Tilahun Kebede

Tilahun Kebede President of South Ethiopia Regional State https://t.me/tilahunkebede
(5)

02/09/2026
ኣይካ ዳኜ ገብሬ ኣሪ ዎርሸንከን የለክ ማትኪዳይክ ኤድ ሙዳከን ኤስምታባብ፣ ኤስንቲ ካሽዳብ፣ ጋምሴዳም ኤድምስዳብከ ኤድ ሙዳ ይም ናሽዳብ ኣሪት ሺፊ ሀቄ።በክልላችን የሀገር ሽማግሌዎች መማክር...
26/08/2026

ኣይካ ዳኜ ገብሬ ኣሪ ዎርሸንከን
የለክ ማትኪዳይክ
ኤድ ሙዳከን ኤስምታባብ፣
ኤስንቲ ካሽዳብ፣
ጋምሴዳም ኤድምስዳብከ
ኤድ ሙዳ ይም ናሽዳብ
ኣሪት ሺፊ ሀቄ።

በክልላችን የሀገር ሽማግሌዎች መማክርት አባል፤
የአሪ ብሄረሰብ ባህል፣ ታሪክ፣ ቋንቋና እሴት አዋቂ የአንድነት እና የፍቅር አባት፤ የወንድማማችነት እሴት አቀንቃኝ የነበሩ።

አቶ ዳኜ ገብሬ ከዚህ ዓለም ድካም ዛሬ ጠዋት ማረፋቸዉን ስሰማ ልቤ ተሰበረ። ታላቅ መካሪና አስተማሪ አባት አጣን።

ለመላዉ ቤተሰቦች፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ፈጣሪ መጽናናትን እንዲሰጥ እየተመኘሁ፤ ፈጣሪ ነፍሳቸውን በአፀደ ገነት ከደጋጎች አጠገብ ያሳርፍ።

24/08/2026

እንኳን ለ1501ኛው የነቢዩ መሐመድ(ሰዐወ) የመውሊድ በዓል አደረሳችሁ

የነቢዩ መሐመድ ታሪክ ትውልድን ለበጎ ከሚቀርጹ ታሪኮች መካከል አንዱ ነው፡፡ የተጠሩበትን ዓላማ ማክበር፤ ለተጠሩበት ዓላማ ዋጋ መክፈል፤ የተጠሩበትን ለሌሎች ማካፈል፤ የተጠሩበትን አክብሮ መኖር - እነዚህ ሁሉ ሺ መጻሕፍት የሚወጧቸው ትምህርቶች ናቸው፡፡

ነቢዩ የተጠሩበትን ዓላማ በሚገባ ስለተገነዘቡ አክብረው ኖረዋል፡፡ የተጠሩት ለተራና ርካሽ ነገር እንዳልሆነ ተገንዝበዋል፡፡ የተጠሩት ትውልድን ለመቅረጽና ታሪክን ለመቀየር መሆኑን አምነዋል፡፡ ያንንም በቃላቸው፣ በሥራቸውና በኑሯቸው አክብረውት ነኖረዋል፡፡ ለታላቅ ሀገራዊ ዓላማ ተጠርተናል ብለን የምናምን ከሆነ ይህ የነቢዩ ሕይወት ታላቅ ትምህርት ይሆነናል፡፡ የተጠራንበትን ዓላማ በንግግራችን፣ በሥራችንና በሕይወታችን እንግለጠው፡፡

ነቢዩ ለተጠሩበት ዓላማ ዋጋ ከፍለዋል፡፡ ከቦታቸው ተሰደዋል፤ ምግብና መጠለያ ተነፍገዋል፤ ከቤተሰቦቻቸው ተለይተዋል፡፡ ለሞት በሚያበቁ ፈተናዎች ውስጥ አልፈዋል፡፡ ጦርነት ተከፍቶባቸዋል፡፡ ነገር ግን ሁሉንም በአላህ ኃይል አሸንፈዋል፡፡ ክብር ያለ መከራ አይገኝምና፡፡ እውነተኛ ሰው ለዓላማው እንደ ነቢዩ መሐመድ(ሰዐወ)ዋጋ ይከፍላል፡፡ ዓላማው የሚያስገኘውን ክብርና ጥቅም ብቻ ሳይሆን ዓላማው የሚያስከፍለውን መሥዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ይሆናል፡፡

