Gamo Zone Tourism Department

Gamo Zone Tourism Department የጋሞ ዞን ባህል ታሪክ ቅርስ ቋንቋ ስነ ጥበብ ዕደ ጥበብና የተፈጥሮ መስህብ ተጠብቆ ለምቶና ተዋውቆ ለኢኮኖሚያዊ ፋይዳ እንዲውል እንሰራለን።
(1)

የጋሞ ዞን ቱሪዝም መምሪያ ማኔጅመንት አባላት የ2018 በጀት አመት ማጠቃለያ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት እና የ2019 ዓ.ም መነሻ እቅድ ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡
17/07/2026

የጋሞ ዞን ቱሪዝም መምሪያ ማኔጅመንት አባላት የ2018 በጀት አመት ማጠቃለያ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት እና የ2019 ዓ.ም መነሻ እቅድ ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡

አርባ ምንጭ በኢትዮጵያ ሁለንተናዊ የተፈጥሮና የሰው ሠራሽ ሀብቶችን አሟልታ የያዘች ልዩ ከተማ መሆኗን የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ አስታወቁ።​አርባ ምንጭ ፦ ሐምሌ 07 / 20...
14/07/2026

አርባ ምንጭ በኢትዮጵያ ሁለንተናዊ የተፈጥሮና የሰው ሠራሽ ሀብቶችን አሟልታ የያዘች ልዩ ከተማ መሆኗን የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ አስታወቁ።

​አርባ ምንጭ ፦ ሐምሌ 07 / 2018 ዓ.ም

በአርባ ምንጭ ከተማ የተገነቡ መሠረተ ልማቶችን ዕውቅና የመስጠት መርሃ ግብር በአርባምንጭ ከተማ ተካሂዷል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልልን ለመቀየር የተጀመሩ የልማት ሥራዎች ሌት ተቀን ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የገለጹት ደግሞ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ናቸው።

ርዕሰ መስተዳድሩ በአርባ ምንጭ ከተማና አካባቢው ተገንብተው ለአገልግሎት የበቁ ፕሮጀክቶች በበርካታ ፈታኝ ሁኔታዎች ውስጥ የተከናወኑ መሆናቸውን ጠቁመው፤ እነዚህ ሥራዎች የተፈጥሮ ሀብትን በአግባቡ በማልማት ረገድ "ትንሽ ሠርቶ ብዙ ማትረፍ" እንደሚቻል በተግባር ያሳዩ መሆናቸውን አብራርተዋል።

ለፕሮጀክቶቹ ስኬት በተለይም ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ለማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ የገንዘብ፣ የሰው ኃይልና የቅርብ ክትትል ድጋፍ ስላደረጉ ምስጋና አቅርበው፣ ይህ ድጋፍ ለአርባ ምንጭና ለአካባቢው ብቻ ሳይሆን ደቡብ ኢትዮጵያን በማልማት ረገድ የታየ መሆኑን ጠቅሰው "ለዚህ ሕዝብ ይህ ፕሮጀክት ያንሰዋል፣ ገና ወደፊት ብዙ እንሠራለን" ሲሉ ቁርጠኝነታቸውን ገልጸዋል።

የኢፌድሪ ማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ​ከተማዋ ከጎኗ የያዘቻቸውን ውብቶቹን አባያና ጫሞ ሐይቆች፣ አርባዎቹን ምንጮች፣ ነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክና የተፈጥሮ ደኖቿን ለአብነት ጠቅሰው ከምንም በላይ ደግሞ የጋሞን ማኅበረሰብ የፍቅርና የእንግዳ ተቀባይነት ምሳሌ ሲሉ ገልጸውታል።

ከተማዋ በቅርቡ ተመርቆ ለአገልግሎት የበቃውን የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክትን ጨምሮ በበርካታ ግዙፍ ሥራዎች ውበቷ ይበልጥ እየተገለጠ "እየሞሸረች" እንደሚገኝ የጠቀሱት ኢንጂነር ሀብታሙ፤ ከአካባቢው አልፎ ለአገር የሚተርፈውን የአርባ ምንጭና አካባቢውን የተፈጥሮ ጸጋ ይበልጥ የሚያጎሉና የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የልማት ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።

