Zada Construction and Industrial College

Zada Construction and Industrial College Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Zada Construction and Industrial College, Government Organization, Zada; Gamo, Arba Minch'.

የ2017 የቴክኒክና ሙያ ስልጠና የመግቢያ መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆኗል***- ከ 526ሺ  በላይ ተማሪዎች የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ይቀላቀላሉ ተብሎ ይጠበቃል የስራና ክህሎት ሚኒስቴር የ2017 የ...
21/10/2024

የ2017 የቴክኒክና ሙያ ስልጠና የመግቢያ መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆኗል
***

- ከ 526ሺ በላይ ተማሪዎች የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ይቀላቀላሉ ተብሎ ይጠበቃል

የስራና ክህሎት ሚኒስቴር የ2017 የቴክኒክና ሙያ ስልጠና የመግቢያ መቁረጫ ነጥብን አሳዉቋል።

በስራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ተሻለ በሬቻ(ዶ/ር) እንደገለጹት ፤
በደረጃ አንድና ሁለት የሚመዘገቡ ሰልጣኞች
በአስራ ሁለተኛ ብሄራዊ ፈተና ወንዶች 141 እና ከዚያ በታች፣ ሴቶች 138ና ከዚያ በታች ያመጡ ናቸው።

ለታዳጊ ክልሎችና አርብቶ አደር አካባቢዎች ለወንዶች 137ና ከዚያ በታች፣ ለሴቶች 134ና ከዚያ በታች፣ ለሁሉም ክልል አካል ጉዳተኞች 124ና ከዚያ በታች መሆኑንም ገልጸዋል።

በደረጃ ሶስትና አራት የሚመዘገቡ በ12ኛ መልቀቂያ ፈተና ወንዶች 142ና ከዚያ በላይ፣ ሴቶች 139ና ከዚያ በላይ ያመጡ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

ለታዳጊ ክልሎችና ከአርብቶ አደር አካባቢዎች ለወንዶች 138 እናና ከዚያ በላይ፣ ለሴቶች 135ና ከዚያ በላይ፣ ለሁሉም ክልል አካል ጉዳተኞች 125ና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ ናቸዉም ብለዋል።

በደረጃ አምስት የሚሰለጥኑ ወንዶች 179ና ከዚያ በላይ፣ሴቶች 170ና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ ተማሪዎች ይሠለጥናሉ ተብሏል።

ከታዳጊ ክልሎችና ከአርብቶ አደር አካባቢዎች ወንዶች 167ና ከዚያ በላይ፣ ሴቶች 162ና ከዚያ በላይ እንዲሁም ከሁሉም ከልል አካል ጉዳተኞች 154ና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡት በደረጃ አምስት ገበተው መሠልጠን እንደሚችሉ ሚኒስትር ዴኤታዉ አብራርተዋል።

(ኢ ፕ ድ)

Shagida!   shagida!  2017 M.L Zada keeththanne industire hiila loohisiza eqota goochcha!!UFAYSA ODA!Zada keethaninne ind...
21/10/2024

Shagida! shagida! 2017 M.L Zada keeththanne industire hiila loohisiza eqota goochcha!!

UFAYSA ODA!
Zada keethaninne industire macara loohisiza Eqqotay 2017M.L 3tho yuushsho loohanchchata ekkanas othiza koyro ooso wursidi haydi loohanas masgabetite gishe dhoqa UFAYSA athees.
Gujowara zada hiila loohiso Eqqotay loohisiza otho maacarati:-
-may'o medhonne siko hiilata(garment and fashion design)
-keeththanne keexo hiila maacaran(structural construction)
-biiratanne biirata hiilatan(mechanics)
-hard ware nne networking hiilatan(hard ware and networking service) 1-2 detha
-macatanne addete huphphenne bolla yegeltho/lo'ththo hiilan(beauty salon) 1-2 detha

Haray qase ba oththo medhdhanas koyzaytas ooso demisanas qanththa wode bollan qonc'c'ida hiilatan gallasanne omarsan loohisanas gigetidaysa gujora erises!
2017 M.L lohisanas gigetidaysa keehipe ufaysan qonc'c'isees imetida Soho guutha gidida gishas
Lohanchchati sinthatidi masgabetanas koshshees
Eqqotay betiza Sohoy zada kataman diita worada huphe ayso keeththappe diita efiza kame ogappe ushshacha bagan beetees.
DUUMMA QOFISO
Wolqqay baydaytanne duumma duumma meton qohetidayta MELA loohisizays nu eqota haratappe duummases!!

