የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን

  • Home
  • Ethiopia
  • Arba Mintch
  • የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከሙስና የፀዳች ኢትዮጵያ!!!

የሕዝብና የመንግሥትን ሀብት ከሙስናና ከምዝበራ ለመጠበቅ ችግሮችን በጊዜ ለመለየትና በሕግ ማስጠየቅ የሚያስችል ትክክለኛ መረጃ የመያዝ  ስራ በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ ነሐሴ 30/...
05/09/2026

የሕዝብና የመንግሥትን ሀብት ከሙስናና ከምዝበራ ለመጠበቅ ችግሮችን በጊዜ ለመለየትና በሕግ ማስጠየቅ የሚያስችል ትክክለኛ መረጃ የመያዝ ስራ በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ

ነሐሴ 30/2018ዓ.ም

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከሥነ-ምግባር መከታተያ ክፍሎችና ከተቋሙ ሠራተኞች ጋር መክሯል።

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አቶ ተካልኝ ጋሎ እንደገለጹት የሕዝብና የመንግሥትን ሀብት ከሙስናና ከምዝበራ ለመጠበቅ ችግሮችን በጊዜ ለመለየትና በሕግ ማስጠየቅ የሚያስችል ትክክለኛ መረጃ የመያዝ ስራ በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑ ገልጸዋል ።

ትክክለኛ መረጃን በአግባቡ ማደራጀትና ሚስጥራዊነቱን መጠበቅ የሙስና ጉዳዮችን በሕግ ለማስጠየቅ ወሳኝ መሆኑንም አሳውቀዋል።

አንድ ድርጊት አጠራጣሪ መሆኑን ማወቅ ብቻ በቂ አለመሆኑን የጠቆሙት ኮሚሽነሩ ድርጊቱ ሙስና መሆኑን በሕግ ፊት ለማረጋገጥ የሚችል ግልጽ፣ ተአማኒና በአግባቡ የተደራጀ ማስረጃ መያዝ ተገቢ እንደሆነ አመላክተዋል።

የጠራ መረጃ ለኮሚሽኑ ትልቅ መሣሪያ ነው ያሉት ኮሚሽነር ተካልኝ፣ ከኮሚሽኑ ጀምሮ እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ የመረጃ አያያዝና አጠቃቀም ሥርዓትን ለማጠናከር የጋራ ጥረት እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል።

በተጨማሪም ትክክለኛ መረጃ ተይዞ እንኳን በአግባቡ ካልተደራጀና ሚስጥራዊነቱ ካልተጠበቀ የሕግ ሂደቱን ሊያደናቅፍ እንደሚችል ጠቁመው፣ መረጃን በማደራጀትና በመጠበቅ የሙስና ወንጀል ተጠርጣሪዎች ሕጋዊ ክፍተት እንዳያገኙ መሥራት እንደሚገባ አስረድተዋል።

የክልሉ ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነርና የሙስና መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ኮሚሽነር አማኑኤል አብደላ በበኩላቸው፣ የሙስና መከላከል ሥራን ለማጠናከር መረጃን በሥርዓት መሰብሰብ፣ ማደራጀትና መተንተን የሚያስችል አቅም መገንባት እንደሚገባ ገልጸዋል።

የመረጃ ሥርዓቶችን ዲጂታል ማድረግ፣ የተለያዩ የመረጃ ምንጮችን ማስተሳሰርና የመረጃ ጥራትን ማረጋገጥ የሙስና ስጋቶችን በተሻለ ሁኔታ ለመለየትና ተገቢውን የመከላከል እርምጃ ለመውሰድ የሚያግዝ መሆኑንም አስታውቀዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት መረጃን በጥራት ሰብስቦ በአግባቡ ማደራጀትና ለውሳኔ አሰጣጥ ማዋል በሙስና ትግል ውጤታማነት ላይ ያለውን ሚና በተሻለ መልኩ መገንዘባቸውን ገልጸዋል።

በመድረኩ የተገኘውን እውቀት ወደ ተግባር በመቀየር የመረጃ ጥራትንና የትንተና አቅምን ለማጎልበት፣ በተለይም መረጃን ለሕግ ማስከበርና ለውሳኔ አሰጣጥ በተገቢው ሁኔታ ለመጠቀም በትኩረት እንደሚሠሩ አስታውቀዋል።

05/09/2026
ትክክለኛና ተአማኒ መረጃ ለውጤታማ የሙስና ትግል ወሳኝ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ገለጸ።ነሐሴ 30/2018 ዓ.ም“የመረጃ ጥራት ለውጤታማ የሙስና ትግል”...
05/09/2026

