Gamo Wogga

Gamo Wogga gamooo

በአርባምንጭ ከተማ የኮሪደር ልማት አካል የሆነው የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ በከፊል
08/06/2026

በአርባምንጭ ከተማ የኮሪደር ልማት አካል የሆነው የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ በከፊል

05/05/2026

የአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር ለ85ኛው የአርበኞች መታሰቢያ ቀን (የድል በዓል) የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ
**********
አርባምንጭ፦ ሚያዚያ 27/2018 ዓ.ም (አርባምንጭ ከተማ መንግስት ኮሙኒኬሽን )

መስፍን መንዛ (ዶ/ር) የአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር 85ኛውን የአርበኞች መታሰቢያ ቀን (የድል በዓል) አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ከንቲባው በመልዕክታቸው "የአርበኞች ቀን" የሚያላብሰን ተምሳሌታዊ ትጋት እና ወኔ በልዩነት እና በከፍታ የሚታይ ነውና እኛም የጀግኖች አርበኞች ልጆች በህብረት ተግተን ድህነትን በመቀልበስ ልዕልናዋ የጠነከረ የብልፅግና ተምሳሌት ሀገር በማኖር የዘመኑን አርበኝነት መወጣት ይጠበቅብናል ብለዋል።

የከንቲባው ሙሉ መልዕክት እንደሚከተለው ቀርቧል፡-
***************
ዘንድሮ ለ85ኛ ዓመት የምንዘክረው #የአርበኞች ቀን በዓል ሀገራችን ኢትዮጵያን ዳግም በኃይል በመውረር ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎችን ታጥቆ ሰፊ ወታደራዊ ዝግጅት በማድረግ የቆየውን የፋሺስት ኢጣልያ ወራሪ ኃይል በ1928 ዓ.ም ያደረገውን ወረራ በአምስት ዓመታት ፍጹም የአርበኞች ተጋድሎ የተሸነፈበትን የአርበኞች ድል የምናከብርበት የኢትዮጵያዊነታችን የኩራት በዓላችን ነው ።

የፋሺስት ኢጣልያ ወራሪ ኃይል ኢትዮጵያን በቅኝ ለመግዛት የዓድዋ ጦርነት ሽንፈቱን ለመበቀል የዓድዋ ጦርነት ከተካሄደ ከ40 ዓመት በኋላ የምዕራቡ ዓለም የደረሰበትን ስልጣኔ በመጠቀም የተፈበረኩ በዓለም አቀፍ ሕግ የተከለከለውን መርዛማ ጋዝ በመጠቀም ጭምር ነበር ኢትዮጵያውያንን ለማንበርከክ የወረረው።

ይህም ማለት ፋሺስት ኢጣሊያ ኢትዮጵያን ዳግም ለመውረር የመጣው በ1888 ዓ.ም በዓድዋ ጦርነት የደረሰበትን አሳፋሪ የወታደራዊ፣ ፖለቲካዊና ስነ-ልቦናዊ ሽንፈት በድል ለመቀየር ለ40 ዓመታት በመዘጋጀት ኢትዮጵያን ለመበቀል፣ ሕዝቦቿን በዓለም አደባባይ ለማዋረድ እና በምስራቅ አፍሪካ የቅኝ ግዛቱ አካል ለማድረግ በእብሪትና በፋሺስታዊ እሳቤ በማቀድ ነበር።

ፋሺስት ኢጣሊያ ኢትዮጵያዊያንን በግፍና በጭቆና ለመግዛት ዳግም ወረራ በማድረግ አርበኞች በሀገር ፍቅር ወኔና ጽኑ ትግል ለአምስት ዓመታት ሲያደርጉት በነበረ ተጋድሎ ባይሸነፍ ኖሮ እንደሀገር አንገት የሚያስደፋ የቅኝ ግዛት ታሪክ ይኖረን ነበር።

ፋሺስት ኢጣሊያ በአምስት ዓመት ቆይታው ኢትዮጵያዊያንን ለማንበርከክና ነፃነታቸውን ለመውሰድ የሚችለውን ሁሉ ቢያደርግም የቅኝ ግዛት ህልሙ ሊሳካ አልቻለም፡፡

እናት አባት ኢትዮጵያዊያን አርበኞች ዱር ቤቴ ብለው በዱር በገደል ነፍጥ አንግበው፤ ጎራዴ ስለው፣ በዱር በገደሉ እየተዋደቁ፣ ረሀብ፣ ቸነፈር መከራው ሳይበግራቸው ፋሺስት ኢጣሊያን መግቢያና መውጫ በማሳጣት የአምስት ዓመታት መሪር ተጋድሎ ፈጽመዋል።

