Berhanu Zewdie Zeta

Berhanu Zewdie Zeta Head of South Ethiopia Regional State Urban and Infrastructure Bureau.

 በራስ (በዞን እና በጋልማ አቅም የተገነባው እና የሚተዳደረው) ባይራ ሞዴል ት/ቤት ያስፈተናቸውን ሙሉ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርስቲ በማስገባቱ ታላቅ ደስታ ተሰምቶኛል። በወቅቱ በድፍረት ስንጀም...
26/08/2026


በራስ (በዞን እና በጋልማ አቅም የተገነባው እና የሚተዳደረው) ባይራ ሞዴል ት/ቤት ያስፈተናቸውን ሙሉ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርስቲ በማስገባቱ ታላቅ ደስታ ተሰምቶኛል። በወቅቱ በድፍረት ስንጀምር የነበራችሁ፣ በሂደቱ የተሳተፋችሁ እና ለውጤቱ የተጋችሁ የለፋችሁ ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ! የልፋት፣ የትብብርና የድፍረት ውጤት!! ይህ ተሞክሮ በሰፊው ክልላችንም ሊሰፋ ይገባል!!

🏥ሰብዓዊነት በቀይመስቀል!!
22/08/2026

🏥ሰብዓዊነት በቀይመስቀል!!

የዳሞታዋ ፀዳል፤የድምቀት አምሳል!ወ/ሶዶ
20/08/2026

የዳሞታዋ ፀዳል፤
የድምቀት አምሳል!
ወ/ሶዶ

የሻላይቱ ዲላ ከተማ ልማት፤በህብረተሰብ ተሳትፎ ፍክት!!
16/08/2026

የሻላይቱ ዲላ ከተማ ልማት፤
በህብረተሰብ ተሳትፎ ፍክት!!

 ታሪካዊው እና ታሪክ የቀጠለበት ጋርዱላ ተራራ ላይ የአንድ ጀንበር አሻራ አኑረናል። ሳላጋንነው ለመግለፅ ብዙ ልምድ የሚወሰድበት ስፍራ ነው!!
03/08/2026


ታሪካዊው እና ታሪክ የቀጠለበት ጋርዱላ ተራራ ላይ የአንድ ጀንበር አሻራ አኑረናል። ሳላጋንነው ለመግለፅ ብዙ ልምድ የሚወሰድበት ስፍራ ነው!!

01/08/2026

"አረንጓዴ ከተሞች ለነገዋ ኢትዮጵያ የማይተካ የዘላቂ ልማት መሠረቶች ናቸው"
አቶ ብርሃኑ ዘውዴ
********************************

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ እና የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አስመልክቶ መልዕክት አስተላልፈዋል።

አርባ ምንጭ ሐምሌ 25/2018 ዓ.ም (ከመልቢ)

የመልዕክቱ ሙሉ ቃል ከዚህ እንደሚከተለው ቀርቧል፤

ኢትዮጵያ የጀመረችው የአረንጓዴ አሻራ ተነሳሽነት የአካባቢ ጥበቃ ፕሮግራም ብቻ ሳይሆን ለትውልድ የሚተላለፍ የልማት፣ የኢኮኖሚ እና የአካባቢ ዘላቂነት መሠረት
​መሆኑን ገልጸዋል።

በተለይም ከከተማ ልማት አንጻር የአረንጓዴ አሻራ እንቅስቃሴ ከተሞች ውብ፣ ንጹህ፣ ተወዳዳሪ እና ለነዋሪዎቻቸው ምቹ እንዲሆኑ ወሳኝ ሚና እንደሚኖረው የገለፁት ቢሮ ሀላፊው፣ ዛፎችን መትከል ብቻ ሳይሆን መርሃ ግብሩ የአካባቢ ጥበቃን ለማጠናከር፣ የአየር ጥራትን ለማሻሻል፣ የከተሞችን ሙቀት ለመቀነስ፣ የጎርፍ አደጋን ለመከላከልና የተፈጥሮ ሀብቶችን በመጠበቅ ለመጪው ትውልድ ጤናማ አካባቢን ለመተው ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው ብለዋል።

በክልሉ እየተካሄዱ ያሉ የኮሪደር ልማት፣ የወንዝ ዳርቻ ልማት፣ የመናፈሻዎች ግንባታና ማስዋብ ሥራዎች ከብሔራዊው የአረንጓዴ አሻራ እንቅስቃሴ ጋር ተቀናጅተው እየተተገበሩ እንደሚገኙ ያነሱት አቶ ብርሃኑ ይህም ከተሞችን ውብ፣ ንጹህ እና ለነዋሪዎች ምቹ ከማድረግ ባለፈ ለቱሪዝምና ለኢንቨስትመንት ሳቢ ያደርጋቸዋል ብለዋል በመልዕክታቸው።

ነገር ግን የአረንጓዴ አሻራ ስኬት በሚተከሉት ችግኞች ብዛት ብቻ አይለካም፤ በሚጸድቁትና በሚያድጉት ዛፎች ይለካል ሲሉም አክለዋል።

በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በመሳተፋችን፣ ለአካባቢያችን ብቻ ሳይሆን ለልጆቻችንና ለመጪው ትውልድ የማይረሳ አሻራ እያኖርን ነው ያሉት ቢሮ ሀላፊው አንድ ችግኝ መትከል አንድን ዛፍ ከመትከል በላይ የሕይወት ተስፋ፣ የንጹህ አየር ዋስትና እና የዘላቂ ልማት መሠረት መጣል ነው ብለዋል።

በመሆኑም ሁሉም የክልሉ ከተሞች ነዋሪዎች፣ ተቋማት፣ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ የግሉ ዘርፍ እና የማህበረሰብ አባላት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በንቃት እንዲሳተፉ፣ የተተከሉትንም ችግኞች በአግባቡ እንዲንከባከቡ ጥሪ አቅርበዋል።

በሀገራችን የተጀመረውን የለውጥ ጉዞ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በመጪው ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም በሚከናወነው ታሪካዊ ሀገራዊ ዘመቻ በአንድ ቀን ብቻ 800 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል በታቀደው ግብ ከክልላችን 69 ሚሊዮን ላይ 9.7 ሚሊየኑ በከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ አስተባባሪነት የሚተከሉ ሲሆን ለዚህም ስኬት እውን መሆን መላው የክልላችን ከተሞች ነዋሪዎች፣ አመራሮችና ባለሙያዎች በጋራ እንዲነሱ ጥሪ አስተላልፈዋል።

ብርሃኑ ዘውዴ ዘታ
ቢሮ ኃላፊ
ሐምሌ 25/2018 ዓ.ም
አርባ ምንጭ

 #ማዘመንመረጃዎቻችን እና አገልግሎታችንን ዲጂታል በማድረግ ከቢሮው እስከ ቀበሌ የተገልጋዩን እንግልት እናስቀራለን!!
28/07/2026

#ማዘመን
መረጃዎቻችን እና አገልግሎታችንን ዲጂታል በማድረግ ከቢሮው እስከ ቀበሌ የተገልጋዩን እንግልት እናስቀራለን!!

24/07/2026
The most dedicated and devoted engineers! Deserved!
14/07/2026

The most dedicated and devoted engineers! Deserved!

10/07/2026

Address

Ethiopia
Arba Minch'
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Berhanu Zewdie Zeta posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Berhanu Zewdie Zeta:

Shortcuts

Share