ትክክለኛና ተአማኒ መረጃ ለውጤታማ የሙስና ትግል ወሳኝ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ገለጸ።

ነሐሴ 30/2018 ዓ.ም

“የመረጃ ጥራት ለውጤታማ የሙስና ትግል” በሚል መሪ ቃል የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከስነምግብር መከታተያ ክፍሎችና የተቋሙ ሰራተኞች ጋር በአርባምንጭ ከተማ እየመከረ ይገኛል።

መድረኩ በመረጃ አያያዝና አጠቃቀም ያሉ ክፍተቶችን በመለየት፣ የሙስና ትግሉን በትክክለኛና በተረጋገጠ መረጃ ላይ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተጠቁሟል።

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አቶ ተካልኝ ጋሎ መድረኩን ሲከፍቱ እንደገለጹት ሙስናን በጠራ መረጃ በመታገል የሕዝብን መብት፣ ተጠያቂነትና ፍትሕን በማስፈን እንዲሁም ለነገው ትውልድ የተሻለ አገር ለማስረከብ በቁርጠኝነትን መስራት እንደሚገባ አመላክተዋል።

ሙስና አንድን ቢሮ ፣ተቋም ወይም አካባቢ ብቻ የሚጎዳ ሳይሆን፣ የሀገርን ራዕይ ከማጨለሙም ባለፈ ልማትን የሚያዳክምና ሕዝቡ ፍትሃዊ የልማት ተጠቃሚ እንዳይሆን እንቅፋት የሚሆን ከባድ ችግር መሆኑን አስረድተዋል።

ይህንን ችግር ለመታገልም ጥራት ባለውና በተረጋገጠ መረጃና ማስረጃ ላይ በመመስረት፣ ከንቁ ሕዝባዊ ተሳትፎ ጋር ሁሉም አካላት በትብብር መሥራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የሙስናን መዋጋትና ማጋለጥ ትግል ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ያስገነዘቡት ኮሚሽነሩ የተሟላና ግልጽ መረጃ ሳይዙ በጥርጣሬና በፍረጃ ላይ ብቻ ተመስርቶ የሙስና ትግል ማካሄድ ተጠያቂነትን ከማስፈን ይልቅ ለሙሰኞች መሸሸጊያ የሚሆን ሁኔታ ሊፈጥር እንደሚችል ጠቁመዋል።

በመሆኑም ለሙስና ትግል ሲነሳ በቂ፣ ተአማኒ፣ ትክክለኛና በጥራት የተደራጀ መረጃ በመያዝ መሆን እንዳለበት አቶ ተካልኝ አስገንዝበዋል።

የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር አማኑኤል አብደላ የመወያያ ሰነዱን እያቀረቡ ሲሆን በመረጃ አሰባሰብ፣ ትንተና፣ አያያዝና አጠቃቀም ዙሪያ እንዲሁም በጸረ-ሙስና ትግሉ ውስጥ የመረጃ ጥራት ያለው ድርሻና በመረጃ አያያዝ ላይ መሟላት የሚገባቸውን ጉዳዮች አብራርተዋል።

የመረጃ ጥራትን ማረጋገጥ የሙስና ክስተቶችን በትክክል ለመለየት፣ ተገቢ ምርመራና ክትትል ለማካሄድ እንዲሁም በማስረጃ የተደገፈ ውሳኔ ለመስጠት ወሳኝ መሆኑንም ጠቁመዋል።

በመድረኩ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝብ ምክር ቤት አፈጉባኤ የህግ ጉዳይ አማካሪ ወ/ሮ መስከረም ወ/ማሪያምን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣የስነምግብር መከታተያ ክፍሎችና የኮሚሽኑ ማኔጅመንት አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።

ሀሰተኛ ሰነዶችን ሲያዘጋጅ የነበረ ግለሰብ ላይ ክስ ተመሰረተ***********************ነሐሴ 21/2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8፣ አዲሱ ገበያ አካባ...
27/08/2026

ሀሰተኛ ሰነዶችን ሲያዘጋጅ የነበረ ግለሰብ ላይ ክስ ተመሰረተ

***********************

ነሐሴ 21/2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8፣ አዲሱ ገበያ አካባቢ በሚገኝ የገበያ ማዕከል ውስጥ ሀሰተኛ ሰነዶችን ሲያዘጋጅ ነበር የተባለ ግለሰብ ላይ ክስ መመስረቱን ፖሊስ ገለጸ።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ ኢንተለጀንስ በተከታታይ ሦስት ቀናት ባደረገው ክትትልና ቁጥጥር፣ ካሊድ አወል የተባለ ግለሰብ ሀሰተኛ ሰነዶችን ሲያዘጋጅ እንደነበር ተጠርጥሮ በሚሰራበት የህትመት ድርጅት ላይ ብርበራ መካሄዱን ገልጿል።