እናት አባቶቻችን ዘመኑ የጠየቃቸውን ሁለንተናዊ መሥዋዕትነት ከፍለው ከቅኝ ተገዥነት ውርደት ነፃ የሆነች፤ የግዛት አንድነቷ የተጠበቀ ነፃ ሀገር በክብር ለቀጣዩ ትውልድ አስረክበው አልፈዋል፡፡

የቀደሙ ጀግኖች አርበኞቻችንን የድል አድራጊነት ታሪክ፤ ዘመኑ በሚጠይቀን የትግል አውድ ላይ መድገም አስፈላጊ በመሆኑ እኛ የዛሬው ትውልድ ኢትዮጵያዊያን የአያት አባቶቻችን ታሪክ ወራሽ ብቻም ሳንሆን ድህነትን በመቀልበስ ልዕልናዋ የጠነከረ የብልፅግና ተምሳሌት ሀገር በማኖር የዘመኑን አርበኝነት መወጣት የራሳችንን የአርበኛነት ታሪክ በደማቁ ልንፅፍ ይገባል፡፡

የአርበኞች ቀን" የሚያላብሰን ተምሳሌታዊ ትጋት እና ወኔ በልዩነት እና በከፍታ የሚታይ ነውና ለከተማው ማህበራዊ መሠረትና የኢኮኖሚ ምንጭ የሆኑ የተጀመሩ
የልማት እንቅስቃሴዎችን በማስቀጠል የለውጥ ትልሞቻችን እውን እንዲሆኑ ሁላችንም በልማቱ ተሰናስለን በመትጋትና በተሰማራንባቸው መስክ የበኩላችንን ልንወጣ ይገባል።

ዘላለማዊ ክብር ለእናት አባት አርበኞች! እንኳን አደረሳችሁ! አደረሰን! መልካም የድል በዓል ቀን!

መስፍን መንዛ(ዶ/ር)

የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ
ሚያዚያ 27፣2018 ዓ፣ም
አርባምንጭ|| ኢትዮጵያ

05/05/2026

ፍርድ ቤት የያዘውን ጉዳይ በሚዲያ ጋጋታ ለማሸነፍ ለምን ታሰበ?
የስዩም ተሾመ ሚዛናዊነት የጎደለው ውንጀላ!

የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ (አዋጅ ቁጥር 1238/2013) ይህ አዋጅ በሚዲያና በፍትህ አካላት መካከል ያለውን ግንኙነት በዝርዝር ያስቀምጣል። መገናኛ ብዙሃን በፍትህ ሂደት ላይ ያሉ ጉዳዮችን ሲዘግቡ ትክክለኛ፣ ሚዛናዊና የሕግ የበላይነትን ያከበሩ መሆን እንዳለባቸው ይጠቁማል።

ፍርድ ቤቶች የዜጎች የመጨረሻ የመብት ማስከበሪያ ናቸው። ፍርድ ቤቶች በሕግ አውጭው አካል አስቀድመው የወጡ ሕጎችን የመተረጎም ሥልጣን የተሰጣቸው በየትኛውም አካል ተፅዕኖ ውስጥ ሳይወድቁ ነፃና ገለልተኛ ሆነው የፍህት ስርዓቱን የሚያሳልጡ ተቋማትም ናቸው። መገናኛ ብዙሃን ፍርድ ቤት በያዘው ጉዳይ ላይ ሚዛናዊ ያልሆኑ ዘገባዎችን ማሰራጨት እንደማይችሉ የመገናኛ ብዙሃን አዋጅ ይደነግጋል።

የዳኝነት ነፃነት ( በኢፌዲሪ ሕገ መንግሥ አንቀጽ 79)፦ ፍርድ ቤቶች በማንኛውም ደረጃ የዳኝነት ስልጣናቸውን ሲጠቀሙ ከማንኛውም የተፅዕኖ ፈጣሪ አካል (ሚዲያን ጨምሮ) ነፃ መሆናቸውን ያመላክታል።

ምንም እንኳን አዋጁ ይህንን ቢያስቀምጥም አንዳንድ የማህበራዊ ሚዲያ አንቀሳቃሾች ይህንን ድንጋጌ ወደ ጎን በመተው ፍርድ ቤት በያዛቸው ጉዳዮች ላይ ሚዛናዊነት የጎደላቸውን ዘገባዎችን የመስራት እና የፍርድ ቤት የዳኝነት ስርዓት ላይ ተፅዕኖ የመፍጠር ስራዎችን ሲሰሩ ይስተዋላል።

