Arbaminch Media House

Arbaminch Media House Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Arbaminch Media House, Landmark & historical place, Arba Minch'.

ከአንድ ታካሚ ሆድ በቀዶ ሕክምና 57 ብረታ ብረቶች ወጡአዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሣውላ አጠቃላይ ሆስፒታል ከሁለት ሰዓት በላይ በፈጀ ቀዶ ሕክምና ከአንድ ታካሚ ሆ...
04/01/2025

ከአንድ ታካሚ ሆድ በቀዶ ሕክምና 57 ብረታ ብረቶች ወጡ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሣውላ አጠቃላይ ሆስፒታል ከሁለት ሰዓት በላይ በፈጀ ቀዶ ሕክምና ከአንድ ታካሚ ሆድ 57 ብረታ ብረቶች ወጡ።
‎ ‎
‎በቀዶ ሕክምናው 28 ሚስማር፣ 8 ብሎን እና ሌሎች የተለያዩ ብረታ ብረቶች መውጣታቸው ነው የተገለጸው፡፡

የቀዶ ሕክምናው በስኬት መጠናቀቁን የሆስፒታሉ አጠቃላይ ቀዶ ሕክምና ሐኪም ዶክተር ጌታነህ በላይ ገልጸዋል።

‎የአንጀት ቀዶ ሕክምናው ከ2 ሰዓት በላይ የፈጀ እንደነበርም የሆስፒታሉ መረጃ ያመላክታል።

10/08/2024
አትሌት ለሜቻ ግርማ በመልካም የጤና ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተገለፀአዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ3 ሺህ መስናክል አትሌት ለሜቻ ግርማ ካጋጠመው ጉዳት አገግሞ በመልካም የጤና...
08/08/2024

አትሌት ለሜቻ ግርማ በመልካም የጤና ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ3 ሺህ መስናክል አትሌት ለሜቻ ግርማ ካጋጠመው ጉዳት አገግሞ በመልካም የጤና ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ፡፡

አትሌቱ ትናንት ምሽት በፈረንሳይ ፓሪስ ኦሊምፒክ በተካሄደው የወንዶች 3 ሺህ ሜትር መሰናክል ውድድር በመጨረሻ ዙር የመሰናከሉ ጠልፎት በመውደቁ ጉዳት ማስተናገዱ ይታወሳል፡፡

በዚህም ወደ ሆስፒታል ገብቶ በተደረገለት ምርመራ በእግሩና በጭንቅላቱ ላይ ጉዳት እንዳልደረሰበት የህክምና ባለሙያዎች አረጋግጠዋል።

የአትሌት ለሜቻ ግርማ አሰልጣኝ ተሾመ ከበደን ዋቢ አድርጎ ያሁ ኒውስ እንደዘገበው፤ አትሌቱ በዛሬው እለት ከሆስፒታል ወጥቶ ወደ ኦሊምፒክ መኖሪያ መንደሩ መመለሱ ተገልጿል፡፡

የ3 ሺህ መሰናክል ባለሪከርዱ ለሜቻ ግርማ በኦሊምፒኩ የወርቅ አሸናፊነት ግምት ተሰጥቶት የነበረ ቢሆንም አጨራረስ ላይ ያጋጠመውን ጉዳት ተከትሎ ሞሮኳዊው የመሰናክል ተፎካካሪው ሶፊያን ኤል ባካሊ አሸንፏል፡፡

አቶ ጥላሁን ከበደ መላው ኢትዮጵያውያን ላሳዩት አጋርነት ምስጋና አቀረቡ*************የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ መላው ኢትዮጵያውያን ላሳዩት አጋርነት ...
27/07/2024

አቶ ጥላሁን ከበደ መላው ኢትዮጵያውያን ላሳዩት አጋርነት ምስጋና አቀረቡ
*************

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ መላው ኢትዮጵያውያን ላሳዩት አጋርነት ምስጋና አቅርበዋል።

ርዕሰ መስተዳደሩ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ጎፋ ዞን፣ ገዜ ጎፋ ወረዳ፣ ኬንቾ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ዙሪያ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል።