"Bananne ba ooson ammanetiza issippe medhdhoos!!"

UFAYSA ODA!Zada keethaninne industire macara loohisiza Eqqotay 2017M.L 3tho yuushsho loohanchchata ekkanas othiza koyro ...
20/10/2024

UFAYSA ODA!
Zada keethaninne industire macara loohisiza Eqqotay 2017M.L 3tho yuushsho loohanchchata ekkanas othiza koyro ooso wursidi haydi loohanas masgabetite gishe dhoqa UFAYSA athees.
Gujowara zada hiila loohiso Eqqotay loohisiza otho maacarati:-
-may'o medhonne siko hiilata(garment and fashion design)
-keeththanne keexo hiila maacaran(structural construction)
-biiratanne biirata hiilatan(mechanics)
-hard ware nne networking hiilatan(hard ware and networking service) 1-2 detha
-macatanne addete huphphenne bolla yegeltho/lo'ththo hiilan(beauty salon) 1-2 detha

Haray qase ba oththo medhdhanas koyzaytas ooso demisanas qanththa wode bollan qonc'c'ida hiilatan gallasanne omarsan loohisanas gigetidaysa gujora erises!
2017 M.L lohisanas gigetidaysa keehipe ufaysan qonc'c'isees imetida Soho guutha gidida gishas
Lohanchchati sinthatidi masgabetanas koshshees
Eqqotay betiza Sohoy zada kataman diita worada huphe ayso keeththappe diita efiza kame ogappe ushshacha bagan beetees.
DUUMMA QOFISO
Wolqqay baydaytanne duumma duumma meton qohetidayta MELA loohisizays nu eqota haratappe duummases!!

"Bananne ba ooson ammanetiza issippe medhdhoos!!"

👉👉👉 የ2016 ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት መግቢያ የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ************ 👉👉👉  ከደረጃ 1-8 በአዲስ መልክ ተጀምሯል የ2016 ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት መግቢያ...
16/11/2023

👉👉👉 የ2016 ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት መግቢያ የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ
************
👉👉👉 ከደረጃ 1-8 በአዲስ መልክ ተጀምሯል

የ2016 ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት መግቢያ የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደርጓል።

ደረጃ አምስት ተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ 218 እና ከዚያ በላይ ሴቶች 199 እና ከዚያ በላይ።

ታዳጊ ክልሎችና ወንድ 192 እና ከዚያ በላይ ሴት 187 እና ከዚያ በላይ።

ደረጃ ሶስትና አራት ተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ 173 እና ከዚያ በላይ ሴት 163 እና ከዚያ በላይ።

