Bureau of Urban and Infrastructure/South Ethiopia

Bureau of Urban and Infrastructure/South Ethiopia Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Bureau of Urban and Infrastructure/South Ethiopia, Government Organization, Arba Mintch.
(1)

03/09/2026
የከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ሀላፊ ክቡር አቶ ብርሃኑ ዘውዴ ከወላይታ ዞን አስተዳደር የቀረበላቸውን የ "ጊፋታ " በዓል ጥሪ ተቀበሉ ​ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም (ከመልቢ)​የደቡብ ኢትዮጵያ ክ...
02/09/2026

የከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ሀላፊ ክቡር አቶ ብርሃኑ ዘውዴ ከወላይታ ዞን አስተዳደር የቀረበላቸውን የ "ጊፋታ " በዓል ጥሪ ተቀበሉ

​ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም (ከመልቢ)

​የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ሀላፊ ክቡር አቶ ብርሃኑ ዘውዴ ከወላይታ ዞን አስተዳደር የተላከውን የወላይታ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ "ጊፋታ " ክብረ በዓል የጥሪ ደብዳቤ በቢሮአቸው ተቀብለዋል።

የ​"ጊፋታ " በዓል መስከረም 10 /2018 ዓ.ም በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ በልዩ ልዩ ኩነቶች በድምቀት ይከበራል።

"ከተሞችን ዲጂታላይዝ በማድረግ የብልጽግና ማሳያ እንዲሆኑ  ለማድረግ ሁሉም የሚጠበቅበትን ሊወጣ ይገባል።"አቶ ብርሃኑ ዘውዴነሐሴ 26/2018 ዓ/ም በሌ አዋሳ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎትን ማዘ...
01/09/2026

"ከተሞችን ዲጂታላይዝ በማድረግ የብልጽግና ማሳያ እንዲሆኑ ለማድረግ ሁሉም የሚጠበቅበትን ሊወጣ ይገባል።"አቶ ብርሃኑ ዘውዴ

ነሐሴ 26/2018 ዓ/ም

በሌ አዋሳ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎትን ማዘመን/ ዲጂታላይዜሽን ሥራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው።

በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የደቡብ ኢትዮጵያ ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ እንደተናገሩት ከተሞች ዘመናዊ፣ ምቹ እና የተቀላጠፈ አገልግሎት የሚሰጥባቸው ማዕከላት ናቸው።

አቶ ብርሃኑ አክለውም በከተሞች ኅብረተሰቡን በማሳተፍ በርካታ ለውጦች እየተመዘገቡ መሆናቸዉን ገልጸዋል።

ከተሞች የብልጽግና ማሳያ እንዲሆኑ የኛ የሁላችንም ጥረት ይጠይቃል ሲሉ ተናግረው የሚመጣውን የከተሞችን ዕድገት የዋጀ አሠራር መከተል ያስፈልጋል ብለዋል።

ኅብረተሰቡ ማዘጋጃን ከሚያማርርበት ወጥቶ በአገልግሎቱ የሚረካበት ምዕራፍ ለመድረስ እየተሠራ ያለዉ ስራ አመርቂ ዉጤት እየተመዘገበ ይገኛል ብለዋል።

የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ረ/ፕሮፈሰር ሳሙኤል ተሰማ ማዘጋጃን በማዘመን የማህበረሰባችንን እርካታ ለማሳደግ ይሠራል በማለት ህዝቡ ከመንግሥት ጋር ያለውን ቁርጠኝት እና ተባባሪነትንም ያሳድግልናል ብለዋል።

ማዘጋጃ ቤትን ማዘመን የከተማውን ገቢ በአግባቡ ለመቆጣጠር ጭምር የሚያግዝ በመሆኑ ለገቢ ማደግ ትልቅ ሚና የሚጫወት ነዉ ብለዋል።

አኮለዉም ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ ለነዋሪዎች ምቹ የሆኑ ስማርት እና ዲጂታል ከተሞችን ለመፍጠር ሁሉም ርብርብ ሊያደርግ ይገባል ብለዋል።

መሬትን እና ገቢን ከእጅ ንኪኪ ነፃ በሆነ መልኩ በማቅረብ ረጅም ጊዜ ሲወስድ የነበረውን በአጭር ጊዜ በመፈጸም አገልግሎትን ቀልጣፋ ለማድረግ ማዘመን ወሳኝ እንደሆነ ተናግረዋል።

