06/09/2026
ጳጉሜን 1 «የእመርታ ቀን»፦ የምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ከተረጅነት ወደ አምራችነት እያደረገው ያለው ታሪካዊ ሽግግር
«የኢትዮጵያ መንሰራራት» በሚል መሪ ቃል በድምቀት እየተከበረ የሚገኘውን የጳጉሜን 1 «የእመርታ ቀን» ምክንያት በማድረግ፣ የምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ሀገራችን ከተረጂነት ወደ አምራችነት እያደረገች ያለውን ታሪካዊ ሽግግር የሚያበስር ሰፊ የመስክ ግምገማና ምልከታ አካሄደ።
በምልከታው መርሃ ግብር በጨረቻ ቀበሌ በክላስተር እና በምርጥ ዘር የለማው፣ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራበት የሚገኘው ሰፊ የስንዴ ሰብል በማዕከላዊነት ተጎብኝቷል። የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ፖለቲካል ዘርፍ ሀላፊ ወ/ሮ የኔነሽ አንበሉ በአረንጓዴው አሸብርቆ የሚታየው ይህ ሰብል የወረዳውን አምራችነትና የምግብ ዋስትና የማረጋገጥ ራዕይ በተግባር የሚያሳይ ከመሆኑም በላይ፣ የህዝባችንን የጽናት ጉዞ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል።
ከግብርናው የልማት ስራ ጎን ለጎን፣ ኢንተርፕራይዝ ላይ ማተኮር ለዘላቂ ፈጠራና ውጤታማነት መሰረት መሆኑ ይታመናልና በባልጪ ከተማ በሚገኘው የመንግስት የዕድል ማዕቀፍ የተደራጁ የእንጨት ውጤቶች ማምረቻ እና ሌሎችም ማዕከላት ተጎብኝተዋል። በዚሁ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ላይ የተሰማራው ሞዴል መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ የዕለቱን የበዓል ስሜት በማስተጋባት የኢትዮጵያን የዕድገትና የብልጽግና ጉዞ በተግባር አሳይቷል።