Gebremichael Gudrie

Gebremichael Gudrie My page

ህዝብን፣ አገርን ማገልገል ክብር ነዉለተሰጠን እዉቅና እናመሰግናለን!
04/09/2025

ህዝብን፣ አገርን ማገልገል ክብር ነዉ
ለተሰጠን እዉቅና እናመሰግናለን!

ዘመን ያልፋል ዘመን ይተካል!!! ዘመንን ለፍሰሀ እድሜን ለንሰሀ የሰጠን ፈጣሪ የተመሰገነ ይሁን:: እንኳን ለአዲሱ ዓመት  በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን አዲሱ ዓመት  የሰላም ፣ የፍቅር ፣ የ...
10/09/2024

ዘመን ያልፋል ዘመን ይተካል!!! ዘመንን ለፍሰሀ እድሜን ለንሰሀ የሰጠን ፈጣሪ የተመሰገነ ይሁን::

እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን አዲሱ ዓመት የሰላም ፣ የፍቅር ፣ የአብሮነት ፣ የይቅር ባይነትና የብልጽግና ዘመን ይሁንልን።

16/08/2024

ከግል ጥቅም ይልቅ የአገር ክብርና ልእልና ይቅደም!!! የአገራችን የአትሌቲክስ ጉዳይ ሊስተካከል ይገባል::

የአሁኑ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴና የአትሌቲክስ ፌደሬሽን እንዲሁም አንዳንድ የአትሌቲክስ አሰልጣኞች ተግባር እጅግ አሳዛኝም አሳሳቢም ሆኗል በፍጥነት መስተካከል አለበት፣

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ገና ኦሎምፒክ እና የአለም ሻምፒዮና ሲደርስ የአገር ማሸነፍና ከአገር ክብር ይልቅ የግል ጥቅማቸዉ የሚያስጨንቃቸዉ ወራዳዎች አማካኝነት ተገቢ ባለሆነ መንገድ ከአትሌቶችና አሰልጣኞች ምርጫና በሌሎች ለግል ጥቅም ገመድ ጉተታ መሯሯጥ ዉዝግብ ሲፈጠር ነበር፣ በመሆኑም በአትሌቲክስ የአገራችን ክብር ካለበት የከፍታ ማማ ጎትተዉ በግድ ያወረዱ ህሊና ቢስ ጥቅመኞች በሶስት ተከታታይ የኦሎምፒክ ዉድድሮች የኢትዮጵያን ልዕልና የማይመጥን ውጤት የተመዘገበበት ነበር፣

የዘንድሮዉ የፓሪስ ኦሎምፒክ ደግሞ ያላሳየዉ ጉድ ምን አለ? በእዉነታዉ ማሸነፍ የሚችሉ አትሌቶች በግል ጥቅመኞች ተመዝነዉ ተጠባባቂ የሆኑት አልያም የቀሩት፤ በ38 አትሌቶች 70 ኮሚቴ የተንበሻበሹበት፤ አገራችን ኢትዮጵያ በአንድ ሲድኒ ኦሎምፒክ/በ2000 ዓ.ም/ አራት /4/ ወርቅ እንዳላመጣች አንድ ወርቅና በድምር አራት ሜዳልያ የተገኘበት፤ ይባስ ብሎ የኦሎምፒክ ኮሚቴ አመራሮች ዉድድሩ ለሜዳልያ ሳይሆን ለተሳትፎ ነዉ ብለዉ ያፌዙበት፤ ጭራሽ ደግሞ ለግል ጥቅማቸዉ ብለዉ የሰሩትን ጥፋት ክደዉ በሚዲያ ስልጣን አንለቅም ሲሉ ሰማን ወይ ጉድ!!!