በተካሄደው ብርበራም በተለያዩ የመንግሥት ተቋማት ስም የተዘጋጁ ሀሰተኛ ሰነዶችና ለማምረት የሚያገለግሉ የህትመት መሣሪያዎች መገኘታቸው ተመላክቷል።

ከተያዙት ማስረጃዎች መካከል የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 እና የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ወሳኝ ኩነት ሰነዶች፣ የየካ ክፍለ ከተማ ሰነዶች ማረጋገጫ ጽሕፈት ቤት ራስጌና ክብ ማህተም፣ የልደት ምስክር ወረቀት፣ የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ የግብር አከፋፈል ማስረጃ፣ የፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ የፎረንሲክ ማስረጃ እና ዓመታዊ የተሽከርካሪ ምርመራ ማስረጃ ይገኙበታል።

በተጨማሪም ሀሰተኛ ሰነዶችን ለማዘጋጀት ይጠቀምባቸው ነበር የተባሉ ሁለት ዴስክቶፕ ኮምፒውተሮች፣ ፍላሾችና ፕሪንተር መያዛቸውን ፖሊስ አስታውቋል።

ፖሊስ በማስረጃ ያጠናቀረውን የምርመራ መዝገብ ለክፍለ ከተማው ዐቃቤ ሕግ በመላክ፣ በግለሰቡ ላይ ክስ እንዲመሰረት መደረጉን የአዲስ አበባ ፖሊስ በፌስቡክ ገጹ አስታውቋል።

ትውልድን በሥነምግባር፣ ተቋምን በአሰራር!

ዝምታን በመስበር ሙስናን ማጋለጥ ለሀገራችን ብልጽግና!!ነሐሴ 13/2018 ዓ.ም (አርባምንጭ) ሙስና ህሊና ቢስና  ሀገራዊ ኃላፊነት በጎደላቸዉ አካላት ሆን ተብሎ የራስ ቡድንና ኔትወርክ በመ...
19/08/2026

ዝምታን በመስበር ሙስናን ማጋለጥ ለሀገራችን ብልጽግና!!

ነሐሴ 13/2018 ዓ.ም (አርባምንጭ) ሙስና ህሊና ቢስና ሀገራዊ ኃላፊነት በጎደላቸዉ አካላት ሆን ተብሎ የራስ ቡድንና ኔትወርክ በመዘርጋት በድብቅ የሚፈፀምና የሚያድግ አዋራጅ ተግባር ነው። የሕዝብ ንቃተ ሕሊና ሲያድግ፣ ዝምታ ሲሰበርና የሙስና ተግባራት በሕጋዊ መንገድ መጋለጥ ሲጀምሩ የሙስና ፈፃሚዎች የመሸሸግ ዕድላቸው ይጠብባል። እንደ ደቡብ ኢት/ያ ክልል በብልሹ አሠራርና የፀረ-ሙስና ትግል ላይ የህዝብ ተሳትፎ እያደገ በመምጣቱ በ 2018 በጀት ዓመት ኮሚሽኑ ማዳን ከቻለው የመንግስትና የሕዝብ ሀብትና ንብረት በተጨማሪ በርካታ የብልሹ አሠራርና የሙስና ጥቆማዎች ዙርያ የማጣራትና ህጋዊ ሥረዓት ለመዘርጋት በርካታ ሥራዎች እየተሠሩ ይገኛል፡፡
አርሶ አደሩ፣ የከተማ ነዋሪዎች፣ ወጣቶችና በመላዉ ማህበረሰባችን ዉስጥ ሙሰኞች የሚዘርጉትን አልሸነፍ ባይ ኔትዎርኮችን በመበጣጠስ እንዲሁም በትግል ሂደት የሚገጥማቸዉን የማሸማቀቅና ስልታዊ ጥቃቶች በጽናት በመቋቋም ለሀገርና ህዝብ ሀብትና ንብረት ዘብ የመቆም ልምምድ እየጨመረ መምጣቱ ለጀመርነዉ ሁለንተናዊ ሀገራዊ ብልጽግና ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል፡፡

