Arba Minch Zuria Wereda Government Communication Affairs Office

Arba Minch Zuria Wereda Government Communication Affairs Office ArbaMinch Zuria Wereda Gov.t Communication Affairs Office
(1)

8 የእግር ኳስ ቡድኖችን ያሳተፈው የጋንታ መይጨ ክላስተር የ2018 ዓ.ም የክረምት ወራት የእግር ኳስ ውድድር ፍፃሜውን አገኘ።አርባ ምንጭ፦ ጷጉሜ 1/2018 ዓ.ም (አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ...
06/09/2026

8 የእግር ኳስ ቡድኖችን ያሳተፈው የጋንታ መይጨ ክላስተር የ2018 ዓ.ም የክረምት ወራት የእግር ኳስ ውድድር ፍፃሜውን አገኘ።

አርባ ምንጭ፦ ጷጉሜ 1/2018 ዓ.ም (አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ መንግስት ኮሙዩንኬሽን አገልግሎት)፦

በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ባህል ቱሪዝም ስፖርት ጽ/ቤት አዘጋጅነት በጋንታ መይጨ ክላስተር ስካሄድ የሰነበተው የ2018 ዓ.ም የክረምት ወራት የእግር ኳስ ውድድር ፍፃሜውን አግኝቷል።

ዛሬ በተካሄደው የፍፃሜ የእግር ኳስ ጨዋታ መይጨ አንድነት ከ ኦርዛ ድቻ ተገናኝተዋል።

በጨዋታው መይጨ አንድነት ተጋጣሚውን ኦርዛ ድቻን 6 ለ 4 በሆነ ውጤት በመለያ ምት በማሸነፍ የ2018 ዓ.ም የክረምት ወራት የእግር ኳስ ውድድር የክላስተሩ ሻምፕዮን በመሆን የዋንጫ ሽልማት አግኝቷል።

እንዲሁም በውድድሩ ሁለተኛ ሆኖ ላጠናቀቀው ኦርዛ ድቻ እና በውድድሩ ለተሳተፉ የእግር ኳስ ቡድኖች፣ ኮከብ ተጨዋቾች፣ የጨዋታ ዳኞች እና ለውድድሩ ስኬት አስተዋፅኦ ላበረከቱ ግለሰቦች የእውቅና ምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።

በመርሐ ግብሩ ላይ አቶ ሀብታሙ በየነ የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ፣ አቶ ሶፎንያስ ቲቶስ የወረዳው ባህል ቱሪዝም ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ ካሳሁን የወረዳው መንግስት ኮሙዩንኬሽን አገልግሎት ጽ/ቤት ኃላፊን ጨምሮ የቀበሌው ነዋሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

ለአርባ ምጭ ሁለገብ ስታድየም ግንባታ እየተደረገ የሚገኘው ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል።አቶ ሀብቴ ፔዣ የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ የዘይሴ ዳንቢሌ ቀበሌ ተወላጅና አሁን ላይ ነዋሪነታቸውን አሜርካ ...
06/09/2026

ለአርባ ምጭ ሁለገብ ስታድየም ግንባታ እየተደረገ የሚገኘው ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

አቶ ሀብቴ ፔዣ የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ የዘይሴ ዳንቢሌ ቀበሌ ተወላጅና አሁን ላይ ነዋሪነታቸውን አሜርካ ያደረጉት ግለሰብ የ130,000 (አንድ መቶ ሰላሣ ሺህ ብር)ገቢ አደረጉ።

አቶ ሀብቴ ፔዣ "በጋራ እንነሳ፣ በትብብር እንገንባ፣ በአንድነት እንጨርስ!" በሚል ሶስተኛ ዙር የአርባ ምንጭ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ግንባታ የ 130,000 የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል።

እርስዎስ አሻራዎን አኖሩ? የነገውን ትልቅ የጋራ ስኬታችንን ለመገንባት የእያንዳንዱ ዜጋ አስተዋጽኦ ወሳኝ ነውና የበኩልዎን ድጋፍ በማድረግ የታሪኩ አካል ይሁኑ!

​📌 የገቢ ማሰባሰቢያ ባንክ ሂሳብ ቁጥር፡
🏦 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE): 1000640532851
!

