የደቡብ ኢትዮጲያ ክልላዊ መንግስት ሥራና ክህሎት ቢሮ South Ethiopia bureau of Labor & Skills

  • Home
  • Ethiopia
  • Arba Mintch
  • የደቡብ ኢትዮጲያ ክልላዊ መንግስት ሥራና ክህሎት ቢሮ South Ethiopia bureau of Labor & Skills

የደቡብ ኢትዮጲያ ክልላዊ መንግስት ሥራና ክህሎት ቢሮ  South Ethiopia bureau of Labor & Skills በክልላችን የወጣቱን ስራ ክህሎትና የስራ ፈጣሪነት አመለካከት በማጎልበት የቁጠባ ባህሉን በማሻሻል የስራ አጥነት ችግር መቅረፍ::

05/09/2026
‎"ብቃት" የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት ውጤታማ እንዲሆን ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሊረባረቡ ይገባል:-  ዶ/ር መስፍን መንዛ‎‎ ነሐሴ 29/2018 ዓ/ም  አርባምንጭ ‎‎በአርባምንጭ ...
04/09/2026

‎"ብቃት" የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት ውጤታማ እንዲሆን ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሊረባረቡ ይገባል:- ዶ/ር መስፍን መንዛ

‎ ነሐሴ 29/2018 ዓ/ም አርባምንጭ

‎በአርባምንጭ ከተማ ሥራና ክህሎት መምሪያ "ብቃት" የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት አተገባበርን አስመልክቶ ለመንግሥት ግዙፍ ፕሮጀክቶች፣ ለመካከለኛ ኢንተርፕራይዞችና ለግሉ ዘርፍ ባለሀብቶች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።

‎በመድረኩ "ብቃት" የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት ምንነትና አተገባበር ዙሪያ ሰነድ ተዘጋጅቶ በዝርዝር ቀርቧል።

‎የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ዶ/ር መስፍን መንዛ ከለውጡ ወዲህ በትብብር መንፈስ በጋራ የሚሰሩ በርካታ የልማት ስራዎች የከተማውን እድገት ከማሳለጥ ባለፈ ለበርካታ ወጣቶች የስራ እድል መፍጠሩን አውስተው በከተሞች የሚስተዋለውን የስራ አጥነት ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ከመንግስት ጎን ለጎን መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት የጎላ ሚና ሊጫወቱ እንደሚገባም አብራርተዋል።

‎አክለውም የሥራ አጥነት ችግር ሀገራዊ አሳሳቢነቱ እየጨመረ በመምጣቱ ወጣቶችን ለአላስፈላጊ ችግሮች እንዳያጋልጥ በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

«ብቃት» ፕሮጀክት ከሚሰጠው ጠቀሜታ አኳያ የሥራ ዕድል ፈጠራውን በስፋት ተደራሽ ለማድረግና አርባ ምንጭን በሁሉም ዘርፍ የቱሪዝም ልህቀት ማዕከል ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ባለድርሻ አካላት ከመንግሥት ጎን በመቆም የፕሮጀክቱን ዓላማ ከግብ እንዲያደርሱ ጥሪ አቅርበዋል።

‎የከተማው ም/ከንቲባና ሥራና ክህሎት መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ከንቲባ በበኩላቸው "ብቃት" የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት ዋና ዓላማ ወጣቶች የመጀመሪያ ደረጃ የሥራ ላይ ልምድ እንዲያገኙ በማድረግ ቋሚ የቅጥር ሥራ ዕድል መፍጠርና የከተማ ወጣቶችን ሥራ አጥነትን ለመቀነስ ለማገዝ እንደሆነ ተናግረዋል።

‎ፕሮግራሙ በሚቀጥሉት 2 ዓመታት የሚተገበር ሲሆን ከ18 እስከ 29 የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ 12ኛ ክፍል ያጠናቀቁ፣ በተለያዩ ምክንቶች ያቋረጡና ምንም አይነት የሥራ ልምድ የሌላቸው ወጣቶች ተጠቃሚ እንደሚያደረግ የጠቆሙት ወ/ሮ ሊዲያ ከ60 በመቶ በላይ ተጠቃሚ ሴቶችን መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