ርዕሰ መስተዳደሩ በመግለጫቸው መላው ኢትዮጵያውያን ላሳዩት አጋርነት ምስጋና አቅርበው፤ ተፈናቃዮችን ለማቋቋም በሚደረገው ርብርብ ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ እስካሁን የ232 ሰዎች አስከሬን ተገኝቶ ሥርዓተ ቀብር የተፈፀመ ሲሆን፤ ህብረተሰቡ ባከናወነው የነፍስ አድን ስራ 10 ሰዎችን በሕይወት ማትረፍ መቻሉን ርዕሰ መስተዳደሩ ገልፀዋል።

አሁን ላይ 500 ያህል ሰዎች ከመኖሪያ ቀዬአያቸው የተፈናቀሉ ሲሆን፤ ከ6 ሺህ በላይ የሚሆኑት ደግሞ የአደጋ ስጋት ያለባቸው መሆኑን ጠቅሰዋል።

እነዚህን ዜጎች በዘላቂነት ለማቋቋም በጥናት ላይ የተመሰረተ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን አቶ ጥላሁን ተናግረዋል።

በክልሉ ያጋጠመውን አደጋ ተከትሎ በተደረገው ርብርብ ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የዓይነት እና 16 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ መደረጉ ተገልጿል።

በአስረሳው ወገሼ

በጎፋ ዞን ከደረሰው የመሬት መንሸራተት የተረፉት ኢንስፔክተር ምን ያስታውሳሉ? ***************************በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ቀበሌ ከተከሰተው መሬት መንሸራተት...
26/07/2024

በጎፋ ዞን ከደረሰው የመሬት መንሸራተት የተረፉት ኢንስፔክተር ምን ያስታውሳሉ?
***************************

በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ቀበሌ ከተከሰተው መሬት መንሸራተት በተዓምር ተርፈው ለዛሬው ምስክርነት የበቁት ኢንስፔክተር በዛብህ ቡናሮ አደጋው ሲከሰት መረጃው እንደደረሳቸው ባለድርሻ አካላትን ይዘው የነፍስ አድን ስራ ለመስራት ይወስናሉ፡፡

ከወረዳው ማዕከል 10 አባላትን ይዘው ወደ ስፍራው ያቀኑት የገዜ ጎፋ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር በዛብህ፤ የቀበሌው አስተዳዳሪ ከነሙሉ ቤተሰባቸው ናዳው ስለተጫናቸው እነሱን ለማዳን የአካባቢው ነዋሪዎች ሲረባረቡ እንደነበር ገልጸዋል፡፡

ታዲያ በዚህን ሰዓት ያልተጠበቀ የመሬት ናዳ ከኋላቸው በቅርብ ርቀት መፈጠሩን ተከትሎ ሌላ አደጋ መፈጠሩን እና ለነፍስ አድን የተሰበሰቡ ከ200 የሚልቁ የአካባቢው ነዋሪዎች በቅጽበት በናዳው ከመሬት ስር ሆኑ ይላሉ በተሰበረ ልብ፡፡

አብረዋቸው ከነበሩ ባልደረቦች መካከል ሁለቱ ወዲያውኑ የተከሰተው ናዳ ሲወርድ ይዟቸው እንደወረደ የሚናገሩት ኢንስፔክተር በዛብህ፤ ከቀሪ የስራ ባለደረቦቻቸው እና የወረዳው አስተዳደሪ ጋር በመሆን ከአደጋው ሮጠው “በተዓምር” ማምለጣቸውን ነው የገለፁት፡፡

ከዚህ በኋላ ለዞን፣ ለክልል አደጋ ስጋትና ስራ አመራር መዋቅሮች የድረሱልኝ ጥሪ ማሰማታቸውን በተለይም ለኢቢሲ ሳይበር ሚዲያ ተናግረዋል፡፡

አደጋውን ይበልጥ የከፋ ያደረገው የወረዳው አደጋ ስጋትና ስራ አመራር ባለሙያዎች ከመድረሳቸው በፊት ነዋሪዎች የነፍስ አድን ስራ ለመስራት የአደጋ ክልል ውስጥ በመግባታቸው እንደሆነም ገልጸዋል ኢንስፔክተር በዛብህ ቡናሮ።

አደጋው የከፋና ቅጽበታዊ በመሆኑ ከአካባቢው መራቅ እንዳለባቸው የማያውቁትን ይቅርና የሚያውቁት እራሱ ራሳቸውን ማዳን ያልቻሉበት ሁኔታ እንደነበር ተናግረዋል፡፡