ሚኒስትሩ ይህንን ያመለከቱት በአርባ ምንጭ ከተማ ተገንብተው ለአገልግሎት ለበቁ ግዙፍ መሠረተ ልማቶች እውቅና ለመስጠት በተዘጋጀ ልዩ መርሃ ግብር ላይ በተደረገ ንግግር ነው።

​የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶክተር ደምሴ አድማሱ በበኩላቸው፣ የአርባ ምንጭና አካባቢው የተፈጥሮ ሀብት ከስምንት ዓመታት በፊት በሚገባ ሳይገለጥና ሳይለመልም መቆየቱን አስታውሰው፣ አሁን ላይ ግን ምቹ ፖሊሲዎችና ለሕዝብ ቅርብ የሆኑ መሪዎች በመገኘታቸው ይህ እምቅ ሀብት ለልማትና ለድህነት ቅነሳ እንዲውል መደረጉን አስረድተዋል።

በመሆኑም ለፌደራል፣ ለክልል እና በየደረጃው ለሚገኙ ባለሀብቶች የተሰጠው እውቅና ተገቢና የሚጠበቅ መሆኑን ዶክተር ደምሴ አመልክተዋል።

የአርባ ምንጭ ከተማ ከንቲባ ዶክተር መስፍን መንዛ በበኩላቸው ለመሠረተ ልማቶቹ የተሰጠው እውቅና በቀጣይ ይበልቱኑ ለመሥራት ትልቅ መነሳሳትን የሚፈጥር መሆኑን ሲገልጹ፣ በሽልማት መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙ የሀገር ሽማግሌዎች ደግሞ በከተማው ተገንብተው ለአገልግሎት የበቁ መሠረተ ልማቶች አርባ ምንጭን የቀየሩ ብቻ ሳይሆኑ ወጣቶች ሌት ተቀን በሥራ ላይ እንዲበራከቱና ከተማዋ እንድትነቃቃ ትልቅ አስተዋጽኦ ማድረጉን በደስታ ገልጸዋል።

የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ የጋሞ ሁዱጋ ባህላዊ የክብር ማዕረግ ተሰጣቸው አርባምንጭ፣ ሐምሌ 07/2018 ዓ/ም የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ በጋሞ ማህበረሰብ ዘን...
14/07/2026

የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ የጋሞ ሁዱጋ ባህላዊ የክብር ማዕረግ ተሰጣቸው

አርባምንጭ፣ ሐምሌ 07/2018 ዓ/ም

የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ በጋሞ ማህበረሰብ ዘንድ ባህላዊ የክብር ማዕረግ የሆነው የሁዱጋ ማዕረግ ተሰጣቸው።

ሚኒስትሩ የክብር ማዕረጉ የተሰጣቸው በአርባ ምንጭ ከተማ የተገባውን የገበታ ለትውልድን ጨምሮ በርካታ መሠረተ ልማቶች እውቅና ለመስጠት ዛሬ በአርባ ምንጭ ከተማ በተዘጋጀው መርሀ ግብር ነው።

ሚኒስትሩ ከባህላዊ ማዕረግ በተጨማሪ ከጋሞ ማህበረሰብ የፈረስ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
ለሚኒስትሩ ሽልማቱን ያበረከቱት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ፣የአርባ ምንጭ ከተማ ከንቲባ ዶክተር መስፍን መንዛ፣ የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶክተር ደምሴ አድማሱ፣ ፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ሌሎችም ናቸው።

ሽልማቱን የሰጡት አመራሮቹና የሀገር ሽማግሌዎች በተለይ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ ለሚኒስትሩና ለፕሮጀክቱ ስኬት አስተዋጽኦ ላበረከቱት አስተዋጽኦ አመስግነዋል።

የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ኢኒሼቲቭ ''የገበታ ለትውልድ'' አካል የሆነው የአርባ ምንጭ ኮንፈረንስ ሪዞርት ግንባታ እንዲጠናቀቅ ለተደረገው አስተዋጽኦ የምስጋና እና ዕውቅና...
14/07/2026

የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ኢኒሼቲቭ ''የገበታ ለትውልድ'' አካል የሆነው የአርባ ምንጭ ኮንፈረንስ ሪዞርት ግንባታ እንዲጠናቀቅ ለተደረገው አስተዋጽኦ የምስጋና እና ዕውቅና መርሃ ግብር እየተካሄደ ይገኛል

አርባምንጭ፣ሀምሌ 7/2018
የገበታ ለትውልድ አካል የሆነው የአርባምንጭ ኮንፍረንስ ሪዞርት በባለፈው ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር )በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።

ይህ ፕሮጀክት እውን እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋፅኦ ለነበራቸው አካላት የእውቅናና የምስጋና መርሃ ግብር ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በተገኙበት በአርባምንጭ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
ይህ ዘመናዊ ሪዞርት ከ1 ሺህ 300 በላይ ሰዎችን ማስተናገድ የሚችል ሰፊ የስብሰባ አዳራሽ እና በሐይቅ ላይ የተገነባ ልዩ ተንሳፋፊ ሬስቶራንትን በውስጡ ያካተተ ነው።

ፕሮጀክት የኮንፈረንስ ቱሪዝምን በማስፋፋት ኢትዮጵያን የዓለም አቀፍ መድረኮች ማዕከል የማድረግ ርዕይን በከፍተኛ ደረጃ የሚያጠናክር ከመሆኑ ባሻገር ለአካባቢው ማኅበረሰብ ሰፊ የሥራ ዕድል መፍጠር ችሏል።

በመርሃግብሩ የማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስትር ሚኒስቴር ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ፣ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ፣የአርባምንጭ ከተማ ከንቲባ ዶ/ር መስፍን መንዛ፣የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ደምስ አድማሱ ፣ የክልል፣ የዞን፣ የከተማ የመንግስትና የፓርቲ የሥራ ኃላፊዎች፣የጋሞ ሀገር ሽማግሌዎች፣መንግስት ሠራተኞች፣ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
አርባምንጭ ከተማ መ/ኮሚዩኒኬሽን

የጋሞ ዞን ቱሪዝም መምሪያ የግንቦት ወር ክንውን አፈጻጸም እና በቀጣይ አንድ ወር ዕቅድ ዙሪያ  ከማኔጅመንት አባለት ጋር ውይይት አካሂዷል።ግንቦት 28/2018 ዓ.ም
05/06/2026

የጋሞ ዞን ቱሪዝም መምሪያ የግንቦት ወር ክንውን አፈጻጸም እና በቀጣይ አንድ ወር ዕቅድ ዙሪያ ከማኔጅመንት አባለት ጋር ውይይት አካሂዷል።

ግንቦት 28/2018 ዓ.ም

የጋሞ ልማት ማህበር አባያ ሐይቅን በሙሉ አቅም ለቱሪዝም አገልግሎት ለማዋል በትኩረት እየሰራ መሆኑን አስታወቀ።ግንቦት 21/2018 ዓ.ምየደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እና የጋሞ ል...
29/05/2026

የጋሞ ልማት ማህበር አባያ ሐይቅን በሙሉ አቅም ለቱሪዝም አገልግሎት ለማዋል በትኩረት እየሰራ መሆኑን አስታወቀ።

ግንቦት 21/2018 ዓ.ም

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እና የጋሞ ልማት ማህበር ሥራ አመራር ቦርድ አባል አቶ ጥላሁን ከበደ፣ የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የማህበሩ ሥራ አመራር ምክትል ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ደምሴ አድማሱ፣ የጋሞ ልማት ማህበር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ኢ/ር ማንደፍሮት ዱባለ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች በቱሪዝም ልማትና አገልግሎት ድርጅት ስር የሚገኙ አርባምንጭ አዞ ራንች፣ አባያ ሐይቅ ላይ በሚገኘው የሞጨ ደሴት እና በነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ የስራ ጉብኝት አድርገዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እና የጋሞ ልማት ማህበር ሥራ አመራር ቦርድ አባል አቶ ጥላሁን ከበደ፣ መንግሥት ለቱሪዝም ዘርፍ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልፀው በክልሉ ውስጥ እስካሁን ጥቅም ላይ ያልዋሉ የቱሪዝም አቅሞችን ወደ ስራ በማስገባት ላይ እንገኛለን ብለዋል::

የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የማህበሩ ሥራ አመራር ምክትል ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ደምሴ አድማሱ፣ ዞኑ የበርካታ ባህላዊ ፣ ታሪካዊ እና ተፈጥሯዊ ባለቤት እንደሆነ አብራርተዋል:: ይህንን ሀብት ወደ ኢኮኖሚ ለመቀየር መስህቦችን የመለየት እና የማልማት ስራ የተጀመረ ሲሆን ከእነዚህ መካከል የአባያ ሀይቅና በዙሪያው ያሉ የቱሪስት መስህቦች ቀዳሚዎቹ እንደሆነ ገልፀዋል::

የጋሞ ልማት ማህበር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ኢ/ር ማንደፍሮት ዱባለ እንደገለጹት፤ ማህበሩ ትኩረት ካደረገባቸው ዋና ዋና ዘርፎች አንዱ ቱሪዝም በመሆኑ በተቋሙ ስር የቱሪዝም ልማትና አገልግሎት ተቋቁሞ በርካታ ሥራዎችን እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

በዚህም መሰረት የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት ውስጥ የአርባምንጭ አዞ ራንችን በማዘመን ከጉብኝት ባለፈ
የዱር እንስሳትን ከተፈጥሮ መኖሪያቸው ውጪ በሰው ሰራሽ መንገድ በተዘጋጀ አስተማማኝ ስፍራ ውስጥ በመንከባከብ፣ ለህዝብ እይታ፣ ለትምህርት፣ ለምርምር እና ለዝርያ ጥበቃ ክፊት (Wild Life Zoo) ያደረገ ሲሆን ጥራት ያለው የመስተንግዶ አቅርቦትንም በማሟላት የቱሪስቶችን ቆይታ ማራዘም መቻሉን ዋና ሥራ አስፈፃሚው ገልጸዋል።

ዶ/ር ኢ/ር ማንደፍሮት በአባያ ሐይቅ ላይ የሚገኘውን ውብ የሞጨ ደሴትን ለመጎብኘት የሚያስችል ዘመናዊ የጀልባ ትራንስፖርት አገልግሎት ሁልጊዜ እየሰጠ ይገኛል ብለዋል።

በጋሞ ዞን የሚገኘውን ታዋቂውን የ 40-42 ደረጃ፣ አባያ ሀይቅ እና አርባምንጮችንጽ፣ ማዜ ብሄራዊ ፓርክ ጉጌ ተራራን ጨምሮ የዞኑን የቱሪዝም አቅም ለዓለም ለማስተዋወቅ ሰፊ ስራ እየተሰራ መሆኑን የቱሪዝም ልማትና አገልግሎት ድርጅት ሥራ አስኪያጅ አቶ ደጉ ደሳለኝ ተናግረዋል ።

የክልሉና የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች የተፈጥሮን ውበት፣ ባህልንና ታሪክን በአንድ ላይ አጣምሮ የያዘውን ይህንን አስደናቂ የጋሞ ዞን የቱሪዝም አቅም ሁሉም ኢትዮጵያውያንና አለም አቀፍ ጎብኚዎች መጥተው እንዲጎበኙና የተፈጥሮን እውነተኛ ገጸ-በረከት እንዲካፈሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

#ጋልማ

የጋሞ ዞን ቱሪዝም መምሪያ የኤች አይቪ ኤድስ ሚንስትሪሚንግ ውይይት አካሄደግንቦት 21/2018 ዓ/ምመምሪያው የ2018 ዓ/ም 4ኛ ሩብ ዓመት የኤች አይቪ ኤድስ ሚንስትሪሚንግ ውይይት አካሂዷል...
29/05/2026