‎በቀጣይም ወደ ስራ ልምምድ የሚገቡ ወጣቶችን ከድርጅቶች ጋር በማስተሳሰር እየተሰተዋለ ያለውን የስራ አጥነት ችግር ለመቅርፍና የወጣቶቾን የስራ ክህሎት ለማጎልበት በትኩረት እንደሚሰራም አስረድተዋል።

‎አክለውም ኃላፊዋ በመጀመሪያ ዙር 1ሺህ ወጣቶችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ተናግረው ፕሮግራሙን ውጤታማ ለማድረግ የባለድርሻ አካላት ንቁ ተሳትፎ ወሳኝ እንደሆነ ጠቁመዋል።

‎ከለውጡ ወዲህ በከተማው በሁሉም ዘርፎች እየተከናወኑ ስራዎች እንዲሁም የሚታዩ ለውጦች አበርታች መሆናቸውን የተናገሩት የመድረኩ ተሳታፊዎች የከተማውን እድገት የሚመጥን ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሰለጠነ የሰው ኃይል ወሳኝ በመሆኑ ፕሮጀክቱ ያመጣውን ጥሩ እድል ለመጠቀም የሚጠበቅባቸውን ለማድረግ ቁርጠኛ ነን ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

‎የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ ወጣቶች ለ12 ቀናት ስልጠና ከወሰዱ በኃላ በማኑፋክቸሪንግ፣ በአገልግሎት፣ በኮንስትራክሽን፣ በከተማ ግብርና እንዲሁም በንግድ ዘርፍ እንደሚሰማሩ በቀረበው ሰነድ ተመላክቷል።

‎በመርኃ-ግብሩ የአርባምንጭ ከተማ ከንቲባ ዶ/ር መስፍን መንዛን ጨምሮ፣ የከተማው ምክትል ከንቲባና ሥራና ክህሎት መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ከንቲባ፣ ባለድርሻ አካላትና የተቋሙ ማኔጅመንት አካላት ተሳትፈዋል ሲል የዘገበዉ የአርባምንጭ ከተማ መንግስት ኮሚኒኬሽን ነው ።

የጌዴኦ ዞን ስራና ክህሎት መምሪያ በበጀት ዓመቱ ከ43 ሺህ በላይ ሥራ አጥ ወጣቶችን በበይነ መረብ ለመመዝገብ እየሠራ መሆኑ ተገለጸ ። ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም.  አርባምንጭየሥራ እድል ለማ...
04/09/2026

የጌዴኦ ዞን ስራና ክህሎት መምሪያ በበጀት ዓመቱ ከ43 ሺህ በላይ ሥራ አጥ ወጣቶችን በበይነ መረብ ለመመዝገብ እየሠራ መሆኑ ተገለጸ ።

ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም. አርባምንጭ

የሥራ እድል ለማመቻቸትና የሥራ ፈላጊዎችን መረጃ በተገቢው መንገድ ለመያዝ የሚያስችል የምዝገባ ሥርዓት በዞኑ እየተዘረጋ ይገኛል።

መምሪያዉ በ2019 በጀት ዓመት ከ43 ሺህ በላይ ሥራ አጥ ወጣቶችን በበይነ መረብ ለመመዝገብ የሚያስችል ሥልጠና ከዞኑ ሁሉም መዋቅሮች ለተውጣጡ ወጣት መዝጋቢዎች እየሰጠ ይገኛል ።

ሥልጠናው ለተሳታፊዎቹ የምዝገባ ሥርዓቱን በተገቢው መንገድ እንዲፈጽሙ አቅም ለማሳደግ ያለመ ነው ተብሏል።

የጌዴኦ ዞን ሥራና ክህሎት መምሪያ ኃላፊ አቶ ታደለ ጥላሁን ሥልጠናውን ሲያስጀምሩ በሰጡት ማብራሪያ፣ እያንዳንዱ ዜጋ የላበር አይዲ (Labour ID) ሊኖረው እንደሚገባ ገልጸዋል።