አገልግሎቱን ተቀብሎ ቶሎ ውጤታማ ማድረግ ከተሞችን በሙሉ ዲጂታላይዝ ማድረግ የሁሉም ኃላፊነት እንደሆነ አንስተው ተግባሩን በመቶ ቀን ዕቅድ ውስጥ በማካተት መሥራት ያስፈልጋል።

የወላይታ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ እና የከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ተስፋሁን ታዴዎስ በተለመደው አሠራር ከተሞችን ማዘመን አይቻልም ሲሉ ተናግረው ከተሞች የብልጽግና ተምሳሌት እንዲሆኑ አገልግሎት አቅርቦት መዘመን እንዳለበት ተናግረዋል።

በዞኑ ያሉ ከተሞች ዲጂታላይዝ ተደርገው ኅብረተሰቡ በከተሞች አገልግሎት የረኩ እንዲሆን መሥራት ከሁሉም ይጠበቃል ብለዋል።

የበሌ አዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ዶ/ር አባይነህ አጫ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት አሰጣጥ ዲጂታላይዝ ማድረግ መቻሉ የተቀላጠፈ አገልግሎት ለህብረተሰቡ ለመስጠት የሚያግዝ ነው ብለዋል።

‎እንዲሁም ዘመናዊ አሰራር በመዘርጋት የከተማውን ዕድገት በማፋጠን ከተማው የሚጠበቅበትን የመሪነት ሚና እንዲጫወት የሚያችል መሆኑንም ገልጿል፡፡

‎የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት አሰጣጥ ማዘመን የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ከመቅረፍ ባለፈ የከተሞች ተወዳዳሪነትንና ተመራጭነትን በማስፋት ቀጣይነት ያለው ዕድገት ለማስመዝገብ ሚናው የጎላ እንደሆነም ጠቁሟል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ በአዲሱ የአደጋ ጊዜ ደንብ ላይ ተወያየነሐሴ 25/2018 ዓ.ም (ከመልቢ)​የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ አመራሮችና ሠራ...
31/08/2026

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ በአዲሱ የአደጋ ጊዜ ደንብ ላይ ተወያየ

ነሐሴ 25/2018 ዓ.ም (ከመልቢ)

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ አመራሮችና ሠራተኞች በክልሉ መንግስት በጸደቀው የአደጋ ጊዜ ዝግጁነት፣ ምላሽና መልሶ ማቋቋሚያ ፈንድ አሰራርና አደረጃጀት ደንብ ቁጥር 112/2018 ላይ የምክክር ውይይት አካሂደዋል።

በውይይቱ ወቅት የደንቡ ዋና ዋና ዓላማዎችና አሰራሮች ቀርበው ሰፊ ግንዛቤ የተፈጠረ ሲሆን፣ አደጋዎች ከመከሰታቸው በፊት የሚደረጉ ቅድመ ዝግጅቶችን ማጠናከርና ድገት አደጋ ሲያጋጥም ፈጣን ምላሽ የመስጠት አቅምን ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተመክሯል።

በተጨማሪም ቢሮው ከመሠረተ ልማት ዝርጋታና ከከተሞች እድገት አንጻር የአደጋ ስጋቶችን የመቀነስና መልሶ የማቋቋም ድርሻውን በተመለከተ ሰፊ ሀሳብ ተለዋውጠዋል።

የአስተዳደር ዘርፍ ሀላፊና ምክትል ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ቱፋኔ ቱራ በወቅቱ እንደተናገሩት ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄዎች በማምጣት እንደዚህ አይነት ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ችግሮችን በጋራ በመቆም በመደጋገፍ ማለፍ መቻል ባህል በማድረግ ከጠባቂነት በመላቀቅ ራዕያችንን እውን ልናደርግ እይደሚገባ ገልጸው የድጋፍ አግባቡም እንደ ችግሩ ዘላቂነት ጊዜን መነሻ ያደረገ እንደሚሆንም ገልጸዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎቹ በበኩላቸው የጉዳዩን አንገብጋቢት በመረዳት ሀሳባቸውን በሰፊው በመግለፅ ወደ ተግባር ለመተርጎምና በሚደረገው ድጋፍ ከደመወዝ እንዲቆረጥ በመወሰን አጋርነታቸውን አሳይተዋል።

