04/09/2026
"ጠንካራ መንግሥትና ውጤታማ የፓርቲ አመራር ለመገንባት በዕውቀትና በክህሎት የታነፀ አባል ማፍራት ያስፈልጋል" - አቶ ገዛኸኝ ጋሞ
ዛዳ፣ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም(ዲታ ወረዳ መ/ኮሚዩኒኬሽን)
የጋሞ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የ2018 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ግምገማ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ሀሳቦችና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ ከመድረክ በመስጠት ተጠናቋል።
በመድረኩ በበጀት ዓመቱ የፓርቲ ስራዎች አፈፃፀም፣ የተመዘገቡ ጥንካሬዎች፣ የታዩ ክፍተቶችና በቀጣይ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ምክክር ተካሂዷል።
የጋሞ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ገዛኸኝ ጋሞ እንደገለጹት፣ በ2018 በጀት ዓመት የተገኙ ውጤቶች በመዋቅሮች መካከል በተደረገ የተቀናጀ ስራ የተመዘገቡ ናቸው ብለዋል።
ጠንካራ መንግሥትና ውጤታማ የፓርቲ አመራር ለመገንባት በዕውቀትና በክህሎት የታነፀ አባል ማፍራት ወሳኝ መሆኑንም ገልጸዋል።
በተለይም ሀገራዊ ምርጫው በስኬት መጠናቀቁን በማንሳት ለዚህ ውጤት አስተዋጽኦ ያደረጉ አመራሮችና የፓርቲ መዋቅሮችን አቶ ገዛኸኝ አመስግነዋል።
የጋሞ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ ጽ/ቤት ፖለቲካ እና ርዕዮተ - ዓለም ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተመስገን እዩኤል በበኩላቸው፣ ዕቅዶችን ለማሳካት አፈጻጸምን በየጊዜው መገምገም፣ የተመዘገቡ ጥንካሬዎችን ማስቀጠል እና ዝቅተኛ አፈጻጸም የታየባቸው ስራዎችን በቀጣይ ዕቅድ በመከለስ መስራት እንደሚጠበቅ ገልጸዋል።
በተለይ የፓርቲ አደረጃጀቶችን ማጠናከር ፣ ጠንካራ አባል መፍጠር፣ በፓርቲ ገቢ አሰባሰብ ላይ በትኩረት መሰራት ፣ በፓርቲ በሚሰሩ እና በሌሎች ዘርፎች ላይም ትኩረት ያስፈልጋል ብለዋል።
የጋሞ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አዲሱ ግርማ በምርጫው ወቅት የታየውን የቅንጅት አሰራር በቀጣይ ስራዎች በማስቀጠል የታቀዱ ግቦችን ማሳካት እንደሚገባ አሳስበዋል።
በአንዳንድ መዋቅሮች የሚታዩ የመረጃ አያያዝ ክፍተቶች ሊታረሙ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
በውይይቱ ሀሳብና አስተያየት የሰጡ ተሳታፊዎች የሀገራዊ ምርጫ ስኬት በዞኑ የተቀናጀ ስራ ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል።
ተግባራትን በተሻለ አቅም ለመፈጸም መስራት እንደሚጠይቅም አመላክተዋል።
በመድረኩ በተነሱ ሀሳቦችና አስተያየቶች ላይ ማብራሪያ በመስጠት ፣ የ2018 በጀት ዓመት ግምገማ የተመዘገቡ ጥንካሬዎችን በማስቀጠልና ክፍተቶችን በማረም ቀጣይ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ከስምምነት ተደርሷል።
በመጨረሻም የውል ስምምነት በመፈራረም መድረኩ ተጠናቋል ።