ለነገሩ ህገ ወጥ ኮሚቴ ሰርተዉ የተመራረጡበት እና የመሰረቱት ቡድን እንደሆነ የእዉነት የሀገር ፍቅር ስሜት ያላቸዉ እንደነ አትሌት ገዝሀኝ አበራና ሌሎች ኢትዮጵያዉያን ከጅምሩ ጀምረዉ ሲጮሁ እንደነበር ሰሞኑን በሚዲያ ነግረዉናል::

በአንፃሩ የሀገር ክብርና ፍቅር ዉስጣቸዉን የሚያቃጥላቸዉ ኢትዮጵያዉያን እንደነ የእስፖርት መምህርና ተንታኝ ኢንስትራክተር መሠረት መንግስቱ፣ እንደነ አትሌት ገዝሀኝ አበራ፣ ሲሳይ ለማና ሌሎች በእዉቀትና በአሰራር ስርዓት እዲሰራና የሀገር ክብር ከፍ እዲል የሚጥሩ፣

ስለሆነም አትሌቲክሱ የመዋቅር፣ የአመራር/ የአትሌቲክስ ፌደሬሽንና የኦሎምፒክ ኮሚቴ/ እና የአሰራር ለዉጥ በማድረግና በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢ የተሻለ ችሎታና አቅም ያላቸዉን በመለየትና በማሰልጠን ከግል ጥቅም ይልቅ ለሀገር ክብር በመስራት በቀጣይ ኦሎምፒክና በዓለም ሻምፒዮና የሀገራችን ሰንደቅአላማ እንደነበረበት የከፍታ ማማ እንደሚዉለበለብ እንደ ሚደረግ ባለ ሙሉ ተስፋ ነን::

ሰላም ለሀገራችን!!!

4 ቀን ብቻ ቀረ! ፈጥነው እድለኛ ይሁኑ!>>>አጓጊው የሰፋሪኮም ሽልማቶች እጣ ልወጣ 4 ቀን ብቻ ይቀራል። እስካሁን 22 ሺ ሰዎች ሁሉንም  መስፈርቶች አሟልተው ለሽልማቱ እጩ መሆናቸውን ሲስ...
28/06/2023

4 ቀን ብቻ ቀረ! ፈጥነው እድለኛ ይሁኑ!
>>>
አጓጊው የሰፋሪኮም ሽልማቶች እጣ ልወጣ 4 ቀን ብቻ ይቀራል። እስካሁን 22 ሺ ሰዎች ሁሉንም መስፈርቶች አሟልተው ለሽልማቱ እጩ መሆናቸውን ሲስተማችን ያሳያል።
>>>
1ኛ ዕጣ 3 ቅንጡ ቤቶች፣ 2ኛ ዕጣ 5 ዘመናዊ የቤት መኪኖች፣ 3ኛ ዕጣ 10 ባጃጆች፣ 4ኛ ዕጣ 20 ሞተርሳይክሎች፣ እና ሌሎች በርካታ ሽልማቶች እድለኞችን እየጠበቁ ነው።
>>>
ለሰፋሪኮም ሽልማቶች እጩ ለመሆን ማስፈርቱ ምንድነው?
1ኛ) የኩባንያችን ገጽ Safaricom - Ethiopia Countryን follow ማድረግ፣
2ኛ አንድ post ቢያንስ በProfile እና በ3 የተለያዩ Groups share ማድረግ፣
3ኛ) በComment ስር "Safaricom - Ethiopia Country" መጻፍ፣
እድለኞቹን በJune 30, 2023 በፌስቡክ ገፃችን በኩል እንገልፃለን!
>>>
ሼር በማድረግ ብቻ እድለኞች ይሁን! ብዙ ሼር ያደረገ በዛው ልክ እድሉን ያሰፋል አንድ ሼር አንድ ዕጣ ስለሆነ።

ዛሬ ህዳር 30/2015 ዓ.ም ህፃን ሔኖክ ገ/ሚካኤል 5ኛ ዓመት የልደት በዓሉን በእደዚህ ከጓደኞቹ ጋር አክብሮ ዉሏል:: ልጄ እንኳን ተወለድክል:: ፈጣሪ በጥበቡ ያሳድግህ::
09/12/2022

ዛሬ ህዳር 30/2015 ዓ.ም ህፃን ሔኖክ ገ/ሚካኤል 5ኛ ዓመት የልደት በዓሉን በእደዚህ ከጓደኞቹ ጋር አክብሮ ዉሏል::
ልጄ እንኳን ተወለድክል:: ፈጣሪ በጥበቡ ያሳድግህ::

