሞ ዞን ቆጎታ ወረዳ ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to ጋሞ ዞን ቆጎታ ወረዳ ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት:

Shortcuts

Share