የገዜ ጎፋ ወረዳ አካል የሆነውና የመሬት ናዳ አደጋ ስጋት አለበት የሚባለው አካባቢ ስፋት በግምት ወደ 150 ሄክታር ስፋት እንዳለው የሚናገሩት ኢንስፔክተሩ፤ የመሬት አቀማመጡ በተፈጥሮ ተራራማ፣ ገደላማና ወጣ ገባ የሚበዛበት መሆኑን ጠቁመዋል።

እንዲህም በመሆኑ አደጋው ሲከሰት ቶሎ ሰዎችን ለማዳን ርብርብ ከመደረጉ ውጭ ሊናድ ይችላል ተብሎ በአይን ሊታወቅ የሚችል ምንም ምልክት ለማየት የማይቻልበት እንደነበር ገልጸዋል።

አካባቢው ባቄላ፣ አተር፣ ስንዴና ገብስ እንዲሁም እንሰት በብዛት የሚመረትበት ለም መሬት ያለው በመሆኑም ነዋሪዎች ለቀው መውጣት አይፈልጉም የሚሉት ኢንስፔክተር በዛብህ፤ አደጋው ከደረሰ ጀምሮ እየተደረገ ያለው ርብርብ የአደጋው ሰለባዎች እስኪያገግሙ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል፡፡

በመሀመድ ፊጣሞ

ከነማ ዝግጁ???
17/07/2024

ከነማ ዝግጁ???

ማስታወቂያየአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያ እና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሕክምና አገልግሎት መጀመሪያ ቅድመ ዝግጅት ያጠናቀቀ ስለሆነ ከነገ ማክሰኞ ሐምሌ 9/2016 ዓ/ም ጀ...
15/07/2024

ማስታወቂያ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያ እና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሕክምና አገልግሎት መጀመሪያ ቅድመ ዝግጅት ያጠናቀቀ ስለሆነ ከነገ ማክሰኞ ሐምሌ 9/2016 ዓ/ም ጀምሮ በሕጻናት፣ በማኅፀንና ጽንስ፣ በአጠቃላይ ቀዶ ጥገና እና በውስጥ ደዌ ተመላላሽ ሕክምና እንዲሁም የተለያዩ የላቦራቶሪ እና ኢሜጂንግ አገልግሎቶች መስጠት የሚጀምር መሆኑን እያሳወቅን አገልግሎቱን በጉጉት ስትጠብቁ የነበራችሁ ሁሉ መጠቀም የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

አርባምንጭ ዩኒቨርስቲ
የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

ኩረጃ በኢትዮጵያ ያለበት ደረጃ ምን ይመስላል?*********በኢትዮጵያ ተማሪዎች በፈተና ወቅት የሚያደርጉት ኩረጃ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከተ እና ዘዴውም እየተራቀቀ መምጣቱን ብዙዎች ይናገራ...
15/07/2024

ኩረጃ በኢትዮጵያ ያለበት ደረጃ ምን ይመስላል?
*********

በኢትዮጵያ ተማሪዎች በፈተና ወቅት የሚያደርጉት ኩረጃ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከተ እና ዘዴውም እየተራቀቀ መምጣቱን ብዙዎች ይናገራሉ።

በኢትዮጵያ የኩረጃ ደረጃ ምን ያህል ነው? ሀገርንስ ምን ያህል ይጎዳል? በሚል በ2004 በተደረገ ጥናት መደረጉን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የአካቶ ትምህርት ክፍል ተመራማሪ የሆኑት አለማየሁ ተ/ማሪያም (ዶ/ር) ገልፀዋል፡፡

ተመራማሪው በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዳጉ ፕሮግራም በነበራቸው ቆይታ፤በተደረገው ጥናት 90 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች ኮራጅ መሆናቸው መረጋገጡን ነው የተናገሩት፡፡

በቀደመው የትምህርት ሥርዓት የመመዘኛ ፈተናዎች የሚሰጡበት ሂደት ለኩረጃ ምቹ እንደነበሩ ነው ያስታወሱት፡፡

ተማሪዎች በፈተና ወቅት የማያውቁትን ጥያቄ መልስ ከሌሎች ለመቅዳት ድሮም ይሞክሩ እንደነበር ገልጸው፤ አሁን ላይ ሥር ሰዶ በዘመቻ መልክ የሚካሄድ ሆኗል ሲሉ ነው የተናገሩት፡፡

