14/08/2026
አስደሳች ዜና ለዓይን ህሙማን በሙሉ!
በዓይነቱ ልዩ የሆነ የዓይን ምርመራ እና የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ሕክምና ከነሐሴ 18/2018 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 25/2018 ዓ.ም ከሂሊያን ካትራክት ፕሮጀክት ጋር ከአሜሪካን ሀገር በሚመጡ ከፍተኛ ልምድ ባላቸው የዓይን ስፔሻሊስት ሐኪሞች በአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል በነፃ ይሰጣል ።
ከጋሞ ዞን ፣ አጎራባች ዞኖችና ክልሎች ለሚመጡ ሕሙማን ሕክምናው በነጻ ይሰጣል። ስለሆነም መላው ማህበረሰብ የሕክምናው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ ተላልፏል።