ይህም ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት በ2019 ዓ.ም. በዞኑ 43 ሺህ ወጣቶችን ለማስመዝገብ እንደሚሠራ አስታውቀዋል።

ቀደም ሲል የምዝገባ ሥራውን ለማከናወን ረጅም ሂደትና ጉዞ የሚጠይቅ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ግን በቀላሉ በሞባይል ስልክ ብቻ መመዝገብ የሚያስችል አሠራር መዘርጋቱን አቶ ታደለ ገልጸዋል።

አዲሱ የምዝገባ አሠራር ለበርካታ ሥራ ፈላጊ ዜጎች ተደራሽ ከመሆኑም በላይ፣ የሥራ ፈላጊዎችን መረጃ በበይነ መረብ በማሰባሰብ ለተለያዩ የሥራ ፍላጎቶችና ዕድሎች እንዲውል ለማስቻል የራሱን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ተገልጿል ።

የሥልጠናው ተሳታፊ ወጣቶችም በበኩላቸው፣ ያገኙት ሥልጠና የተሰጣቸውን የምዝገባ ተግባር በአግባቡና በብቃት እንዲወጡ የሚያግዛቸው መሆኑን ገልጸዋል።

ምንጭ የጌዴኦ ቴሌቭዥን ነው ።

‎የስራ ዕድል መፍጠር የዳቦ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የሀገር ግንባታ ህልውና ጉዳይም ነው -አቶ ስምኦን ገልገሎ‎‎ነሐሴ 29/2018 ዓ/ም አርባምንጭ ‎‎የኮንሶ ዞን ስራና ክህሎት መምሪያ ለወረዳዎ...
04/09/2026

‎የስራ ዕድል መፍጠር የዳቦ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የሀገር ግንባታ ህልውና ጉዳይም ነው -አቶ ስምኦን ገልገሎ

‎ነሐሴ 29/2018 ዓ/ም አርባምንጭ

‎የኮንሶ ዞን ስራና ክህሎት መምሪያ ለወረዳዎችና ለከተማ አስተዳደር ባለሙያዎች የመፈጸምና የማስፈጸም አቅም ለማሳደግ የክህሎት ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።

‎በስልጠና መድረኩ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉ የዞኑ ስራና ክህሎት መምሪያ ኃላፊ አቶ ስምኦን ገልገሎ እንደገለጹት የስራ ዕድል መፍጠር የዳቦ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የሀገር ግንባታ ህልውና ጉዳይም ነው ሲሉ አሳስበዋል።

‎ክህሎት የሁሉም ስኬት መሠረት ሲሆን የሚፈጠሩ የስራ ዕድሎች ክህሎትን መሠረት ሊያደርጉ ይገባል ያሉት አቶ ስምኦን፤ያለ በቂ ክህሎት በዘርፉ ውጤት ሊመጣ ስለማይችል የስልጠና መድረኩ በክህሎት የዳበረ ስራ ፈጣሪ ባለሙያን ለመፍጠርና የመፈጸምና የማስፈጸም አቅም ለማሳደግ የታለመ መሆኑን ጠቅሰዋል።

‎የሚደራጁ ኢንተርፕራይዞች ከፋይዳ እና ከELMIS ምዝገባ ጋር በማስተሳሰር ከስልጠናው የሚናገኘው የክህሎት እውቀትን ከቴክኖሎጂ ጋር ለማቀናጀት የዕሴት ሰንሰለታቸው የተጠበቁ ኢንተርፕራይዞችን ለመፍጠር መትጋት ይጠበቅብናል ብለዋል።