ተማሪዎች ከትምህርቱ በበለጠ የኩረጃ መንገዶችን ያጠናሉ የሚሉት ተመራማሪው፤ በጥናቱ 27 የሚሆኑ የኩረጃ ዘዴዎች እንዳሉ ደርሰንበታል ብለዋል፡፡

በዚህ ሂደት ውስጥ ተማሪዎች ብቻ ሳይሆኑ ወላጆች ልጆቻቸው እንዲያልፉ ከመፈለግ አንፃር እንዲሁም መምህራን፣ ርዕሰ መምህራን፣ የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ጭምር ለኩረጃው እገዛ እንደሚያደርጉ ይናገራሉ፡፡

ይህም ፈተናውን አልፈው ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ተማሪዎች የሥብዕና ጉድለት እንደሚታይባቸው እዲሁም መሰረታዊ የሆነው መፃፍ እና ማንበብ ሲቸግራቸው እንመለከታለን ይላሉ፡፡

ተመራማሪው፤ ከፈተና አሰጣጥ በተጨማሪ ለግምት አጋላጭ የሆኑ የፈተና ዓይነቶችን ለማስተካከል መስራት እንደሚገባ አዲሱ የፈተና ሥርዓት ያመላከተ መሆኑንም ይናገራሉ፡፡

በተለይም የተጀመረው የበይነ በረብ (ኦን ላይን) ፈተና አሰጣጥ ሲጠናከር የተንሰራፋውን የኩረጃ መጠን በመቀነስ እና ተማሪዎችን በማብቃት ረገድ ላቅ ያለ ሚና ይኖረዋል ነው ያሉት፡፡

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ከ700 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች ከሐምሌ 3 ጀምሮ እስከ ሐምሌ 11 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥ ይታወቃል።

የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የግድያ ሙከራ ተደረገባቸው ********ትራምፕ በመጪው ህዳር ለሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በፔንሲልቬንያ የምረጡኝ ቅስቀሳ ሲያካሂዱ ነው የግድያ...
14/07/2024

የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የግድያ ሙከራ ተደረገባቸው
********

ትራምፕ በመጪው ህዳር ለሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በፔንሲልቬንያ የምረጡኝ ቅስቀሳ ሲያካሂዱ ነው የግድያ ሙከራ የተደረገባቸው።

በደጋፊዎቻቸው መሃል በመድረክ ላይ ቆመው የምረጡኝ ቅስቀሳ ሲያሰሙ የተተኮሰባቸው ዶናልድ ትራምፕ፤ በጆሯቸው አካባቢ ጉዳት እንደደረሰባቸው የተለቀቁ ምስሎች አሳይተዋል።

በወቅቱ በነበረው የተኩስ ልውውጥ የግድያ ሙከራውን ያደረገው ግለሰብ ህይወት ማለፉ ተነግሯል።

ሁለት ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት መድረሱን የአሜሪካው ኤንቢሲ ኒውስ ዘግቧል።

ዶናልድ ትራምፕ በመልካም ጤንነት ላይ ናቸው ተብሏል።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ክስተቱን ተከትሎ በሰጡት መግለጫ ጥቃቱን አውግዘዋል።

አሜሪካ ውስጥ በኃይል የሚደረግ እንቅስቃሴ ቦታ የለውም ሲሉም ተናግረዋል።

ሌሎች የሀገሪቱ ባለስልጣናትና የዓለም ሀገራት መሪዎችም ጥቃቱን እያወገዙ መሆኑ ተዘግቧል።

ምትሃተኛው ተወልዷል!' ላሚን ያማል ማን ነው?በእግር ኳስ ጨዋታ የሚቆጠር የትኛውም ጎሎ ይብዛም ይነስም ትርጉም አለው።ይሁን እንጂ ከጎልም ግን ጎል አለው። ልዩ የሆኑ ጎሎች አሉ። የጨዋታ እ...
14/07/2024

ምትሃተኛው ተወልዷል!' ላሚን ያማል ማን ነው?