ለአብነትም ከሰሞኑን ጦማሪ ስዩም ተሾመ ነፃ ውይይት በተሰኘው የዩቲዩብ ዝግጅቱ ላይ በጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተያዘውን የአቶ ብርሃነ መስቀል ክንፈ የማራማይንስ ማዕድን ምርመራ እና ማዕድን ማምረት ስራ ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ ጉዳይን ሚዛናዊነት በጎደለው መልኩ በዘፈቀድ በሚዲያ ሲያራግብ ተስተውሏል።

ጉዳዩን የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በከባድ ሙስና ክሥ የእርሡን እና የግብር አበሩን እያየ የሚገኝ ሲሆን፤
የፌደራል የመጀመሪ ደረጃ ፍ/ቤት እና የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ግራ ቀኙን በፍታብሔር ችሎቶች እያከራከሩ ለመጨረሻ ውሣኔ ተቀጥሮ ሣለ ለምን አሁን ሚዲያ ላይ ማሥጮህ ተፈለገ?

ፍርድ ቤት ውሳኔ ለመስጠት ቀጠሮ በያዘው ጉዳይ ላይ የሕግ የበላይነትን ባለከበረ መልኩ በአክቲቪስት ስዩም ተሾመ አማካኝነት ለአንድ ወገን ያደላ ሃሰተኛ መረጃ መሰራጨቱ በብዙዎች ዘንድ ቅሬታን ፈጥሯል።

ሚዲያ እውነተኛ መረጃን ከሁለት ወገን አጣርቶ ገለልተኛ በሆነ መልኩ መረጃን ለሕዝብ የማድረስ ኃላፊነት ያለው ቢሆንም ስዩም ተሾመ ያልተረጋገጡ መረጃዎችን የማሰራጨት እና ፍርድ ቤት የያዘውን ጉዳይ ላይ ውሳኔ ሲሰጥበት ተስተውሏል።

ፍርድ ቤት ውሳኔ ለመስጠት ከጫፍ በደረሰው ጉዳይ ላይ
ስዩም ተሾመ ከአንድ ወገን ተላከልኝ ያለውን መረጃ ይዞ ወደ ሚዲያ መውጣት ለምን አሰፈለገ። ይህ ከሚዲያ ስነምግባር ያፈነገጠና ሚዛናዊነት የጎደለው ውንጀላ በፍርድ ቤት ላይ ተገቢነት የሌለው የሚዲያ ጫና በማሳደር የፍህት ስርዓቱን ለማደናቀፍ ያለመ ሴራ መሆኑን ሕዝብ ሊረዳ ይገባል።

ጉዳዩን በተመለከተ ፍርድ ቤት በራሱ አሰራር ተገቢውን ብይን የመስጠት ሙሉ ስልጣን ያለው ቢሆንም በሚዲያ ጋጋታ ይህን ዕውነታ ለመደበቅ እና የፍህ ስርዓቱ ላይ ጫና ለማሳደር በግልጽ ዘመቻ መከፈቱን መረዳት ይቻላል።

ስዩም ተሾመ የሰራው ሚዛናዊነት የጎደለው ዘገባ የፍርድ ቤትን ነፃነት የሚነካ፤ ለአንድ ወገን ያዳላ፤ በእውነተኛ መረጃ ላይ መሠረት ያላደረገ፤ በፍርድ ቤት አሰራር ላይ ጣልቃ ለመግባት ያለመና በሕግ የተያዘ ጉዳይን በሚዲያ ፕሮፓጋንዳ ለማሸነፍ ያለመ መሆኑ አነጋጋሪ ሆኗል።

ሕዝብን በአሉባታ ልታደናግር ትችል ይሆናል እንጂ ውሸት ስለደጋገም እውነት አይሆንም፤ የለቅሦ ቦታ እየቀያየረሩ አብዝቶ ሰለተለቀሠ ሐቀኝነት አይረጋገጥም፤ ሌላኛው ወገን እውነትን ይዞ ሕግን አክብሮ ጉዳዩ በሀላፊነት ስሜት ስለመራ ሀቅ የለውም ማለት አይደለም፤ ከዚህ በኋላ ዱቡሻ ሚዲያ ኔትዎርክ እውነታውን በሚዛናዊነት ለሕዝባችን በተከታታይ የሚያቀርብ ይሆናል።
~ ሚያዚያ 27/2018 ዓ.ም

05/05/2026
05/05/2026
የጋሞና የአርባ ምንጭ የልማት ስኬት እና የወላይታ ኢሊቶች ሴራ !! የአርባምንጭ ከተማና የጋሞ ህዝብ የጽናት ጉዞ​በአሁኑ ወቅት በአርባምንጭ ከተማና በጋሞ ዞን እየታዩ ያሉ ግዙፍ የልማት ስራ...
15/04/2026

የጋሞና የአርባ ምንጭ የልማት ስኬት እና የወላይታ ኢሊቶች ሴራ !!