29/08/2026

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔትና ሥራ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት ማሳደጉ ተገለፀ

28/08/2026
የከተማ ልማታዊ ሴፍትኔት በከተሞች የድህነት ቅነሳ ስራ ላይ ጉልህ ሚና እየተወጣ ነው - አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር)ነሐሴ 22/2018 ዓ.ም (ከመልቢ)የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔትና ሥራ ፕሮግራም የ...
28/08/2026

የከተማ ልማታዊ ሴፍትኔት በከተሞች የድህነት ቅነሳ ስራ ላይ ጉልህ ሚና እየተወጣ ነው - አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር)

ነሐሴ 22/2018 ዓ.ም (ከመልቢ)

የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔትና ሥራ ፕሮግራም የነዋሪዎችን የኑሮ ደረጃ ከማሻሻል ባሻገር፣ ከተሞችን የኢኮኖሚ ዕድገትና የሀብት ፈጠራ ማዕከላት ለማድረግ የሚያስችል ትልቅ አቅም እንዳለው የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አበባየሁ ታደሰ(ዶ/ር) ተናግረዋል።

የክልሉ የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔትና ሥራ ፕሮጀክት የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸምና የ2019 ዕቅድ ዝግጅት በስትሪንግ ኮሚቴ ተገምግሟል።

በግምገማ መድረኩ ላይ የተገኙት ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ እንዲሁም የፕሮጀክቱ ስቲሪንግ ኮሚቴ ሰብሳቢ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ በ2019 በጀት ዓመት ከ98,800 በላይ ዜጎችን የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዷል ብለዋል።

በከተሞች የሚታየውን ከፍተኛ የድህነት መጠን ለመቀነስ የፕሮግራሙን ግቦች በቅርበት መከታተልና መሬት ማውረድ እንደሚገባ ያሳሰቡት ም/ርዕሰ መስተዳደሩ፤ ተጠቃሚዎቹ በተለያዩ ተቋማት በሚያደርጉት የሥራ ላይ ልምምድ አማካኝነት ለ95 በመቶ ያህሉ ቋሚ የሥራ ዕድል እንደሚፈጠርላቸው አስታውቀዋል።

የተያዙትን ግቦች ስኬታማ ለማድረግ ተግባራቱን በቀናት፣ በወራትና በየሩብ ዓመቱ ከፋፍሎ መምራት እንደሚገባ ያሳሰቡት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ፤ የሴፍቲኔት ተጠቃሚዎችን የገቢ አቅም ለማሳደግ በቂ የክህሎት ሥልጠና መስጠት አስፈላጊ መሆኑን አስምረውበታል።

የክልሉ ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ በበኩላቸው በፕሮጀክቱ ተጠቃሚ ዜጎች የኑሮ ሁኔታን ለማሻሻልና ዘላቂ የከተማ ልማትን ለማረጋገጥ በትኩረት መሥራት እንደሚገባ ገልጸው የልማታዊ ሴፍቲኔት ሥራው የተጠቃሚዎችን ኑሮ ከመደገፍ ባለፈ፣ የሥራ ዕድል ፈጠራን፣ የገቢ ማስገኛ አቅምንና የማህበረሰብ ተሳትፎን በማጠናከር ዜጎች በራሳቸው እንዲቆሙ የሚያግዝ መሆኑን አስገንዝበዋል።

ኃላፊው አክለውም የፕሮጀክቱ ውጤታማነት በተቋማት የተቀናጀ አሠራር፣ በጠንካራ ክትትልና ግምገማ እንዲሁም በተጠቃሚዎች ንቁ ተሳትፎ ላይ የተመሠረተ መሆኑን ጠቁመው የስትሪኒግ ኮሚቴውም የፕሮጀክቱን አፈጻጸም በመከታተል፣ ችግሮችን በጋራ በመፍታትና የሚያስፈልጉ የአመራር ውሳኔዎችን በወቅቱ በመስጠት ለስኬቱ የጎላ ሚና እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

በከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ዘርፍ ኃላፊና ምክትል የቢሮ ኃላፊ አቶ አፈወርቅ ለማ እንደተናገሩት በፕሮግራሙ ዘጠና ስምንት ሺህ የሚደርሱ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ማድረግ የተቻለ ሲሆን በተለይም ቀደም ሲል ፕሮግራሙ ከሚሰራባቸው ኮምፖነንቶች መካከል የተወሰኑትን ላይ ብቻ እየተሰራ መቆየቱን ገልጸው በዚህ ዓመት በአምስቱም ኮምፖነንቶች ላይ በመስራት አመርቂ ውጤት መታየት መቻሉን ገልጸዋል።

ተጠቃሚዎች በቀን አራት ሰዓት በመስራት ከሚያገኙት ገቢ በመቆጠብ በዘላቂነት ከተረጂነት ተላቀው በራሳቸው መቆም እንዲችሉ በከተሞች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ድጋፍ በማድረግና ተቀናጅተው በመስራት አቅም መሆን እንዲችሉም አቶ አፈወርቅ ለማ ጥሪ አቅርበዋል።

የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔትና ስራ ፕሮጀክት በከተሞች የሚገኙ የተጋላጭ የማህበረሰብ ክፍሎችን በመደገፍ የኑሮ ሁኔታቸውን ለማሻሻል፣ የገቢ ማስገኛ አቅማቸውን ለማሳደግና ወደ ዘላቂ የኑሮ መሠረት እንዲሸጋገሩ ለማስቻል የተዘረጋ መሆኑን የገለፁት የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ ገልገሎ ገዛኻኝ ፕሮጀክቱ የሚያተኩረው የአጭር ጊዜ ድጋፍ ብቻ ሳይሆን፣ ተጠቃሚዎች ክህሎት እንዲያገኙ፣ የሥራ ዕድል እንዲፈጥሩና በራሳቸው እንዲቆሙ የሚያስችል ዘላቂ የኑሮ መሻሻል ላይ መሆኑንም አስረድተዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ፕሮጀክቱ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን በመደገፍ የኑሮ ሁኔታቸውን ለማሻሻል ጠቃሚ ሚና እየተወጣ መሆኑን ገልጸው ፕሮጀክቱ የሚያስገኘው ውጤት እንዲጠናከር ተቋማት በቅንጅት መሥራትና የተጠቃሚዎችን ተሳትፎ ማሳደግ እንደሚገባም አስተያየት ሰጥተዋል።

የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔትና ሥራ ፕሮጀክት ስትሪንግ ኮሚቴ የጋራ መድረክ ተጀመረነሐሴ 22/2018 ዓ.ም (ከመልቢ)በከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔትና ሥራ ፕሮጀክት ስትሪንግ...
28/08/2026

የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔትና ሥራ ፕሮጀክት ስትሪንግ ኮሚቴ የጋራ መድረክ ተጀመረ

ነሐሴ 22/2018 ዓ.ም (ከመልቢ)

በከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔትና ሥራ ፕሮጀክት ስትሪንግ ኮሚቴ የጋራ መድረክ በዛሬው ዕለት በአርባ ምንጭ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በመድረኩ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የሥራና ክህሎት ቢሮ ሀላፊ እንዲሁም የስትሪኒግ ኮሚቴው ሰብሳቢ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) ፣የክልሉ ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ብርሃኑ ዘውዴን ጨምሮ ሌሎች የክልል ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሀላፊዎች፣ከንቲባዎችና የማዘጋጃ ቤታዊ ሥራ አስኪያጆች ተሳታፊ ሆነዋል።

በዕለቱም የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔትና የሥራ ፕሮጀክቶች አፈጻጸምን በመገምገም፣ ያሉ ተግዳሮቶችን በመለየትና ቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎችን በጋራ ለማስቀመጥ ውይይት ይካሄዳል።

በተለይም የሴፍቲኔት ተጠቃሚዎችን የሥራ ዕድልና የገቢ አቅም ማሳደግ፣ የፕሮጀክቶችን ውጤታማነት ማሻሻልና በተቋማት መካከል የተቀናጀ አሠራር መፍጠር በውይይቱ የሚጠበቁ ዋና ውጤቶች ናቸው።

መድረኩ በቀጣይ የተሻለ ቅንጅት፣ ግልጽ የሥራ አቅጣጫና ተጨባጭ ውጤት ለማምጣት የሚያግዝ የጋራ ውሳኔ በማስቀመጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