ታዳጊ ክልሎች ወንድ 157 እና ከዚያ በላይ ሴት 156 እና ከዚያ በላይ።

ተፈጥሮ ሳይንስ ደረጃ እንድና ሁለት ወንድ 172 እና ከዚያ በላይ ሴት 162 እና ከዚያ በላይ።

ታዳጊ ክልል ወንድ 156 እና በላይ ሴት 155 እና ከዚያ በላይ።

ማህበራዊ ሳይንስ ደረጃ አምስት ወንድ 179 እና ከዚያ በላይ ሴት 170 እና ከዚያ በላይ።

ታዳጊ ክልል ወንድ 166 እና ከዚያ በላይ ሴት 162 እና ከዚያ በላይ።

ደረጃ ሶስትና አራት ማህበራዊ ሳይንስ ወንድ 149 እና ከዚያ በላይ ሴት 147 እና ከዚያ በላይ ።

ታዳጊ ክልል ወንድ 138 እና ከዚያ በላይ ሴት 137እና ከዚያ በላይ።

ደረጃ አንድና ሁለት ማህበራዊ ሳይንስ ወንድ 148 ከዚያ በላይ ሴት 146ና ከዚያ በላይ።

ታዳጊ ክልል ወንድ 137 እና ከዚያ በላይ ሴት 136 ከዚያ በላይ ያመጡ ተማሪዎች ቴክኒክና ሞያ ስልጠና መመዝገብ እንደሚችሉ ስራና ክህሎት ሚኒስቴር ገልጿል ።

ዘንድሮ ከ632 ሺህ በላይ ተማሪዎች የቴክኒክና ሞያ ስልጠና ይወስዳሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፤ የተሻለ ዕድል ለመስጠት መታሠቡን የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈርያት ካሚል ተናግረዋል።

1400 በሚሆኑ የቴክኒክና ሞያ ስልጠና ተቋማት ከ 28 ሺህ በላይ አሠልጣኞች መዘጋጀታቸውን የገለፁት የስራና ክህሎት ሚኒስትሯ፤ እስከ ደረጃ አምስት የነበረው ስልጠና ወደ ደረጃ ስምንት ማደጉን ገልፀዋል።

በኮሌጆች የሚሰሩ የቴክኖሎጂ ፈጠራ  ውጤቶች የህብረተሰቡን ችግር በተጨባጭ የሚቀርፉ ሊሆኑ ይገባል ተባለ። አርባምንጭ ፣ ጥቅምት 27/2016 ዓ.ም(ጋሞ ዞን መ/ኮሚዩኒኬሽን)፦ በ2015 የስራ...
07/11/2023

በኮሌጆች የሚሰሩ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ውጤቶች የህብረተሰቡን ችግር በተጨባጭ የሚቀርፉ ሊሆኑ ይገባል ተባለ።

አርባምንጭ ፣ ጥቅምት 27/2016 ዓ.ም(ጋሞ ዞን መ/ኮሚዩኒኬሽን)፦ በ2015 የስራ ዘመን በዞኑ የሚገኙ ኮሌጆች ከ20 በላይ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ለኢንተርፕራይዞች ማሸጋገራቸውም ተገልጿል

በጋሞ ዞን ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና መምሪያ የልማት ዕቅድ ቡድን መሪ አቶ ሚሊዮን ደሳለኝ የተቋሙን አፈፃፀም ባቀረቡበት ወቅት እንደገለፁት በዞኑ የሚገኙ ኮሌጆች 25 አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመቅዳት 23ቱን ለኢንተርፕራይዞች አሸጋግረዋል።

በ2015 በጀት ዓመት በዞኑ የሚገኙ ኮሌጆች በመደበኛ 2 ሺህ 300 አዲስና ነባር ሰልጣኞችን በመቀበል ከደረጃ 1 እስከ 5 በተለያዩ የሙያ ዘርፎች እያሰለጠኑ እንደሚገኝ ባለሙያው አስረድተዋል።

የምክክር መድረኩ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ከተማሪ ቅበላ አንፃር የሚስተዋሉ ክፍተቶችን አሁንም መሻገር አለመቻሉን ጠቁመው ለዚህ ዋነኛ ምክንያት ተቀናጅቶ አለመስራት ነው ብለዋል።

ከመደበኛ እና ከግል እንዲሁም ከኢንተርፕራይዝ ምዘና አንፃር የሚስተዋሉ የኪራይ ሰብሳቢነት አዝማሚያዎች በመኖራቸው ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባም የውይይቱ ተሳታፊዎች አመላክተዋል።

የክልሉ ቢሮ በኮሌጆች የሚገኙ የአሰልጣኞች አቅም ለማጎልበት ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባ የጠየቁት አስተያየት ሰጪዎች ከስራ ዕድል ፈጠራ አንፃር ከተዳራጁ በኋላ ስለሚሰማሩበት የስራ ዘርፍ ስልጠና እንዲወስዱ ሊደረግ ይገባል ብለዋል።