በእግር ኳስ ጨዋታ የሚቆጠር የትኛውም ጎሎ ይብዛም ይነስም ትርጉም አለው።
ይሁን እንጂ ከጎልም ግን ጎል አለው። ልዩ የሆኑ ጎሎች አሉ። የጨዋታ እና የውድድሮችን ቅርጽ የሚቀይሩ ልዩ ጎሎች ሁሌም ይታወሳሉ። ተደጋግመው ይታያሉ።
የትናንት ምሽቷ የያሚል ጎል ለአስርት ዓመታት መነጋገሪያ ሆና ትቀጥላለች።
ላሚን ያማል አገሩ ስፔን በዩሮ 24 ፈረንሳይ ላይ የበላይነትን እንድትጎናጸፍ ያስቆጠራት አስደናቂ ጎል ለታሪክ የምትቀመጥ ናት ያለው በአሊያንዝ አሬና ጨዋታውን የተከታተለው ጌሪ ሮስ ነው።
ስፔን 1 ለ 0 እየተመራች ሳለ ላሚን በጥበበኛው ግራ እግሩ ከሳጥኑ ውጪ ጠቅልሎ ያስቆጠራት ጎል ድንቅ ከመሆኗ በተጨማሪ ለአገሩ አቻ ያደረገች እጅግ ወሳኝ ጎል ነበረች።
ይህ ጎል ሲያስቆጥር 16 ዓመት ከ 362 ቀናት ላይ እያለ በመሆኑ በአውሮፓ ዋንጫ ታሪክ በዕድሜ ትንሹ ጎል አስቆጣሪ ሆኖም በታሪክ ተመዝግቧል።
ያማል ይህችን ጎል ሲያስቆጥር የቀድሞ የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አጥቂ ጋሪ ሊኒከር “ምትሃተኛ ተወልዷል። . . . ይህ የውድድሩን አካሄደ የቀየር አጋጣሚ ነው” ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል።
“ጨርሶ ማመን የማይቻል። በዚህ ትንሽ ዕድሜው ይህን ማድረግ መቻል የማይታመን ነው” ያለው ደግሞ አለን ሽረር ነው።
ስፔናዊው ላሚን ያማል በአውሮፓ ዋንጫ ተሰልፎ የተጫወተ በዕድሜ ትንሹ ተጫዋች በመሆነ ሌላ ክብረ ወሰን ሰብሯል።
ላሚን ያማል በብሔራዊ ቡድን ብቻ ሳይሆን በክለብ ደረጃም በትንሽ ዕድሜው ብዙ ክብረ ወሰኖችን ይዟል።
ያማል ለክለቡ ባርሴሎና በትንሽ ዕድሜው ጎል ያስቆጠረ ተጫዋች ነው። ከዚህ በተጨማሪ በትንሽ ዕድሜው በቻምፒየንስ ሊግ ግጥሚያ ተሰልፎ የተጫዋተ፣ በላ ሊጋ እና ኮፓ ዴላሬ ጎል ያስቆጠረ ተጫዋች ነው።
ከትናንት ምሽቱ ጨዋታ በኋላ በእርሱ ዕድሜ ያሉ አብዛኛዎቹ ታዳጊዎች በሚተኙበት ሰዓት ያማል በሰጠው አስተያየት፤ “ከቡድኑ ጋር ለፍጻሜ መድረስ ሰመኘው የነበረው እውነት ሆኗል” ብሏል።
ላሚን ያማል ማን ነው?
ይህ የክንፍ ተጫዋች ሙሉ የመዝገብ ስሙ ላሚን ያማል ናስራዊ ኤባና ይባላል።
ከሞሮኳዊ አባቱ እና ከኢኳቶሪያል ጊኒ እናቱ በስፔን ተወልዷል። ቅዳሜ ሐምሌ 6/2016 ዓ.ም. 17 ዓመት የሚደፍነው ያማል፤ ከባርሴሎና የእግር ኳስ ክለብ ጋር የፕሮፌሽናል የእግር ኳስ ሕይወቱን የጀመረው ገና የአምስት ዓመት ታዳጊ ሳለ ነበር።
ያማል ተወልዶ ያደገው በባርሴሎናዋ የድሆች ሰፍር በሆነችው ሮካፎንዳ 304 በሚባል ሰፈር ነው።
ጎሎችን ካስቆጠረ በኋላም በጣቶቹ 304 በመስራት ደስታውን ይገልጻል።
ተጫዋቹ የቀኝ እጁን ሦስት ጣቶች በመዘርጋት 3፣ አውራ ጣቱን እና ጠቋሚ ጣቱን በማገጣጠም 0 እንዲሁም የእግራ እጁ አራት ጣቶች በመጠቀም 4 ቁጥርን ያመላክታል።
ያማል ገና ከአሁኑ ለበርካታ ለሮካፎንዳ ጨቅላዎች የስፋ ምልክት ሆኗል።
ያማል በእግር ኳስ ፍቅር የወደቀው ወላጅ አባቱ እና የቅርብ ዘመዶቹ በዛረ የድሆች ሰፈር በኮንክሪት ግንብ ውስጥ ኳስ ሲጫወቱ ከተመለከተ በኋላ ነው።
“ከቤት ይለቅ አብዛኛውን ጊዜያን የማሳልፈው ኳስ በመጫወት ነው። ከቤት ውጪ ነኝ ማለት ሁሌም ኳስ እየተጫወትኩ ነው ማለት ነው። የኳስ ፍቅር ሁሌም አብሮ የሚኖር ነገር” በማለት ያማል ይናገራል።

