በቤ/ጉ/ክ/መ በአሶሳ ዞን የአቡራሞ ወረዳ ግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ጽ/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Asosa
  • በቤ/ጉ/ክ/መ በአሶሳ ዞን የአቡራሞ ወረዳ ግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ጽ/ቤት

በቤ/ጉ/ክ/መ በአሶሳ ዞን የአቡራሞ ወረዳ ግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ጽ/ቤት This page is owned by Assosa Woreda Agriculture & Natural Resource office page.

The main objective of the page is to disclose information in relation to agricultural and natural resource activities.

በአሶሳ ዞን በአቡራሞ ወረዳ በቡልዲግሉ ቀበሌ በኩታ ገጠም እየለማ ያለ የድንች ሰብል በከፊል፤ሐምሌ 02/10/2018 ዓ.ምአቡራሞ
09/07/2026

በአሶሳ ዞን በአቡራሞ ወረዳ በቡልዲግሉ ቀበሌ በኩታ ገጠም እየለማ ያለ የድንች ሰብል በከፊል፤

ሐምሌ 02/10/2018 ዓ.ም
አቡራሞ

የአቡራሞ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የአራተኛ ሩብ አመት ሪፓርት በመገምገም ለቀጣይ የሚሠሩ ወቅታዊ የግብርና ስራዎችን የማጠናከሪያ  ስምሪት ሰጠ፤*************...
26/06/2026

የአቡራሞ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የአራተኛ ሩብ አመት ሪፓርት በመገምገም ለቀጣይ የሚሠሩ ወቅታዊ የግብርና ስራዎችን የማጠናከሪያ ስምሪት ሰጠ፤
******************************************
የአቡራሞ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የአራተኛ ሩብ አመት ሪፓርት በመገምገም ለቀጣይ የሚሠሩ ወቅታዊ የግብርና ስራዎችን የማጠናከሪያ ስምሪት ሰጥቷል።

የአቡራሞ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አታላይ ደረጀ እንዲሁም ም/ኃላፊው አቶ ያሲን ሀሰን እና የጽ/ቤታችን ቡድን መሪዎች፣አጠቃላይ ባለሙያዎች በተገኙበት ሪፓርቶችን በመገምገም በቀጣይ የሚሰሩ ስራዎች በተለይ የአረንጓዴ አሻራ ፣የመኸር እርሻ ስራ፣የሌማት ትሩፋት ስራዎች፣የአርሶ አደር ማሰልጠኛ ተቋማትን ዘር የማዘራት ስራ፣ የአቮካዶ ኢንሸቲቭ የቦታ ዝግጅት ስራዎች በአጠቃላይ ወቅታዊ የግብርና ስራዎችን ወቅቱን በጠበቀ መልኩ እንዲሰሩ እና እንዲደግፉ ለባለሙያዎች ስምሪት ተሰጥቷል።

ሰኔ 19/10/2018 ዓ.ም
አቡራሞ፤

በአቡራሞ ወረዳ ለዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከ13 ነጥብ 8 ሚሊዮን በላይ ችግኞች ለተከላ መዘጋጀታቸውን የአቡራሞ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት አስታወቀ፤********************...
22/06/2026

በአቡራሞ ወረዳ ለዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከ13 ነጥብ 8 ሚሊዮን በላይ ችግኞች ለተከላ መዘጋጀታቸውን የአቡራሞ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት አስታወቀ፤
******************************************
በአቡራሞ ወረዳ ለዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከ13 ነጥብ 8 ሚሊዮን በላይ ችግኞች ለተከላ መዘጋጀታቸውን የአቡራሞ ወረዳ ግብርና ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አታላይ ደረጀ አስታውቀዋል።

ኃላፊው አክለውም ከሚተከሉት ችግኞች መካከል 65 በመቶ የፍራፍሬ ችግኞች ሲሆኑ 35 በመቶው ደግሞ የደን ልማት አገልግሎት የሚውሉ መሆናቸውን ኃላፊው ገልፀዋል።