የጋሞ ዞን ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ አብረሃም አርጋው በዞኑ የሚገኙ ኮሌጆች ባላቸው አቅም ሰልጣኞችን ተቀብሎ እያሰለጠኑ አለመሆናቸውን ጠቁመው ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ በመስራት ችግሩን ሊቀርፉ እንደሚገባ አብራርተዋል።

በኮሌጆች የሚሰሩ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ውጤቶች የህብረተሰቡን ችግር በተጨባጭ ሊቀርፉ የሚችሉ ሊሆኑ እንደሚገባም አቶ አብረሃም አሳስበዋል።

የመምሪያው ኃላፊ አቶ ዳመነ ነጋሽ በበኩላቸው የምክክር መድረኩ ባለድርሻ አካላት በቀጣይ በሚሰሯቸው ተግባራት ዙሪያ ግንዛቤ መፍጠሩን ጠቁመው በተለይ ኮሌጆች በቀጣይ ያቀዱትን ለመተግበር በቁርጠኝነት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።

የክልሉ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ በዛብህ ገበዬሁ ቢሮው ተቋማዊ አቅም ለማሳደግ እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀው ኮሌጆች ሠልጣኞቻቸውን ከስራ ጋር ሊያገናኙ ይገባል ብለዋል።

ጉባኤው የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘጉ ኮሌጆች እውቅና በመስጠት እና በ2016 ዕቅድ ዙሪያ የግብ ስምምነት በመፈራረም ተጠናቋል።

በዞኑ የሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት በዕውቀትና በክህሎት የበለፀገ ሰልጣኝ ለማፍራት ተግባር ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ እንደሚገባ ተጠቆመ አርባምንጭ ፣ ጥቅምት 27/2016 ዓ.ም(ጋሞ ዞን መ/ኮ...
07/11/2023

በዞኑ የሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት በዕውቀትና በክህሎት የበለፀገ ሰልጣኝ ለማፍራት ተግባር ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ እንደሚገባ ተጠቆመ

አርባምንጭ ፣ ጥቅምት 27/2016 ዓ.ም(ጋሞ ዞን መ/ኮሚዩኒኬሽን)፦ የጋሞ ዞን ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና መምሪያ በ2015 በጀት ዓመት አፈፃፀምና በ2016 ዓ.ም ዕቅድ ዙሪያ ሴክቶሪያል ጉባኤ ማካሄድ ጀመረ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ቢሮ ምክትል ኃላፊ እና የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክተር አቶ በዛብህ ገበዬሁ ዘርፉ በመካከለኛ እና ዝቅተኛ ደረጃ የሠለጠነ የሰው ሀይል እያፈራ እንደሚገኝ ገልፀው ሰልጣኞች ተወዳድረው የሚያሸንፉ ብቁ መሆን እንዳለባቸው ተናግረዋል ።

የቴክኒክና ሙያ ተቋማት የሚሰሯቸው የፈጠራ እና የቴክኖሎጂ ሽግግሮች ስቶር ውስጥ ከመቀመጥ ወጥተው የህብረተሰቡን ችግር የሚቀርፉ ሊሆኑ እንደሚገባም የቢሮው ምክትል ኃላፊ አመላክተዋል።

የቴክኒክና ሙያ ተቋማትን አስመልክቶ ህብረተሰቡ ዘንድ የሚስተዋለውን የአመለካከት ችግር ለመቅረፍ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ በትኩረት ሊሰራ ይገባል ሲሉ አቶ በዛብህ ጠቁመዋል።

የጋሞ ዞን ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ አብረሃም አርጋው በበኩላቸው የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሀገራችን ያለመችውን የብልፅግና ጉዞ እንዲሳካ ከማድረግ ባሻገር ከግብርና መር ወደ ኢንዱስትሪ መር ለሚደረገው የኢኮኖሚ ሽግግር ቁልፍ ሚና የሚጫወቱ ባለሙያዎችን እያፈራ እንደሚገኘ ተናግረዋል።