በዳዊት ሽፈራው

በክልሉ ባለፉት 3 ዓመታት ከኮሪደር ልማት አንፃር በተለያዩ ከተሞች በተከናወኑ ተግባራት ተጨባጭ ስኬቶች ተመዝግበዋል
20/08/2026

በክልሉ ባለፉት 3 ዓመታት ከኮሪደር ልማት አንፃር በተለያዩ ከተሞች በተከናወኑ ተግባራት ተጨባጭ ስኬቶች ተመዝግበዋል

የደቡብ ኢትዮጵያ የኮሪደር ልማት ሞዴል፦ ወላይታ ሶዶ በአዲስ ገፅታ*******************ነሐሴ 14/2018 ዓ.ም (ከመልቢ)የዓለም ህዝቦች የባህል ቅርስ ሆኖ በተባበሩት መንግስታት ድ...
20/08/2026

የደቡብ ኢትዮጵያ የኮሪደር ልማት ሞዴል፦ ወላይታ ሶዶ በአዲስ ገፅታ
*******************

ነሐሴ 14/2018 ዓ.ም (ከመልቢ)

የዓለም ህዝቦች የባህል ቅርስ ሆኖ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የተመዘገበው የወላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ "ጊፋታ" በዓል በመስከረም 10 ቀን 2019 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ከተማ በድምቀት ይከበራል።

ከሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ በርካታ እንግዶች በሚታደሙበት በዚህ ታላቅ በዓል አቀባበል ለማድረግ በወላይታ ሶዶ ከተማ የተለያዩ ቅድመ-ዝግጅቶች እየተደረጉ ይገኛሉ። የዚሁ ዝግጅት አካል የሆነው የከተማዋ የኮሪደር ልማት ስራ ለአይን ማራኪና ለቀልብ ሳቢ ሆኖ ከተማዋን አስውቧታል።

በከተማዋ በየደረጃው እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር ልማት የተቀናጁ የመሠረተ ልማት ስራዎችን አስተሳስሮ የያዘ ነው። ይህም የመንገድ ጥገናን፣ የዘመናዊ መንገድ ማብራት ዝርጋታን፣ የውሃና የኤሌክትሪክ መስመሮችን፣ እንዲሁም የፍሳሽ ማስወገጃዎችን አቀናጅቶ በሁለቱም የመንገድ ዳርቻዎች የማዋሃድ ስራን ያካተተ ነው።

በተጨማሪም የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎች፣ የመናፈሻ ስፍራዎች፣ የህዝብ መገልገያ ካፌዎች፣ የህፃናት መጫወቻዎች እና ሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቶች ተካተውበታል።

ባህልን ከታሪክ ጋር አስተሳስሮ በሚከናወነው በዚህ ዙር የኮሪደር ልማት፣ ቀደም ሲል ለህዝባቸው ታላቅ ውለታ የዋሉ ጀግኖች መታሰቢያ ሐውልቶች እየተገነቡ ይገኛሉ።

ከእነዚህም መካከል ግንባታቸው ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት የሆኑት የካዎ ጦና እና የፍሬው አልታዬ መታሰቢያ ሐውልቶች ለከተማዋ ተጨማሪ ሞገስና ውበት ሆኗታል።

በሌላ በኩል የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን፣ ቀልጣፋ፣ ጊዜና ወጪ ቆጣቢ ለማድረግ በተጀመረው ሀገራዊ ኢኒሼቲቭ መሰረት የ"ሶዶ መሶብ አንድ ማዕከል" ግንባታም በተፋጠነ ሁኔታ እየተከናወነ ይገኛል።

ከተሞችን ለነዋሪዎቻቸው ምቹ፣ ፅዱና ተመራጭ የማድረግ ሀገራዊ እንቅስቃሴ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በሚገኙ ከተሞች ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን፤ በክልሉ በሚገኙ ብሔር ብሔረሰቦች ዘንድ የሚከበሩ የዘመን መለወጫ በዓላት ለከተሞች ልማትና ዝግጅት ልዩ ዕድል ፈጥረዋል።

በዚህም መሰረት ቀን ቀጠሮ ለተቆረጠለትና በመስከረም 10/2019 ዓ.ም ለሚከበረው የጊፋታ በዓል በወላይታ ሶዶ ከተማ ልዩና ደማቅ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል።

ምንጭ EBC

Address

Arba Mintch

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bureau of Urban and Infrastructure/South Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share