በወረዳው ባሉ ቀበሌዎች ለችግኝ ተከላው ቀደም ብሎ መሬት በመለየት X,y ኮርድኔት በመውሰድ እና የጉድጓድ ቁፋሮ እና ሌሎች አስፈላጊ ዝግጅቶች እየተደረጉ ይገኛሉ ብለዋል።

በአሶሳ ዞን በአቡራሞ ወረዳ ቡልዲግሉ ቀበሌ በኩታ ገጠም እየለማ ያለ የበቆሎ ማሳ አሁናዊ ቁመና በከፊል፤ሰኔ 09/10/2018 ዓ.ምአቡራሞ፤
17/06/2026

በአሶሳ ዞን በአቡራሞ ወረዳ ቡልዲግሉ ቀበሌ በኩታ ገጠም እየለማ ያለ የበቆሎ ማሳ አሁናዊ ቁመና በከፊል፤

ሰኔ 09/10/2018 ዓ.ም
አቡራሞ፤

በአቡራሞ ወረዳ በ2018/19 የምርት ዘመን በክላስተር እየለማ ያለ በቆሎ አሁናዊ ቁመና በከፊል፤ሰኔ 01/10/2018 ዓ.ም አቡራሞ፤
08/06/2026

በአቡራሞ ወረዳ በ2018/19 የምርት ዘመን በክላስተር እየለማ ያለ በቆሎ አሁናዊ ቁመና በከፊል፤

ሰኔ 01/10/2018 ዓ.ም
አቡራሞ፤

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በአሶሳ ዞን በአቡራሞ ወረዳ በጎልፅሃ ቀበሌ በኩታ ገጠም እየለማ ያለ ጥቅል ጎመን አሁናዊ ቁመና በከፊል፤ሚያዚያ 29/08/2018 ዓ.ምአቡራሞ፤
07/05/2026

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በአሶሳ ዞን በአቡራሞ ወረዳ በጎልፅሃ ቀበሌ በኩታ ገጠም እየለማ ያለ ጥቅል ጎመን አሁናዊ ቁመና በከፊል፤

ሚያዚያ 29/08/2018 ዓ.ም
አቡራሞ፤

02/05/2026
ሚያዚያ 22/08/2018 ዓ.ምበቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በአሶሳ ዞን በአቡራሞ ወረዳ በ2018 ዓ.ም በጀት አመት   መስኖ በክላስተር እየለማ ያለ የበቆሎ ማሳ አሁናዊ ቁመና  በከፊል፤
30/04/2026

ሚያዚያ 22/08/2018 ዓ.ም

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በአሶሳ ዞን በአቡራሞ ወረዳ በ2018 ዓ.ም በጀት አመት መስኖ በክላስተር እየለማ ያለ የበቆሎ ማሳ አሁናዊ ቁመና በከፊል፤

የአቡራሞ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አታላይ ደረጀ ለመላዉ የክርስትና እምነት ተከታዮችን አስመልክቶ  የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አሰተላልፈዋል።       የትንሳኤ በዓል ጌታችን መድ...
11/04/2026

የአቡራሞ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አታላይ ደረጀ ለመላዉ የክርስትና እምነት ተከታዮችን አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አሰተላልፈዋል።

የትንሳኤ በዓል ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደሙ የሰው ልጆችን ከኃጢያት ለማንጻት ራሱን አሳልፎ በመስጠት ወደር የማይገኝለት ፍቅሩን በመስቀል ላይ ገልፆ በሞቱ ለሰዉ ልጆች ሁሉ ምህረት ያስገኘበት እና ሞትንም ድል በመንሳት ከሞት የተነሳበት በዓል ነው።

በዚህም የሰዉ ልጆች ከጨለማ ወደ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት የተሸጋገሩበት የሽግግር፣ የእርቅና የሰላም በዓል ነው።