የጋሞ ዞን ቱሪዝም መምሪያ የኤች አይቪ ኤድስ ሚንስትሪሚንግ ውይይት አካሄደ

ግንቦት 21/2018 ዓ/ም

መምሪያው የ2018 ዓ/ም 4ኛ ሩብ ዓመት የኤች አይቪ ኤድስ ሚንስትሪሚንግ ውይይት አካሂዷል ።

የጋሞ "ዱቡሻ" እና "ዱቡሻ ዎጋ" የሰላምና የአብሮነት እሴትን በዩኔስኮ ለማስመዝገብ የተደረገው ሂደት የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ መድረሱ ተገለጸ​አርባ ምንጭ፦ ግንቦት 12/2018 ዓ.ም (ጋሞ ዞ...
20/05/2026

የጋሞ "ዱቡሻ" እና "ዱቡሻ ዎጋ" የሰላምና የአብሮነት እሴትን በዩኔስኮ ለማስመዝገብ የተደረገው ሂደት የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ መድረሱ ተገለጸ

​አርባ ምንጭ፦ ግንቦት 12/2018 ዓ.ም (ጋሞ ዞን ቱሪዝም መምሪያ)

​የጋሞ ብሔረሰብ መገለጫ የሆነውን የጋሞ "ዱቡሻ" እና "ዱቡሻ ዎጋ" (የዱቡሻ ሥርዓት) የማይዳሰስ ቅርስ አድርጎ በዩኔስኮ (UNESCO) ለማስመዝገብ የተካሄደው ታሪካዊ ሂደት አሁን ላይ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ መድረሱ ተገለፀ ።

ይህ የተገለጸው ቅርሱን ለማስመዝገብ የተካሄደውን ጥናት አስመልክቶ በአርባ ምንጭ ከተማ በተካሄደ የውይይት መድረክ ላይ ሲሆን፤ በመድረኩ የፌደራል፣ የክልልና የዞን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የአገር ሽማግሌዎችና ባለሙያዎች በተገኙበት የጋሞ አባቶች ይህንን ታላቅ የሰላም እሴት ጠብቀው ለትውልድ ማሻገራቸው በከፍተኛ ደረጃ ተወድሷል።

​የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በመድረኩ ላይ እንደገለጹት የጋሞ ዱቡሻ ከጋሞ አልፎ ለኢትዮጵያም ሆነ ለዓለም ትልቅ መማሪያ የሚሆን የሰው ልጅ ድንቅ ወካይ ቅርስ ነው።

የዱቡሻ ዎጋ የጋሞ ሕዝብ መገለጫ የሆነ ታላቅ ባህላዊ ቅርስ ከመሆኑም በላይ የሀገሪቱን መልካም ገጽታ ለመገንባት ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ያመለከቱት ዋና ዳይሬክተሩ፤ ቅርሱን በዩኔስኮ ለማስመዝገብ ቢያንስ አምስት መመዘኛዎችን ማሟላት የሚጠይቅ ቢሆንም የጋሞ ዱቡሻ ግን አምስቱንም መስፈርቶች ሙሉ በሙሉ የሚያሟላ መሆኑን አረጋግጠዋል።

አሁን ላይ የተጀመረው ሂደት የመጨረሻውና ወሳኙ ምዕራፍ ላይ የደረሰ በመሆኑ፣ ሂደቱ ሙሉ በሙሉ ስኬታማ እንዲሆን የጋራ ትብብርና ትዕግሥት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።

​የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ደምሴ አድማሱ በበኩላቸው የጋሞ አባቶች ይህንን ታላቅ ባህልና የሰላም እሴት ሳይበረዝ ጠብቀው ከትውልድ ወደ ትውልድ በማስተላለፋቸው ልባዊ ምስጋና አቅርበው፣ ለዚህ ጥናት መሳካትና ሂደቱ አሁን ለደረሰበት የመጨረሻ ምዕራፍ ታላቅ አበርክቶ ላደረጉት የቅርስ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤትና ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዕውቅና ሰጥተዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ወይኒቱ መልኩ ቅርሱን ለዓለም ለማስተዋወቅና ይፋዊ ዕውቅና እንዲያገኝ የሚደረገውን የተደራጀ ጥናት በማድነቅ፣ የክልሉ መንግሥት ለሂደቱ ፍጻሜ ማማር አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርግ ገልጸው ቅርሱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከተመዘገበ በኋላም ማኅበረሰቡ ይበልጥ በትኩረት ሊጠብቀውና ሊንከባከበው እንደሚገባ አሳስበዋል።

​የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ትብብር ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ተክሉ ወጋየሁ የጥናት ሂደቱ እጅግ ሰፊ፣ ጥልቅና መሠረታዊ ክዋኔዎችን ያካተተ እንደነበር ጠቁመው፣ ጥናቱ ተጠናቆ አሁን ለደረሰበት አስተማማኝና የመጨረሻ የዕውቅና ምዕራፍ በመብቃቱ የተሰማቸውን ከፍተኛ ደስታ ገልጸዋል።

​የመድረኩ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ዱቡሻ ጋሞን የሰላም፣ የአብሮነት፣ የትዕግሥትና የትብብር ተምሳሌት አድርጎ ያቆመ እሴት መሆኑን ያብራሩ ሲሆን፣ የወረደው ጥናት መሬት ላይ ያለውን እውነታ በትክክል ያንጸባረቀ፣ ሙያዊ ብቃት የተሞላበትና ሥርዓቱን ሙሉ በሙሉ ያካተተ መሆኑን መስክረዋል።

አክለውም ወጣቱ ትውልድ ይህንን የሰላምና የእርቅ እንቁ ባህል በአግባቡ ተረድቶ ማስቀጠልና የመጠበቅ ኃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

​በማጠቃለያውም፣ ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የምርምር ቡድንና በዚህ ታሪካዊ ዘርፍ ላይ የተሳተፉ አካላት ሁሉ ላሳዩት ከፍተኛ ቁርጠኝነት ምስጋና የቀረበ ሲሆን፣ በዘርፉ ላይ የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላትም የዕውቅና አሰጣጥ ሥነ-ሥርዓት ተከናውኗል።

# ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን

የዱቡሻ ዎጋን በዩኔስኮ ለማስመዝገብ የሚያስችሉ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ገለጸ ግንቦት 12/2018 ዓ.ም የዱቡሻ ዎጋን በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ ሳይንስና...
20/05/2026

የዱቡሻ ዎጋን በዩኔስኮ ለማስመዝገብ የሚያስችሉ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ገለጸ

ግንቦት 12/2018 ዓ.ም

የዱቡሻ ዎጋን በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የሰው ልጅ የማይዳሰሱ ባህላዊ ቅርሶች ወካይ ዝርዝር ውስጥ ለማስመዝገብ የሚያስችሉ የቅድመ-ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸውን የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን አስታወቀ።

​በመድረኩ መልዕክት ያስተላለፉት የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባ አያሌው የዱቡሻ ዎጋ የጋሞ ሕዝብ መገለጫ የሆነ ታላቅ ባህላዊ ቅርስ ከመሆኑም በላይ የሀገሪቱን መልካም ገጽታ ለመገንባት ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ገልጸዋል።

ቅርሱ ይበልጥ ተጠንቶ በዓለም አቀፍ ደረጃ መመዝገቡ የቅርሱ ባለቤት የሆነው ወጣቱ ትውልድ እሴቶቹን ጠብቆ እንዲያስተላልፍና ለቅርሱ ልዩ ጥበቃ ለማድረግ እንደሚያስችልም አስገንዝበዋል።

ረዳት ፕሮፌሰር አበባ አክለውም የዱቡሻ ዎጋ ለዓለም አቀፍ ምዝገባ ተመራጭ ሊሆን የቻለው ሰላምን፣ ፍቅርንና ይቅርታን በጉልህ የሚሰብክ በመሆኑና ለዓለም ማኅበረሰብም ትልቅ መማሪያ ሊሆን ስለሚችል መሆኑን ጠቅሰዋል።

ቅርሱ ሁሉን አቀፍና የራሱ የሆኑ ልዩ ልዩ ክውኔዎች ያሉት መሆኑን ያብራሩት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ፤ ማኅበረሰቡ ያለ ምንም ቂምና በቀል ግጭቶችን በውይይት ለመፍታትና ሰላሙን በዘላቂነት ለማስጠበቅ የሚጠቀምበት በመሆኑ በወካይ ቅርስነት እንዲመዘገብ የተመረጠበት ዋና ምክንያት መሆኑን አስረድተዋል።