የሕዝብ ተሳትፎ እያደገ መጥቷል ስንል ሀገራዊና ክልላዊ ዉግንና ያላቸዉ የማህበረሰብ አካላት ለህሊናቸዉና ለእዉነተኛ ፍትህ በመቆም ሰዎችን በጥርጣሬና ያለመረጃ ከመፈረጅ ወጥተዉ ትክክለኛ መረጃ ላይ በመመስረት የማጋለጥ ባህል እያደገ መጥቷል ማለት ነዉ፡፡
ትክክለኛው የፀረ-ሙስና ተሳትፎ ሕጋዊ መረጃን በማቅረብ፣ ለተገቢው አካል ማሳወቅና የምርመራና የፍርድ ሂደቱ እንዲከበር በማድረግ የሚገለጽ ነው። ይህ ሥርዓት ያለዉ ተሳትፎ የሕግ የበላይነትንም ሆነ የፍትሕ እሴቶችን ያጠናክራል። በአጠቃላይ በሙስና ትግሉ ሁሉም የማህብረሰብ ክፍል ለእዉነትና ለህሊናው ተገዢ በመሆን የድርሻውን ተሳትፎ ቢያደርግ ለሀገራችን ራዕይ መሳካት ጉልህ አስተዋጽኦ አለዉና ሁላችንም እንረባረብ እላለሁ!!

ኮሚሽነር ተካልኝ ጋሎ
የደ/ ኢት/ያ ክ/ የሥነምግባርና ፀረሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር

ህዝቡ የፀረ ሙስና ትገሉ ባለቤት እየሆነ መጥቷል - ኮሚሽነር ሳሙኤል ኡርቃቶ (ዶ/ር)ነሐሴ 09/2018 (አርባምንጭ)፦ በሀገሪቱ ግንዛቤ ለመፍጠር በተሰሩ ስራዎች ህዝቡ የፀረ ሙስና ትገሉ ባ...
15/08/2026

ህዝቡ የፀረ ሙስና ትገሉ ባለቤት እየሆነ መጥቷል - ኮሚሽነር ሳሙኤል ኡርቃቶ (ዶ/ር)

ነሐሴ 09/2018 (አርባምንጭ)፦ በሀገሪቱ ግንዛቤ ለመፍጠር በተሰሩ ስራዎች ህዝቡ የፀረ ሙስና ትገሉ ባለቤት እየሆነ መምጣቱን የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሳሙኤል ኡርቃቶ (ዶ/ር) አስታወቁ።

ኮሚሽኑ ያሰናዳው 17ኛው ሀገር አቀፍ የሥነምግባርና የፀረ- ሙስና ኮሚሽኖች ትስስር ጉባኤ ዛሬ በአዳማ ተካሂዷል።

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ሳሙኤል ኡርቃቶ(ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ ባለፉት ዓመታት በፀረ ሙስና እና ስነ ምግባር ረገድ በተከናወኑ ተግባራት ዋነኛውና ትልቁ ማዕቀፍ የሆነው የትውልድ ሥርዓት ግንባታ ጥሩ አቅጣጫ ይዟል።

በዚህ ረገድ በፀረ ሙስና ትግል ዙሪያ በየደረጃው ለሚገኘው የህብረተሰብ ክፍል ግንዛቤን ለማስረፅ በተሰራው ስራ ህዝቡ የሙስና ትግሉ ባለቤት እየሆነ መምጣቱን ገልጸዋል።

ህዝቡ ሙስና በሀገሪቱ የመልካም አስተዳደር፣ የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊ እና የሰላም አለመረጋጋትን ከሚፈጥሩ ችግሮች መካከል አንዱ እና ዋነኛው ተግዳሮት መሆኑን በጽኑ አቋም በማመን መንግሥት ችግሩ እንዲገታ ያለውን አቋም በተለያዩ መድረኮች ማሳወቁ ለፀረ ሙስና ትግሉ ትልቅ አቅም ነው ብለዋል።

አሁን ላይ መንግሥት በሙስና ላይ የያዘው አቋምና እርምጃ ችግሩን ለማስወገድ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው፤ በተለይም ትግሉን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ ጊዜው የሚጠይቀውን የአሰራር፣ የትብብርና የቅንጅት ስራን ተግባራዊ ማድረግ ወሳኝ መሆኑን አመላክተዋል።

ኮሚሽኑ ባለፈው በጀት ዓመት የፀረ ሙስና ትግሉ በሥነ ምግባር ግንባታ፣ ሙስናን አስቀድሞ መከላከልና ሕግ ማስከበር እንዲሁም የአንድ ዕቅድ አንድ ሪፖርት ስትራቴጂዎች ከመካከለኛ ዘመን ዕቅድ ጋር በማስተሳሰር ውጤታማ አፈጻጸም ማከናወኑን አብራርተዋል።