ከመደበኛ ስልጠናዎች ባሻገር ለአጫጭር ስልጠናዎች ትኩረት ሊሰጥ ይገባል ያሉት ረዳት የመንግስት ተጠሪው ከመደበኛ ስልጠና አንፃር የሚስተዋሉ ውስንነቶች ሊታረሙ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በዞኑ የሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች በተለይ በዕደ ጥበብ ዘርፍ ለሚገኙበት አከባቢ ህብረተሰብ ስልጠናዎችን ሊሰጡ እንደሚገባ አቶ አብረሃም አሳስበዋል።

የመምሪያው ኃላፊ አቶ ዳመነ ነጋሽ በጉባኤው መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት ትምህርትና ስልጠና የአንድን ሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት እውን ለማድረግ የጎላ ድርሻ እንዳለው ገልፀው በዚህ ዘርፍ መምሪያው ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

መምሪያው የትምህርትና ስልጠና ፍትሃዊነት እና ተደራሽነት ከማሳደግ ባሻገር የተቋማቱ ውስጣዊ ብቃት የተረጋገጠ እንዲሆን እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የአርባምንጭ ፖሊ ቴክኒክና ሳታላይት ኢንስቲትዩት በተለይ በፈጠራ ስራና በኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ዘርፍ በሀገር አቀፍና በአህጉር ደረጃ ውጤታማ ተግባር ማከናወኑን የገለፁት አቶዳመነ ሌሎች ተቋማት ተሞክሮውን በመቅሰም ሊያሰፉ እንደሚገባም አሳስበዋል።

የመምሪያው የ2015 አፈፃፀም እና የ2016 ዕቅድ ቀርቦ ውይይት የሚደረግ ሲሆን የተሻለ አፈፃፀም ያስመዘገቡ ጽ/ቤቶች እና ኮሌጆች እውቅና እንደሚሰጣቸው ከመምሪያው የተገኘ መረጃ ያመለክታል።

ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ክበብ አባላት ከወዳደቁ ግብአቶች  ባለ 5 ማርሽ ያለው መኪና መሥራታቸው ተገለፀ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።ጋሞ ዞን ብርብር ከተማ አስ...
19/07/2023

ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ክበብ አባላት ከወዳደቁ ግብአቶች ባለ 5 ማርሽ ያለው መኪና መሥራታቸው ተገለፀ።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ጋሞ ዞን ብርብር ከተማ አስተዳደር መንግሥት ኮሚኒኬሽን (ሐምሌ 12 /2015 ዓ.ም ብርብር)

ብርብር ከተማ አሥተዳደር ም/ ዓባያ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ክበብ ተማሪዎች ከወዳደቁ ግብዓቶች በመጠቀም ባለ 5 ማርሽ ያለውን መኪና መሥራታቸውን የት/ት ቤቱ ር/መምህር አቶ በርገነ ባፋ ገለፁ።

የ11ኛ ክፍል ተማሪ የሆኑ በቁጥር 8 የሚደርሱ ተማሪዎች ሞዴል MAHS8 የሆነውን በለ5 ማርሽና በቤንዚን የምትሰራ መኪና መስራታቸው ለት/ቤቱ የመጀመሪያ የፈጠራ ስራ እንደሆነ ተናግረዋል።

ከተማሪዎች መካከል ምንያስ አዲሱ እንደተናገረው መኪና ለመሥራት ያነሳሳቸው እስካሁን ድረስ በክበባቸው ምንም የፈጠራ ስራ አለመሰራቱን ቁጭት እንዳሳደረባቸው ገልጾ ከክበብ አባላት ጋር በጋራ በመሆን ከወዳደቁ እቃዎች ሞዴል MAHS8 መኪና ልንሰራ ቸለናል ብሏል ።