ይህን ታላቅና ሰላም-አውራጅ የሆነ ባህላዊ ቅርስ በዩኔስኮ ለማስመዝገብ የሚያስችሉ የቅድመ-ዝግጅት ሂደቶችና የአራቱዮሽ ስምምነቶች ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ተጠናክረው መቀጠላቸውን የገለጹት ረዳት ፕሮፌሰር አበባ፤ ሂደቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ የምዝገባ ሂደቱ ስኬታማ እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ሁሉ የላቀ ምስጋና አቅርበዋል።

​የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ደምሴ አድማሱ (ዶ/ር) በበኩላቸው የጋሞ ዞን በርካታ ተፈጥሮአዊ እና ሰው ሰራሽ ቅርሶች ባለቤት መሆኑን ጠቅሰው እነዚህን ቅርሶች ከመጠበቅና ከመንከባከብ አንፃር ሰፊ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

የጋሞ ዱቡሻ ዎጋ በርካታ ማህበራዊና ስነ-ልቦናዊ ትስስርን እንዲሁም የባህልን ቀጣይነት የሚያበስር እንዲሆን በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ዋና አስተዳዳሪው፤ የዛሬው መድረክም ቅርሱን ለማስመዝገብ በሚደረገው ጥረት የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ መደረሱን የሚያሳይ ነው ብለዋል።

የቅርሱ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ማግኘት የባህል ጥበቃን ከማበረታታትና ወጣቶች ባህላቸውን እንዲያውቁ ከማድረግ ባለፈ ዘርፈ-ብዙ ጥቅም እንዳለው ያመለከቱት ዶ/ር ደምሴ ለዚህ ስኬት አስተዋጽኦ ላበረከቱት ለኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን፣ ለአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም ለክልሉ ባህል ቢሮ ላደረጉት ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

​የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ወይኒቱ መልኩ በበኩላቸው ክልሉ በተፈጥሮ ፀጋ የታደለ፣ የ32 ብሔረሰቦች ባለቤትና ለየት ባሉ ባህላዊ እሴቶች የሚታወቅ መሆኑን አውስተው፣ ቢሮው እነዚህ ውድ ቅርሶች በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲመዘገቡ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት እየተወጣ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

የጋሞ ዱቡሻ ዎጋን በዩኔስኮ ወካይ የሰው ልጆች የማይዳሰስ ባህላዊ ቅርስነት ለማስመዝገብ በሚደረገው ጥረት ውስጥ አስተዋጽኦና ድጋፍ ላደረጉ አካላት ሁሉ ኃላፊዋ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ሲል የጋሞ ዞን መ/ኮሚዩኒኬሽን ዘግቧል።

የጋሞ ዱቡሻ ወጋን በዩኔስኮ ለማስመዝገብ የተከናወኑ ተግባራትን የሚገመግም የቫሊዴሽን መድረክ በአርባ ምንጭ እየተካሄደ ነውአርባምንጭ፦ ግንቦት 12/2018ዓ.ም (ጋሞ ዞን ቱሪዝም መምሪያ )የ...
20/05/2026

የጋሞ ዱቡሻ ወጋን በዩኔስኮ ለማስመዝገብ የተከናወኑ ተግባራትን የሚገመግም የቫሊዴሽን መድረክ በአርባ ምንጭ እየተካሄደ ነው

አርባምንጭ፦ ግንቦት 12/2018ዓ.ም (ጋሞ ዞን ቱሪዝም መምሪያ )

የጋሞ ዱቡሻ ወጋን በዩኔስኮ ለማስመዝገብ የሚደረገው ሂደት ተጠናቆ ለሚመለከተው አካል ለመላክ የሚያስችሉ ተግባራትን የምገግም የቫሊዴሽን መድረክ በአርባምንጭ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል ።

በመድረኩ ከፌደራል፣ ከክልልና ከዞን የተወጣጡ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም የሀገር ሽማግሌዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ ።

Address

SNNPR
Arba Mintch

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00

Telephone

+251468810004

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gamo Zone Tourism Department posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Gamo Zone Tourism Department:

Shortcuts

Share