27/03/2025
#ዜና ችሎት
#አስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በፅኑ እስራት መቀጣቱ ተገለፀ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ጋዜሶ ፣ መጋቢት:- 11/2017 ዓ/ም (ቦንኬ ወረዳ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን)
የቦንኬ ወረዳ ፍ/ቤት ዛሬ በቀን 15/7/2017ዓ.ም በዋለው 4ኛ ወንጀል ችሎት ተከሳሽ አቶ ዘመደ ዛጳ በቦንኬ ወረዳ ጮሻ ቀበሌ በተለምዶ ግያሶ ተብሎ በሚጠራበት ሠፈር ዕለት ቅዳሜ ቀን 12/4/2017ዓ.ም ከቀኑ 9:00 የወንድሙ ልጅ የሆነችውን የግል ተበዳይ ወደ ራሱ ቤት ጠርተው በማስገባት የአስገድዶ መድፈር ወንጀል እንደፈፀመ የቦንኬ ወረዳ ፖሊስ ምርመራ መዝገብ ያሳያል።
ምርመራው ተጣርተው የቀረበውን ያረጋገጠው የቦንኬ ወረዳ ዐቃቤ ሕግ ተከሳሽ የፈፀመውን ወንጀል ድርጊት ከኢፌዴሪ ወንጀል ህግ አንፃር በመመልከት ተከሳሽ በ1997 ተሻሽሎ የወጣውን የኢፌዴሪ ወንጀል ህግ አንቀጽ 620 (2) /ሀ/ እና /ሐ/ ሥር የተደነገገውን በመተላለፍ ተከሳሽ በቤተዘመድ ላይ እና መናገር የማትችል እንዲሁም ራሷን መከላከል የማትችል ሴት ላይ ድርጊቱን የፈፀመው መሆኑን የሚያስረዳ የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎችን በማደራጀት ክስ መሥርተዋል።
ክሱን ተቀብለው ያስቻለው የቦንኬ ወረዳ ፍ/ቤት ተከሳሽ ክሱን መከላከል ባለመቻሉ ዛሬ በቀን 15/7/2017ዓ.ም በዋለው 4ኛ ወንጀል ችሎት ተከሳሽን ያርማል ሌሎችንም መሰል ወንጀል አድራጊዎችን ያስተምራል በማለት ተከሳሽን በ10 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስነዋል።
የቦንኬ ወረዳ ፍትሕ ጽ/ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ ሲሳይ ዳዊት ህብረተሰቡ በተለይም በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ላይ በፍትህ አካላት ጎን በመቆም መራራ ትግል ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበው በአስገድዶ መድፈር ወንጀል በባሕሩ ሰው በሌለበት የሚፈፀም በመሆኑ ጋር ተያይዞ ወንጀለኞች ማስረጃ በማሳጣት ብዙ ግዜ ብመክሩም ህግ በሰውና በተለይም በሰነድ ማስረጃ ማረጋገጡ የማይቀር ስለሆነ ህብረተሰቡ ከዚህ አይነት ድርጊቶች ራሱን እንዲቆጥቡ አሳስበው የተጣለው ቅጣት አስተማሪ መሆኑን ገልፀዋል።