ዘገባው:- ብርብር ከተማ መንግሥት ኮሚኒኬሽን ነው።

የጋሞ ዞን ተወላጅ የሆኑት አቶ ብርሃኑ ዋሬ ለጋሞ ባይራ አዳሪ ትምህርት ቤት ግማሽ ሚሊዮን ብር የሚገመት  የተለያዩ ቁሳቁሶች ድጋፍ አበረከቱ።አርባምንጭ ፡ ሰኔ 15/2015 ዓ.ም (ጋሞ ዞን...
22/06/2023

የጋሞ ዞን ተወላጅ የሆኑት አቶ ብርሃኑ ዋሬ ለጋሞ ባይራ አዳሪ ትምህርት ቤት ግማሽ ሚሊዮን ብር የሚገመት የተለያዩ ቁሳቁሶች ድጋፍ አበረከቱ።

አርባምንጭ ፡ ሰኔ 15/2015 ዓ.ም (ጋሞ ዞን መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን)፦ ባለሀብቱ ለትምህርት ቤቱ ውጤታማነት የሚጠበቅበትን ድጋፍ ሊያደርግ እንደሚገባም ተጠቁሟል።

የጋሞ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ማዶ መንገሻ በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት የጋሞ ባይራ አዳሪ ትምህርት ቤት የተቋቋመበትን ዓለማ እንዲያሳካ በተለይ ባለሀብቶች አስፈላጊውን ድጋፍ ሊያደርጉ እንደሚገባ ተናግረዋል።

አቶ ብርሃኑ ዋሬ በዞኑ ለሚገኙ ሌሎች ባለሀብቶች አርአያ የሆነ ተግባር ፈፅመዋል ያሉት የጽ/ቤቱ ኃላፊ ተማሪዎች ለውጤታመነት ተግተው ሊሰሩ እንደሚገባም አሳስበዋል።

ነዋሪነታቸውን አዲስ አበባ ያደረጉት ባለሀብት አቶ ብርሃኑ ዋሬ ለጋሞ ባይራ አዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪዎች 214 አንበሳ ጫማ እና የትምህርት ቤቱ አርማ የታተመበት 22 የመምህራን ደንብ ልብስ ድጋፍ አድርገዋል።

ትምህርት ለአንድ አከባቢም ሆነ ለሀገር ዕድገት የጎላ አስተዋፅኦ አለው ያሉት ባለሀብቱ ተቋሙ ለሀገር የሚተርፉ ምሁራን ለማፍራት እየጣረ የሚገኝ በመሆኑ ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልፀዋል።

በዞኑ ሆነ ከዞኑ ውጭ የሚገኙ ባለሀብቶች የመደጋገፍ ባህላቸውን በማሳደግ ለዞኑ ሁለንተናዊ ለውጥ ድጋፍ ሊያደርጉ እንደሚገባም አቶ ብርሃኑ ዋሬ አሳስበዋል።

የጋሞ ባይራ አዳሪ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አቶ አብረሃም ዶቤ የትምህርት ቤቱ ዋና ዓላማ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆኑ ተማሪዎችን ማፍራት መሆኑን ገልፀው ለመምህራንና ለተማሪዎች ለተደረገው ድጋፍ አመስግነዋል።

ባለሃብቱ ከዚህ ቀደም በአርባምንጭ ከተማ የሚገኘውን ዘመናዊ የመኖሪያ ቤታቸውን በኮሮና ቫይረስ ለተያዙ ግለሰቦች የማገገሚያ ማዕከል እንዲሆን ማድረጋቸውም ይታወሳል።

በሩፋኤል ግርማይ

“በሁለት አመታት ውስጥ 10 ዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ ይሆናሉ”      ትምህርት ሚኒስቴር ‼️ ለመሆኑ ራስ ገዝ ማለት ምን ማለት ነው⁉️    ✏️ ዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝነት ወይም በሌላ ስሙ ...
22/06/2023

“በሁለት አመታት ውስጥ 10 ዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ ይሆናሉ”
ትምህርት ሚኒስቴር ‼️