‎በስራ ዕድል ፈጠራ አዲሱ ዕሳቤ ዙሪያ የተዘጋጀ የክህሎት ስልጠና ሰነድ እና በተለያዩ የስልጠና ርዕሶች የተዘጋጁ ሰነዶች የቀረቡ ሲሆን በመጨረሻም የ2019 በጀት ዓመት የ2 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በዛሬዉ ቀን ይገመግማል ተብሎም ይጠበቃል።

የስራና ክህሎት ቢሮ ሕዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ።

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ላለፉት አምስት ዓመታት ያከናወናቸውን የልማት ጉዞዎች አስመልክቶ በሚያደርገው የምክክር መድረክ 3ኛ ቀን ውሎ ዉይይት እያካሄደ ይገኛል ነሐሴ 27/2018  ዓ.ምየሁሉ...
02/09/2026

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ላለፉት አምስት ዓመታት ያከናወናቸውን የልማት ጉዞዎች አስመልክቶ በሚያደርገው የምክክር መድረክ 3ኛ ቀን ውሎ ዉይይት እያካሄደ ይገኛል

ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም

የሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊዎችና ምክትል የቢሮ ኃላፊዎች እንድሁም ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ከ2014 እስከ 2018 ዓ.ም ባከናወናቸው የመዋቅር፣ የፖሊሲና የአሠራር ሪፎርሞች ከ20.7 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ገለጸ።

በዚህም አጠቃላይ የሥራ ዕድል ውስጥ ከ19 ሚሊዮን በላይ ዜጎች በሀገር ውስጥ የሥራ ዕድል ማግኘታቸውን የገለጹ ስሆን ከ1.6 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ደግሞ በሕጋዊ መንገድ በውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ተጠቃሚ መሆን መቻላቸውንም አንስተዋል ።

ይህ አፈጻጸም ሚኒስቴር መ/ቤቱ በዘርፉ ያካሄዳቸው ዘመናዊ አሠራሮችና የፖሊሲ ማሻሻያዎች ውጤት ማምጣታቸውን የሚያሳይ እንደሆነ ተጠቅሷል።

በዚህም ባለፉት አምስት ዓመታት 166 ቢሊዮን ብር ብድር በማቅረብ ከ900 ሺህ በላይ ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚ ማድረግ የተቻለ ሲሆን፣ 295 ቢሊዮን ብር የሚያወጣ የገበያ ትስስር በመፍጠርም ከ1.2 ሚሊዮን በላይ ኢንተርፕራይዞች የድጋፉ ተጠቃሚ መሆናቸውን ፤ ከመሬትና መሠረተ ልማት አቅርቦት ጋር ተያይዞ የተከናወኑት ሥራዎችም ለሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት ጉልህ አስተዋጽኦ ማበርከት መቻሉንም አንስተዋል።

በተጨማሪም የህግ ማዕቀፎች ማሻሻላቸው፣ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እስከ አንድ ማዕከል የተናበበ መዋቅር መዘርጋቱ፣አዳዲስ እሳቤዎችና ዘረ-መሎች መዘጋጀታቸውና ተቋማትን በቴክኖሎጂ ለማዘመን የሚደረጉ ጥረቶች ተቋሙ እያደረገ ያለዉን ጉዞ ከማሳለጥ አንፃር ጉልህ ሚና እንደነበርም ተገልጿል።

ከአዲሶቹ እሳቤዎች አንዱ ተቋማቱን «ኢንተርፕረነሪያል» ማድረግ እንደመሆኑ ተቋማት የኢንተርፕረነርሽፕ እሳቤን በመተግበር በዜጎች ተጠቃሚነትና በሀገር እድገት ላይ የራሳቸውን አሻራ እንዲያሳርፉ እድል እንደሰጣቸው ውይይቱ ላይ በስፋት ተነስቷል ስል የዘገበዉ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ነዉ።

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ባለፉት 5 ዓመታት የሪፎርም ውጤቶች እና በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ የሚያክር ሀገር አቀፍ ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረነሐሴ25/2018 ዓ.ምበአዲስ አበባ ኮንቬንሽ...
31/08/2026