የክልልና የከተማ አስተዳደር የሥነ ምግባርና የፀረሙስና ኮሚሽኖች ቀደም ሲል 16 ዙር ሀገር አቀፍ የትስስር ጉባኤዎች መካሄዳቸው ለፀረ ሙስና ትግሉ ፍሬያማ እንዲሆን ምቹ መደላድል መፍጠሩንም አንስተዋል።

በ17ኛው ጉባዔም በ2018 በጀት ዓመት ሲከናወኑ በነበሩ የሥነ ምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ስራዎች በጥልቀት በመወያየት ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በመለየት በቀጣይ የተሻለ ስራ ለመስራት የሚያስችል አቅጣጫ መቀመጡን ኮሚሽነሩ አስታውቀዋል።

ምንጭ:- ኢዜአ

14/08/2026
ኮሚሽኑ 25ኛ ዓመት የምስረታ በዓል የማጠቃለያ ፕሮግራም በማካሄድ ላይ ይገኛል********************* (ደ.ኢ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ነሃሴ 08/2018 ዓ.ም) የፌደራል የሥነምግባር እና የፀ...
14/08/2026

ኮሚሽኑ 25ኛ ዓመት የምስረታ በዓል የማጠቃለያ ፕሮግራም በማካሄድ ላይ ይገኛል

*********************

(ደ.ኢ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ነሃሴ 08/2018 ዓ.ም) የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የተመሠረተበትን 25ኛ ዓመት የምስረታ በዓል የማጠቃለያ መርሃ-ግብር በዛሬው ዕለት በድምቀት በማካሄድ ላይ ይገኛል።

ኮሚሽኑ ባለፉት የሩብ ክፍለ-ዘመን ጉዞው በሀገሪቱ የሥነምግባር እሴቶችን በመገንባት፣ የሙስና ስጋቶችን በቅድመ-መከላከል ስራዎች በማስወገድ እንዲሁም የህግ ማስከበር ተግባራትን በስፋት በማከናወን ረገድ በርካታ አዎንታዊ ውጤቶችን ማስመዝገቡ በመድረኩ ተገልጿል።

በመድረኩ ኮሚሽኑ በ25 ዓመቱ የፀረ-ሙስና ትግሉ ትናንት፣ ዛሬ እና ነገን ላይ ትኩረት ያደረጉ ዶክመተሪ ፕሮግራም እና የመወያያ ሰነድ እየቀረበ ይገኛል።

በመርሃ-ግብሩ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ የሥነምግባር ግንባታ፣ የሙስና ቅድመ መከላከል እና የሙስና ወንጀል የህግ ማስከበር ዋና ዋና ተግባራት፤ ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ መፍትሄዎች እና በቀጣይ ትኩረት የሚሹ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት ይደረጋል።

በዚሁ ታሪካዊ የማጠቃለያ መርሃ-ግብር ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ሎሚ በዶን ጨምሮ የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ፣ ምክትል ሰብሳቢ እና አባላት፣ የባለድርሻ አካላት ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ የፌዴራል፣ የክልል እና የከተማ አስተዳደር የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽነሮችና የቀድሞ ኮሚሽነሮች፣ እንዲሁም የኮሚሽኑ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ተገኝተዋል።

ትውልድን በሥነምግባር፣ ተቋምን በአሰራር!

የሙስና ወንጀል መጠቆሚያ አማራጮችን፣ ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት👇🏾

ሞባይል መተግበሪያ

ስልክ ተጠቃሚዎች

የዘገባው ምንጭ የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ነው

 #ሌብነት ላይ ጠንከር ያለ ርምጃ እንወስዳለን፤ ማን ላይ እንደሚያርፍ አላውቅም፤ ማንም ላይ ቢያርፍም ግን ጠንከር ያሉ ሥራዎችን እንሰራለን!  (ዶ/ር)                      **...
09/08/2026

#ሌብነት ላይ ጠንከር ያለ ርምጃ እንወስዳለን፤ ማን ላይ እንደሚያርፍ አላውቅም፤ ማንም ላይ ቢያርፍም ግን ጠንከር ያሉ ሥራዎችን እንሰራለን!

(ዶ/ር)

**************

"ሌብነት ነቀርሳ ነው፤ ሀገርን ይበላል፤ ትንሽም ሆነ ትልቅ ሌብነት መጥፋት አለበት!"  (ዶ/ር)
08/08/2026

"ሌብነት ነቀርሳ ነው፤ ሀገርን ይበላል፤ ትንሽም ሆነ ትልቅ ሌብነት መጥፋት አለበት!"

(ዶ/ር)

Address

Arba Mintch

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share