የአርባምንጭ ከተማና የጋሞ ህዝብ የጽናት ጉዞ

​በአሁኑ ወቅት በአርባምንጭ ከተማና በጋሞ ዞን እየታዩ ያሉ ግዙፍ የልማት ስራዎች የበርካታ ወገኖችን ቀልብ እየሳቡ ይገኛሉ። ሆኖም ይህ እምርታ እና ለውጥ እንቅልፍ የነሳቸው አንዳንድ የዎላይታ ኤሊቶች፣ የልማት ጉዞውን ለማደናቀፍና የጋሞን ህዝብ ከአጎራባች ህዝቦች ጋር ለማጋጨት የተጠናከረ የሴራ ስራ ውስጥ ተጠምደው ይስተዋላሉ።

​ይህ ሴራ በዋናነት ያነጣጠረው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የከተማዋን ከንቲባና የዞኑን አመራሮች ስም በማጠልሸት ላይ ይገኛሉ።

የልማት ስራዎቹን ውጤት ለማደብዘዝ እና ህዝብን ከልማት አጋሮቹ ጋር ለማጋጨት የሚነዙት አጀንዳዎች የከተማዋን ሰላምና እድገት የማይመኙ አካላት መኖራቸውን በግልጽ ያሳያል።

​በተግባር የተመለሱ የልማት ድሎች
​ሴራዎች ቢኖሩም፣ አርባምንጭ ከተማ ግን በስራ ምላሽ መስጠቷን ቀጥላለች። ከተማዋን የቱሪዝም እና የኢንቨስትመንት ማዕከል ለማድረግ የታለሙ በርካታ ፕሮጀክቶች አሁንም በከፍተኛ ፍጥነት እየተከናወኑ ይገኛሉ፦

ከተማዋን ውብ እና ለኑሮ ምቹ የሚያደርጉ የኮሪደር ልማት ስራዎች፣ ሰፊ የመንገድ ከፈታ እና የዘመናዊ መብራት ዝርጋታዎች በተሳካ ሁኔታ እየተከናወኑ ይገኛል።

​የአርባምንጭ ዓለም አቀፍ ስታዲየም፦ የደቡብ ክልልና የጋሞ ህዝብ ኩራት የሆነው የአለምአቀፍ ስታዲየም ግንባታ በከፍተኛ ርብርብ እየተሳለጠ ይገኛል።

​40/42 የቱሪዝም መንደር፦ አርባ ምንጭን የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ የተጀመረው ታላቅ መንደር ግንባታ የከተማዋን ገጽታ የቀየረ ድንቅ ስራ ነው።

​ማህበራዊ ተቋማት፦ ከጤና ተቋማት እስከ ትምህርት ቤቶች፣ እንዲሁም ግዙፍ ድልድዮች ግንባታ ድረስ ያሉ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት እያረጋገጡ ነው።

​ማንኛውም የጥፋት አጀንዳ የጋሞን ህዝብና የአርባ ምንጭን ልማት ወደኋላ ሊያስቀር አይችልም። በሴራና በወሬ የከተማዋን ከንቲባም ሆነ አመራሩን ለማዳከም የሚደረገው ጥረት፣ በተግባር በታዩ የልማት ውጤቶች ይፈርሳል። የአርባምንጭ ከተማና የጋሞ ህዝብ ሰላሙን እየጠበቀ፣ ልማቱን አጠናክሮ ይቀጥላል !!

የጽናት ተምሳሌት የሆነ መሪ !!የተከበሩ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ጥላሁን ከበደ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአዲስ መዋቅር በተቋቋመበት ወቅት ሀላፊነቱን ተረክበው በግልጽ ራዕይ፣ በጽኑ አመራር እና...
22/03/2026

የጽናት ተምሳሌት የሆነ መሪ !!