የፖሊስ ሠራዊት አመራርና አባላት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ሁለተኛ ቀን ውሎ ቀጥሎ እየተካሄደ ነው።አርባ ምንጭ፦ ጷጉሜ 1/2018 ዓ.ም (አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ መንግስት ኮሙዩንኬሽን...
06/09/2026

የፖሊስ ሠራዊት አመራርና አባላት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ሁለተኛ ቀን ውሎ ቀጥሎ እየተካሄደ ነው።

አርባ ምንጭ፦ ጷጉሜ 1/2018 ዓ.ም (አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ መንግስት ኮሙዩንኬሽን አገልግሎት)፦

በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ የ2018 ዓ.ም የፖሊስ ሠራዊት አመራርና አባላት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ሁለተኛ ቀን ውሎ ቀጥሎ እየተካሄደ ይገኛል።

የአርባ ምንጭ ዙርያ ወረዳ መሬት አስተዳደር ጽ/ቤት በ2018 ዓ.ም የላቀ አፈፃፀም በማስመዝገብ የእውቅና ምስክር ወረቀት አገኘ።አርባ ምንጭ፦ ጷጉሜ 1/2018 ዓ.ም (አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረ...
06/09/2026

የአርባ ምንጭ ዙርያ ወረዳ መሬት አስተዳደር ጽ/ቤት በ2018 ዓ.ም የላቀ አፈፃፀም በማስመዝገብ የእውቅና ምስክር ወረቀት አገኘ።

አርባ ምንጭ፦ ጷጉሜ 1/2018 ዓ.ም (አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ መንግስት ኮሙዩንኬሽን አገልግሎት)፦

የጋሞ ዞን መሬት አስተዳደር መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም ግምገማ፣ የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ፣ የዓመታዊ ጉባኤ እና የንቅናቄ አጀንዳዎችን ለመወያየት ያለመ የምክክር መድረክ ተካሂዷል ማካሄዱ ይታወቃል።

በመድረኩ የአርባ ምንጭ ዙርያ ወረዳ መሬት አስተዳደር ጽ/ቤት በ2018 ዓ.ም በዞኑ ከሚገኙ ወረዳዎች በተግባር አፈፃፀም ሁለተኛ ደረጃ በመውጣት የምስክር ወረቀት አግኝቷል።

የተበረከተውን የእውቅና የምስክር ወረቀት ወ/ሮ ምህረት ገልገሎ ከጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ደምሴ አድማሱ እጅ የተቀበሉ ሲሆን፣ ውጤቱ የአጠቃላይ የጽህፈት ቤቱ ባለሙያዎች እንዲሁም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጥረት በመሆኑ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸውን ገልፀዋል።

የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ የ2018 ዓ.ም የፖሊስ ሠራዊት አመራርና አባላት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ መካሄድ ተጀመረ።‎አርባ ምንጭ፦ ነሐሴ 30/2018 ዓ.ም (አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ...
05/09/2026

የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ የ2018 ዓ.ም የፖሊስ ሠራዊት አመራርና አባላት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ መካሄድ ተጀመረ።

‎አርባ ምንጭ፦ ነሐሴ 30/2018 ዓ.ም (አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ መንግስት ኮሙዩንኬሽን አገልግሎት)፦

የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ የ2018 ዓ.ም የፖሊስ አመራርና አባላት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

‎የፖሊስ ተቋም የህዝብን ሰላምና ደህንነት በማስጠበቅ ውስጥ የማይተካ ሚና እንዳለው አቶ ዳዊት ታደሠ የአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ በመድረኩ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ገልጸዋል።

የፖሊስ አባላት የተለያዩ ሀገራዊ ተልዕኮዎችን በስኬት እያከናወኑ እንደሚገኙ አቶ ዳዊት ጠቁመው በቀጣይም አባላቱ ከአላስፈላጊ ድርጊቶች በመቆጠብ ለህገ መንግስቱና ለህግ ታዛዥ በመሆን ሙያዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የፖሊስ ተቋም ዋና ተልዕኮ ህገ መንግስታዊ ሥርዓቱን በማክበር የወንጀልና የትራፊክ አደጋ በቅድሚያ መከላከል፣ የህዝብና የንብረት ደህንነትን ማስጠበቅ እና የህዝቡን ዘላቂ ሰላም ማስፈን መሆኑን የገለፁት ደግሞ እ/ር አዲሱ ቡዛየሁ የወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ኃላፊ ናቸው።