ተዓምረኛዋ ላም «ምንተዓምር» በጋሞ ዞን ጨንቻየዓለማችን ድንቆች በመመዝገብ የሚታወቀው ጊነስ ቡክ በዓለም ላይ በቀን 37 ሊትር ወተት በመስጠት ድንቅ ላም ብሎ የመዘገባት ሰምሩፍ የተባለችውን...
13/07/2024

ተዓምረኛዋ ላም «ምንተዓምር» በጋሞ ዞን ጨንቻ

የዓለማችን ድንቆች በመመዝገብ የሚታወቀው ጊነስ ቡክ በዓለም ላይ በቀን 37 ሊትር ወተት በመስጠት ድንቅ ላም ብሎ የመዘገባት ሰምሩፍ የተባለችውን ወደ ሆላንድ የተገኘችውን ላም ነው፡፡

ይህች ላም በቀን 37 ሊትር ወይም 83 ፓውንድ ወተት ለጌቶቿ ታበረክታለች፡፡ በዚህም የህይወት ዘመን ትልቁ የወተት ምርት በሚል እውቅናን ችሯታል፡፡

ከሰሞኑ በሀገራችን ከወደ ጋሞ ዞን የተመለከትናት ላም ግን ይህንን ዜና ፉርሽ ያደረገች ሆና አገኝተናታል፡፡ በጬንቻ ከተማ የሚኖሩት ወይዘሮ ትዝብት ተስፋዬ ምን ተዓምር ሲሉ ስያሜ የሰጧት ላማቸው በቀን ከ40 ሊትር በላይ ወተት እንደምትሰጣቸው ይናገራሉ፡፡

ወይዘሮ ትዝብት የምንተዓምር፤ ተዓምራት በዚህ የሚያበቃ አይደለም ይላሉ፡፡ ለተዓምር የፈጠራት ናትና ገና ሳትወልድ በየቀኑ አራት ሊትር ወተት ብትሰጣቸው፤ ተደናግጠው ወደ ጤና ጣቢያ ማምራታቸውን ከሳቅ ጋር ታጅበው ያስታወሳሉ፡፡

የአስር ዓመቷ ምንተዓምር ከሌሎች ላሞች ለየት ያለ ጠባይና አፈጣጠር አላት፡፡ ምንተዓምር ቶሎ አትሰንፅም፤ የወለደች እንደሆነም ወተቷ ከሌሎች ላሞች በተለየ ረዥም ጊዜ ይቆያል፡፡ በቀን 40 ሊትር ወተት የምትታለበው ምንተዓምር!

ወይዘሮዋ ሁኔታውን ሲያስታውሱ ከመውለዷ በፊት ያለውን ወተት ለመጠቀም እንደሚቸግራቸውና ወደ ጉድጓድ ይጨምሩት እንደነበረ ይናገራሉ፡፡ ይህንንም ሲያስረዱ በሀገራችን ባህል ላም ጥጃ ከሌላት ወተት አትሰጥም እና ጥጃ የሌላትን ላም ወተት መጠጣት እንደቸገራቸው ተናግረዋል፡፡

ወይዘሮ ትዝብት ላማቸውን ለምን ምንተዓምር እንዳሏት ሲናገሩ በየትም ሀገር ላም ከመውለዷ በፊት ወተት እንደምትሰጥ ባለመስማታቸውና ባለማየታቸው የተነሳ ምን አይነት ተዓምር ነው በማለት «ምንተዓምር» ብለው ስም እንዳወጡላት ይናገራሉ፡፡
ዋልታ

Address

Arba Minch'
ROBEL

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Arbaminch Media House posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share