የተከበሩ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ጥላሁን ከበደ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአዲስ መዋቅር በተቋቋመበት ወቅት ሀላፊነቱን ተረክበው በግልጽ ራዕይ፣ በጽኑ አመራር እና በማይናቅ ትጋት ክልሉን ወደ ሰላም፣ ልማት እና ብልፅግና ለመመራት እየሰሩ ያሉ ተስፋ ሰጪ መሪ ናቸው።

ከተሾሙበት ጊዜ ጀምሮ ክልሉን በሁሉም ዘርፎች ለማሻሻል በታላቅ ቁርጠኝነት የተሞላ እና የሚያስደንቅ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ። ክልሉን ሲረክቡ ብዙ ችግሮችና ፈተናዎች ቢኖሩም፣ በብልሃት፣ በትዕግስት እና በጥንካሬ መሪነታቸው እያንዳንዱን ችግር በመፍታት ክልሉን ወደ ዘላቂ ሰላም እና እድገት መንገድ እየመሩ ናቸው።

አቶ ጥላሁን በፈተናዎች የተጋረጠ ክልል ውስጥ ፈተናዎችን ወደ እድል በመቀየር የህዝብ አንድነትን ማጠናከር፣ ሰላምን መጠበቅ እና ሕግና ስርዓትን ማስከበር ውስጥ ታላቅ ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ። ክልሉን ለማፍረስ የሚሞክሩ ኃይሎችን በጽናት በመታገል እና በውይይት መፍትሄ በመፈለግ ከአደጋ መጠበቅ ችለዋል።

በሰላም ዘርፍ፣ የተነሱ ግጭቶችን በመቆጣጠር ህዝቡ በመረጋጋትና በእርግጥ እንዲኖር ያስችሉ ዘላቂ የሰላም መንገዶችን አበርክተዋል። እንዲሁም ማኅበራዊ አንድነትን በማጠናከር እና የህዝብ መተማመንን በመጨመር ክልሉ የተረጋጋ የሰላም መሠረት እንዲኖረው አስተዋፅኦ አድርገዋል።

በልማት ዘርፍ ደግሞ፣ መንገዶች፣ ትምህርት፣ ጤና እና የመሠረተ ልማት ስራዎች በሰፊው እንዲከናወኑ በትጋት እየሰሩ ናቸው። ክልሉ ከነበረበት ሁኔታ ወደ ተሻለ ደረጃ መሻሻሉ የመሪነታቸው ግልፅ ምልክት ነው። ለወጣቶች የስራ እድል መፍጠር፣ ኢኮኖሚውን ማነቃቃት እና ክልሉን ወደ ብልፅግና መምራት ላይ በቀንና በሌሊት እየሰሩ ናቸው።

በቱሪዝም ዘርፍም ያለውን የተፈጥሮ ፀጋ፣ ውብ አካባቢዎች እና ባህላዊ ቅርሶች በማስተዋወቅ ወደ ክልሉ የቱሪዝም ፍሰት እንዲጨምር ታላቅ ስራ አከናውነዋል። ይህም ለክልሉ ኢኮኖሚ እድገት ብቻ ሳይሆን ለዜጎች የስራ እድል ፍጠር ውስጥ አስፈላጊ ሚና ተጫውቷል።

ከዚህ በላይ ለህዝብ ቅርብ የሆነ አመራር በመስጠት፣ ችግር ሲኖር በቦታው በመገኘት ፈጣን መፍትሄ የሚያመጡ እና የህዝቡን ድምፅ በእውነት የሚሰሙ መሆናቸው ለዜጎች ታላቅ እምነት ፈጥሯል። ይህም ያላቸውን የአገልግሎት መንፈስ እና ልዩ የመሪነት ባህሪ ያሳያል።

በአጠቃላይ፣ አቶ ጥላሁን ከበደ ክልሉን ወደ ሰላም፣ ልማት እና ብልፅግና ለመመራት በራሳቸው መስጠት የሚሰሩ ተስፋ ሰጪ እና የሚያነሳሳ መሪ ናቸው። ያደረጉትና እየሰሩት ያለው ሥራ ለቀጣይ ትውልድ የሚታሰብና የሚዘከር ታላቅ ምሳሌ ነው፤ ለሌሎች መሪዎችም አርአያ ይሆናል።

ታሳ ታሳ ጋሞ ታዴሬ 😭😭😭😭😭
13/03/2026

ታሳ ታሳ ጋሞ ታዴሬ 😭😭😭😭😭

25/02/2026

Address

Sikela
Arba Minch'

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gamo Wogga posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share