በትንሳኤ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰብአዊነትን፣ እርቅን፣ፍፁም ትህትናን፣ያለዉ ለሌለዉ ማካፈልን፣ ይቅርታን፣ምህረት ማድረግን፣ኅብረትን፣ አንድነትን፣ አርቆ አሳቢነትንና ጽናትን አሳይቶናል።

እኛም ኢየሱስ ክርስቶስን በተምሳሌትነት በመከተል እርስ በርስ በመፋቀር፣ በመተሳሰብ፣ ይቅርታና ምህረት በማድረግ ፣በመካከላችን ያለውን ልዩነት በፍቅርና በይቅርታ በመተካት፣ ለወገኖቻችን የምንራራበትና አብሮነታችንን በማጠናከር ከሰዉ ልጆች ጋር ሁሉ በሰላም እንድንኖር ያስፈልጋል።በተጨማሪም እርስ በእርስ በመረዳዳትና የተቸገሩትን በማሰብ በዓሉን በሰላም እንድታሳልፉ ጥሪዬን አቀርባለሁ።

በዓሉ የፍቅር፣ የሰላም፣ የይቅርታ፣ የምህረት፣ የመተሳሰብ፣ የመረዳዳት፣ የደስታ እና አብሮነታችን የሚጠናከርበት እንዲሆን በድጋሜ ምኞቴ ነዉ።

መልካም የትንሳዔ በዓል!!!

ሚያዚያ 03/08/2018 ዓ.ም
አሶሳ፣

በቤ/ጉ/ክ/መ በአሶሳ ዞን አቡራሞ ወረዳ በእንስሳትና ዓሳ ሀብት ፕሮጀክት(LFSDP) ድጋፍ ጋምባሽሪ ቀበሌ በዶሮ ምርት የተደራጁ ማህበራት በዛሬው እለት የአርሶ አደር መስክ ትምህርት(FFS)...
22/02/2026

በቤ/ጉ/ክ/መ በአሶሳ ዞን አቡራሞ ወረዳ በእንስሳትና ዓሳ ሀብት ፕሮጀክት(LFSDP) ድጋፍ ጋምባሽሪ ቀበሌ በዶሮ ምርት የተደራጁ ማህበራት በዛሬው እለት የአርሶ አደር መስክ ትምህርት(FFS) መስክ በዓል አከበሩ።

ከፌደራራል ብሄራዊ የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ፕሮጀክት አስተባባሪ ዶ/ር ቶማስ ቸርነት እንዲሁም ከግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ከፍተኛ ኤክስፐርት አቶ እንደሻው፣የክልሉ ግብርና ቢሮ ም/ሀላፊ አቶ አብደልከሪም እንዲሁም የአቡራሞ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ባበክር ሃሚድ እና ካቢኒያቸው እንዲሁም የክልል ግብርና ቢሮ ባለሙያዎች፣የወረዳ ግብርና ባለሙያዎች፣የልማት ጣቢያ ባለሙያዎች እና የቀበሌው ማህበረሰብ በተገኙበት የመስክ በዓሉ በደማቅ ሁኔታ ተከብራሯል።

FFS( የአርሶ አደር መስክት ትምህርት) አርሶ አደሩ ከባለሙያ ጠባቂነት ተላቆ በራሱ ለውጥ የሚያመጣበት ፕሮግራም መሆኑን በእንግዶች የተገለጸ ሲሆን አባላቱም ትምህርቱን በአግባቡ በመከታተል ለምረቃ እንዲበቁ የወረዳው አስተዳዳረለ አቶ ባበክር አጽንኦት ሰተውበታል።
FFS, "School without wall" በየሳምንቱ ይቀጥላል.......

የካቲት 16/06/2018 ዓ.ም
አቡራሞ፤

Address

Assosa
Asosa
5220

Telephone

+251577750772

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when በቤ/ጉ/ክ/መ በአሶሳ ዞን የአቡራሞ ወረዳ ግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share