እ/ር አዲሱ አክለውም የፖሊስ አባላት የወንጀል መከላከል ሥራን በተለይም በቅድመ መከላከል ላይ ትኩረት በማድረግ የህዝብን እምነት ለማጠናከር በትጋት መሥራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

መድረኩን ኮ/ር ረታ ተክሉ የጋሞ ዞን ዞን ፖሊስ መምሪያ ታክትክ ምርመራ ድቪዥን ኃላፊ እና ረ/ኢ/ር ቶፍሎስ መርዕድ የዞኑ ማህበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል ዲቪዥን ኃላፊ በመምራት ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ ሂደቱም ለሁለት ተከታታይ ቀናት እንደሚቆይ እና ሁሉም ባለድርሻ አካላት በንቁ ተሳትፎ በመሳተፍ የተቋሙን የሥራ አፈፃፀም በጥንካሬና በድክመት ለይቶ በመገምገም ቀጣይ የሥራ አቅጣጫ ይቀመጣል ተብሎ ይጠበቃል።

በዘይሴ አካባቢ የተጀመረው የእርቀ ሰላም ሂደት ከግብ እንዲደርስ የማህበረሰቡ ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ​በዘይሴ አካባቢ የተፈጠረውን አለመግባባት በሰላማዊና በሰለጠነ ውይይት ለመፍታት ሁሉም ...
04/09/2026

በዘይሴ አካባቢ የተጀመረው የእርቀ ሰላም ሂደት ከግብ እንዲደርስ የማህበረሰቡ ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ

​በዘይሴ አካባቢ የተፈጠረውን አለመግባባት በሰላማዊና በሰለጠነ ውይይት ለመፍታት ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ የቀረበ ሲሆን፤ የዘይሴ ደምብሌ ቀበሌ ጋርዜታ ንዑስ ነዋሪዎችም የተጀመረው የእርቀ ሰላም ሂደት ከግብ እንዲደርስ የበኩላቸውን እንደሚወጡ ገልጸዋል።

​በአካባቢው በተከሰተው አለመረጋጋት ምክንያት ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች በዘይሴ ደምብሌ ቀበሌ ጋርዜታ ንዑስ የመጽናናትና መርሃ ግብር ተካሂዷል።

በዚህም የዘይሴ አካባቢ አባቶችና ምሁራን፣ ከጋሞ ደሬዎች፣ ከአጎራባች ጎፋ፣ ቡርጅ፣ ኮንሶና ኮሬ ዞኖች የተወጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የባህል መሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶች በተገኙበት ሀዘንተኞችንና የሟች ቤተሰቦችን አጽናንተዋል።

​በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የሀገር ሽማግሌዎች እንደገለጹት፤ በግጭቱ ምክንያት ከቀያቸው ተፈናቅለው የነበሩ ነዋሪዎች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ በማድረግ ውይይቶች መካሄዳቸው ለዘላቂ ሰላም ግንባታ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው ብለዋል።

አክለውም በጫካ የሚገኙ የአካባቢው ነዋሪዎች ትጥቃቸውን ፈትተው ወደ ቀያቸው በመመለስ ሰላማዊ ኑሮ እንዲመሩ ህብረተሰቡ የማሳመንና የመምከር ሚናውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

​የዘይሴ ብሔረሰብ ባላባት ካዎ ተወካይ ፓስተር አዲሱ ፆና በበኩላቸው፤ የአካባቢውን ሰላም ወደቀድሞው ለመመለስና የነዋሪዎችን ደህንነት ለማረጋገጥ ሁሉም ወገን በትብብር መስራት እንዳለበት ገልጸዋል።

ሰላም የሁሉም ነገር መሠረት በመሆኑ ባህላዊው የእርቅ ሂደት እንዲሳካ የጋራ ጥረት እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል።

​የአካባቢው ምሁራንም ሁሉንም የሚያግባባውን የሰላም ጉዳይ ቅድሚያ መስጠት እንደሚገባ ገልጸው፤ ታጥቀው በጫካ የሚገኙ አካላት ትጥቃቸውን በመፍታት ጥያቄዎቻቸውን በጠረጴዛ ዙሪያ በውይይት እንዲፈቱ አሳስበዋል።