ለመሆኑ ራስ ገዝ ማለት ምን ማለት ነው⁉️

✏️ ዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝነት ወይም በሌላ ስሙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተቋማዊ ነጻነት ማለት ተቋማቱ የአስተዳደራዊ፤ የአካዳሚክ፤ የምርመር፤ የሰው ሃብት አስተዳደር፤ የፋይናንስ ጉዳዮቻቸውን ነጻነት ኖሯቸው በዛው ልክ ደግሞ ተጠያቂነትም እንዳለባቸው አውቀው የሚተገብሩበት ሥርዓት ነው፡፡

አንድ ተቋም ተቋማዊ ነጻነት ተጎናጽፏል ወይም ራስ ገዝ ሆኗል ብለን ስናስብ በዋናነት ከአካዳሚና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ጋር ተያይዞ ነጻነት ኖሯቸው ይህንንም ከተጠያቂነት ጋር በመያዝ የተሻለና ውጤታማ ስራን እንዲሰሩ የማስቻል ጅምር ነው፡፡

አስተዳደራዊ ነጻነቱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ የራሳቸውን አደረጃጀት እና መዋቅር የመዘርጋት ስልጣን ይሰጣቸዋል፤ በዚህ መሰረት ዩኒቨርሲቲዎቹ ከፍተኛ አመራሮቻቸውን ጨምሮ በመዋቅራቸው ውስጥ የሚያስፈልጓቸውን የአመራር እና የአስተዳደር አካላትን በራሳቸው መመደብ እንደሚችሉ መንገድ ይከፍትላቸዋል፡፡

በሌላ በኩልም ፋይናንሻል አቅማቸውን በጀታቸውን በአግባቡ የመጠቀም እድል ይፈጥርላቸዋል። ዩኒቨርሲቲዎች አመራሮችን የመሻር፤ የመሾም፤ ሀብት የመፍጠር ፤የውስጥ መመሪያዎችንና አስተዳደራዊ ስርዓቶችን የመዘርጋት ነጻነት ይኖራቸዋል። ከሁሉም በላይ ደግሞ የሰው ሀብታቸውን በአግባቡ ከመጠቀም ብሎም ብቃት ያላቸውን ባለሙያዎች የመቅጠርና ሥርዓቱን እንዲሁም ደመወዝና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞችን የመወሰን አቅም ይፈጥርላቸዋል። በተለይም ለዩኒቨርሲቲው ብሎም ለአገር ይጠቅማል፡፡ ችግር ፈቺ የምርምር ስራዎችን ይሰራል ብለው ያመኑበትን ባለሙያ በድርደር እስከ መቅጠር ድረስ የሚደርስ ነጻነት እንዲኖራቸው ያስችላቸዋል፡፡

ከተማሪዎች ቅበላ ጀምሮ አስመርቆ እስከማውጣት ድረስ ያለው ሂደት ጤናማ ብሎም በእውቀት ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ለማድረግ ተማሪዎችን አወዳድሮ እስከመቀበል ድረስ ያለውን ውሳኔ የማንንም ድጋፍ ሳይጠይቁ የመወሰን አቅም ይፈጥርላቸዋል፡፡

ተቋማት ራስ ገዝ በሆኑ ቁጥር ለሚያስተምሯቸው ተማሪዎች ምን ዓይነት የትምህርት ሥርዓት መከተል እንዳለባቸው ገበያውም በሚፈልገው ልክ የመወሰን ከዛም አልፎ የሚያስትምሩበትን ቋንቋም እስከ መወሰን ድረስ እድል ይኖራቸዋል፡፡

አዲስ ዘመን ፦ከዚህ ቀደም ከፍተኛ የትምህርት ተቋማቱ በቦርድ ይተዳደሩ ነበር፡፡ በዛም አንዳንድ ጉዳዮቻቸውን በቦርድ የማስወሰን አካሄድም እንደሚከተሉ ይታወቃል ፤ አሁን ራስ ገዝ መሆናቸው ምን ይጨምርላቸዋል?