ህዝብን የሚያዳምጥ ለተሰራዉ ስራ እንዲህ እዉቅና ይሰጣል
28/09/2022

ህዝብን የሚያዳምጥ ለተሰራዉ ስራ እንዲህ እዉቅና ይሰጣል

የ2015 ድንቅና ልዩ  #የጋሪ ዎሮ በዓል አከባበር በአሶሳ
27/09/2022

የ2015 ድንቅና ልዩ #የጋሪ ዎሮ በዓል አከባበር በአሶሳ

" ጋሪ - ዎሮ " የዘመን መለወጫ በዓል                  " ዎርጋዌ - ዎሮ ቦር " # ጋሪ - ዎሮ በአል የቦሮ ሺናሻ ማህበረሰብ የዘመን መለወጫ በአል ነዉ:: በአሉ የሚከበረዉ በ...
17/09/2022

" ጋሪ - ዎሮ " የዘመን መለወጫ በዓል
" ዎርጋዌ - ዎሮ ቦር "
# ጋሪ - ዎሮ በአል የቦሮ ሺናሻ ማህበረሰብ የዘመን መለወጫ በአል ነዉ:: በአሉ የሚከበረዉ በየአመቱ ከመስከረም 16 -18 ነዉ:: ከመስከረም 16 ጀምሮ ማህበረሰቡ እርስ በርስ ሲገናኝ አንዱ ወደ ሌላኛዉ ቤት ሲሄድ በአሉን የሚገልፅበት " ዎርጋዌ " ሲሉ ተቀባዮች " ዎሮ ቦረ " ብለዉ ይቀበላሉ::

በአሉ አሮጌዉን አመት ሸኝተዉ አዲሱን አመት በአዲስ ተስፋ የሚቀበሉበት፣ አባቶች ለሀገር እርቅ ሰላምና በረከት እ/ርን የሚለምኑበት በአል ነዉ::

የተጣላ የሚታረቅበት በመሆኑ የእርቅ፣ ተለያይተዉና ተራርቀዉ የቆዩ የሚገናኙበት ስለሆነ የፍቅር፣ ያለዉ ለሌለዉ አካፍሎ ከጎረቤትና ከአካባቢዉ ጋር አብሮና ተባብሮ የሚያከብሩበት በመሆኑ የአብሮነት፣...በአል ነዉ:: በመሆኑም በአሉ የእርቅ የሰላምና የአብሮነት በአል ነዉ::
ጨለማዉ አልፎ ብርሀን የሚተካበት፣ ረሀብ አልፎ ጥጋብ የሚሆንበት(አዲስ እሸት የሚቀመስበት)፣ ያላገቡ ወጣቶች ለመጋባት የሚተጫጩበት ወቅት... በመሆኑ በአሉ በማህበረሰቡ ዘንድ ልዩ ቦታ አለዉ::

በአሉ በዚህ አመት የሺናሻ ማህበረሰብ በሚኖሩበት በሁሉም ቦታዎች ከሌሎች ወንድም እህት ማህበረሰብ ጋር በጋራ በድምቀት የሚከበር ሲሆን አሶሳ ላይ የሚከበረዉ ሀገር አቀፍ የቱሪዝም ቀን ከመስከረም 13-15 አሶሳ የሚከበር በመሆኑ #ጋሪ ዎሮ በአልም ለዚህ የቱሪዝም ቀን የተለየ ድምቀት የሚሰጥ በመሆኑ በልዩ ድምቀት ይከበራል::

ስለሆነም በአሉን በደመቀ ሁኔታ ለማክበር ኮሚቴ ተዋቅሮ ሀብት የማሰባሰብና የዝግጅት ስራ እየተሰራ ይገኛል:: በመሆኑ ሀገር ዉስጥም ከሀገር ዉጭም ያላችሁ በአሉን መደገፍ የምትቸሉ የበኩላችሁን አስተዋፅኦ እንድታበረክቱ እንጠይቃለን:: መልካም በዓል::

15/09/2022

Good

Address

Asosa

Telephone

+251913854046

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gebremichael Gudrie posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Gebremichael Gudrie:

Share