​የዘይሴ ደምብሌ ቀበሌ ጋርዜታ ንዑስ ነዋሪዎች በበኩላቸው፤ ባለፉት ዓመታት በተከሰተው ግጭት ከፍተኛ ማህበራዊ ቀውስ መፈጠሩን ጠቁመው፣ አሁንም ቂምና ቁርሾን በይቅርታ በማስወገድ ለእርቀ ሰላሙ ቅድሚያ በመስጠት እንደሚተባበሩና መንግስት ከክልልና ከዞን የሀገር ሽማግሌዎችን በማሰባሰብ እያደረገ ላለው ጥረት ምስጋና አቅርበዋል።

ስሌ ሰጎ 01 ቀበሌ 3ኛ ዙር ለአርባ ምንጭ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ግንባታ ድጋፍ 2 ዘለላ ሙዝ ለስታዲየማችን የሀብት አሰባሰብ ድጋፍ አበረከቱ።አርባ ምንጭ፦ ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም (አርባ ...
04/09/2026

ስሌ ሰጎ 01 ቀበሌ 3ኛ ዙር ለአርባ ምንጭ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ግንባታ ድጋፍ 2 ዘለላ ሙዝ ለስታዲየማችን የሀብት አሰባሰብ ድጋፍ አበረከቱ።

አርባ ምንጭ፦ ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም (አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ መንግስት ኮሙዩንኬሽን አገልግሎት)፦

በጋሞ ዞን አርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ስሌ ሰጎ 01 ቀበሌ 3ኛ ዙር ለአርባ ምንጭ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ግንባታ ድጋፍ
2 ዘለላ ሙዝ ለስታዲየማችን የሀብት አሰባሰብ ድጋፍ አበርክተዋል።

የ3ኛ ዙር የሀብት አሰባሰብ ንቅናቄ የስታዲየም ግንባታው የሁሉም የጋራ ተሳትፎና ኃላፊነት መሆኑን በተግባር የሚያሳይ ሲሆን፣ስሌ ሰጎ 01 ቀበሌ ነዋሪዎችና የተለያዩ የህብረት አደረጃጀቶች ለአካባቢው ልማት ያላቸውን የተሳትፎ ፍላጎት ያሳዩበት መሆኑ ተገልጿል።

በወረዳው ለአርባ ምንጭ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ግንባታ የሀብት አሰባሰብ ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተጠቁሟል።

የሸሌ ሜላ ቀበሌ 3ኛ ዙር ለአርባ ምንጭ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ግንባታ ድጋፍ 2 ዘለላ ሙዝ ለስታዲየማችን የሀብት አሰባሰብ ድጋፍ አበረከቱ።አርባ ምንጭ፦ ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም (አርባምንጭ...
03/09/2026

የሸሌ ሜላ ቀበሌ 3ኛ ዙር ለአርባ ምንጭ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ግንባታ ድጋፍ 2 ዘለላ ሙዝ ለስታዲየማችን የሀብት አሰባሰብ ድጋፍ አበረከቱ።

አርባ ምንጭ፦ ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም (አርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ መንግስት ኮሙዩንኬሽን አገልግሎት)፦

በአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ የሸሌ ሜላ ቀበሌ 3ኛ ዙር ለአርባ ምንጭ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ግንባታ ድጋፍ 2 ዘለላ ሙዝ ለስታዲየማችን የሀብት አሰባሰብ ድጋፍ አበርክተዋል።

የ3ኛ ዙር የሀብት አሰባሰብ ንቅናቄ የስታዲየም ግንባታው የሁሉም የጋራ ተሳትፎና ኃላፊነት መሆኑን በተግባር የሚያሳይ ሲሆን፣ የሸሌ ሜላ ቀበሌ ነዋሪዎችና የተለያዩ የህብረት አደረጃጀቶች ለአካባቢው ልማት ያላቸውን የተሳትፎ ፍላጎት ያሳዩበት መሆኑ ተገልጿል።

በወረዳው ለአርባ ምንጭ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ግንባታ የሀብት አሰባሰብ ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተጠቁሟል።

የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስ እና ፕላን ልማት ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀምና የ2019 ዕቅድ ትግበራ ላይ የምክክር መድረክ አካሄደ።አርባ ምንጭ፦ ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም (...
02/09/2026

የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስ እና ፕላን ልማት ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀምና የ2019 ዕቅድ ትግበራ ላይ የምክክር መድረክ አካሄደ።

አርባ ምንጭ፦ ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም (አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ መንግስት ኮሙዩንኬሽን አገልግሎት)፦

የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስ እና ፕላን ልማት ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት ማጠቃለያ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 ዓ.ም ዕቅድ ትግበራ ዙሪያ የሚያተኩር የምክክር መድረክ አካሂዷል።

በመድረኩ የተገኙት የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ያዕቆብ ኤርምያስ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የወረዳውን የፋይናንስና ፕላን ልማት ግቦች ለማሳካት እንዲሁም የመንግሥትን ሀብት በአግባቡ ለማስተዳደር ለተከናወኑት ተግባራት ለጽሕፈት ቤቱ የሥራ ሂደት አስተባባሪዎችና ፈጻሚ ባለሙያዎች ምስጋና አቅርበዋል።

ኃላፊው አክለውም፣ የመድረኩ ዋና ዓላማ ያለፈውን ዓመት ስኬቶች ማስቀጠልና በኦዲት ግኝቶች፣ በንብረት አስተዳደር እንዲሁም በሪፖርት ጥራት ላይ የታዩ ክፍተቶችን በግልጽ ለይቶ በማረም ለአዲሱ በጀት ዓመት ስትራቴጂካዊ ዝግጅት ማድረግ መሆኑን ገልጸዋል።

የጽ/ቤቱ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ሕይወት ጮራ በበኩላቸው፣ የምክክር መድረኩ በመንግሥት ፋይናንስ እና በንብረት አስተዳደር የታዩ ድክመቶችን ለማረም ያለመ መሆኑን ጠቁመዋል።

ወ/ሮ ሕይወት አበክረውም እንደገለጹት፣ መድረኩ የፋይናንስ ቁጥጥር ሥርዓቱን በማጠናከር ሀብትን ከብክነት ለመከላከል፣ የተሰብሳቢና ተከፋይ ሂሳቦችን ሥርዓት ለማስያዝ እንዲሁም የኦዲት ግኝቶችን ለመቀነስ ያለሙ የማስተካከያ እርምጃዎች የሚወሰዱበት ነው።

በ2019 በጀት ዓመትም የበጀትና የፋይናንስ ዲሲፕሊንን በጥንቃቄ ማስጠበቅ፣ ከባለድርሻ አካላት ጋር የተቀናጀ አሠራር መዘርጋት፣ እንዲሁም አገልግሎቶችን በቴክኖሎጂ በማስደገፍ ቀልጣፋና ከሙስና የጸዳ አሠራርን ማረጋገጥ ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች መሆናቸው ተመላክቷል።

በመድረኩ የጽሕፈት ቤቱ የሥራ ሂደት አስተባባሪዎችና ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን፣ በቀረበው የሥራ አፈጻጸምና የ2019 ዕቅድ ላይ ሰፊ ውይይት ከተደረገ በኋላ የቀጣይ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ተጠናቋል።

በአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ቆላ ሸሌ ቀበሌ ለአርባ ምንጭ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ግንባታ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለፀ።አርባ ምንጭ፦ ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም (አርባ ምንጭ ዙሪያ ...
02/09/2026

በአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ቆላ ሸሌ ቀበሌ ለአርባ ምንጭ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ግንባታ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለፀ።

አርባ ምንጭ፦ ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም (አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ መንግስት ኮሙዩንኬሽን አገልግሎት)፦

ለአርባ ምንጭ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ግንባታ የሚደረገው የ3ኛ ዙር የሀብት አሰባሰብ ንቅናቄ በአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ቆላ ሸሌ ቀበሌ ሁለተኛ ዙር ህዝባዊ ተሳትፎና ንቅናቄ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገልጿል።

በዕለቱም የቀበሌው ነዋሪዎች ለስታዲየሙ ግንባታ ማጠናቀቂያ የሚሆን ሁለት አይሱዙ የጭነት መኪና የሙዝ ድጋፍ ለአስተባባሪዎቹ አስረክበዋል።

​የቀበሌው ነዋሪዎች ያደረጉት ይህ ድጋፍ ለልማት ያላቸውን ቀጥተኛ ፍላጎትና ተሳትፎ የሚያሳይ ሲሆን የ3ኛ ዙር የሀብት አሰባሰብ ንቅናቄውም የታቀደለትን ግብ ለማሳካት ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ተጠቁሟል።

Address

Arba Minch'

Telephone

+251916854517

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Arba Minch Zuria Wereda Government Communication Affairs Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share