Arbaminch zuriya wereda revenue autority

Arbaminch zuriya wereda revenue autority Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Arbaminch zuriya wereda revenue autority, Government Organization, Arba Minch'.

በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ የ2018 ዓ.ም የደረጃ "ለ" ግብር አሰባሰብ እና የ2019 ዓ.ም የንግድ ፈቃድ እድሳት በ 6ቱም ክላስተር በይፋ ተጀምሯል።
08/07/2026

በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ የ2018 ዓ.ም የደረጃ "ለ" ግብር አሰባሰብ እና የ2019 ዓ.ም የንግድ ፈቃድ እድሳት በ 6ቱም ክላስተር በይፋ ተጀምሯል።

በአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ የ2018 ዓ.ም ደረጃ «ለ» ግብር አሰባሰብ እና የ2019 ዓ.ም ንግድ ፈቃድ እድሳት ተካሄደ ።​በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ የ2018 ዓ.ም ደረጃ «ለ» ግ...
07/07/2026

በአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ የ2018 ዓ.ም ደረጃ «ለ» ግብር አሰባሰብ እና የ2019 ዓ.ም ንግድ ፈቃድ እድሳት ተካሄደ ።

​በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ የ2018 ዓ.ም ደረጃ «ለ» ግብር አሰባሰብ እና የ2019 ዓ.ም ንግድ ፈቃድ እድሳት የንቅናቄ መድረክ ተካሂዷል።

​በዚህ የንቅናቄ መድረክ የ2018 ዓ.ም የገቢ አሰባሰብ አፈጻጸም እንደሚገመገም፣ በግብር አሰባሰብ ዕቅድ ላይ ውይይት ተደርጎ ቀጣይ አቅጣጫ እንደሚቀመጥ ተገልጿል።

​በመድረኩ መክፈቻ ላይ የተገኙት የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ታደሠ ገቢን በአግባቡ በመሰብሰብ ለሕዝብ የሚያስፈልጉ መሠረታዊ ፍላጎቶችን ማሟላት እንደሚገባ ገልጸዋል።

አክለውም ገቢን በአግባቡ አሟጦ በመሰብሰብና ለታለመለት ዓላማ በማዋል የሕዝብ ተጠቃሚነትን ማሳደግ እንደሚገባ አሳስበዋል።

​የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ገነቱ ቡናቤ በበኩላቸው በበጀት ዓመቱ በተከናወነ ጠንካራ ሥራ ከዕቅድ በላይ ከ61 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰብ መቻሉን ተናግረዋል።

​የመድረኩ ዓላማ የ2018 ዓ.ም ንግድ ፈቃድ እድሳት ገቢ አሰባሰብ አፈጻጸምን ከባለድርሻ አካላት ጋር በመገምገም በ2019 ዓ.ም ንግድ ፈቃድ እድሳት ዕቅድ ላይ የጋራ መግባባት ላይ ለመድረስ መሆኑም ተጠቁሟል።

​በዚሁ የንቅናቄ መድረክ ላይ የወረዳው መንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ተመስገን ተሾመ፣ የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ቱላ ቱኮ፣ የወረዳው አጠቃላይ አመራሮች፣ የገቢ ባለድርሻ ተቋማት ባለሙያዎችና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ተሳትፈዋል።

‎በሂሳብ መዝገብ አያያዝ ፣ በመረጃ አደረጃጀትና በአመታዊ ሂሳብ ሪፖርት አቀራረብ ላይ በግብር ከፋዩ ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ማረም የሚያስችል ስልጠና በዞኑ በሁሉም ወረዳና ከተማ አስተዳደ...
27/05/2026

‎በሂሳብ መዝገብ አያያዝ ፣ በመረጃ አደረጃጀትና በአመታዊ ሂሳብ ሪፖርት አቀራረብ ላይ በግብር ከፋዩ ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ማረም የሚያስችል ስልጠና በዞኑ በሁሉም ወረዳና ከተማ አስተዳደሮች እንደሚሰጥ የጋሞ ዞን ገቢዎች መምሪያ ገለጸ።

ግንቦት 18/2018 ዓ,ም

መምሪያው ከአርባምንጭ ዙርያ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት ጋር በጋራ በመሆን ለደረጃ "ሀ" ግብር ከፋዮች የሂሳብ መዝገብ አያያዝ ፣ አስተዳደራዊና የወንጀል ቅጣቶች ላይ ያተኮረ የክህሎት ስልጠና መስጠቱንም ገልጿል።