ዶክተር ሰለሞን፦ልዩነቱ ዩኒቨርሲቲዎች የመንግስት ተቋማት በመሆናቸው በጀታቸውንም ሙሉ በሙሉ የሚያገኙት ከመንግስት ነው፤ በቦርድ ይተዳደሩ እንጂ የራሳቸው የሆነ የፋይናንስ የሰው ሃብት የግዢ አስተዳደር አልነበራቸውም ። የሲቪል ሰርቪስ የሚወጣ የሰው ሃብት አስተዳደር ነው የሚከተሉት። በገንዘብ ሚኒስቴር የሚወጣ የግዢና የፋይናንስ ሥርዓትን ነው ሲከተሉ የኖሩት። ይህ ደግሞ አሁን ባለው ሁኔታ ብሎም ተቋማቱ ካላቸው ልዩ ባህርይ አንጻር ምቹ ሆኖ አልተገኘም። ምቹ አለመሆን ብቻ ሳይሆን ተቋማቱ ለቆሙለት የትምህርት ጥራት የማረጋገጥ ስራ እንቅፋት ፈጥሯል። በመሆኑም ተቋማቱ ተቋማዊ ነጻነትን ተጎናጸፉ ስንል የራሳቸው የሆነ የፋይናንስ የግዢ ሥርዓት እንዲኖራቸው እድል ሰጥቷል ማለት ነው። አዋጁም ጸድቋል። በመሆኑም ከዚህ በኋላ ወደራስ ገዝ የሚመጡት ተቋማት የራሳቸው የሆነ በቦርድ የሚጸድቅ የፋይናንስ የግዢ የሰው ሃብት አስተዳደር ይኖራቸዋል። ይህ ደግሞ እንደ ተቋም ትልቅ ነጻነትን የሚፈጥር ነው።

ተቋማቱ ተማሪን

job notes
17/06/2023

job notes

የመማር ማስተማር ስነዜደ(methodology), የቴክኖሎጂ አሰራር እና የአድሱ ዉጤት  አሰጣጥ ሥልጠና  ተሠጠ ።የዛዳ/ኮ/ኢ/ኮ ሰኔ 7/2015 አ.ም አዲስ  የተቀጠሩ አሰልጣኝ መመምህራን የ...
14/06/2023

የመማር ማስተማር ስነዜደ(methodology), የቴክኖሎጂ አሰራር እና የአድሱ ዉጤት አሰጣጥ ሥልጠና ተሠጠ ።

የዛዳ/ኮ/ኢ/ኮ ሰኔ 7/2015 አ.ም አዲስ የተቀጠሩ አሰልጣኝ መመምህራን የቴክኖሎጂ ፣የትምህርት ሥነዜደ እና የአዲሱን ሠልጣኝ ዉጤት አሰጣጥ ዙርያ ግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ከሰኔ 5 -7/2015 አ.ም ድረስ 3 ተከታታይ ቀናት ላይ በነባር አሰልጣኞች አማካኝነት ተሰቷዋል።

ማስታወቂያ  አስደሳች ዜና  ለአጫጭር ስልጠና ፈላጊዎች በሙሉ  የዛዳ  ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ  ከዚህ  በፊት  ለሁለት  ሙያዎች ላይ ሥራ ፈጣሪዎችን ከሥራ ጋር የሚያስትሳስር አ...
12/06/2023

ማስታወቂያ
አስደሳች ዜና ለአጫጭር ስልጠና ፈላጊዎች በሙሉ

የዛዳ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ከዚህ በፊት ለሁለት ሙያዎች ላይ ሥራ ፈጣሪዎችን ከሥራ ጋር የሚያስትሳስር አጭር ጊዜ ሥልጠና መሰጠቱ ይታወቃል ። አሁን ግን ሁለተኛ ዙር ሥልጠና ፈላጊዎችን ለማሰልጠን ዝግጅቱን ጨርሶ መጠባበቅ ላይ ይገኛል ።ኑ ሰልጥነዉ በሙያው የሚተማመን ብቁ ዜጋ እንሁን !!

Address

Zada; Gamo
Arba Minch'

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Zada Construction and Industrial College posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share