ነቢዩ መሐመድ(ሰዐወ) ከአላህ የደረሳቸውን መልእክት ለራሳቸው ብቻ አላስቀሩም፡፡ የተጠሩበትን ለሌሎች ለማካፈል ተግተዋል፡፡ መጀመሪያ በጣት ለሚቆጠሩ ሰዎች፣ በኋላም ለቅርብ ሱሐባዎች፣ በመጨረሻም ለዓለም መልእክቱን አዳርሰዋል ፡፡ እሳቸው የዘሩት ዘር እያፈራና እየጎመራ ተጉዟል፡፡ ዓላማችንን እኛ ማወቃችንና ማመናችን ብቻ ጥቅም የለውም፡፡ ሌሎች እንዲያውቁና እንዲያምኑ ልክ እንደነቢዩ ተገትተን መድከም አለብን፡፡

የነቢዩን መውሊድ ስናከብር ከሕይወታቸው እየተማርን፤ የተማርነውንም ለሀገረ መንግሥት ግንባታችን እየተጠቀምን እንዲሆን አደራ እላለሁ፡፡

በድጋሚ መልካም የመውሊድ በዓል ይሁንልን።

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ.ም

ደሬ ዎጋ ኤራ አዋዉ፤ ሲቆኔ እስፔቴታ ኦዳን ኤሬትያ አዋዉ፤ ባቾሬ አብራሜ ቶሳ ቶፒያ አዋዉ፤ ታሳ ታሳ ታሳ ታሳ ታሳ ታሳ ታሳ ኑ አዋዉ።  ፆስ ሼምፑዋ ማሮ። ታላቁ የክልሉ አገር ሽማግሌ እና...
14/08/2026

ደሬ ዎጋ ኤራ አዋዉ፤
ሲቆኔ እስፔቴታ ኦዳን ኤሬትያ አዋዉ፤
ባቾሬ አብራሜ ቶሳ ቶፒያ አዋዉ፤
ታሳ ታሳ ታሳ ታሳ ታሳ ታሳ ታሳ ኑ አዋዉ።
ፆስ ሼምፑዋ ማሮ።

ታላቁ የክልሉ አገር ሽማግሌ እና የዎላይታ ህዝብ የታሪክና ባህል ተመራማሪ አቶ አብራሃም ባቾሬ ከዚህ ዓለም በሞት በመለየታቸዉ የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን እየገለጽኩ ለመላው ቤተሰቦች መፅናናትን እመኛለሁ።
ነፍሳቸዉን ፈጣሪ ከደጋጎች አጠገብ በአፀደ ገነት ያሳርፍ።

14/08/2026
06/08/2026
በኅብረት የተስፋ አሻራችንን በማኖር ዳግም ታሪክ መስራት ችለናል! ዛሬ ሐምሌ 27/2018 ዓ/ም በሀገራዊው የአረንጓዴ አሻራ የአንድ ጀንበር ተከላ በክልላችን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸውን 69...
03/08/2026

በኅብረት የተስፋ አሻራችንን በማኖር ዳግም ታሪክ መስራት ችለናል!

ዛሬ ሐምሌ 27/2018 ዓ/ም በሀገራዊው የአረንጓዴ አሻራ የአንድ ጀንበር ተከላ በክልላችን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸውን 69 ሚሊዮን ችግኞች ለመትከል አቅደን፤ ተፈጥሮን መጠበቅ የህልውና ጉዳይ መሆኑን በውል በተረዳው የክልላችን ህዝብ ንቁ ተሳትፎ ለመጪው ትውልድ የተስፋ አሻራችንን ለማኖር በጋራ ባደረግነው ርብርብ ከዕቅድ በላይ 76 ሚሊዮን ችግኞች በመትከል እንደ ሀገር ዳግም ለአለም ተምሳሌት የሆነ ታሪክ መስራት በመቻላችን የተሰማኝን ልባዊ ደስታ እየገለጽኩ ለመላው የክልሉ ህዝብ የላቀ ምስጋናዬን ለማቅረብ እወዳለሁ፡፡

በዕለቱ በመላዉ የክልላችን ህዝቦች ፅናት እና ትጋት ለተመዘገበው ስኬት በማስተባበርና በመምራት ጉልህ አስትዋጽኦ ላበረከታችሁ እንዲሁም ከማለዳ እስከ ምሽት በትጋት ለተከላችሁ በሙሉ ዳግም ልባዊ ምስጋናዬን እያቀረብኩ፤ በቀጣይ የተተከሉትን በመንከባከብና በመጠበቅ ደህንነቱ የተጠበቀ አረንጓዴ ከባቢን ለትውልድ ለማሻገር እንድንተጋ ከአደራ ጭምር አሳስባለሁ፡፡

ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!!

Address

Hawassa
Arba Minch'
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tilahun Kebede posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Tilahun Kebede:

Shortcuts

Share