ከአርባ ምንጭ ዙርያ ወረዳ የደረጃ "ሀ" ግብር ከፋዮች መካከል በሆቴል ዘርፍ የተሰማሩት አቶ ዝናቡ ከበደና በአታክልትና ፍራፍሬ ንግድ የተሰማሩት ወ/ሮ አዳነች ኤልያስ በጋራ እንዳሉት የክህሎት ስልጠናው መዘጋጀት ከዚህ ቀደም ባለቸው እውቀት ላይ ተጨማሪ እውቀት የሚጨምርላቸው ከመሆኑም ባሻገር ካላስፈላጊ ቅጣት የሚታደጋቸው እንደሆነ ገልጸዋል።

ሌለኞቹ በአታክልትና ፍራፍሬ የተሰማሩት የደረጃ ሀ ግብር ከፋዮች አቶ ነጻነት ቀቼ እና ጭንባቼ ጽጌ እንዳሉት ለግብር ከፋዩ የሂሳብ መዝገብ አያያዝና ከቅጣቶች ጋር በተያያዘ ስልጠና ማግኘታቸው ለስራቸው እንደሚያግዛቸውና ባለማወቅ ከሚመጣ መቀጮ የሚታደጋቸው እንደሆነ ተናግረዋል።

ስልጠናውን ከሰጡት መካከል በጋሞ ዞን ገቢዎች መምሪያ የታክስ ትምህርትና ድጋፍ ባለሙያ አቶ የማነ ተክሉና በመምሪያው የታክስ ትምህርትና ድጋፍ ባለሙያ አቶ ብርሀኑ ተስፋዬ በጋራ እንዳሉት ስልጠናው ግብር ከፋዩ በግብር ህጉ መሠረት የራሱን የንግድ ስራ በአግባቡ ለመምራት ለመስራትና ለመቆጣጠር ከማስቻሉም ባሻገር ፍትሀዊ የሆነውን ግብር በአግባቡ ለመክፈል ያስችላል ብለዋል።

ለግብር ከፋዩ በየወቅቱ መሠል ስልጠናዎች ሊሰጡ እንደሚገባ ገልጸው በተለይ በሂሳብ መዝገብ አያያዝ ፣ በመረጃ አደረጃጀትና በአመታዊ ሂሳብ ሪፖርት አቀራረብ ላይ ግብር ከፋዩ ላይ ክፍተቶች እንደሚስተዋሉና ስልጠናው ይህን የሚቀርፍ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በስልጠናው ማጠቃለያ ለሰልጣኝ የደረጃ ሀ ግብር ከፋዮች የሙከራ ፈተና የተሰጠ ሲሆን ይህም መደረጉ ከስልጠናው ምን ያህል ግንዛቤ እንደጨበጡ ለማወቅና ክፍተቶቻቸውን በመለየት ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችል ነው ብለዋል።

የጋሞ ዞን ገቢዎች መምሪያ የታክስ ስርአት ዳይሮክተሬት የታክስ ስጋት ስራ አመራርና የትምህርትና ድጋፍ ቡድን መሪ አቶ ሄኖክ ናፋቆ እንዳሉት ስልጠናው ግብር ከፋዩ መሰረታዊ የሂሳብ መዝገብ አያያዝ መርህን ይዞ መስራቱ ከራስ ጥቅም ባሻገር ለመንግስት የሚገባው ገቢ በተገቢው እንዲሰበሰብ የሚይስችል ነው ብለዋል።

እንደዚሁም የታክስ ህጉን በመጣስ ከሚከሰቱ አላስፈላጊ ቅጣቶች ግብር ከፋዩ እንዲጠበቅ የሚያስችል በመሆኑ ግብር ከፋዮች የታክስ ህጉን በመጣስ የሚከሰቱ ክፍተቶችን አውቀው ቅድሚያ ተጠንቅቀው እንዲሰሩ የሚያስችል ነው ብለዋል።

የአርባምንጭ ዙርያ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት ሀላፊ ተወካይ አቶ ፍሬው ዘለቀ በበኩላቸው የስልጠናው መዘጋጀት ግብር ከፋዮች ላይ በተደረገው ዳሰሳ ጥናት ክፍተት ያለባቸውን ቦታዎች በመለየት ስልጠናው መዘጋጀቱን ገልጸዋል።

በዙርያ ወረዳው 167 የደረጃ ሀ እና 1453 የደረጃ ለ ግብር ከፋዮች ግብር ከፋዮች መኖራቸውን የሚጠቅሱት አቶ ፍሬው ግብር ከፋዩ ሁሉንም ተግባር ለሂሳብ ሰራተኛ መጣሉና የሚፈጠሩ ቅጣቶች ጋር ተያይዞ ለቅጣት ሲዳረግ ከመረዳት ይልቅ ቀድሞ ግንዛቤ እንዲኖረው በማሰብ መዘጋጀቱን ጠቅሰዋል።

Address

Arba Minch'

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Arbaminch zuriya wereda revenue autority posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share