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ባለፉት 5 ዓመታት የሪፎርም ውጤቶች እና በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ የሚያክር ሀገር አቀፍ ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ

ነሐሴ25/2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ኮንቬንሽን ማዕከል በተጀመረው በዚህ ሀገር አቀፍ መድረክ፣ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማት፣ ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ እና የቋሚ ኮሚቴው አባላት፣ የፌዴራልና የክልል ባለድርሻና አጋር አካላት በተገኙበት ነው የተጀመረው።

ከዛሬ ጀምሮ ለአራት ተከታታይ ቀናት በሚካሄደው ጉባኤ በዘርፉ ባለፉት አምስት ዓመታት የተከናወኑ ዋና ዋና የልማትና የሪፎርም ሥራዎች በጥልቀት ይገመገማሉ፤ በዘርፉ አንኳር ጉዳዮች ዙሪያም የፓናል ውይይቶች ይካሄዳሉ።

ጉባኤው ያለፉትን አምስት ዓመታት የሚዘክር ብቻ ሳይሆን፣ የተገኙ ውጤቶችንና ተሞክሮዎችን በመገምገም፣ የታዩ ክፍተቶችን በመለየትና የተሻሉ አሠራሮችን በማስፋፋት ለቀጣዩ የልማት ዘመን የሥራ አቅጣጫ ለማስቀመጥ መሆኑን በመክፈቻ መርሃ ግብሩ ላይ ተመላክቷል፡፡

ከጉባኤው ጎን ለጎን የክህሎት ኢትዮጵያ 2.0 ሁለተኛ ዙር ማጠቃለያና የቀጣዩ ዙር ይፋዊ ማብሰሪያ መርሃ ግብር እንዲሁም የቴክኖሎጂ ኤክስፖ እየተካሄደ ይገኛል።

በቴክኖሎጂ ኤክስፖው በክህሎት ኢትዮጵያ 2.0 መርሃ ግብር የታቀፉ ወጣቶች ያበለጿቸው፣ ተጨባጭ ችግሮችን የሚፈቱ እና ከሀሳብ ወደ ምርትና አገልግሎት የተሸጋገሩ የፈጠራና የቴክኖሎጂ ውጤቶች ለእይታ ቀርበዋል።

የኤክስፖው ውጤቶች ክህሎት ከሥልጠና ባለፈ ወጣቶች ተጨባጭ ችግሮችን በመለየት መፍትሔ እንዲያመነጩ፣ ሀሳባቸውን ወደ ፈጠራ እንዲቀይሩ እና ፈጠራቸውን ወደ ምርትና አገልግሎት እንዲያሸጋግሩ የሚያስችል አቅም መፍጠሩን የሚያሳዩ ተጨባጭ ማሳያዎች ናቸው።

በተጨማሪም በኤክስፖው ባለፉት አምስት ዓመታት በተተገበረው የክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ አቅጣጫ ውጤት ያመጡና ማሳያ የሆኑ ኢንተርፕራይዞችና ሥራ ፈጣሪዎች፣ እንዲሁም የተመረጡ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ምርትና አገልግሎቶቻቸውን እያስተዋወቁ ይገኛሉ።

ይህም ክህሎትን ከሥራ ዕድል፣ ከሥራ ፈጠራ፣ ከፈጠራ እና ከምርታማነት ጋር በማስተሳሰር የዜጎችን አቅምና የሀገርን ኢኮኖሚያዊ አቅም ለማሳደግ የተያዘውን አቅጣጫ በተግባር የሚያሳይ ነው።

በጉባኤው የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የዘርፉ ባለድርሻና አጋር አካላት፣ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት፣ ሥራ ፈጣሪዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

#የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር

Address

Ethiopia South Ethiopian Region
Arba Mintch

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የደቡብ ኢትዮጲያ ክልላዊ መንግስት ሥራና ክህሎት ቢሮ South Ethiopia bureau of Labor & Skills posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share